Bashewam Primary & Junior School 1-8
رفتن به کانال در Telegram
2 784
مشترکین
+624 ساعت
+317 روز
+8630 روز
آرشیو پست ها
Repost from Bashewam Primary & Junior School 1-8
የጥናት እቅድ አወጣጥ
(ለተማሪዎች ሼር)
1. ለነገ ዝግጁ ሁኑ
ሁሌም ዛሬ ለምነሰራው ብቻ ሳይሆን ነገ ለምንሰራው ስራ እቅድ በማውጣት ዝግጁ ልንሆን ይገባል! ለነገ ዝግጁ ሰትሆኑ ሰአታችሁን በአግባቡ ተጠቅማችሁ የቤት ስራችሁን በብቃት ወይንም በጊዜው ለማጠናቀቅ ይረዳችኃል!
2. የጥናት ቡድን ፍጠሩ
ይህ የድሮ ዘዴ ሊመሰል ይችል ይሆናል! ነገር ግን አሁንም ቢሆን የጥናት ቡድን መፍጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው! እድሜ ለቴክኖሎጂ መሻሻል በሁላችንም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ በምንጠቀምባቸው ስልኮች የሚገኙት እንደ ጎግል ፕላስ የመሰሉ ማህበራዊ ድረገፆች ከአስር በላይ ለሆኑ የጥናት ቡድኖች በቀጥታ የምስል እና የድምፅ ውይይት ለማድረገ ያስችላሉ! ስለሆነም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከሚገኙ የትምህርት አቻ ጓደኞች ጋር በአካልም ሆነ በተለያዩ የቴክኖሎጂ መገልገያዎች የጥናት ቡድኖች በመፍጠር እውቀትን እና ልምዶችን ልንጋራ ይገባል!
3. አንድ ነገር ለመስራት መደበኛ ልምድ ይኑራችሁ!
– ከትምህርት ጋር የተገናኙ
ስራዎችን ለመስራት እለታዊ የሆነ መደበኛ ጊዜ ስትመድቡ ሁሌም ቢሆን የሚሰጣችሁን የትምህርት ሀላፊነቶች እና የቤትስራዎች በአግባቡ እና በጊዜው ሰርቶ ለመጨረስ ይረዳችኃል! በአካባቢያችሁ ያሉ ሰዎችም ይህን ተረድተው ከአላማችሁ እንዳያሰናክሏችሁ አድርጉ!
4. ለጥናት ምቹ የሆነ ቦታ ያመቻቹ !
– ሁሌም ቢሆን የምታጠኑበት ስፍራ ምቾት ሊሰጣችሁና ትኩረት ለማድረግ የሚረዳችሁ ሊሆን ይገባል!
5. ሁሌም ቢሆን ተጠባባቂ እቅድ ይኑራችሁ
– ብዙ ጊዜ ለትምህርት እና ለጥናት የምንገለገልባቸው እንደ ኮምፒውተር የመሳሰሉ መሳሪያዎች በማንጠብቃቸው ሰአቶች ሊበላሹ ብሎም ሊጠፉና ሊሰረቁ ይችላሉ! ስለዚህም አስፈላጊ የምንላቸውን ፋይሎች በተለያየ መልኩ በተጠባባቂነት ልንይዛቸው ይገባል!
6. የቀን መቁጠርያ አዘጋጁና ተጠቀሙ
– በሁሉም የትምህርት ተቋማትና ደረጃዎች የአጭርና የረጅም ጊዜ የጥናት ስራዎች ይሰጣሉ! ታዲያ እንደ ርዝመታቸው እና እጥረታቸው ተማሪዎች በመዘናጋት ስራቸውን በአግባቡ ሳይወጡ ሲቀሩ ይስተዋላል! ይህን አስወግዶ ሀላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት ከእለት ተእለት የትምህርት እና የጥናት እንቅስቀሴ ጀምሮ የረጅምና የአጭር ጊዜ ሀላፊነቶቻችንን በቀን መቁጠርያ አማካይነት እቅድ ልናወጣላቸው እና ልንተገብራቸው ይገባል!
7. የተደራጃችሁ ሁኑ
በትምህርት ቆይታችሁ የምትገለገሉባቸውን መሳሪያዎች የትምህርት ሰአት የጥናት ሰአታችሁን የመዝናኛ ሰአታችሁን የገንዘብ አጠቃቀም እቅዳችሁን በመለየት ሁሉንም በስርአት በቦታውና በሰአቱ በመጠቀም የተደራጃችሁ ሁኑ!
8. አዎንታዊ አስተሳሰብን ያጎልብቱ !
የትምህርት ቤት ሕይወት ጠንካራ ስራን የሚፈልግና በጭንቀት ብሎም በመሰናክሎች የተመላ ነው! እነዚህን የሚገጥሙንን ጭንቀቶችና መሰናክሎች ተቋቁመን ስኬታማ ለመሆን ከምንመኛው የምረቃ በዓላችንም ለመድረስ አዎንታዊ አስተሳሰብን ልናጎለብት ይገባል! እንዴት አዎንታዊ አስተሳሰብን ማጎልበት እንደምንችል ኩሉ ኔትወርክ በቀጣይ ጠቃሚ ምክሮች ይዞላችሁ የሚመጣ ይሆናል!
9. እረፍት ውሰዱ
ጥናት ከመጀመራችሁ በፊት ሆነ በጥናት መሀል አጭር የእረፍት ጊዜ መውሰድ ችግር እንደሌለው ልንረዳ ይገባል! ምክንያቱም የእረፍት ጊዜያቶች መንፈሳችሁን እንድታድሱ እና ወደጥናት ስትመለሱ ትኩረት አድርጋችሁ እንድትሰሩ ይረዳችኃል!
10. ዝርዝር የስራ እቅድ ወይንም check list ይኑራችሁ!
– ብዙን ጊዜ የምንማራችሁ ትምህርቶች እለታዊ የሙከራ ስራ እና የቤት ስራዎች ይኖራቸዋል! በመሆኑም የሁሉንም የምንማራቸውን የትምህርት አይነቶች ሀላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የስራ ዝርዝር በማዘጋጀት እቅድ ልናዘጋጅላቸው ይገባል! ይህም የስራ ሀላፊነታችንን በአግባቡ ለመወጣት ይረዳናል!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Students 1 to 5 group discussion on friday,24 March partially.
Repost from Addis Ababa Education Bureau
ቀን 1/7/2015 ዓ.ም
ማስታወቂያ!
በ2015 የትምህርት ዘመን 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ እና ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ
ቀደም ሲል በቀጥታ / ኦላይን መመዝገባችሁ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋርም በተያያዘ የተመዘገባችሁበትን መረጃ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንዲቻል
ለ6ኛ ክፍል https://aa6.ministry.et እና
ለ8ኛ ክፍል https://aa.ministry.et ሊንኮችን በመጫን View Result የሚለውን በመጫን የመለያ ቁጥራችሁን እና ስም / Registration Number and First Name በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ስህተት ካለበት ለትምህርት ቤታችሁ በስቸኳይ እንድታሳውቁ እናሳስባለን፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Blog: - https://aacaebc.blogspot.com
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Repost from N/a
physical exercise hp grade 6 no page 106 size A4 q 74303 .pdf18.44 MB
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
