fa
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

رفتن به کانال در Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

نمایش بیشتر
213
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 عوز
-430 عوز
آرشیو پست ها
Following the withdrawal of Israeli forces, scenes of the unprecedented destruction of homes and a mosque on Abu Shabak Street in Tal al-Hawa, southwest of Gaza.

💫ፆመኛ ሆኖ ምራቅን መዋጥ   ~ ምራቅን መዋጥ ፆምን የሚያበላሽ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ቦታ ከተቀመጡ አካባቢያቸውን ምራቅ በምራቅ ሲያደርጉት ያጋጥማል፡፡ ምራቅ ፆም ያበላሻልን? 1.💥 መደበኛ ወይም ከወትሮው ያልበዛ ከሆነ ከተለመደው ያልተጋነነ ምራቅ ከአፍ አውጥተው ካልመለሱት በስተቀር ባለበት ሁኔታ ቢዋጥ ፆም እንደማያበላሽ ኢብኑ ሐዝምና ነወዊ #ኢጅማዕ ጠቅሰዋል፡፡ 2.💥 ታስቦበት ባልሆነ መንገድ ከበዛና ከተጠራቀመስ? ሆን ብለን ሳናጠራቅመው እንዲሁ ወሬ ስናወራ ወይም ቁርኣን ስንቀራ፣… ምራቃችን ሊበዛ ይችላል፡፡ ይህንንስ የዋጠ ፆሙ ይበላሻል? ነወዊ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ሳይታሰብበት ብዙ ምራቅ ቢጠራቀም፣ ለምሳሌ ንግግሩ በመብዛቱና መሰል ሰበብ የተነሳ ሆን ብሎ ሳያደርገው ቢበዛና ቢውጠው (በሻፍዒያ መዝሀብ) ያለ ልዩነት ፆሙ አልተበላሸም፡፡” ይሄ የብዙ ዑለማዎች አቋም ነው፡፡ 3.💥 ታስቦበት ከተጠራቀመስ? አንድ ሰው ስራየ ብሎ ምራቁን ካጠራቀመ በኋላ ቢወጠው ፆሙ ይበላሻል ወይስ አይበላሸም በሚለው ላይ ውዝግብ አለበት፡፡ በሻፍዒያ መዝሀብ ትክክለኛው አቋም ሐንበልያም ዘንድ እንዲሁ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለው ነው፡፡ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚንም ረሒመሁላህ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለውን መርጠዋል፡፡ ሆኖም ግን እራስን ከውዝግብ ማራቅ ተገቢ ነውና መጠንቀቁ ሰላማዊ ምርጫ ነው፡፡ 💫አክታን መዋጥስ? ~~~ 4. 💥ከአቅም በላይ ከሆነ ማስወገድ በማይችለው መልኩ ከጭንቅላቱ ቀጥታ ወደታች የሚወርድ አክታ ከሆነ ሊጠነቀቀው አይችልም፡፡ አላህ ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ነገር አይዝም፡፡ 5.💥 መቆጣጠር ሲቻል ቢዋጥስ? ነገር ግን ስራዬ ብሎ አውጥቶ አፉ ጋር ካደረሰው በኋላ መትፋት ሲችል ቢውጠው ፆሙ ይበላሻል ያሉ ዐሊሞች አሉ፡፡ ከፊሎቹ ግን ይህም ቢሆን አይበላሽም ብለዋል፡፡ ለምሳሌ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን ረሒመሁላህ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለውን መርጠዋል፡፡ ታዲያ “ፆሙ አያበላሽም” ይበሉ እንጂ ድርጊቱ ፆመኛ ለሆነም ይሁን ላልሆነ  ነው ሐራም እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ አንደኛ አፀያፊ ነው፡፡ ሁለተኛ ምናልባትም በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን የተሸከመ ሊሆን ስለሚችል ወደ ሆድ ሲገባ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል የሚል ነው፡፡ [ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 6/428] እራስን ከውዝግብ ለማራቅ ሲባል መራቁም እራሱን የቻለ ዋጋ አለው፡፡ 🍁ወልላሁ አዕለም፡፡ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇 https://t.me/tolehaahmed

✍ ✨የአላህ ልዩ ሰዎች✨ የአላህ መልእክተኛ  እንዲህ ብለዋል፦ ÂŤ( إِنَّ لِلَّهِ أَهْلِينَ مِنْ النَّاسِ ) قَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، مَنْ هُمْ ؟ قَالَ : ( هُمْ أَهْلُ الْقُرْآنِ ، أَهْلُ اللَّهِ وَخَاصَّتُهُ )Âť «ለአላህ ከሰዎች መካከል ቤተሰቦች አሉት። "እነርሱ እነማን ናቸው?Âť ተብለው ሲጠየቁ፤ እነርሱ የቁርኣን ባለቤቶች ናቸው። የአላህ ቤተሰቦች እና ልዩ ሰዎቹ ናቸው።» (ኢብኑ ማጃህ: 215 ዘግበውታል። አሕመድ: 11870፣ አል-አልባኒም ሰሒሕ ብለውታል።) وقال الشيخ ابن جبرين رحمه الله : " الذين يقرؤون القرآن طوال عامهم ، هم أهل القرآن ، الذين هم أهل الله وخاصته  💥 ዑለማዎች በዚህ ሐዲሥ ውስጥ የቁርኣን ሰዎችን የአላህ ወዳጆች እና ልዩ ሰዎች ያሰኛቸው ምንድን ነው? ስለሚለው ሲያብራሩ ቁርኣንን መሐፈዛቸው ወይም መሸምደዳቸው፣ በእርሱ መስራታቸው፣ ጠዋት ይሁን ማታ እሱን ማንበባቸው፣ ልባቸው ከተለያዩ በሽታዎች የጠራ እንዲሁም አላህን በመታዘዝ ህይወታቸው ያሸበረቀ መሆኑ ነው ብለዋል። በተጨማሪም "የአላህ ቤተሰቦች" የሚለው የአላህ ውዴታ እና ልዩ እንከብካቤን የሚያገኙ መሆናቸውን የሚጠቁም መሆኑን ገልፀዋል። ረመዿን ላይ ከሌላው ግዜ በበለጠ ቁርኣን ለመቅራት ትልቅ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል። ደጋግመን ለማኽተም እንሞክር። ሌላ ወር ላይ ከሚገኘው አጅር እጥፍ ድርብ የሆነ አጅር ነውና የሚገኝበት። ✒️📖  አላህ አላማቸውን አውቀው ለዚያ ኖረው ከርሱ ዘንድ የተዘጋጀላቸው ምንዳ ከሚቋደሱ ባሮቹ ያድርገን። ኣሚን!🤲🤲🤲 ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇 https://t.me/tolehaahmed

💻 ዝም በላቸው፤ አንተ የተሳሳትክና ያሸነፉህ ይምሰላቸው። አንተ ግን ይህን በል «እኔ አላህ በቂዬ ነው»❗️ 🔰 ከጌታዬ ጋር ያለኝ ግንኙነት የተስተካከለ ከሆነ ስለ ሰዎች ለምን ልጨነቅ⁉️ 💻 በ
💻 ዝም በላቸው፤ አንተ የተሳሳትክና ያሸነፉህ ይምሰላቸው። አንተ ግን ይህን በል «እኔ አላህ በቂዬ ነው»❗️ 🔰 ከጌታዬ ጋር ያለኝ ግንኙነት የተስተካከለ ከሆነ ስለ ሰዎች ለምን ልጨነቅ⁉️ 💻 በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ummalife.com/ReshadMuzemil t.me/SharpSwords1

#ድንቅ_እሁድ #ውብ_ውሎ #መጋቢት_አንድ #ሚሊኒየም_አዳራሽ #ስድስት_ቀናት
#ድንቅ_እሁድ #ውብ_ውሎ #መጋቢት_አንድ #ሚሊኒየም_አዳራሽ #ስድስት_ቀናት

በረመዿን ፆም ዙርያ ጥያቄና መልስ፦ 11ኛ - ጥያቄ፦ እናቴ አላህ ይማራትና ከመሞቷ በፊት በጭንቅላቷ ወድቃ አዕምሮዋ ስለተነካ ለአንድ አመት ያክል ሰላትም ሆነ ፆም አትችልም ነበር። አሁን እኔ ልጃ* ምን ላድርግላት ? መልስ፡- እናትህ እንደምትለው አዕምሮዋ ከተነካ ፆም ግዴታ አይሆንባትም ነበር። ግን አዕምሮዋ ጤነኛ ከሆነና ከተወችው ከውርስ ንብረት ላይ ተወስዶ ከፋራ መከፈል አለበት። የተወችው ንብረት ከሌለ ከቤተሰብ አንዱ ቢከፍልላትም ሆነ ቢፆምላት ሊጠቅማት ይችላል፡፡ 12ኛ - ጥያቄ áĄ- እድሜው አሥራ ስድስት አመት የሞላው ተማሪ በረመዿን ፆም የትምህርት ቤት ፈተና ቢገጥመው ለፈተናው እንዲመቸው ብሎ ማፍጠር ይችላል? መልስ áĄ- ለአካለ መጠን የደረሰ ተማሪ በፈተና ሰበብ ማፍጠር አይችልም አላህ በቁርአኑ ፡- ‏{‏فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ...} «ከናንተ ውስጥ ወሩን ያገኘ ይፁም።» [አል-በቀረህ: 185] ስለዚህ ካለ ሕመም በስተቀር በሌላ ምክንያት ፆምን መተው አይቻልም። ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት ግን ቢያፈጥሩ ምንም አይደለም ፡፡ 13ኛ - ጥያቄ áĄ- አራት መቶ ኪሎ ሜትር የሚገዝ መንገደኛ ማፍጠር ይችላል። የሚችል ከሆነ ስንት ቀን ድረስ ነው የሚያፈጥረው? መልስ áĄ- መንገደኛ የሚገዘው ከሰማንያ ኪሎ ሜትር በላይ ከሆነ ማፍጠርም ሆነ ሰላትን አሳጥሮ መስገድ ይችላል። መንገደኛው የሚመለስበትን ቀን የማያውቀው ከሆነ ላልተወሰነ ጊዜ ፆሙን ማፍጠርም ሆነ ሰላቱን ማሳጠር ይችላል። የተጓዘበት አካባቢ ሲደርስ እዛው ለመኖር ከነየተ ከአራት ቀንና ሌሊት በላይ ማፍጠርም ሆነ ሰላት ማሳጠር አይችልም። 14 - ጥያቄ áĄ- እባኮትን እስኪ ሾለ ረመዿን የመጨረሻ አስር ቀኖች (ዓሸረል አዋኺር) ጥቅምና ደረጃውን ቢያብራሩልን? መልስ áĄ- የዓሸረል አዋኺር ደረጃው በጣም ትልቅ ነው። ረሱልም  በረመዿን ከመጀመርያዎቹ ቀኖች ይበልጥ በዓሸረል አዋኺር በዒባዳሀወ ይጥራሉ፣ ተሐጁድ ሰላት ይሰግዳሉ፣ ኢዕቲካፍ ለማድረግ መስጅድ ተጠቃለው ይገባሉ። ለይለተል ቀድርንም ለማግኘት በዓሸረል አዋኺር በይበልጥ ተስፋ ያደርጋሉ ፡፡ 15 - ጥያቄ áĄ- በተባረከው የረመዿን ወር የተወደዱት ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? መልስ áĄ- በረመዿን የተወደዱ ሥራዎች በጣም ብዙ ናቸው። ከነሱም ውስጥ አላህ ግዴታ ያደረጋቸውን ሰላትም ሆነ ፆም በትክክል መፈፀም፡ ግዴታ ያልሆኑ ተጨማሪ ሥራዎችን ማብዛት። ይኸውም ቁርአን መቅራት ፣ ተራዊሕ እና ተሃጁድ መስጀድ፣ ሰደቃ መስጠት፣ ኢዕቲካፍ መግባት ፣ አላህን ማውሳት ማብዛት፣ ለዒባዳ ብሎ መስጊድ መቀመጥ ማብዛት፣ ከተጠሉና ከተከለከሉ ሥራዎችና ቃሎችን መቆጠብ እና ፆም እንዳይበላሽ መጠንቀቅ ናቸው ፡፡ 16ኛ - ጥያቄ áĄ-ኢዕቲካፍ ምን ማለት ነው? ደንቡስ እንዴት ነው? ቤቴ ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ እችላለሁ? መልስ áĄ- ኢዕቲካፍ በኢስላም ትልቅ ዒባዳ ነው። አላህም በቁርአኑ ‏ለነብዩ ኢብራሂምና ኢስማዒል (ዐለይሂማ ሰላም) እንዲህ ብሏቸዋል፡- «ለኢብራሂም የቤቱን (የከዕባን) ስፍራ መመለም ባደረግንለት ጊዜ በኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸው ለሚደፉት ንፁሕ አድርግላቸው። /ባልነው ጊዜ አስታውስ/Âť [አል-ሐጅ: 26] ረሱልም  በረመዿን ግማሽ ጀምሮ ኢዕቲካፍ ይገቡ ነበር። በሕይወታቸው መጨረሻ አካባቢ ለይለቱል ቀድር ይበልጥ ተስፋ የሚደረገው በዓሸረል አዋኺር ሊሆን እንደሚችል ሲገለፅላቸው በረመዿን በመጨረሻ አስሩ ቀኖች ኢዕቲካፍ ለማድረግ ከነባለቤቶቻቸው መስጅድ ይገቡ ጀመር፡፡ ኢዕቲካፍ ከመስጅድ በስተቀር ቤትም ሆነ ሌላ ቦታ አይቻልም። አላህም በቁርአኑ፦ «እናንተም በመስጅዶች ተቀማጮች ስትሆኑ /ሴቶችን/ አትገናኙዋቸው!Âť ይላል። 17ኛ- ጥያቄ -፡ በረመዿን ቀኑን ሙሉ ተኝቶ በማፍጠርያ ሰዓት ከንቅልፉ የሚነሳ ሰው እንዴት ይታያል? (ሑክሙ) ምንድነው? መልስ፡- ከፈጅር በፊት ፆም ነይቶ ቀኑን ሙሉ የተኛ ጿሚ ፆሙ ትክክል ነው። ነገር ግን በሰላቶች ወቅት መተኛቱ ሐራም ነው። መጀመርያ ሰላቱን በወቅቱ ያለመስገዱ፣ ሁለተኛ ጀማዓ ሰላት መስጅድ ያለመሄዱ፣ ሲደመርበት ትልቅ ወንጀል ሠል ማለት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ በጣም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ብዙ ሰዎች ልምድ አድርገዋ የያዙት በረመዳን ሌሊቱን በማይረባ ነገር አምሽተው ፈጅር ሲደርስ ሰሑር በልተው ቀኑን ሙሉ ይተኛሉ። ፆም ደግሞ ያለሰላት ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ሰዎች አደጋ ላይ ነው ያሉት፡፡ 18ኛ-ጥያቄ:በረመዿን ወር ቴሌቪዥን እና ቪዲዮ መመልከት ፆምን ያጓድላልን? መልስ: አንድ ሠው የሚያዳምጠው ወይም የሚመለከተው ነገር ከተፈቀዱ ነገሮች (ሙባሀት) ከሆነ ምንም ችግር የለውም። ፆሙ ላይ እንከን አይሆንም፡፡ ሆኖም ግን ፆመኛ ሰው ጊዜውን ወደ አላህ ሊያቃርበው በሚችል ነገር ብቻ ነው ማሳለፍ ያለበት፡፡ ቁርኣንን ያነባል፣ አላህን ያወድሳል ወዘተ... አላህ ሐራም ያደረገውን ነገር ማዳመጥ ወይም መመልከት ግን ፆምን እንደሚያጓድል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የዚህም ምክንያት ፆም የተደነገገበት አላማ የአላህን ፍራቻ(ተቅዋን) መላበስ ነው፡፡ ምንጭ፦ የረመዷን ስንቅ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇 tiktok.com/@secretsof_truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 ummalife.com/ReshadMuzemil

✍ በረመዿን ፆም ዙርያ ጥያቄና መልስ፦ 1ኛ - ጥያቄ፦ባጠቃላይ ፆም የሚያበላሹ ነገሮች ምን ምን ናቸው? መልስ:- ፆም የሚያበላሹ ነገሮች: 1. እያወቁ መብላትና መጠጣት ፡፡ 2. የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ፡፡ 3. አውቆ ከብልት ፈሳሽ ማስወጣት ፡፡ 4. የአይን፣ የጆሮ፣ እና የአፍንጫ ጠብታ ተንሸራቶ ወደ ጉሮሮ መግባት ፡፡ 5. እንደ ግሉኮስ አይነትና ምግብ ነክ መርፌ መውሰድ፡፡ 6. ዋግምት ማድረግ፡፡ 7. በወር አበባና በወሊድ ደም ወቅት፡፡ ( መፆሙ ሐራም ነው!) 8. አውቆ ማስታወክ ናቸው ፡፡ (ገፍቶ የመጣ ትውከት ፣ ረስቶ መብላትና መጠጣት ፆም አያበላሹም።) 2ኛ - ጥያቄ፡- :-የአይን ኩሁል ሽቶ ኮስሞቲክ የመሳሰሉት ለፆመኛ ይፈቀዳል? መልስ:- ኩሁል አይን ላይ ሲኳሉት ወደ ጉሮሮ ይዘልቃል። ስለዚህ ብዙ የዲን ዕውቀት ባለቤቶች ከልክለዋል ፓውደር ሽቶ የመሳሰሉት ለፆመኛ ምንም አይደለም። ሴቶች ግን ሽቶ ተቀብተው ከቤት መውጣታቸው ሐራም ነው። ሴቶች ከቤታቸው ውጪ ሲወጡ ከማጋጌጥና ሽቶ ከመቀባት መራቅ አለባቸው። አላህም በቁርአኑ ፡- قال تعالى‏:‏ ‏{‏..وَلا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الأُولَى ...‏}‏ ÂŤ...እንደፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥን በማጌጥ አትገለጡ...። ይላል። [አል-አሕዛብ: 33] قال صلى الله عليه وسلم‏:‏ ‏(‏لا تمنعوا إماء الله مساجد الله وليخرجن تَفِلات‏)‏ ረሱልም  «ሴት የአላህ ባሮችን መስጅድ አትከልክሉ። ያላጌጡትም ሆነው ይውጡ!Âť ብለዋል። [ሱነን አቡ ዳውድ] 3ኛ - ጥያቄ:-ፆመኛ በአደጋም ሆነ በጭረት ከሰውነቱ ደም ቢፈስ ፆሙ ይበላሻል? መልስ፡- በአደጋ ምክንያት የሚፈስ ደም በፍላጎት ስላልሆነ ፆም አያጠፋም ፡፡ ደም መስጠትና ዋግምት ግን ስለሚያደክምና ስለሚያስፈጥር በፆም ወቅት ክልክል ነው ፡፡ 4ኛ - ጥያቄ፡- በየፋርማሲው የሚሸጥ የአፍ ሽታ የሚያጠፋ የሚነፋ ፈሳሽ (ስፐሬይ) ፆም ያበላሻል? መልስ፡- ፈሳሹን ለአፍ መጠቀም እንደመፋቂያ ስለሆነ ይቻላል። ወደ ጉሮሮ ዘልቆ እንዳይገባ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ፡፡ እዚህ ላይ ፆመኛ የአፉን ጠረን በጣም መጥላት የለበትም። ምክንያቱም አላህን የመታዘዝ ምልክትና የተወደደም ነውና ፡፡ خلوف فم الصائم أطيب عند الله من ريح المسك‏) ‏ قال صلى الله عليه وسلم :‏ ረሱልም () «የፆመኛ የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከምስክ ሽቶ የተሸለ ነው።» ብለዋል! [አል-ቡኻሪይ እንደዘገበው] 5ኛ - ጥያቄ፡- አንዲት ሴት ከወር አበባ ወይንም ከወሊድ ደም ከጠራች በኋላ የሚያጠራጥር ነገር ካየች እንዴት ትሆናለች? መልስ፡- የወር አበባ ባስለመደው ቀን ጊዜውን ጨርሶ ምልክት አሳይቶ ከቆመ በኋላ መስገድም ሆነ መፆም ትችላለች። ምናልባት የሚያጠራጥር ነገር ካየች ያለማወላወል ጾሟን መቀጠልም ሆነ መስገድ ትችላለች። ነገር ግን ከወሊድ ደም ጠርቻለሁ ካለች በኋላ የሚያጠራጥር ነገር ካየች የግድ አርባ ቀን መሙላት አለባት ከአርባ ቀን በኋላ አጠራጣሪ ነገር ብታይም ሳታወላውል ጾሟን መቀጠልም ሆነ መስገድ ትችላለች፡፡ أم عطية رضي الله عنها‏:‏ ‏(‏كنا لا نعد الكدرة والصفرة بؚد الطهر شيئًا‏)‏ ኡሙ ዓጢያ (ረዲየ-ል'ሏሁ ዓንሃ) «ከወር አበባ ከጠራን በኋላ አረንጓዴውን ፈሳሽ (ኩድራ) እና ቢጫውን ፈሳሽ (ሱፍራን) እንደ ወር አበባ አንቆጥረውም ነበር።) ብላለች! 6ኛ - ጥያቄ፡- የአሥራ አራት አመት ኮረዳ እያለሁኝ የወር አበባ ታየኝ በዛኑ አመት ረመዳን ሲመጣ አልፆምኩም። መፆም እንደሚገባኝ እኔም ሆንኩኝ ቤተሰቦቼ አናውቅም። አሥራ አምስት አመት ሲሞላኝ መፆም ጀመርኩኝ። ከዛም ሴት ልጅ የወር አበባ ከታያት ዕድሜዋ ባይደርስም መፆም አለባት! የሚል ፈትዋ ሰማሁኝ ታድያ አሁን ምን ላድርግ ? መልስ፡- ጠያቂዋ የወር አበባ ሲታያት ለአካለ መጠን መድረሷ” ባለማወቋ እንደ ጥፋት አይቆጠርም። ያለማወቅ ነውና! ስለዚህ አሁን ለአካለ መጠን ስለደረሰች ያልፆመችውን አመት ፆም ቀዿ ማውጣት አለባት ፡፡ ሴት ልጅ ለአካለ መጠን መድረሷ የሚታወቅበት አራት ነጥቦች አሉ፡፡ ሀ. ዕድሜዋ አሥራ አምስት አመት ሲሞላት፡፡ ለ.ፀጉር ስታበቅል (ብልት አካባቢ) ሐ.በስሜት ማፍሰስ ስትጀምር (በብልት በኩል) መ.የወር አበባ ሲታያት ናቸው ፡፡ ከአራቱ አንዱ ከተከሰተ ሴት ልጅ ልክ እንደ ትልቅ ሴት ግዴታ የሆኑ ዒባዳዎችን ሁሉ መፈፀም አለባት ፡፡ 7ኛ - ጥያቄ፡- ያለፉትን ብዙ ረመዿኖች ለዓመታት አልፆምኩም አሁን ተውበት አድርጌ በደንብ መፆም ከጀመርኩኝ ገና ዓመቴ ነው። ታድያ ያለፉትን ዓመታት ቀዿ እንዴት ነው የማወጣው? መልስ፡- ይህንን ጥያቄ ለመመለሾ ትንታኔ ያስፈልገዋል ያለፉትን ሳትፆም ያሳለፍካቸው ረመዿኖች በዛን ወቅት ሰላት የማትሰግድ ከሆነ ከኢስላም ውጪ ስለሆንክ ብትፆምም ፆምህ ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን ባለፉት ባልፆምክባቸው ረመዿኖች ዘመን ሶላትህን አስተካክላ የምትሰግድ ከሆነ ያልፆምካቸውን ረመዿኖች ሁሉ ቀዿ ማውጣት አለብህ። ቀዿ ስታወጣ ቀዿውን ያዘገየህበት ምክንያት ከሌለህ በእያንዳንዱ ቀን ምስኪን ማብላት አለብህ። ቀዿውን በምክንያት ካዘገየህ ምስኪን ባታበላም ምንም አይደለም ፡፡ 8ኛ - ጥያቄ፡- ፈርዽ የሆነ ፆም ቀዿ በማውጣት ላይ ያለ ሰው ቀን ላይ ፆሙን ማቋረጥ ይችላል? የሱንና ፆም (ነፍል) ቢሆንስ? መልስ፡- ፈርዽ የሆነ ፆም ቀዿ በመፆም ላይ ያለ ሰው ፆሙን ማቋረጥ አይችልም። ፈርዽ ነውና! ነገርግን የሱንና ፆም (ነፍል) ከሆነ ቀን ላይ ማቋረጥ ይችላል ፡፡ 9ኛ - ጥያቄ፡- እናቴ የስልሳ አመት አዛውንት ናት። አባቴን ካገባች ጀምሮ በወር አበባ ሰበብ ያልፆመቻቸውን ፆሞች ለሃያ ዓመት ቀዿ አላወጣችም። ምክንያቱ አባቴ ከፋራ ካደረግሽ በቂ ነው ይላት ነበር። አሁን ታድያ ምን ማድረግ አለባት? መልስ፡- እናትህ በወር አበባ ሰበብ ያልፆሙትን ቀን በሙሉ መፆም አለባቸው። እንዲያውም ቀዿውን ስላዘገዩ በያንዳንዱ ቀን ምስኪን ማብላት አለባቸው ፡፡ አባትህን በተመለከተ በማያውቁት ነገር ፈትዋ መስጠታቸው ትልቅ ስህተት ተሳስተዋል ፡፡ 10ኛ - ጥያቄ፡- አንድ ሰው በሕመም ምክንያት ሐኪም ከልክሎት የአራት ዓመት ረመዿኖችን አልፆመም አሁን ጤንነቱ ስለተሟላ ምን ማድረግ አለበት? መልስ፡- በሕመም ምክንያት ያሳለፋቸው ፆሞች ጤናው ከተመለሰ ቀዳዿ ማውጣት ግዴታው ነው። አላህም በቁርአኑ ፡- ‏{....وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَى سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ‏} «ከናንተ ውስጥ በሽተኛ ወይንም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ከሌሎች ቀኖች የተወሰነውን መፆም አለበት .... ― [አል-በቀራህ: 185] ቀዿ ሲወጣ ግን እንደፈለጉ አከታትሎም ሆነ አቆራርጦ መፆም ይቻላል። አላህ ከአቅም በላይ አያዝም። በቁርአኑም፦ ‏{‏. فَاتَّقُوا اللَّهَ مَ اسْتَطَعْتُمْ‏} «አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት።» ብሏል! [አ-ት'ተጛቡን: 16] ምንጭ፦ የረመዿን ስንቅ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share

#ኢስላማዊ_ትምህርቶች_በአማርኛ_ትርጉም #ክፍል_13 ★አላህ በሰጠህ ጸጋ ትጠየቃለህ‼ ★ በ Toleha Ahmed የተተረጎመ ይ🀄ጥላል.... ሌሎችንም የትርጉም ዳዕዋዎች በ ዩቱብ ለማግኘት👇👇 https://youtu.be/KGfPrWZ2Vio ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓ @tolehaahmed @islamic_records ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛ ለሌሎች ሼር የሚያደርግን አካል አላህ ይዘንለት❕

At least 30,320 people have been killed in Israel’s attacks on Palestine’s Gaza in nearly 5 months. Some two-thirds of those
At least 30,320 people have been killed in Israel’s attacks on Palestine’s Gaza in nearly 5 months. Some two-thirds of those killed in Israel’s relentless bombardment of Gaza are women and children, according to the Palestinian Ministry of Health. That staggering number of fatalities since October 7 means that more than 1% of the enclave’s pre-war population of 2.3 million people have been killed. The Israeli offensive has damaged or destroyed 60 percent of Gaza’s infrastructure and has left 85 percent of the enclave’s population internally displaced amid acute shortages of food, clean water and medicine, according to the UN.

🔰 የእኛ ምኞትና ፍላጎትስ ምንድነው⁉️ ረቢዓ ኢብን ከዕብ አል-አስለሚ (ረዲያሏሁ አንሁ ወአርዳህ) የአሊህን መልዕክተኛ (ﷺ) ይኻድማቸው የነበረ ሰሃቢይ ነው። የአላህን መልዕክተኛ ለረጅም አመታት የኻደማቸውን ኻዲማቸውን ለመካስ በማሰብ «የምትፈልገውን ያሻህን ነገር ጠይቅ አሉት»! ➞ ኻዲማቸውም፦ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) የኔ ጥያቄ በጣም ከባድ ነው አላቸው። እነሱም:- ጠይቅ አሉት። ➞ ኻዲማቸው፦ እኔ የምፈልገው ነገር በጀነት ያንቱ ጓደኛ መሆን ነው አላቸው❗️ ይህን ጥያቄ፦ እኛ ብንጠየቅ *“እንፈልጋለን የምንለው ነገር ምን ይሁን⁉️”* ► ስልጣን፣ ብር፣ ቤት፣ መኪና⁉️ ▮እንደው ፍላጎታችን ከዱንያዊ ነገር ያልፋል!? የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ኻዲም የጠየቃቸው ጀነትን ብቻ አልነበረም፤ “በጀነት ውስጥ ያንቱ ጓደኛ መሆን ነው የምፈልገው” ነው ያላቸው❗️ የእኛ ምኞትና ፍላጎትስ ምንድነው⁉️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል 💻 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬⌨️ ሀሳቡና ታሪኩ ከኡስታዝ ሐሰን ማሜ ሙሐደራ የተወሰደ

This Ramadhan let's Free our... #Ramadan_1445
This Ramadhan let's Free our... #Ramadan_1445

ፍልስጤማውያን የጁመአ ስግደታቸውን በመስጂድ ፍርስራሽ ውስጥ ሰገዱ! … በጋዛ ራፋህ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን የጁምዓ ጸሎታቸውን በእስራኤል ጥቃት ወድሞ በነበረው የፋሩክ መስጊድ ፍርስራሽ ውስጥ ሰግደዋል
+6
ፍልስጤማውያን የጁመአ ስግደታቸውን በመስጂድ ፍርስራሽ ውስጥ ሰገዱ! … በጋዛ ራፋህ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን የጁምዓ ጸሎታቸውን በእስራኤል ጥቃት ወድሞ በነበረው የፋሩክ መስጊድ ፍርስራሽ ውስጥ ሰግደዋል። … የፍልስጤም ጋዛ ባለስልጣናት እንደገለፁት ፦ከጥቅምት 7 ጀምሮ በጋዛ ክልል ውስጥ ከሚገኙት 1,200 መስጊዶች ውስጥ 1,000 የሚሆኑት በእስራኤል ጥቃቶች መውደማቸውን የዘገበው TRT World ነው። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ እንዴት ነሽ ያ! አቅሳ⁉️ እንዴት ነሽ ፈለስጢን⁉️ ድምፃችን ደርሷል - ከዚህ ይሰማሻል፣ የአላህ የሚሉ - አጆች ይታዩሻል፣ እዛ ደርሶ ይሁን - ከአንደበታችን ቃል፣ ጌታቸውን የሚማፀኑ - የረብ  እያሉ ፣ በህመምሽ የታመሙ - ክፉኛ የቆሰሉ፣ በሁኔታው አዝነው - መድማትሽ ያደማቸው፣ በህፃናት ለቅሶ - ያዘነ ውስጣቸው፣ ካንቺ ስለራቁ - አቅም የከዳቸው። ለእውነት የቆሙ - ውሸት አንበርካኪዎች፣ የሀቅ ጓደኛ - የአይሁድ ጠላቶች፣ ጌታችን እያሉ - የነፃነት እጆች፣ ያአላህ የሚሉ - የጨቅላ አንደበቶች፣ ያዓዚዝ የሚሉ - የህፃናት ምላሶች፣ ከጎንሽ እኮ ናቸው - የአላህ ባሮች። አቅም አንሷቸው ነው - ጦር ሜዳ ያልገቡት፣ እሩሩሩሩቅ ስላሉ ነው - አንቺን የራቁት፣ ሙስሊሞች ናቸው - ረስተውሽ አይደለም ሰላምታ ደርሶሻል? - አሰላሙ አለይኩም። ዝም ያሉ መስሎሽ ነው - የታመምሽ ክፉኛ⁉️ ምድርሽ ተበክሎ - በአይሁድ መጋኛ፣ ደምሽን አፍስሰው - በሬሳ ሲረማመዱ፣ የዘናጋው እንዳይመስልሽ - እያየ ነው ሶመዱ። ቁስልሽ ያቁስለን - ውሎሽን ንገሪን፣ አጫውቺን የሆንሽውን - መድማትሽ ያድማን፣ አንገትም እንድፋ - ማዘንሽ ያሳዝነን፣ ማማረር እናቁም - የንቺን ስቃይ አውቀን፣ እንዴት ነሽ በአላህ - ያ! አቅሳ ንገሪን⁉️ እንዴት ነሽ ፈለስጢን - ያ! አቅሳ ንገሪን⁉️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

እንዴት ነሽ ያ! አቅሳ⁉️ እንዴት ነሽ ፈለስጢን⁉️ ድምፃችን ደርሷል - ከዚህ ይሰማሻል፣ የአላህ የሚሉ - አጆች ይታዩሻል፣ እዛ ደርሶ ይሁን - ከአንደበታችን ቃል፣ ጌታቸውን የሚማፀኑ - የረብ እያ
+7
እንዴት ነሽ ያ! አቅሳ⁉️ እንዴት ነሽ ፈለስጢን⁉️ ድምፃችን ደርሷል - ከዚህ ይሰማሻል፣ የአላህ የሚሉ - አጆች ይታዩሻል፣ እዛ ደርሶ ይሁን - ከአንደበታችን ቃል፣ ጌታቸውን የሚማፀኑ - የረብ እያሉ ፣ በህመምሽ የታመሙ - ክፉኛ የቆሰሉ፣ በሁኔታው አዝነው - መድማትሽ ያደማቸው፣ በህፃናት ለቅሶ - ያዘነ ውስጣቸው፣ ካንቺ ስለራቁ - አቅም የከዳቸው። ለእውነት የቆሙ - ውሸት አንበርካኪዎች፣ የሀቅ ጓደኛ - የአይሁድ ጠላቶች፣ ጌታችን እያሉ - የነፃነት እጆች፣ ያአላህ የሚሉ - የጨቅላ አንደበቶች፣ ያዓዚዝ የሚሉ - የህፃናት ምላሶች፣ ከጎንሽ እኮ ናቸው - የአላህ ባሮች። አቅም አንሷቸው ነው - ጦር ሜዳ ያልገቡት፣ እሩሩሩሩቅ ስላሉ ነው - አንቺን የራቁት፣ ሙስሊሞች ናቸው - ረስተውሽ አይደለም ሰላምታ ደርሶሻል? - አሰላሙ አለይኩም። ዝም ያሉ መስሎሽ ነው - የታመምሽ ክፉኛ⁉️ ምድርሽ ተበክሎ - በአይሁድ መጋኛ፣ ደምሽን አፍስሰው - በሬሳ ሲረማመዱ፣ የዘናጋው እንዳይመስልሽ - እያየ ነው ሶመዱ። ቁስልሽ ያቁስለን - ውሎሽን ንገሪን፣ አጫውቺን የሆንሽውን - መድማትሽ ያድማን፣ አንገትም እንድፋ - ማዘንሽ ያሳዝነን፣ ማማረር እናቁም - የንቺን ስቃይ አውቀን፣ እንዴት ነሽ በአላህ - ያ! አቅሳ ንገሪን⁉️ እንዴት ነሽ ፈለስጢን - ያ! አቅሳ ንገሪን⁉️ ። በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ቀን:- እሁድ/ የካቲት 24/2016 ዓ.ል

In support of the Palestinian people in Gaza, Hezbollah carried out the following operations: - At 05:40, the fighters launch
In support of the Palestinian people in Gaza, Hezbollah carried out the following operations: - At 05:40, the fighters launched an air attack targeting the newly established sector command in Liman with an attack drone. -  At 10:10, a gathering of israeli soldiers near the Jal al-Alam site was targeted with missile weapons. - At 15:20, Al-Za’oura site was targeted with missile weapons. - At 16:40, the al-Raheb site was targeted with missile weapons. - At 17:30, the Zibdin barracks in the occupied Lebanese Shebaa Farms were targeted with missile weapons. - At 19:00, the Hadab Yarin site was targeted with two Burkan rockets.

አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ እህት ወንድሞች ታላቁ እንግዳ እየቀረበ ነው በምን ተዘጋጅታቹሃል? ቁርአንንስ ምን ያክል ግዜ ለማኽትም አስባቹሃል❓4፣ 5፣ 6ግዜ ወይስ ከዛበላይ? ኣላህ
አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ እህት ወንድሞች ታላቁ እንግዳ እየቀረበ ነው በምን ተዘጋጅታቹሃል? ቁርአንንስ ምን ያክል ግዜ ለማኽትም አስባቹሃል❓4፣ 5፣ 6ግዜ ወይስ ከዛበላይ? ኣላህ ያግራላቹህ። እኔም ለዚህች ወር የምትሆን ስጦታ ይዤላችሁ መጥቻለሁ። ቁርአንን በየሶላቱ የገፆቹን ልክ ከቀራን በቀላሉ እናኸትማለን። ኣላህ ይወፍቀን 📌 ወንድማቹህ አቡ ዓቲካህ

Imam Schedule for Masjid Al Haram for the coming week until Saturday: Fajr & Dhur: Sheikh Abdullah Juhany Asr, Maghrib & Isha
Imam Schedule for Masjid Al Haram for the coming week until Saturday: Fajr & Dhur: Sheikh Abdullah Juhany Asr, Maghrib & Isha: Sheikh Bandar Baleelah

A Palestinian child anxiously attempts to console his mother, who is grieving the loss of her eldest son to Israeli shells in Gaza.

Hundreds of protesters marched through Berlin today, condemning the Israeli genocide and demanding an immediate ceasefire in Gaza.