cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የ ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ዲጅታል ቤተ-መጽሐፍ

ይህ የተለያዩ መንፈሳዊ መጻሕፍት የሚጋሩበት የ ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ዲጅታል ቤተ-መጽሐፍ ነው። ለ መወያየት : ለ ገንቢ ሀሳባት እና ለ መጻሕፍት ጥቆማ @Girmay_AD11 እንዲሁም @YNSel

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
709
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+27 روز
+1030 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

✨✨<<ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ>>✨✨ ማር 13፡18 ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ድረስ የክረምት ወቅት ነው🌧🌧🌧 🌺#ክረምት የብሉይ ኪዳን ዘመን ምሳሌ ነው የክረምት ገበሬ ጠዋት ጾሙን ይወጣል ቀን ከላይ ዝናም እየወረደበት ከታች ጭቃ እየሆነበት ሲሠራ ውሎ ማታ እራት ጎመን ይቀርብለታል ድካምና ረኃብ ፍርሃትና ስቃይ ይፈራረቁበታል! ነቢያት በዘመነ ብሉይ እንዲሁ ነበሩ። ያለ ልጅነት ወጥተው ያስተምራሉ ፤ትንቢት ይናገራሉ ሲመሽ ማታ (ሲሞቱ) በሥጋ ወደ መቃብር በነፍስ ወደሲኦል ይወርዳሉ(የጎመን እራት)! 🌺#ክረምት የቃል ኪዳን መገለጫ ነው ክረምት በብሉይም በሐዲስም ከተደረጉ ኪዳናት ጋር ተያይዞ ይገለጻል በተለይም ቅዱስ ያሬድ ክረምትን ከኖኅ ኪዳን ጋር እያነጻጸረ የገለጸው የዜማ ድርሰት አስደናቂ ነው "ያከርም በበዓመት ተዘኪሮ ዘመሐለ ለኖኅ ገብሩ" የሚያስደንቀኝ ገለጻ ነው! (ዘፍ 8፥22) #በክረምት፦ መብረቅ ነጎድጓድ በረድ (በረዶ) ማዕበል ሞገድ አለ ሰማዩ ይጠቁራል ደመናው ይከብዳል መሬቱ ይላላል ወንዙ ይሞላል ዘመድ ከዘመድ ሳይጠያየቅ ይከርማል ስለዚህም በዚህ ወቅት ወርኀ ክረምቱን በሰላም እንዲያሳልፍልን ጸሎት/አስተምሕሮ ይደረጋል ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 25 ድረስ ያለው የአስተምህሮ ጊዜው የዚሁ አካል ነው። ዝናሙ ዝናመ ምሕረት ጠሉ ጠለ በረከት ነፋሱ ነፋስ ምሕረት እንዲሆን አስተብቁዖት(ምልጃ) ሊደረግ ይገባል። 🌺#ክረምት የምጽአተ እግዚእ ምሳሌ ነው ማቴ 24፥27 ክረምት የጌታ መምጣት የዘመን ፍጻሜ ምሳሌ ሆኖም ይነገራል በክረምት ከሚሰማው ነጎድጓድ በላይ የሆነ ነጎድጎድ በዕለተ ምጽአት ይሰማል ጌታም እንደ መብረቅ ብልጭታ ከምሥራቅ እስከምዕራብ ያለ ወሰን በምልዓት በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ይገለጣል ይህን እያሰብን በጎ እንድንሠራ ክረምት አስፈሪ ምልክቶች ይታዩበታል! ምልክቶቹም አቅማችንን አውቀን፣ ተፈጥሮ ከእኛ አቅም በላይ መሆኑን ተገንዝበን ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ የሚያሳስቡ ናቸው! #በዚህ ክረምት መርከብ መሥራት በመርከቡ መቀመጥ ያስፈልጋል #መርከቡም፦ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጸሎት ንስሐ በጎ ሥራ ነው! "ግበር ታቦተ በዘትድኅን" የምትድንበትን መርከብ ሥራ! አምላካችን እግዚአብሔር ክረምቱን በሰላምና በጤና ያሳልፈን!!! አሜን!🌽🌽🌽 ከመምህር ነቅዐጥበብ
نمایش همه...
5
🌺🌺💫✨በሕይወታችን የምንሰራው መልካም ስራ፣ትሩፋትም (ጾም፣ጸሎት፣ስግደትን በጎ ነገር ሁሉ በእኛ ብቃት፣ችሎታ ሳይሆን እግዚአብሔር ስለፈቀደ እና ስለወደደ ነው ነገር ግን በሙያዬ፣ በጉልበቴ በችሎታዬ ምንል ከሆነ ከትሩፋታችን እንሰናከላለን...✨ በመጽሐፈ መነኮሳት የሙሴ ጸሊምን ታሪክ እንደምናገኘው... የሙሴ ጸሊም ጌቶች ፀሐይና☀️ ጨረቃን🌙 ያመልኩ ነበር ጌቶቹ ሙተው ለልጆቻቸው ይገዛል ልጆቻቸውም ፀሐይና ጨረቃን ያመልካሉ። ከዕለታት አንድ ቀን ሙሴ ጸሊም ከባልንጀሮቹ ጋር ሊሰርቅ ወደ በረሀ ሲሄዱ የፀሐይ ሙቀት በርትቶባቸው ከጥላ ስር አርፈው ሳለ ቀና ብሎ ፀሐይ ስትባክን አይቶ አሁን ፀሐይ ምን አምላክ ናት አምላክስ የኔ ጌቶች በልተው ጠጥተው ከጥላ ስር አርፈው የሚኖሩ አላቸው። ጓደኞቹም አሻግረው አይተው አምላክ አምላክ ትላለህ አምላክስ ከፈለክ የአባ ኤስድሮስ ገዳም ያውልህ አትሄድም አሉት ወዲያው ተነሥቶ ሄደ። ከገዳሙ ሲደርስ ግብሩን (ስራውንን ያውቃሉና መነኮሳት ተሸበሩ... አበ ምኔቱ (የገዳሙ አስተዳዳሪ አባ ኤስድሮስ ጸጋ እግዚአብሔር ጠርታ አምጥታዋለችና ተቀበሉት አላቸው እነሱም ተቀብሉት። ከዚህ በኋላ ልጄ ምን አመጣህ ብሎ ጠየቀው ትመክረኝ ብዬ ነው አለው መከረው አስተማረው አመነ ተጠመቀ ደግ ሰው ሆነ መንኩሶም ታላቅ አባት ለመሆንም በቃ። ሙሴ ጸሊምን ከመጥፎ ግብር ስቦ ያመጣው ጸጋ እግዚአብሔር እንጂ የሙሴ መልካም ስራ፣ጸሎት አይደለም። 🦋"ሰው የሚሰራት ትሩፋት ሁሉ በእግዚአብሔር አጋዥነት ትፈጸማለች" ይላልና። ጌታችንም በወንጌል. 🦋" ያለ እኔ ምንም ስራ መስራት አይቻላችሁምና'"፤። ብሎ ተናግሯል። 🌾💫በጎ ስራ እንድንሰራ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።
نمایش همه...
10👍 4
✝✝🌾🌾🔊🔊እግዚአብሔር አባታችን እንጂ ጉዳይ አስፈፃሚያችን አይደለም። እንደ አባት ቅረቡት። ወደ ጉዳያችሁ ሳይሆን ወደ❤️ልባችሁ አቅርቡት። የዕለት ጸሎታችሁን ካደረሳችሁ በኋላ (ውዳሴ ማርያም፣ ዳዊት፣ አርጋኖን...) ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤ ራሳችሁን ገልጣችሁ በፊቱ ቁሙ። ሳትሸፋፍኑ ሳትደብቁ ሁሉንም አዋሩት።💫💫 ልጆቹ አይደለን? ይናፍቀናል ስለ ህይወታችን ሊሰማ ሊያግዘን ይፈልጋል። በፀጥታ ውስጥ ለልባችሁ የሚመክራችሁን አዳምጡት፣ በመፅሀፍቱ አናግሩት። እሱ ስትጸልዩ እንደሰማችሁ እናንተም ደግሞ ተረጋግታችሁ አዳምጡት። ባላችሁ አቅም ሁሉ ቅረቡት እንጂ ጉዳያችሁን ተናግራችሁ ዞር የምትሉ አትሁኑ...... .....እግዚአብሔር ይርዳን ....
نمایش همه...
26
የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት challenge የሐዋርያትን ስራ በሐዋርያት ጾም
نمایش همه...
የሐዋርያት ስራ.pdf5.55 KB
👍 1
🌿ጳራቅሊጦስ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን ነው።🌿 በትንሣኤው ተፀንሳ እስከ ዕርገቱ ድረስ ለዐርባ ቀናት ተሥዕሎተ መልክእ የተፈጸመላት ቤተ ክርስቲያን💒 ዛሬ የተወለደችበት ቀን ነው። እግዚአብሔር በባቢሎን ሜዳ የበተነውን ቋንቋ የሰበሰበበትና እንዱ የሌላውን እንዳይሰማው እንደባልቀው ያሉ ሥሉስ ቅዱስ አንዱ የሌላውን እንዲሰማ ያደረጉበት ዕለት ዛሬ ነው።፡ ሰው ወደ ፈጣሪ ግንብ ሰርቶ በትዕቢት ለመውጣት ሲሞክር የወረደው መቅሠፍት ዛሬ በትሕትና ፈጣሪን ሲጠባበቁ ለነበሩ ሐዋርያት ፈጣሪ ራሱ ያለ ግንብ ወርዶ ራሱን የገለጠበት ዕለት ነው።✝ 🦋ዛሬ እስራኤል ከግብፅ በወጡ በሃምሳኛው ቀን በሲናን ተራራ የወረደው እሳትና በጽላት ላይ የተጻፈው ሕግ የተሠጠበት ቀን ነው። ፋሲካችን ክርስቶስ በታረደ በሃምሳኛው ቀን በሐዲስ ኪዳንዋ ደብረ ሲና በጽርሐ ጽዮን በእሳት አምሳል መንፈስ ቅዱስ ወርዶ በሐዋርያት በልባቸው ጽላት ቃሉን የጻፈበት ቀን ነው። በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ በርግብ 🕊🕊አምሳል በትሕትና የወረደው መንፈስ ቅዱስ ዛሬ በእሳትና🔥 በነፋስ አምሳል ወደ ሐዋርያቱ የወረደው ዛሬ ነው።፡ ርግብ ሆኖ የወረደው ሊመሰክርለት እንጂ ኃይል ሊሠጠው ስላልነበረ ነው። ዛሬ ግን ለሐዋርያቱ ኃይል ሊሠጣቸው ፈልጎ በእሳትና በነፋስ ኃይሉን ገለጠ። 🔊✨✨መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ በዚያ መገኘት ከፈለጋችሁ በቅዳሴው መካከል ተገኙ። ካህኑን "ይህች ቀን ምን የምታስፈራ ናት? ይህች ቀን ምን የምታስጨንቅ ናትን መንፈስ ቅዱስ ከመልዕልተ ሰማያት የሚወርድባት?' ሲል ታገኙታላችሁ። ኢሳይያስ ያየውን ራእይ ማየት ከፈለጋችሁ ወደ ቅዳሴ ገስግሱ። ሱራፊ በጉጠት ፍሕም ይዞ ኃጢአታችሁን የሚተኩስበትን ደሙን ለመቀበል ከፈለጋችሁ ወደ ቅዳሴው ገስግሱ: "ፈኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ' እያላችሁ የምታዜሙበት ዕለታዊው ጳራቅሊጦስ ቅዳሴው ላይ ተገኙ: በአዲስ ቋንቋ ትናገራላችሁ። የእናንተ ቋንቋ ሳይቀየር የሁሉም ቋንቋ ተናጋሪ ሰምቶ ይረዳችሁዋል። ለሐዋርያት የተሠጠኸውን ሠጥተኸን ከሐዋርያት ያገኘኸውን ያላገኘህብን ሆይ ቅዱስ መንፈስህ ከእኛ አትውሰድብን። የማዳንህን ደስታ ሥጠን። በእሺታም መንፈስ ደግፈን።. . .አሜን ከዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ
نمایش همه...
5👍 2
💫ልብ በል - ክርስቶስ እርሱን መከተል ለሚፈልጉ የጠየቀዉ “ሰይጣንን ወይንም ክፉ ባልንጀራነትን እና አካባቢን መካድን ሳይሆን ‹ራሰን መካድን› ነዉ፡፡ ራስህን ስትክድ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ወደ ኋላ ፣ ራስህን ደግሞ በእግዚአብሔር እጆች ላይ መጣል ትችላለህ፡፡ ራሱን መካድ የቻለ ሰዉ ‹ነፍሱን በእግዚአብሄር ላይ የጣለ ሰዉ› ነዉ፡፡ ታዲያ ይህንን ሰዉ ‹የሚያስፈራዉ ማነዉ? የሚያስደነግጠዉስ ምንድነዉ? እግዚአብሄር የህይወቱ መታመኛዋ ነዉ!” (መዝ 27፤1) ራሱን መካድ ለቻለ ሰዉ እግዚአብሄርን መዉደድና እርሱን ብቻ መፍራት በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ሁሉን መጣል የሚያስችል ነዉ፡፡ፈቃድ አለንና እግዚአብሄር ግን አያስገድድም፡፡ እኛ ደግሞ ፍቅር ያስገድደናልና ‹አቤቱ ሁሉን ትቶ መከተልን ስጠን! : : : : ምስጋና ይሁን ለአብ ምስጋና ይሁን ለወልድ ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ! አሜን! ከወጣቶች አንዱ
نمایش همه...
7👍 1
✍✍ዉድ አንባቢ ሆይ!💎💎 በልብህ ዉስጣዊ እግዚአብሄርን መዉደድን አሳድግ፡፡- በልብህ እግዚአብሄርን መዉደድ እያደገ ሲመጣ ምድራዊ አሳቦችና ጉዳዮች በዉስጥህ እየቀነሱ ይመጣሉ፡፡ለዚህም ይረዳህ ዘንድ ዘወትር በጸሎትህ ‹ጌታ ሆይ አዉቅህ ዘነድ አንተን ማወቅን ስጠኝ '' ካላወቅሁ እንዴት ልወድህና ልከተልህ እችላለሁ? ካልወደድኩሀስ እንዴት ልከተልህ እችላለሁ? - አንተንስ አዉቆ የማይወድህ ማነዉ? ወዶህስ የማይከተልህ ማነዉ? ፍቅርህ ሥጋዊነትን የማይንቅዉ ማነዉ? ስለዚህ ጌታ ሆይ አዉቅህ ዘንድ አንተን ማወቅን ስጠኝ › በለዉ፡፡ ስለ እርሱ አንብብ ‹ጌታ ሆይ በቃልህ ሰማዮች ጸንተዋል ስለዚህ እኔን ማጽናት ይቻልሃልና በእምነት አጽናኝ - ጠይቁ ይሰጣችኋል አላልክም ይኸዉ ጌታዬ ሆይ ባንተ እንድታጸናኝ እፈልጋለሁ፡፡ ቅዱስ ቃልህን ለማንበብ ንቁ እና ትጉ እንድታደርገኝ እፈልጋለሁ፡፡ ፍጹምና ለበጎ ስራ የተዘጋጀሁ መሆን እፈልጋለሁ ለዚህ ደግሞ ቃልህን በማንበብ እተጋ ዘንድ እና ቃልህ ይለዉጠኝ ዘንድ ነጻ እሆን ዘንድ እለምንሃለሁ” በለዉ። ዝም ብለህ በእርሱ ፊት ተቀመጥ፡፡ ‹ጌታ ሆይ አንተ ምሪትን ካልሰጠኸኝ ከፊተህ አልንሳቀስም - ትናገረኝ ዘንድ ይኀዉ ከፊተህ ቀርቤያለሁ አቤቱ ተናገረኝ› በለዉ፡፡ ምንጭ: ትንሽ እሳት
نمایش همه...
16👍 3
#እንኳን_አደረሳችሁ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅጽል ስሞች👇 • መልአከ ምሕረት • መልአከ ሰላም • መልአከ ኃይል • መልአከ ምክር • መልአከ ኪዳን • መልአከ መዊዕ • መልአከ ሕይወት • መልአከ አድኅኖ • መጋቤ ብሉይ እስራኤል ዘሥጋን • የመራቸውና የጠበቃቸው • ባህር የከፈለላቸው • ጠላት ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያጠፋላቸው • በአምላኩ ፈቃድ መና ከሰማይ ያወረደላቸው • በለዓም እንዳይረግማቸው ሰይፉን መዞ መርገማቸውን የመለሰላቸው • ለመራገም የሄደውን እንዲመርቃቸው ያደረገው ....በዚህም መጋቤ ብሉይ ተብሎ የተጠራው • የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረው • የቅድስት አፎምያን ፈታኝ በሥልጣን የረገጠው ... መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው!!! ቅዱስ ያሬድ "አስተምሕር ለነ ሰአልናከ  በዐሠርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ " ብሎ እንደለመነው.... እኛም እስራኤል ዘነፍስ በቅዱስ ያሬድ ቃል ♥ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ!♥ ተማጽነንሃል! በአሥራ አራቱ ምልጃዎችህ ማልድልን" እንደ አምላክህ በሆነው ርኅሩህነትህ ከፈጣሪያችን ጋር አስታርቀን ክፉውን ሁሉ  በምልጃህ ተቋቋምልን በጠላቶቻችን የተጻፈብንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት ቀይርልን በልዩ ልዩ ደዌ የሚፈትኑንን አጋንንትን ከአምላክህ በተሰጠህ ሥልጣን እርገጥልን .. እያልን እንለምነዋለን! የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ ሁላችንንም በያለንበት ይጠብቀን! አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
نمایش همه...
14
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.