Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
رفتن به کانال در Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
نمایش بیشتر213
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-430 روز
آرشیو پست ها
ታላቁ ዓሊም #ሱፍያን_አስ_ሰውሪ (ረሂመሁላህ) ለአቻቸው #ለዐብዱሏህ ኢብኑል ሙባረክ (ረሂመሁላህ) የላኩት ደብዳቤ እንዲህ ይላል፦
“ያለህን ዕውቀት አሰራጭ፤ነገር ግን እውቅናን (ታዋቂነትን) ከመፈለግ ተጠንቀቅ!።”
📚 [አል-ሂልየህ (7/70)]
📝 አቡ ሙህሲነህ ሙባረክ (ሀፊዘሁሏህ)
˹This is˺ a blessed Book which We have revealed to you ˹O Prophet˺ so that they may contemplate its verses, and people of reason may be mindful. (38:29)
"በጨለማ ወደ መስጂድ የሚጓዙትን በቂያማ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሀን አበስራቸው።"ረሱል(ﷺ)
(ሰሂህ አቡ ዳውድ:561)
🔰 ኋላ ቀርነት
ሰዎችን ዱንያዊ በሆነ ጉዳይ ከሸሪዓ ጋር አያይዘን በምንመክራቸውና በምንገስፃቸው ወቅት እኛን «ኋላ ቀር» አመለካከት ያለው ሰው አድርገው ሊቆጥሩን ይችላሉ‼️ወይም በተግሳፁ ሊሸማቀቁ፣ ሊሳለቁ አሊያም ሊያፍሩ ይችላሉ። ....
.... ይሄኔ ሊከፋን፣ ልናዝን፣ ልንናደድ አሊያም ልንበሳጭ እንችላለን። ነገር ግን እኛ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር እኛ ለአላህ ብቻ ብለን ከመጥፎ ስንከልክልና በጥሩ ስናዝ ምንዳውን (አጅሩን) ከአላህ እናገኘዋለን። ኢንሻአላህ!!
ግዴለም፤ ነገሮችን በአዕምሯችን እንደፈለግን ማድረግ ሳይሆን በሸሪዓ ሚዛን በመመዘናችን «ኋላ ቀር ናችሁ» ብሎ የሚያስብ ተውት እያሰበ ይኑር።
ግዴለም፤ ለአላህ ብለን ሸሪዓዊ ምክርን ስንመክራቸው ካፌዙና ካላገጡ ተዋቸው ያላግጡ ውጤታቸውን ከአላህ ያገኙታል።
አዎ እኛ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል፦ ከውድቀት መማር ብልህነት፣ ደካሞችን መርዳት ጠንካራነት፣ ለሰዎች መጨነቅ አዛኝነት፣ ሰዎችን ማክበር አዋቂነት፣ ይቅርታ መጠየቅ ትልቅነት እንዲሁም ለአላህ ብሎ ሰዎችን በጥሩ ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል የሁሉም ኃላፊነት አድርገን መልካም የሆኑ ማንነቶችን ተንከባክበንና ኮትኩተን ማሳደግ ይኖርብናል። ......
... እኛ ላይ የሚሰነዘሩ ወቀሳዎች፣ ዛቻዎች ወይም ትችቶች ከምንሰራው መልካም ነገር ሊያርቁን ሳይሆን ይበልጥ እንደ ብረት ሀዲድ ጠንካራ ሊያደርጉን ነው የሚገባው። ለአላህ ብሎ መልካም ነገርን የሚፈፅም ሰው ለምንስ ሲል ተስፋ ይቆርጣል!? አጀሩን የሚከፍለን አላህ አይደለን⁉️
አዎ ለአላህ ብለን፣ ከሱ ምንዳን ፈልገን ስራዎችን ስንሰራ ለተስፋ-ቢስነት ምክንያት አይኖረንም፤ ሊኖረንም አይገባም‼️
ውድ እህት ወንድሞች ሆይ!
▬ ለአላህ ብላችሁ ሰዎችን ስትመክሩ፣ ስትገስፁ ትችት ወቀሳ አስተናግዳችሁ ይሆናል። ግን አብሽሩ አጅሩን ከአላህ ታገኙታላችሁ ኢንሻአላህ!!
ተስፋ ሳትቆርጡ ሰዎችን መርዳት መደገፍ፣ በጥሩ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከላችሁን አታቁሙ። አላህ አቅሙንም ሶብሩንም እንዲሰጣችሁ ዱዓ አድርጉ!!
በአላህ ፍቃድ የስራችሁን ፍሬ ከአላህ ታገኙታላችሁ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
► ለአላህ ብላችሁ ዱንያዊ በሆነ ጉዳይም ሆነ አኺራ በሆነ ነገር ላይ ሰዎችን በሸሪዓ ህግጋቶች የምትመክሩና የምትገስፁ እህት ወንድሞቼ ለአላህ ብየ እወዳችኋለሁ!!
እነዛ ይወቁ ሸሪዓ ˝ኋላ-ቀር አይደለም˝ ፤ ኋላ-ቀሮቹና የማንጠቅም እርባና-ቢሶች «ሸሪዓን ኋላ-ቀር» ነው ብለን የምናስብ ሰዎች ነን!!
ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን:- ህዳር 21/2016 አ.ል [Dec 1/2023 G.C]
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
t.me/ReshadMuzemil
⭕️ You can't beat a nation that knows death is not the end‼️
⭕️ ሞት መጨረሻ እንዳልሆነ የሚያውቅን ህዝብ ማሸነፍ አይቻልም‼️
🔰 እሷም እናቴ ናት
በሀዘን በደስታ - ከጎኔ የሆነች፤
ሲከፋኝ ተከፍታ - ሳዝንም እያዘነች፤
ለራሷ ሳትኖር - እኔን ያኖረች፤
ለራሷ ሳትስቅ - እኔን ያሳቀች፤
ወደ ህይወቴ አምጥታኝ- ከህይወቷ የራቀች፤
እሷም እናቴ ናት - በእህት መልክ ያለች።
መክደኛው ተዛብቶ - ቤቱ ሲያፈስ፤
ጥላ ሆነችልኝ - በብርድ እንዳልከለስ፤
እሪ ብዬ ሳለቅስ - ልብሴም ተቀዶ፤
መርፌዬ እሷ ነበረች - ልቧ ተገዶ፤
ልቤም ተራበላት - የሷን ፍቅር ለምዶ፤
እውቀቴም ጨመረ - የሷን ምክር ወስዶ፤
ውስጤም አከበራት - እውነተኝነቷን ወዶ።
የፍቅር ተምሳሌት - የእናት አምሳያ፤
ፍቅሯ ያሸበረቀ - የፍቅር መንትያ፤
ከየትስ ይወለዳል - እንክብካቤዋን መተኪያ!?
ልቧም እውነት ነው - የሐቅ ማቆያ፤
ፈልገን ብንሄድ - የፍቅርን መጠለያ፤
እሷ ዘንድ ነው - የእውነተኝነት ገበያ።
የምወድሽ ለዚህ አደለም - እኔን ስለጠቀምሺኝ፤
የማከብርሽ ለዚህ አደለም - እኔን ስለተረዳሺኝ፤
ይልቁን ለዚህ ነው - ባንቺ ንፁህነትሽ፤
በልብሽ ማሳ - ለጠበቅሺኝ ተክለሽ፤
አምላካችን አላህ - ጀነት ይሸልምሽ፤
ችግርና መከራን - አላህ ዞር ያድርግልሽ፤
አንቺማ አትከፊ - እሾህም አይውጋሽ፤
ያአላህ ያራህማን - እሱ ይጠብቅሽ።
እሷም እናቴ ናት - የኔዋ እህት፤
ፈፅሞ የለም - መልካምነቷን የሚተካት፤
ደከመኝ የማታውቅ - ምን ብዬስ ልሰይማት!?
ሌላ ስም አለ ወይ!? - ስያሜዋ እህት!?
ንገሩኝ እባካችሁ - ሌላ ስያሜ ካላት፤
አያቹኋት የኔን እህት - እሷም እናቴ ናት፤
አያቹኋት የኔ እህት - እሷም እናቴ ናት።
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን: ህዳር 18/2016 አ.ል
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
t.me/ReshadMuzemil
⭕️ // ከትዝብቴ ማህደር //
🔰 ሀላፊነት
/// *« አስተዋይ አእምሮ ላላቸው ብቻ »* ///
ሀላፊነት ማለት በጥንቃቄ ካልተራመድንበት በሚደረመስ ሃዲድ ላይ እንዳለን ነው።
ልብ በሉ እዚህ-ጋር ሃዲዱ ቢደረመስ በሰዓቱ ቁልቁል የምንወረወረው እኛ ብቻ ነን። ሃላፊነት ግን ከዚህ ይለያል... ሃላፊነታችንን በአግባቡ የማንወጣ ከሆነ፣ ያለንን ስልጣን (ሃላፊነት/አደራ) በአግባቡ ማንጠቀምበት ከሆንና ክብራችንን ለማስጠበቅ የምንገለገልበት ከሆነ ወደ ቁልቁል የምንወረወረው እኛ ብቻ ሳይሆን በስራችንም ያሉትን ይዘን ነው። በሉ እንደውም ከኛ በፊት ቀድመን የምናወድማቸው (በጉርጓድ የምንከታቸው) በስራችን ያሉትን ሰዎችን ነው‼️
በስራችን ያሉ ሰዎች የሚችሉትን ያህል ጥረት ካደረጉና የሚችሉትን ያህል ከሰ፤ ... ለምን « እኔ የምፈልገውን ያህል አልሰራችሁም!? » ብሎ ጋጋታ መፍጠር አግባብ አይደለም!! ይህ የፈጠርነው ጋጋታ በስራችን ያሉ ሰዎችን ያቆስልብናል፣ ሞራላቸውን ይጎዳብናል ምናልባት መጀመሪያ የነበራቸው ጥንካሬ ተሸርሽሮ ስንፍናን ባህሪያቸው እንዲያደርጉ ያደርግብናል።
● ከዚህ በፊት ይጥሩ የነበረውን ጥረት ሊያቆሙብን ይችላሉ፣
● ከዚህ በፊት የነበረው ጉብዝናቸው ሊናድ ይችላል፣... ስለዚህ እኛ ስልጣኑ አለን የምንል ሰዎች ጥንቃቄ ልናደገርግ ይገባናል። ሰዎችን ያለአግባብ ማስጨነቅ አላህም አይወድልንም!!
ሁሉም የራሱ እምነት እንዲሁም አስተሳሰብ አለው ነገር ግን የትኛውም እምነት ሆነ አስተሳሰብ ሰዎች ከአቅማቸው በላይ መስራት አለባቸው አይልም፤ ቢል ራሱ አግባብ አይደለም!
➤ እኛ የምንጨነቀው ለሰዎቹ ሞራል ደስታና ስኬት ሳይሆን ለኛ ክብር ከሆነ፤ እኛ የማንጠቅም እርባና-ቢሶች ነን ማለት ነው‼️
➤ እኛ ትግላችን በስራችን ያሉ ሰዎች የሚችሉትን ያህል እንዲሰሩ ሳይሆን እኛ የምንፈልገውን ያህል ብቻ እንዲሰሩ የምናዛቸው ከሆነ፤ የሰጧንን ባህሪ የተላበስን ቆሻሾች ነን ማለት ነው‼️
〽️ ቆይ ከቅማቸው በላይ ኬት አምጥተው ይስሩ!?
የሆነ ነገር እንዲሰሩን የፈለግን እንደሆነ እኛም « ይህን የሰጠናችሁን ስራ በዚህ መልክ ከሰራችሁ ትጨርሱታላችሁ ወይም ጥሩ አድርጋችሁ ትሰሩታላችሁ» የሚል ቀመር ልናስቀምጥላቸው ግድ ይለናል‼️ በዚህ ባስቀመጥንላቸው ቀመር ራሱ ሁሉም እኩል አይሰራም ሊሰራም አይችልም። ይሄኔም ጋጋታ ከመፍጠር ይልቅ መፍትሄ ለማበጀት መሞከርና የሰጠናቸውን ስራ በአግባቡ አልሰሩም ያልናቸውን «ቆይ ግን የአቅማቸውን ያህል ሰርተዋል ወይስ አልሰሩም» የሚለውን መለየት ይኖርብናል! ...
ያአቅማቸውን ያህል ካልሰሩና ካፌዙ (ካሾፉ) ያኔ ጋጋታ ብንፈጥርም ያምርብናል‼️
⭕️ ጥልጣን አለን በሚል በወረደና በዘቀጠ አስተሳሰብ ሰዎችን ያለአግባብ ልንጎዳ፣ ሞራላቸውን ልንነካ፣ ክብራቸውን ልናጎድፍ አይገባንም መብቱም የለንም‼️
⭕️ እኛን «እረፉ የፈጠራችሁን ፍሩ» የሚለን የለንም ማለት በስራችን ያሉ ሰዎችን እንዳሻን እንጫወትባቸው ማለት አይደለም። ህሊና የሚባል ነገር አለ‼️
ፈጣሪያችንን ልንፈራ ይገባል። በተለይ አዋዋላችን ከልጆች፣ ከህፃኖችና ከተማሪዎች የሆንን ሰዎች ቆም ብለን ልናስብ ይገባናል። ለክብራችን መጨነቅ ትተን በስራችን ላሉት (ለተማሪዎች) ስኬትና ውጤት ልንጨነቅ ይገባናል። ተማሪዎቻችን የአቅማቸውን፣ የሚችሉትን ያህል ከሰሩ ለምን «እኔ የምፈልገውን ያህል አልሰራችሁም» በሚል በዘቀጠ ሀሳብ እነሱን ልንጎዳቸው አይገባንም መብቱም የለንም።
አዎ እሩፉ የሚለን ላይኖር ይችላል፤ ያው ሁሉም እኔ «ምንናገባኝ» ስለሚል ማለቴ ነው። ነገር ግን ህሊናስ የለንም⁉️ እምነታችንስ ምንድነው የሚያዘን...⁉️ ይህን ጥያቄ ለራሳችን ደጋግመን እንጠይቀው!
😭 እናተ *ያለአቅማችሁ ለምን አልሰራችሁም* ተብላችሁ የተገፋችሁ ሆይ አብሽሩ አላህ ከናተ ጋር ነው። አብሽሩ ይህ ጊዜ ያልፍና ነገ በአላህ ፍቃድ ትልቅ ቦታ ትደርሳላችሁ‼️ ...........🔰 ኢንሻአላህ!!
❌ እናተ ለምን «እኔ የምፈልገውን ያህል አልሰራችሁም» ብላችሁ በስሮቻቹ ያሉትን ክብር የምትነኩ ሆይ.....
እናተ የምትጨነቁት ለራሳችሁ ክብር እንጂ ለሌሎቹ ስኬት አይደለም። ለሌሎቹ ስኬት፣ ደስታና ተድላ ሳይሆን ለራሱ ክብር ብቻ የሚጨነቅ ደግሞ እሱ የሰጧንን ባህሪ የተላበሰ የሰው ሰጧን ነው‼️ እናም እናተ የሰው ሰይጧኖች ሆይ አምላካችሁን ፍሩ‼️
▬▬▬▬▬▬▬
⭕️ መልዕክቴ አስተዋይ አእምሮ ላላቸው ይድረስልኝ‼️
▬▬▬▬▬▬▬
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን: ህዳር 17/2016 አ.ል
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
t.me/ReshadMuzemil
በዝምታህ አወዛግባቸው...
በተግባርህ አስደምማቸው!!
Confuse them with your silence...
Amaze them with your actions!!
ummalife.com/ReshadMuzemil
🚨 𝐈𝐒𝐑𝐀𝐄𝐋’𝐒 𝐎𝐂𝐓 𝟕𝐭𝐡 ‘ 𝐒𝐂𝐑𝐄𝐄𝐍𝐈𝐍𝐆’ 𝐄𝐗𝐏𝐎𝐒𝐄𝐃!
1️⃣ 17.11.2023 - The IDF stole 111 dead Palestinian bodies from outside Al-Shifa hospital.
2️⃣ 22.11.2023 - IDF returned the bodies in blue bags for a mass funeral.
3️⃣ 22.11.2023 - IDF released ‘new’ images & videos as ‘proof’ of Israeli children massacred by Hamas on Oct 7th.
4️⃣ 23.11.2023 - IDF held ‘private screenings’ for selected individuals.
Million Dollar Question: Why were the ‘new’ images of the ‘aftermath of the Nova festival massacre’ only available *AFTER* the IDF stole the 111 bodies from outside Al-Shifa hospital?
🔗 ummalife.com/ReshadMuzemil
እባክህ አትተወን
በ-1917፣ ሀያል ነኝ ባይ - እንግሊዝ ስታሰፍራቸው
በ-1948፣ 750,000 ፈለስጢያዊያን - ከቄያቸው አባረሯቸው
የህዝቡ 78% - ምድር አልባ አረጓቸው
የገደሉትን ገድለው - የሚያባሩትን አባረሩ
በራሳቸው ምድር - ፈለስጢንን አሸበሩ
በ1967፣ 300,000 ፈለስጢናዊያንን - አፈናቀሏቸው ከቤት
መች ታወቀና - የቆሰለ የሞተው ብዛት
ፈለስጢናዊያን ሲበደሉ - በአይሁዳ ክህደት
አለም ዝም አለች እንጂ - ቃልም አልወጣት
ዛሬም እንደዛው ነው - ልክ እንደ ትላንት
በ-1995 ፈለስጢንን - ለሶስት ከፈሏት
በ2020 በዶናልድ እገዛ - ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት
«ፈለስጢን» ተወገደና - በመንደር “ገዛዕ” አስገቡት።
ኢዩ ወንድሞቼ የፈለስጢንን በደል - የፈለስጢንን ሰቆቃ
በገጋ ቄያቸው መኖር አልቻሉ - እንደው በቡረቃ።
አለም ዝም ጭጭ አለች - ይህንን እያየች
የሙስሊሙን በደል - ችላ ብላም አለፈች
❝ሐማስ ነው ተንኳሹ❞ - ብላም ለፈለፈች
*በአንዳንድ ሙስሊም* - *በንግግር ተደገፈች*።
ከዚህ ሁሉ በደል - በዚህ ሁሉ ግፍ
አውቆም ሳያውቅ - የሁዳን የሚግፍ
ሐማስነው ጥፋተኛ እያለ - ፈለስጢንን የሚነቅፍ
በ1917 ጀምሮ 2020 ድረስ - ኖሮዋል በእንቅልፍ
ወይም ሆኖዋል - ከባጢል ሚሰለፍ።
አእምሮ ያለው - የሚያሰላስል ጭንቅላት
የሚደግፍ አይኖርም - የሁዳን ክህደት
ምሳሌናት እሷ - የጭካኔ የአረመኔነት
ተምሳሌት ናት እሷ - የሙስሊሞች ጠላት
በአላህ ድንበር ያለፈች - እሷ ከኃዲ ናት
ኢሳን (ዐ.ሰ) ሰቀልኩ ያለች - እሷ ቆሻሻ ናት
ይህ ሁሉ ሆኖም - እሷን የሚደግፋት
ወላሂ አቅል የለውም - ተለክፏል በእብደት።
የፈለስጢን ምድር - በደም ተለወሰ
ደም በዝቶበት - ምድርም ከሰሰ
ያውም የሙስሊም - ተጧጧፈ ሬሳ
በፍርስራሽ ቀሩ - አጥንተም ተከሰከሰ።
ፈለስጢን ተጣራች - ሙስሊሞች ሆይ እያለች
ወንድሞች የሰሟት አይመስልም - እሷ እያለቀሰች
ፈለስጢናዊያን አለቁ - እናትም ደማች
ቤቶች ፈረሱ - ወደሙ መስጂዶች።
ሴትችን ተደፈሩ - ህፃናትን ተቀጠፉ
እኛነን የበላይ እያሉ - ቆሻሾች ለፈ።
በቃችሁ የሚለን - ከዚህ ሁሉ ጭንቅ
አላህ ብቻ ነው - በሐሴት የሚያቦርቅ
ዝንጉ አይደለም አላህ - ሁሉንም ያያል
በጌታችን እዝነት - ድሉም ይመጣል
በዱዓ እንበርታ እንጂ - እሱ ይረዳናል
ለነዛ ቆሻሻሽ - የእጃቸውን ይሰጣቸዋል።
የአላህ ያራህማን - እኛን አትተወን
ላንተ ባሪያዎች አሉህ - ለኛ ማንም የለን
ደጋፊያችን አንተነህ - በወንጀላችን አትራቀን
በድል አንበሽብሸን - ነስሩን አቅርብልን
አዎ ወንጀለኞች ነን - አዎ እናጠፋለን
አዛኝ ነህና የራሒም - እባክህ ይቅር በለን
በጌታነትህ ይሁንብህ - እኛን በፈጠርከን
በአንድነትህ ይሁንብህ - ወደዚህ ምድር ባስገኘሀን
ሙስሊሞችነንና ያ! አላህ - እባክህ አትተወን።
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን፦ ህዳር 12/2016 E.C [Nov 22/2023 G.C]
tiktok.com/@sharpswords1
https://t.me/SharpSwords1
www.youtube.com/@SharpSwords1
Instagram.com/sharp_swords1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
🔰 ባሮችህ ረገፉ
በፈለስጢን ምድር - በአላህ ቤት
በመስጂደል አቅሳ - ነብዩ ባረፉበት
በካኃዲዋ እስራኤል - ረገፉ ህፃናት
ቦምብ ዘነበባቸው - እንቅልፋቸውን በተኙበት
ዓለምም ችላ አለው - ይህን የዘር ማጥፋት
ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ
ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ
ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ
ሙስሊም የሆኑ - ኢባዱ ራህማን ናቸው
ሰው ናቸውና ያራሂም - ካጠፉም ማራቸው
መንገድ ስተው እንደሆን - መንገድ አሳያቸው
ሙስሊሞቹም ያንተ - ህፃኖች ያንተው
ካንተ ውጭ ሌላ መጠጊያም ዬላቸው!
አዎ ወጀለኞች ነን - ነብሳችንን በዳይ
ድንበር አላፊዎች ነን - በሰጧን አታላይ
ለብልጭልጭ ህይወት - በርከክ ባይ
ለዚህች ለቀን ጤዛ - ደሞም ለዱንያ
ላትሆነን መንገድ - ጀነትን መዝለቂያ
እያጠለቀችልን - የአዛብ ሜዳሊያ
ግን አንገሰፅም - ከዚህ ሁሉም ነገር
በኛ ወንጀል የተነሳ - ሙስሊሙ ሲሸበር
ጠላት ተጠራርተው - ሁሉም ባአንድ ሲያብር
እኛ ስንባላ - በጎሳ በብሄር
እኛ ስንከፋፋል - በቋንቋ በዘር
አስክሬኖች በርክተው - አፈር ሲለብስ በዶዘር
እኛ ቆይ የት ገባን - ቆይ የትስ አለቅን!?
ቆይ ምን ዋጠን - ምንስ ላይ ሰመጥን!?
ሙስሊም ረገፈ እኮ - እኛ በቁም እያለን
ጂሃዱስ አይሳካ - ያአላህ ማለት አቃተን!
የሙስሊም መሣሪያው - ዱዓ ነው እየተባልን፤
ያራህማን ያራሂም - እኛስ ቀሽሞች ነን፤
ሙስሊሞች ነንና - እባክህን ማረን
አዛኝ ነህና - ያአላህ እዘንልን
ውስጣችን ቆሰለ - ደም ዘነበ ከዓይን
ወንድሞቻችን አለቁ - በከሃዲዎች ረገፉብን
እነዛ የሰው አውሬዎች - ያንተን ቤት ደፈሩብን።
ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ
ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ
ያአላህ ያ! ራህማን - ቤቱም ቤትህ
ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ
ከጭንቅ ጠብቃቸው - ከጭንቅ አውጪ ነህ
ብዙዎች ቆሰሉ - ብዙዎች አለፉ
በህይወት እያሉ - ባሮችህ ደም ተፉ
በዘረጋሃው ምድርህ - ሙስሊሞች ተገፉ
እነዛ አውሬዎች - ሬሳን አሰለፉ
ሴትም አልቀራቸው - ህፃንም ቀጠፉ
ገደልን እያሉ - በደስታም ደነፉ
⭕️ በባረከው ምድርህ - *ባሮችህ ረገፉ* ።
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን: ጥቅምት 20/2016 E.C [Oct 31/2023 G.C]
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
Twitter.com/Secretsof_Truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
t.me/ReshadMuzemil
አሳፋሪ ነው‼
==========
(የእሸቱ መለሰ አሳፋሪ ንግግርና የሙስሊሞችን እምነት የማስቀየር የረጅም ጊዜ እቅድ!)
||
✍ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ በመባል የሚታወቀው ግለሰብና ዶንኪ ቲዩብ የሚባል ቻነል ያለው ግለሰብ በብዙዎች ዘንድ መልካም ሰው ነው ተብሎ የሚታሰብ ሰው ነበር። ግን የእንዲህ አይነት ግለሰቦች መልካምነት ጭምብላቸው እስኪገለጥ ድረስ ብቻ ነው።
ተከታይና ዝና እስኪያተርፉ ድረስ ከዚያም ከዚህም አለን እያሉ ካካበቱ በኋላ፤ መጨረሻ ላይ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ጭምብላቸው ይገለጣል።
ሰሞኑን ወደ ሃገረ ኳታር ዶሓ ከተማ አቅንቶ በቀጥታ ስርጭት ለቤተ ክርስቲያን መገንቢያ እያሰባሰበ ነበር። (እንደ ዐረብ ኢሚሬትና ኳታር ያሉ የዐረብ ሃገራት በብዝሃነትና አካታችነት ሽፋን ተበክለዋል።)
በዚህ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሙ ላይ ህዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ ሲያነሳሳ፤ «ያው እንደምታውቁት የዚህ ሃገር ዜጎች እምነት ይታወቃል። (ሙስሊም ናቸው ማለቱ ነው።) ቤተ ክርስቲያኑን የመገንባት አላማችን ለኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ነገ ጧት ለዓለምና (ሙስሊሞቹም) ክርስትና የሚነሱበት፣ የሚጠመቁበት፣ ንስሐ የሚገቡበት፣ ስጋ ወደሙ የሚቀበሉበት ነው።» የሚል ይዘት ያለው ንግግር በይፋ ተናግሯል።
(ንግግሩን ቃል በቃል ከራሱ አንደበት በቪድዮ በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ።
https://t.me/MuradTadesse/32772)
ይህ የኩፍር ጥሪ ነውር ነው። ቢሳካለት ኖሮ ሙስሊሞችን እምነታቸውን ለማስለቀቅና ወደርሱ እምነት መቀላቀል ዋና አላማው እንደሆነ ንግግሩ ይመሰክራል። እንዲህ አይነቱ ግለሰብ የሙስሊም በሚባል ሃገር ሂዶ እንዲህ አይነቱን ድፍረት የተሞላበት ንግግር ከተናገረ፤ እዚህ ሃገራችን ውስጥ በስውር ሙስሊሙን እምነቱን ለማስለቀቅ የማይሠራ ሰው ስላለመሆኑ ማረጋገጫ የለም።
ከላይ ሲታዩ ሁሉንም አቃፊ ይመስላሉ። ውስጣቸው ግን ጋሬጣ ነው። በርግጥ ውስጠ አዋቂው አላህ ስለማንነታቸው በቅዱስ ቃሉ በቁርኣን ላይ በግልፅ እንዲህ ሲል ነግሮናል፦
(وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ)
«አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ኃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡»
[አል-በቀራህ: 120]
*
ለማንኛውም አቅሙ ያላችሁ ኳታር የምትገኙ ወንድምና እህቶች ይህን የግለሰቡን ንግግር በዐረብኛ የግርጌ ትርጉም አያይዛችሁ ለሚመለከታቸው አካላት ብታቀርቡትና ምናልባት የሚገባቸው ከሆነ እነዚህ ግለሰቦች ያላቸውን የሃገሪቱን ዜጎች እምነት የማስቀየር የረጅም ጊዜ እቅድ እንዳላቸው ጠቁማችሁ ከወዲሁ መቅጨት ቢቻል የተሻለ ነው።
አሊያ እግር ከዘረጉ እዛም ሂደው በለመደው አፋቸው «ኳታር የክርስቲያን ደሴት ናት!» ሊሉ ይችላሉ። የእስራኤል አይሁዳዊያን መላው ዓለም ተጠይፏቸው መግቢያ መውጪያ ሲያጡ ወደ ፈለስጢን ምድር ሂደው በጥገኝነት ተጠልለው ሳሉ፤ ቀስ በቀስ ባላባቱን ፈለስጢናዊ ጭሰኛ አድርገው ይሄው ስቃያቸውን እያሳዯቸው ነው።
በተረፈ ግን በእኛው በሙስሊሙ ታዳሚና ተሳታፊ ጭምር በዩ ቲዩብ ዶላር እየሸቀሉ እምነታችንን እስከማስቀየር ድረስ ከሚያሴሩልን ግለሰቦች የዩ ቲዩብ ቻነል ለቅቃችሁ ብትወጡ የተሻለ ነው። ጠላቶቻችንን መጥቀም የለብንም። ለነርሱ ሴራ ማበረታቻ መሆን የለብንም። Unsubscribe, Unfollow, Unlike, block በማድረግ ከገፃቸው እንውጣ። በምትኩ የንጹሕ ሰዎችንና ዲናችንን የሚያስተምሩ ጠቃሚ ገፆችንና ሚዲያዎችን እንከታተል።
ለ1 መስጂድ ሚናራ ገቢ አሰባሰብኩ ይባልና ለ100 ቤተ ክርስቲያን ግንባታ እንድትሳተፍ የሚያመቻች ብልጥ።መሳይ ያልተነቃበትና ሚዛናዊ መሳይና አስመሳይ ሰው ነው የሚመስለኝ። በጊዜ ቢነቃበት ጥሩ ነው። ዝም ብላችሁ በጭፍን አትደግፉ። እርግጥ ነው ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ እያሰባሰብ ስለ ሙስሊም መልካምነት እንዲያወራ ባይጠበቅም፤ ግን የዚህ ንግግሩ አውድና ይዘት ከጀርባ ያለውን እኩይ አላማና ውስጣዊ እሳቤ ምን እንደሆነ ይጠቁማል።
|| Murad_Tadesse
🔰 ዳገቱን መጨረስ
▣ አንገትህን ቀና አርገህ ስላየህ ዳገቱን መጨረስ አትችልም፤ የተወሰኑ እርምጃዎችን መጓዝ ይኖርብሃል።
◉ ልክ እንዲሁ በህይወት ስትኖርም መልካም ነገሮችን መመኘት ብቻውን በቂ አደለም። የምታልመውን ህልም ለመኖር ስትል ብዙ መስዋዕትነት መክፈል ይኖርብሃል።
አዎ በጣም ብዙ ጫናዎች ሊበዙብን ይችላሉ። ብዙ እንግልቶች ሊገጥሙንም ይችላሉ። ብዙ ዛቻዎች፣ ትችቶችና ወቀሳዎችም ሊደርሱብን ይችላሉ። ግን እነዚህን ሁሉ ችላ በማለት ወደፊት መጓዝን ካልጀመርን ህይወታችን በእንጭጩ ይቀጫል።
ዛሬ ላይ በድካምም ሆነ በመከራ ራሳችንና ሰዎችን ካልረዳን ነገ ህይወትም ሆነ ጊዜ ከኛ አይተባበሩም።
ዛሬ ላይ ምንችለውን ሁሉ ሙከራዎች ካልሞከርን፣ የምንችለውን ሁሉ ጥረቶች ካልጣርንና የምንችለውን ሁሉ ለሰዎች መልካም ነገርን ካልዋልን ነገ ህይወታችን በኛ ላይ ችግር፣ መከራና ስቃይ ትሆንብናለች።
▣ አዎ ሞክረን ላይሳካልን ይችላል፤ ደጋግመን ሞክረንም ደጋግሞም ላይሳካልን ይችላል ግን የኛ ስራ ስኬቶችን መቁጠር ሳይሆን በመውደቃችን የምናገኛቸውን ጥንካሬዎች ማየት ይኖርብናል።
● ደግሞም ይህን አናስብ እኛ ተሳካልን የምንለው ያኔ እንዳይሆን ብር ስናገኝ። እኛ ተሳክቶልናል የምንለው ያኔ ነው ባለን እውቀት፣ ባለን ገንዘብና ባለን ሀሳብ በዙሪያዎቻችን ያሉ ሰዎችን መቀየርና መርዳት ስንችል ነው። ይህ ነው ስኬት ማለት።
● ተሳካልን የምንለው ያኔ እንዳይሆን ትላልቅ ህንፃዎችን መገንባት ስንችል፤ ተሳክቶልናል የምንለው ያኔ ነው ለአላህ ብለን ለሰዎች ደስታ መስጠት ስንችል፣ በሰዎች ደስታ ደግሞ እኛ መደሰት ስንችል ነው።
እናም ወንድምና እህቶቼ፦
➤ ተስፋ ሳንቆርጥ ፈጣሪን ይዘን እንሞክር፣ ጥረት እናድርግ የቀረውን ለአላህ እንተወው!
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
Twitter.com/Secretsof_Truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
t.me/ReshadMuzemil
