Meklit Microfinance S.C.
رفتن به کانال در Telegram
መክሊት ማይክሮፋይናንስ🌟 እምቅ አቅምዎን ወደ ትሩፋት የሚቀይሩበት! ★★★★★ 25 YEARS OF SERVICE IN UNLOCKING YOUR POTENTIAL!
نمایش بیشتر593
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-27 روز
-230 روز
آرشیو پست ها
የስራዎን ጉዞ በጠንካራ መሰረት ከ መክሊት ማይክሮፋይናንስ ጋር ይጀምሩ!
ወጣት ወይም ሴት ስራ ፈጣሪ ነዎት? ስራዎን ለማሳደግ እና ወደ ላቀ ደረጃ ለመሸጋገር ለሚደክሙ ሁሉ መልካም ዜና አለን!
በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለተሰማራችሁ ወጣቶች እና ሴቶች የተዘጋጀውን «ልዩ የቁጠባ ሂሳብ» ያውቃሉ?
ልዩ ጥቅሞች፡
የተሻለ የወለድ ጥቅም ቁጠባዎ በፍጥነት እንዲያድግ ያደርጋል
የስራ እንቅስቃሴን የሚያበረታታ – ንግድዎንና ስራዎን ለማስፋፋት ትልቅ ድጋፍ
አስተማማኝና ምቹ – ለነገው እቅድዎ ዛሬ የሚጣል ጠንካራ መሰረት
ዛሬውኑ ወደ ቅርብ ቅርንጫፋችን በመምጣት የልዩ ቁጠባ ሂሳብ ይክፈቱ፤ የወደፊት ህልምዎን እውን ያድርጉ!
ለበለጠ መረጃ በ 0903004342 ይደውሉ
#ልዩቁጠባ #የሴቶችቁጠባ #የወጣቶችቁጠባ
መክሊት ማይክሮፋይናንስ!
እምቅ አቅምዎን ወደ ትሩፋት የሚቀይሩበት!!
+5
የመክሊት ማይክሮፋይናንስ አ.ማ አቃቂ ቅርንጫፍ የደንበኞች የምስጋና እና
የእውቅና መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
መክሊት ማይክሮፋይናንስ አ.ማ አቃቂ ቅርንጫፍ ከተቋሙ ጋር ለዓመታት በታማኝነት አብረው የዘለቁ፣ ለተቋሙ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ታማኝ ደንበኞቹን እውቅና ለመስጠትና ለማመስገን ያዘጋጀውን ልዩ መርሃ ግብር መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
በዕለቱ በተካሄደው የክብረ በዓል መርሃ ግብር ላይ የመክሊት ማይክሮፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ የመምሪያ ስራ አስኪያጆች ፤ቅርንጫፉ ስራ አስኪያጆች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ከተቋሙ ጋር ለአመታት የቆዩ በርካታ ደንበኞች የተገኙ ሲሆን፣ ለነበራቸው ዘላቂ አጋርነትና ታማኝነት የምስጋናና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
የመክሊት ዋና ስራ አስፈፃሚ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፡"ደንበኞቻችን ለተቋማችን እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ የስኬቶቻችን አጋር ናቸው” ሲሉ ገልፀው፣ ወደፊትም አገልግሎቱን በበለጠ ጥራትና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለማቅረብ ተቋሙ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
እውቅና የተሰጣቸው ደንበኞች በበኩላቸው፣ መክሊት ማይክሮፋይናንስ በስራቸውና በህይወታቸው ላይ ላስመዘገበው አውንታዊ ለውጥና ላሳየው አክብሮት ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ወደፊትም አጋርነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
መክሊት ማይክሮፋይናንስ አ.ማ
የእርስዎን እና የተቋምዎን የፋይናንስ ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አጠቃላይ የቁጠባ አገልግሎቶቻችንን ተጠቅመው የነገ ህልምዎን ዛሬ እውን ያድርጉ።
አስተማማኝ የቁጠባ አማራጮቻችን
የተቋማት የቁጠባ ሂሳብ
ለማህበራት፣ ለድርጅቶች እና ለተለያዩ ተቋማት የተዘጋጀ፤ የድርጅትዎን ትርፋማነት እና የፋይናንስ አቅም የሚያሳድግ እጅግ ማራኪ እና ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስገኝ የቁጠባ አማራጭ።
መክሊት ማይክሮፋይናንስ
እምቅ አቅምዎን ወደ ትሩፋት የሚቀይሩበት!!
ለበለጠ መረጃ በ 0903004342 ይደውሉ!
የጥንቃቄ መልዕክት ከመክሊት ማይክሮፋይናንስ
ውድ ደንበኞቻችን፤
ስልክዎ ወይም ሲምካርድዎ ቢጠፋብዎ ወይም ቢሰረቅብዎት የገንዘብዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሳይዘገዩ ለፋይናንስ ተቋምዎ ያሳውቁ!
ለደንበኞቻችን ደህንነት ቅድሚያ እንሰጣለን!
አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በ0903004342 በመደወል ያሳውቁ፡፡
+4
የመክሊት ማይክሮፋይናንስ አየር ጤና ቅርንጫፍ የደንበኞች የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ
መክሊት ማይክሮፋይናንስ አ.ማ አየር ጤና ቅርንጫፍ ከተቋሙ ጋር ለረጅም ዓመታት በታማኝነትና በፅናት አብረው የዘለቁ፣ ለተቋሙ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ታማኝ ደንበኞቹን እውቅና ለመስጠትና ለማመስገን ያዘጋጀውን ልዩ መርሃ ግብር መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
በዕለቱ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ የዋና መስሪያ ቤት የመምሪያ ሥራ አስኪያጆች ፤የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጆች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ከተቋሙ ጋር እንደ ቤተሰብ አብረው የቆዩ በርካታ ደንበኞች የተገኙ ሲሆን፣ለነበራቸው ዘላቂ አጋርነትና ታማኝነት የምስጋናና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፡ "ደንበኞቻችን የእድገታችን መሰረት፣ የጉዟችን ዋና አካል ናቸው። ባለፉት ዓመታት ያሳያችሁት ታማኝነትና አብሮነት ተቋማችን አሁን ለደረሰበት ደረጃ ትልቅ ጉልበት ሆኖናል" ሲሉ ገልፀው፣ ወደፊትም አገልግሎቱን በበለጠ ጥራትና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለማቅረብ ተቋሙ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
እውቅና የተሰጣቸው ደንበኞች በበኩላቸው፣ መክሊት ማይክሮፋይናንስ በስራቸውና በህይወታቸው ላይ ላስመዘገበው አውንታዊ ለውጥና ላሳየው አክብሮት ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ወደፊትም አጋርነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የጥንቃቄ መልዕክት ከመክሊት ማይክሮፋይናንስ
ክቡራን ደንበኞቻችን፤
ጓደኛ፣ወዳጅ፣ ዘመድ፣ በመምሰል በዋትስአፕ፣ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ኤሜል፣ የጽሁፍ መልዕክት ወይም የስልክ ጥሪዎች የሚመጣልዎትን የገንዘብ ማስተላለፍ ጥያቄዎች ከመፈጸምዎ በፊት የጠያቂውን ማንነት ያረጋግጡ
ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!
ለደንበኞቻችን ደህንነት ቅድሚያ እንሰጣለን!
አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በ0903004342 በመደወል ያሳውቁ፡፡
+2
መክሊት ማይክሮፋይናንስ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አመታዊ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡
መክሊት ማይክሮፋይናንስ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም እና የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ አካሄደ፡፡
ከሐምሌ 24-25, 2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በቆየው ጉባኤ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ አፈፃፀም ለጉባኤው ቀርቦ በተሰብሳቢዎች ውይይት የተደረገበት ሲሆን አፈፃፀሙም ጥሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች እና ሠራተኞች የእውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም ተከናውኗል፡፡በተጨማሪም የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩም የመክሊት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል አቶ አበበ ዳኘ፣ የመክሊት ዋና ስራ አስፈፃሚ ፣ አቶ ዘገየ ባንቴን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ፣ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
መክሊት ማይክሮፋይናንስ
እምቅ አቅምዎን ወደትሩፋት የሚቀይሩበት!
የጥንቃቄ መልዕክት ከመክሊት ማይክሮፋይናንስ
ክቡራን ደንበኞቻችን፤
የብድር ወይም የቁጠባ ክፍያ በሚፈፅሙበት ወቅት የተቋሙ ህጋዊ ደረሰኝ እና ገንዘብ የሚቀበለው ሰው የተቋሙን ህጋዊ መታወቂያ የያዘ ሰራተኛ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጡ፡፡
ለደንበኞቻችን ደህንነት ቅድሚያ እንሰጣለን!
አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በ0903004342 በመደወል ያሳውቁ፡፡
+2
መክሊት ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አጽድቋል
መክሊት ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. የተቋሙ የቦርድ አባላቱና ሁሉም የማኔጅመንት አካላት በተገኙበት በጋራ የ2019 በጀት ዓመት አጠቃላይ አመታዊ ዕቅድ ላይ በመወያየት አመታዊ ዕቅዱን ገምግሞ አጽድቋል።
በቢሾፍቱ አዱላላ ሪዞርት ከሰኔ 19 - 20, 2018 ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ በአዲሱ በጀት ዓመት ተቋሙ በተለይ የቁጠባ ሃብት በማሰባሰብ፣ የዲጂታል ብድር አገልግሎት በማሰጀመር ፣ የማርኬቲንግ ሥራዎችን በማጠናከር እና በየደረጃው ላሉ የተቋሙ አመራር አካላትና ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን በስፋት መስጠት ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም፣ ተቋሙ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎቶችን በማስፋፋት የደንበኞችን ተደራሽነትና እርካታ ለማሳደግ፣ እና የገበያ ተወዳዳሪነቱን በማጠናከር የሰው ኃይል አቅሙን በቀጣይነት ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተብራርቷል።
ከላይ የተገለፁት ተግባራትም ተቋሙ ያስቀመጣቸውን ስትራቴጂያዊ ግቦች በተሳካ ሁኔታ ለማሳካት ወሳኝ መሠረት እንደሚሆኑ በስብሰባው የተገለፀ ሲሆን በመጨረሻም የመክሊት የቦርድ አባላት ማኔጅመንቱ አጠቃላይ ለተቋሙ ስራ እያደረገ ያለውን ጥረት በማመስገን የተለያዩ የስራ አቅጣጫዎችን በመስጠት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡
+5
እንኳን ደስ አላችሁ!
መክሊት ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዪሽን አ.ማ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በሻሸመኔ ከተማ 39ኛ ቅርንጫፉን በተጨማሪም 40ኛ ቅርንጫፉን በወላይታ ሶዶ ከተማ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት አካላት የከተማዋ ነዋሪዎች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አስመርቆ ከፈተ።
መክሊት ማይክሮ ፋይናንስ
እምቅ አቅምዎን ወደ ትሩፋት የሚቀይሩበት!!
+1
የሀዘን መግለጫ
የመክሊት ማይክሮ ፋይናንስ አዳማ ቅርንጫፍ ባልደረባ የነበሩ አቶ ጌታቸው ገበየሁ በድንገት ህይዎታቸው በማለፉ የተሰማንን ታላቅ ሀዘን እየገለፅን ለመላው ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል-አድሀ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መክሊት ማይክሮፋይናንስ
የጥንቃቄ መልዕክት ከመክሊት ማይክሮፋይናንስ !
ውድ ደንበኞች ፤
በተቋማችን ስም በመጠቀም ሕገ-ወጥ ገንዘብ ጥያቄ ፣ የሃሰት የብድር ቃልኪዳን ወይም የመረጃ ስርቆት ሊፈፅሙ የሚችሉ ግለሰቦች ስለሚኖሩ እንዲጠነቀቁ እናሳስባለን፡፡
የተቋማችን አሰራር በአካል ቅርንጫፍ በመቅረብ የሚፈጸም በመሆኑ በስልክም ሆነ በማህበራዊ ድረገፅ የሚመጡ የማታለያ መልዕክቶችን አይመኑ፡፡
በተጨማሪም
• የይለፍ ቃል(password) ወይም የሂሳብ መረጃዎን ለማንም አያጋሩ፡፡
• ከተቋሙ ውጭ ለሚጠየቅ ክፍያ ገንዘብ አይላኩ፡፡
• ያልተረጋገጡ ስልክ ወይም መልዕክቶችን አይመኑ፡፡
• ማንኛውም አጠራጣሪ ድርጊት ሲያጋጥምዎ በ0903004342 ለተቋሙ ያሳውቁ፡፡
ለደንበኞቻችን ደህንነት ቅድሚያ እንሰጣለን !
መክሊት ማይክሮ ፋይናንስ !
