Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
رفتن به کانال در Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
نمایش بیشتر213
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-430 روز
آرشیو پست ها
አላህ ዘንድ የሚወደደውና የሚጠላው…
ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إنَّ أحبَّ الكلامِ إلى اللَّهِ أن يقولَ العبدُ: سبحانَكَ اللَّهمَّ وبحمدِكَ، وتبارَكَ اسمُكَ، وتعالى جدُّكَ، ولا إلَهَ غيرُكَ، وإنَّ أبغضَ الكلامِ إلى اللَّهِ أن يقولَ الرَّجلُ للرَّجلِ: اتَّقِ اللَّهَ، فيقولُ عليكَ نفسَكَ﴾
“አላህ ዘንድ ተወዳጅ ከሆነ ንግግር ባሪያው እንዲህ የሚለው ነው፦ ‘አላህ ሆይ! ከጎደሎ ነገሮች ሁሉ የጠራህ ነህ። ምስጋናዬንም አቀርባለሁ። ስምህ የተቀደሰ ነው። ልዕልናህ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከአንተ ሌላ አምላክ የለም።’ አላህ ዘንድ የተጠላ ንግግር ማለት ደግሞ፦ ‘ሰውዬው ለሰውዬው አላህን ፍራ በሚለው ግዜ ለራስህ ፍራ ብሎ የሚመልስለት መልስ ነው።’”
📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 2939
✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
✅፦ https://bit.ly/4ayf0xJ
👍፦ https://bit.ly/486xnrS
📱፦ https://bit.ly/41zEZkk
✅፦ https://bit.ly/4arMbTx
✅፦ https://bit.ly/41tIUPv
▶️፦ https://bit.ly/3UTTSwh
Hijaab is not a Barrier between you and the people.
It is the Barrier between you and the evil of the people.
Dr.Zakir Naik
t.me/ReshadIbnuMuzemil
ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼
==================
✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ።
ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል።
https://t.me/MuradTadesse/35708
*
ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት።
https://t.me/MuradTadesse/35742
ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር!
አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር።
የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል።
https://t.me/MuradTadesse/35632?single
ከተቋማችንም ጎን እንቁም።
የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
ጥሩ አቀማማጭ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَثَلُ جَلِيسِ الصَّالِحِ وَالسَّوْءِ، كَحَامِلِ الْمِسْكِ وَنَافِخِ الْكِيرِ ، فَحَامِلُ الْمِسْكِ ؛ إِمَّا أَنْ يُحْذِيَكَ، وَإِمَّا أَنْ تَبْتَاعَ مِنْهُ، وَإِمَّا أَنْ تَجِدَ مِنْهُ رِيحًا طَيِّبَةً، وَنَافِخُ الْكِيرِ ؛ إِمَّا أَنْ يُحْرِقَ ثِيَابَكَ، وَإِمَّا أَنْ تَجِدَ رِيحًا خَبِيثَةً﴾
“የጥሩና የመጥፎ ጎደኛ አቀማማጭ ምሳሌው ሚስክ እንደያዘና (እንደሚነግድና) ወናፍ እንደሚነፋ ቢጤ ነው። ሽቶ የሚሸጠው ሰው ስጦታ ይሰጥሀል፣ ወይም ትገዛዋለህ ወይም መልካም ሽታን ከሱ ታገኛለህ። ወናፍ የሚነፋው ሰው ደግሞ ወይ ልብስህን ያቃጥልብሀል ወይም መጥፎ ሽታን ያወርስሀል (ያሸትሀል)።”
📚 ቡኻሪ (5534) ሙስሊም (2628) ዘግበውታል
ኢትዮጵያ ኒቃብ መልበስን ልትከለክል ነው‼
=============================
(የአዲሱ ረቂቅ አዋጅ 15+ ስጋቶች!)
||
✍ የኢትዮጵያ መንግስት ኒቃበ ለብሶ መማርንና መሥራትን የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለማፅደቅ በሂደት ላይ ነው። እስካሁን ድረስ በሃገሪቱ ኒቃብን በግልፅ የሚከለክል ህግ ባይኖርም፤ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊም ጠል ኃይሎች ባልተጻፈ ህግ ኒቃብ መልበስን ሲከለክሉ ነበር። ለናሙና ያክል በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በኒቃብ ሳቢያ 2000 ገደማ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የታገዱበት ሁኔታ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።
ለነዚህና መሰል ኒቃብን በግል ጥላቻቸው ተነሳስተው ለሚከለክሉ አካላት ሽፋን የሚሰጥ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለመፅደቅ በሂደት ላይ ነው። ከኒቃብ ጉዳይ ባሻገር በመሰል ተቋማትና አንዳንድ የህዝብ መገልገያ አካባቢዎች በጀማዓህ ሶላት መስገድን የሚከለክል ክፍልም አለው። ረቂቅ አዋጁ ከመዘጋጀቱ በፊት ለግብዓትነት የሚሆን ጥናት ቀድሞ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉ 10 አባላት መካከል ሙስሊሙን የወከለው አንድ ግለሰብ ብቻ ነበር። ግና ከጥናት ዝግጅቱ ጀምሮ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በአግባቡ ያልወከለው ሂደት፤ ጭራሽ ረቂቅ አዋጁ ላይ ግልፅ የሙስሊሙ መብት ጥሰቶች ተካተዋል።
በዚህ በባለ 15 ገፅ በንድፍ ላይ ያለ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በቀጥታ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር ከሚጋጩ ነጥቦች መካከል፤
የሚከተሉት አንቀፆችና ንዑስ አንቀፆች ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር የሚያጋጩና ጥያቄ የሚያስነሱ ናቸው።
1) 13.8 "የተከለከሉ ቦታዎች ቅስቀሳ ማድረግ" ማለት የትኞቹ በታዎች ናቸው?
2) 13.9 other (ሌሎች) ማለት ምን ማለት ነው?
3) 15.1 መስጂድ ሲጠበን ከመስጅድ ውጪ መስገድ አንችልም ማለት ነው? መስጅድ በሌለበት መስገድ አይቻልም? ይህን መሠረት አድርገው ሰበብ ፈላጊዎች ከመስጅድ ውጭ መስገድን እንዲከለክሉ መንገድ ስለሚከፍት ይህን እንደማይመለከት በግልፅ ሌላ ንዑስ አንቀፅ ላይ መስፈር አለበት።
4) 15.4 ሁሉም ቦታ በሚባል ደረጃ ሶላትን ይከለክላል፡፡
5) 17.4 "በቡድን አምልኮ" በሚል ሽፋን የጀመዓህ ሶላትን ለመከልከል ይውላል።
6) 17.7 ቅጣቶች ለመንግስት መ/ቤቶች ክፍት ሆነዋልና ሌላ ችግር እንዲፈጠር በር ይከፍታል፡፡ ምክንየተቱም የትኛውም መሥሪያ ቤት ተነስቶ የራሱን ቅጣት በጥላቻ ቢያስተላልፍ መብት አለው ማለትን ያሲዛል።
7) 19.1 "ከኃይማኖት ተፅዕኖ ነፃ መሆን" ማለት ምን ማለት ነው? እስከምን ደረጃ?
8) 19.2: የአንዳንድ ኢስላማዊ ትምህርት ቤቶችን አሠራር ለማፈን በር የሚከፍት ነገር አለው።
9) 19.5 በትምህርት ቤቶች የጀመዓህ ሶላት ተከልክሏል፡፡
10) 19.6: "ማንነትን ለመለየት" በሚል ሽፋን ኒቃብን ይከለክላል። በዚህ ቴክኖሎጂው ባደገበት ዘመን እንደ አሻራ ያሉ ቀላል ወጪ የሚጠይቁ ዘዴዎች እያሉ፣ በተለመደው አሠራርም በሴት የጥበቃ ሠራተኛ ማንነታቸውን መለየት እየተቻለ፣ በቢዝነስ ተቋማት ዘንድ ይህ ጥያቄ ሳይነሳ መኗኗር ሲቻል እያዬን… በዚህ ሽፋን ኒቃብን መከልከል ነውር ነው።
11) 22.2 በተለይም በሸሪዓው ውርስንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ለአንዳንድ ሙጅሪሞች በር ይከፍታል።
12) 24.1 የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ በተለይም በሙስሊሙ ዘንድ ሶደቃ የተለመደ ነውና!
13) 25.1: ይህም የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡
14) 25.3 ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ መጅሊስ በአዋጅ የተቋቋመ ራሱን የቻለ ተቋም ከሆነ በዚህ ደረጃ በሌላ የበላይ አካል control መደረግ የለበትም።
15) 25.4: ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ "በአዋጅ መቋቋም" የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ትርጉም አሳጥቶ እንደተለመደው ወደ ተራ NGO ከማውረድ አይተናነስም።
16) 26: "ከኃይማኖት ተፅዕኖ የተላቀቀ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚወስኑት የየትምርት ቤቱ ኃላፊዎች ቢሆኑ የተሻለ ይሆናል፡፡ አለበለዚያ የኢስላማዊ ት/ቤቶችን ነፃነት ያፍናል።
…
ባለ 15 ገፁ ይህ ረቂቅ አዋጅ በሶፍቲ ኮፒ በዚህ ሊንክ ስለሚገኝ፤ አንብቡትና እናንተም የታዘባችኋቸውን ስጋቶችና ህፀፆች አስፍሯቸው።
https://t.me/MuradTadesse/35726
♠
ይህ አፈና ሳይጻፍ የተበደልነው አንሶን ጭራሽ ተልፎ ሊተገበርብን ጫፍ ሲደርስ በዝምታ ማሳለፍ የለብንምና ሁሉም ሰላም ወዳድና ለእምነቱ ተቆርቋሪ ከወዲሁ ጉዳዩ ሳይጸድቅ ይስተካከል ዘንድ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ግደታችን ነው።
መልዕክቱን ለሌሎችም በማሰራጨት ህዝበ ሙስሊሙ እየመጣ ስላለው አዲስ አዋጅ ከወዲሁ በቂ መረጃና ግንዛቤ ኖሮት የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ እናድርግ።
||
t.me/MuradTadesse
x.com/MuradTadesse
fb.com/MuradTadesse
አቡ ኽልደህ አልበስሪ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿أدرَكْتُ النَّاسَ وهُم يعمَلون ولا يقُولُونَ وهُم اليَومَ يقُولونَ ولا يعملُونَ﴾
“ሰዎች ላይ ደርሻለሁ (አግኝቻለሁ) እነሱ መልካም ስራ ይሰራሉ አይናገሩትም። ዛሬ ግን ያሉት ይናገሩታል ግን አይሰሩትም።”
📚 [«አልኪታቡ ሰምት» ሊኢብን አቢ ዱኒያ (678)]
ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM
ፈለስጢናውያን ከትውልድ ቀያቸው ወደየት ይሂዱ? ወራሪያ ያልነጀሰችው የፈለስጢን ክፍል ምን አለ? አላህ ስቃያቸውን ከዚህ በላይ አያርዝምባቸው።
ይህ ቪድዮ ሁኔታውን ይገልፀዋል።
||
t.me/MuradTadesse
"ጌታዉን የሚያወሳና የማያወሳ ሰው
ምሳሌው በህይወት እንዳለና
እንደሞተ ሰው ነው።"
ነብያችን(ﷺ)
(ቡኻሪ ዘግበውታል:6407)
አላህን አምጸኸው፣ ወንጀል ሠርተህ በዛው ቅፅበት የሆነ ኒዕማ ካገኘህ፤ ልብ በል! ወዶህ ሳይሆን ለብርቱና አሳማሚ ቅጣቱ እያመቻቸህ ነው። በተሰጠህ ኒዕማ መደሰቱን ተወውና ቶሎ ደንግጠህ ከወንጀልህ በመፀፀት ወደ አላህ ተመለስ።
አላህ እንዲህ ይላል፦
(وَالَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا سَنَسْتَدْرِجُهُم مِّنْ حَيْثُ لَا يَعْلَمُونَ,
وَأُمْلِي لَهُمْ ۚ إِنَّ كَيْدِي مَتِينٌ)
«እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን ከማያውቁት ስፍራ ቀስ በቀስ (ምቾትን በመጨመር) እናዘነጋቸዋለን፡፡
ለእነርሱም ጊዜ እሰጣቸዋለሁ፤ ጥበቤ ብርቱ ነውና፡፡»
[አል-አዕራፍ: 182-183]
||
t.me/MuradTadesse
And I say by Allah, even if the Niqab were not obligatory, it would be obligatory today with all these temptations!
Shaykh Sulayman Ar-Ruhayli حفظه الله
የአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ጥናት‼
===================
የመንግስት እና ሃይማኖት ግንኙነት በኢትዮጵያ፤ ትናንት ዛሬ እና ነገ
አዘጋጅ፦ የፌዴራል የፍትሕና የህግ ኢንስቲትዩት
የሶፍት ኮፒ (PDF) መገኛ ሊንክ፦ https://t.me/MuradTadesse/35708
♠
እያንዳንዷን መስመር ምን ታሲዛለች፣ ምን ትርጉም አላት፣ ምን ተፈልጎባት ነው ብላችሁ በጥንቃቄና በጥሞና አንብቡት። በተለይም ከኡማው ጥቅምና ጉዳት አንፃር!
||
t.me/MuradTadesse
x.com/MuradTadesse
fb.com/MuradTadesse
ummalife.com/MuradTadesse
tiktok.com/@MuradTadesse
📹 استمع| لأول تسجيل صوتي لتلاوة القرآن بمكة في عهد الدولة العثمانية → 👤 AlJazeera Arabic قناة الجزيرةከዛሬ 137 ዓመት በፊት የተቀዳ ድምፅ ነው ቃሪዑ ከምድር በታች ነው ያለው ነገር ግን ምንዳው አልተቋረጠም ከግማሽ ሚሊዮን ሰው በላይ ዩትዩብ ላይ አዳምጦታል ቀጣይነት ያለው ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከሞተ በኋላ ትተህ የምታልፈውን አዘጋጅ ትንሽ ነገር ናት ብለህ አትናቃት ምናልባት አላህ ዘንድ ትልቅ ሆና ከትውልድ ወደ ትውልድ የምትሸጋገርልህ መልካም ስራህ እሷ ብቻ ልትሆን ትችላለች አላህ ሆይ ለቃሪዑም ለኛም እዘንልን 🤲 ✍ TOLEHA AHMED
"يا عابدَ الحَرَمينِ لوْ أبصرْتَنا .. لَعلمْتَ أنّك في العبادةِ تَلْعبُ
مَنْ كان يَخْضِبُ خدَّهُ بدموعِهِ .. فَنُحُورُنا بِدِمَائِنا تَتَخَضَّبُ "
ابن مبارك لفضيل بن العياض
መቶ ያህል ሰዎች!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿ما من رجلٍ يُصلِّي عليهِ مئةٌ؛ إلّا غَفر اللهُ لهُ﴾
“በሰውዬው ላይ መቶ ያህል ሰዎች በጀናዛው ላይ አይሰግዱበትም አላህ ለሱ ምህረት ቢያደርግለት እንጂ።”
📚 ሶሂህ አተርጊብ: 3506
በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
🌐፦ https://bit.ly/4ayf0xJ
🌐፦ https://bit.ly/486xnrS
🌐፦ https://bit.ly/41zEZkk
🌐፦ https://bit.ly/4arMbTx
🐦፦ https://bit.ly/41tIUPv
▶️፦ https://bit.ly/41yPkNg
የሙስሊም ሁኔታ ለሶላት ወደ መስጂድ ሲጎዝ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إذا أتيتَ الصلاةَ فأْتها بوقارٍ وسكينةٍ، فصلِّ ما أدركتَ، واقضِ ما فاتكَ﴾
“ለሶላት በምትመጡ ግዜ በእርጋታና በዝግታ ተጓዙ። የደረሳችሁበትን ስገዱ። ያመለጣችሁን ደግሞ ሙሉ።”
📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 1198
በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
🌐፦ https://bit.ly/4ayf0xJ
🌐፦ https://bit.ly/486xnrS
🌐፦ https://bit.ly/41zEZkk
🌐፦ https://bit.ly/4arMbTx
🐦፦ https://bit.ly/41tIUPv
▶️፦ https://bit.ly/41yPkNg
ሰበብ እያደረሳችሁ በአላህ ተጠበቁ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿أغلقْ بابَك واذكرِ اسمَ اللهِ، فإنَّ الشيطانَ لا يفتحُ بابًا مُغلقًا﴾
“በርህን ቆልፍ የአላህንም ስም አውሳ፤ ሸይጣን የተቆለፈን በር አይከፍትምና።”
📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል፡ 3731
A shocking video documents the mass destruction in northern Gaza after months of relentless Israeli occupation bombardment.
