cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

⛰Hira Muslim student's Medi@🏔

ይህ ቻናል የሙስሊም ተማሪዎች ድምፅ ነው!! ꧁﷽꧂ ባለንበት ተጨባጭ በተለያዩ ረዕሰ ጉዳዮች ላይ እንመካከራለ እስካሁን በጣም ደስ የሚሉ አስተማሪ ፁሁፎችን አቅርበናል በአላህ ፍቃድ ከዚህ በኋላም ይቀጥላል። # ተከታታይ ታሪኮች # የመፅሀፍ ግብዣ # የጥያቄ ውድድር # የጀምዓው መልዕክት # የውይይት ረዕሶች የመሳሰሉት በዚህ ቻናል ይለቀቃል ለውይይት→https://t.me/HiraMuslimstudent

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
620
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+17 روز
+2530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#ለኢንትራንስ ፈተና ወደ ግቢ ለምትገቡ እህቶች የተላለፈ የጥንቃቄ መልእክት። 1⃣ዶርም ስትይዢ በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ እህቶች ጋር ያዢ። 2⃣ጋጠወጥ ከሆኑና እይታን ከሚሹ መጥፎ ጓደኞች ራስሽን አርቂ። 3⃣በማንኛውም ሰኣት ግቢ ላይ ለብቻሽ አትንቀሳቀሺ። 4⃣ዶርም ውስጥ ለብቻሽ አትሁኚ/አትተኚ/አታንብቢ። 5⃣ሂጃብሽን ጠብቂ፤ስርአት ያለውን አለባበስ ብቻ ልበሺ። 6⃣የሴቶች ተብሎ በሚከለለው የዶርም አከባቢም ቢሆን ብቻሽን አትሁኚ። 7⃣ከመሸ በኋላ በተቻለ አቅም ከዶርምሽ አትውጪ። 8⃣ሰላትሽንም ቢሆን ዶርምሽ ውስጥ ስገጂ። 9⃣"አዑዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቅ" የሚውን አዝካር አዘውትሪ። 🔟አላህ ከክፉዎች ተንኮል እንዲጠብቅሽ ዱዐ አድርጊ። 💥እነዚህን ቅድመ ጥንቃቄዎች በመተግበር ራስሽን ከፆታዊ ጥቃት ከ አላህ ጋር ጠብቂ!! #Share #ሼር
نمایش همه...
👍 6
አስደሳች ዜና ከሂራ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር ሶስት ተከታታይ የ12ተኛ ክፍል የምርቃት ፕሮግራም በልዩ ሁኔታ   አዘጋጅቶ  ያስመረቀው ሂራዕ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር ዘንድሮም ለ 4 ተኛ ጊዜ በሚያከናውነው የምርቃት መርሀግብር ላይ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ግብዣችን ነው ሲል ያበስሮታል። ያሳለፍነውን ልናወጋ ለቀጣይ ትምህርት ህይወታችን ዕውቀትን ልንቀስም ወርቃማው ትውልድ 4 ብለን በመሰየም ነሀሴ 4 ቀን 2016 አ.ል በአንተነህ ሁለገብ አዳራሽ ልዩ የሆነን መሰናዶ አዘጋጅተን እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን።በእለቱም  ፣ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ወርቃማው ትውልድ  ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ትክክለኛው ስኬት እንዲሁም ኡስታዝ ሀሊድ ክብሮም በቁርዕን ማስማማት በሚል ርዕስ በጣፋጭ አንደበታቸው ገለፃ ሲያደርጉልን እንዲሁም መሰል ዱአቶች ምክሮቻቸው ይደመጣሉ።  በተጨማሪም  በግጥም፣ ወግ ፣አንቂ አደበቶች እና በመሰል የመድረክ ፕሮግራሞች እለቱ ይደምቃል ፣ ያሸበርቃል። ይህም መሰናዶ ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ከ ማህበሩ  የምስክር ወረቀት ፣ጋወን ብሎም ለተማሪው  የምሳ ፕሮግራምን አካቶ 1000ብር ብቻ ተሰናድቷል። እርሶም የዚህ ልዩ ፕሮግራም ተሳታፊ ለመሆን እነዚህ አማራጮችን ይጠቀሙ ተመራቂ ባንሆንስ ብሎውም እንዳይጨነቁ ለ እርሶም በ VIP ምሳን አካቶ 500ብር በ ኖርማል ትኬት 250 ብር በመክፈል የፕሮግራሙ ታዳሚ ይሁኑ ስንል ጥሪያችን ነው ለበጠመረጃ :  በ 0983704604/0973538955 ሀሎ ይበሉን።  እዲሁም በቴሌግራም ፔጃችን  https://t.me/HiraEslamicMidea ይጎብኙን። እንዲሁም በ ሂጅራ ባንክ እና በ ዳሽን ባንክ በሁሉም ቅርንጫፍ ትኬቶቻችንን ማግኘት ይችላሉ አልያም ይንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ https://ticket.hijradigital.com/ ከፍለው ሲጨርሱ በ ሂራዕ ቦት ይመዝገቡ ለ ተመራቂ ተማሪ @Hira_Muslim_stu_ass_bot አደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል ያለን ውስን ቦታ ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ።
نمایش همه...
⛰Hira Muslim student's Medi@🏔

ይህ ቻናል የሙስሊም ተማሪዎች ድምፅ ነው!! ꧁﷽꧂ ባለንበት ተጨባጭ በተለያዩ ረዕሰ ጉዳዮች ላይ እንመካከራለ እስካሁን በጣም ደስ የሚሉ አስተማሪ ፁሁፎችን አቅርበናል በአላህ ፍቃድ ከዚህ በኋላም ይቀጥላል። # ተከታታይ ታሪኮች # የመፅሀፍ ግብዣ # የጥያቄ ውድድር # የጀምዓው መልዕክት # የውይይት ረዕሶች የመሳሰሉት በዚህ ቻናል ይለቀቃል ለውይይት→

https://t.me/HiraMuslimstudent

እህቴ 🌹⑤ 🍂…የሰለሀዲን እናት ሰልሀዲንን በልጅነቱ ጀምሮ ድል ድል እንዲሸት፣ እንዳይረታ አድርጋ ባታሳድገው ኖሮ… ቁድስ ጥንትም ልክ እንደሁኑ በጠላት እጅ እንደሆነች በቀጠለች ነበር። 🍂የሙሀመድ ፋቲህ እናት ገና በህፃንነቱ ጀምራ የኮንስታንትኖፕልን ግንድ እያሳየችው እንደሚከፍት ባታነሳሳው ኖሮ… ምናልባት ኢስታንቡል ሚባል ሀገር አናውቅም ነበር። 🍂ሂንድ ቢንት ዑትባ በልጇ በሙዓዊያ ልብ ውስጥ ከልጅነቱ ጀምሮ ጀግንነት ባትኮተኩት ኖሮ… አንዲትን ስንዝር መሬት ድል ባላደረገ ነበር። 🍃ያ ሁላ ፅናትና ታጋሽነት በቡካሪ እናት ልብ ውስጥ ባይኖር ኖሮ… ሰሂሀል ቡኻሪ ሚባል ኪታብ ኺያል በሆነ ነበር። 🍃የአህመድ ኢብኑ ሀንበል እናት ልጇን በአላህ ፍቅር፣ በነብዩ ፈለግ፣ በዲን ፅናት ባታሳድገው ኖሮ… ያ ሰውነት በነዚያ ቢድዓ አራማጆች ፊት ባልፀና ነበር። የሀንበሊያ መዝሀብም ባልኖረ ነበር። 🍃የአህመድ ኢብኑ አብዱል–ሀሊም እናት ልክ እንደዘመናችን ሴቶች ሁላ ጊዜዋን በሙሰልሰልና፣ የተለያዩ የምግብ አይኖትችን በመስራት ብታሳልፍ ኖሮ… ስሙ ብቻ የቢድዓ ሰዎችን ሚያስጨንቀው ‘ኢብኑ ተይሚያ’ ሚባልን ሰው ዓለም ባለወቀው ነበር። 🍃የአብደረህማን አሱመይጢ ሚስት ለባሏ የዲን ፅናትን፣ የአኺራ ሽልማትን እየነገረችው ለታላቅ ዓላማ ባታነሳሳዉ ኖሮ በዚያ በረሃማ የአፍሪካ ምድር ላይ ባልፀና ነበር። 11 ሚልየን ሰዎችን ማስለም ይቅርና መቶ ሰዎችን እንኳን ባላሰለም ነበር። 🍁የሙሀመድ ኢብኑ አብደላህ ሚስት እናታችን ከዲጃ ነብያችንን ባታፅናና ባታበረታታው ኖሮ ይህ ዲን በቀላሉ አጠገባችን ባልደረሰ ነበር። ሳጠቃልለው! በአጭሩ እንዲህ እያልኩሽ ነዉ… «ከሁሉም ታላቅ ህዝቦች /ዑማ/ ጀርባ ጠንካራ ሴት አለች።» በአጭሩ ሴት ልጅ የስኬት መስላል፣ የድል እርከን፣ የታላቅነት መስራች እንደሆነች እየነገርኩሽ ነዉ። አንቺ ጠንካራ ስትሆኚና በዙሪያሽ ያሉትን ስታጠነክሪ ይህ ከየትኛዉም ጊዜ በላይ ችግር ዉስጥ ያለዉን የሙሀመድ ኢብኑ አብደላህን ኡማ ትታደጊዋለሽ። ማወራዉ ኪያል ይመስልሽ ይሆናል፣ ግን እመኚኝ ያንቺ በአላህ መንገድ ላይ መፅናትና ሌሎችን በአላህ መንገድ ላይ እንዲፀኑ ማረገረሽ ብቻ የዚህን ኡማ እጣ ፋንታ ሊቀይረዉ ይችላል። ማን ያዉቃል! ባንቺ እጅ ላይ የሚያድገዉ ልጅ ኮ ልክ እንደ ሰለሀዲን የናፈቀናትን ቁድስ ዳግመኛ ከፍቶለን የደስታ እምባ ያራጨን ይሆናል። (ማን ያዉቃል?) @lendmeurear1
نمایش همه...
👍 1
እህቴ 🌹3️⃣ የውስጥ መረጋጋትን፣ የመንፈስ እርካታን ትፈልጊያለሽ? የሀሳብ ነፃነትን፣ የሞራል ከፍታን ትመኚያለሽ? ሰላምን፣ ደስታን፣ ልዕልናን፣ ከፍታን፣ የበላይነትን፣ አኩልነትን፣ ነፃነትን ትፈልጊያለሽ? ከላይ ለተጠቀሱት ጥያቄዎች በሙሉ፣ አልያም ለከፊሉ፣ ወይም ለአንዱ እንኳን መልስሽ ‘አዎ!’ ከሆነ… የት አንደምታገኚያቸው ልንገርሽ። ከውኑን ሙሉ በፈጠረው ጌታ ይሁንብኝ! ይህ ሁሉም ነገርና ባጠቃላይ መልካም የተባሉ ለህይወትሽ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በዕስልምና ውስጥ ነው ሚገኙት። እስልምና የትኛውም እምነት ያልሰጠሽን ክብርና ዝናን አጎናፅፎሻል። የትኛውም አስተሳሰብ ያልሰጠሽን ከፍታና ነፃነትን ሰጥቶሻል። የትኛው ስርዓት ያልሰጠሽን እኩልነትና ደስታን ችሮሻል። የትኛውም ባህልና ልምድ ያልሰጠሽን የሴትነት ክብርሽን ሚመጥን ደረጃን መርቆሻል። ባጠቃላይ መልካም የተባለን ነገር በሙሉ እስልምና ሰጥቶሻል። የትም ብትሄጂ እንደእምነትሽ ያስከበረሽን አታገኚም። (አራት ነጥብ!) 🍂እስልምና በህይወት የመቀበር ታሪክሽን ፍቆ ከፍታን የሰጠሽ አምነት ነው። 🍂እስልምና ሴት ልጅ ስትወለድለት ፊቱን የሚያጨፈግግን ማህበረሰብ ኮንኖ ሰላት ውስጥ የልጅ ልጁን እያቀፋት የሚሰግድ ታላቅ ነብይን የቸረሽ ዲን ነው። 🍂እስልምና ይሁዶች በመፀሃፋቸው ውስጥ ‘አምላኬ ሆይ! ሴት አርገህ ስላልፈጠርከኝ ምስጋና ላንተ ይሁን!’ ብለው በሚያነቡበት ወቅት ላይ… ‘አኒሳዑ ሸቃዒቁ ሪጃል’ ብሎ የከፍታን ጫፍ ያቆናጠጠሽ ሀይማኖት ነው። 🍃እስልምና የክርስትና እምነት ምሁራን ‘ሴት ልጅ በመንፈሷ ውስጥ ሼይጣን ይኖራል።’ ብለው በተስማሙበት ወቅት ላይ… ታላቋን ሴት ‘ሺፋዕ ቢንት አብደላህን’ የመጀመሪያዋ የሴት ሚንስቴር አርጎ የሾመ እምነት ነው። 🍃እስልምና ‘ሴት ልጅ የወንድን ፍላጎት ለማርካት ነው የተፈጠረችው።’ የሚለውን የአውሮፓውያንን ብሂል ንዶ… ‘ወአሺሩሁና ቢልመዕሩፍ!’ ሲል ስለሴቶች አደራ ያለ ዲን ነው። 🍃እስልምና ማንንም ያላስጨነቀው ክብርሽ ታላቁን ነብይ አሳስቧቸው በሞት አፋፍ ላይ ሆነው እንኳን ስለሴቶች አደራ ያስባለ ዲን ነው። 🍁እስልምና በዓረፋ ላይ ታላቁ ነብይ የመሰናበቻ ሀጃቸውን እያደረጉ ያሁላ ምዕመን በተሰበሰበበት ጊዜ ለሴቶች መልካም መዋልን አስረግጦ ያስተማረ ዲን ነው። አንቺ ብቻ መልካም ነገርን እፈልጋለሁ በዪ! እኔ ደግሞ መልካም ነገር በሙሉ እስልምናሽ እንደሆነ ያለመድከም እነግርሻለሁ። @lendmeurear1
نمایش همه...
አስደሳች ዜና ከሂራ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር ሶስት ተከታታይ የ12ተኛ ክፍል የምርቃት ፕሮግራም በልዩ ሁኔታ   አዘጋጅቶ  ያስመረቀው ሂራዕ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር ዘንድሮም ለ 4 ተኛ ጊዜ በሚያከናውነው የምርቃት መርሀግብር ላይ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ግብዣችን ነው ሲል ያበስሮታል። ያሳለፍነውን ልናወጋ ለቀጣይ ትምህርት ህይወታችን ዕውቀትን ልንቀስም ወርቃማው ትውልድ 4 ብለን በመሰየም ነሀሴ 4 ቀን 2016 አ.ል በአንተነህ ሁለገብ አዳራሽ ልዩ የሆነን መሰናዶ አዘጋጅተን እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን።በእለቱም  ፣ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ወርቃማው ትውልድ  ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ትክክለኛው ስኬት እንዲሁም ኡስታዝ ሀሊድ ክብሮም በቁርዕን ማስማማት በሚል ርዕስ በጣፋጭ አንደበታቸው ገለፃ ሲያደርጉልን እንዲሁም መሰል ዱአቶች ምክሮቻቸው ይደመጣሉ።  በተጨማሪም  በግጥም፣ ወግ ፣አንቂ አደበቶች እና በመሰል የመድረክ ፕሮግራሞች እለቱ ይደምቃል ፣ ያሸበርቃል። ይህም መሰናዶ ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ከ ማህበሩ  የምስክር ወረቀት ፣ጋወን ብሎም ለተማሪው  የምሳ ፕሮግራምን አካቶ 1000ብር ብቻ ተሰናድቷል። እርሶም የዚህ ልዩ ፕሮግራም ተሳታፊ ለመሆን እነዚህ አማራጮችን ይጠቀሙ ተመራቂ ባንሆንስ ብሎውም እንዳይጨነቁ ለ እርሶም በ VIP ምሳን አካቶ 500ብር በ ኖርማል ትኬት 250 ብር በመክፈል የፕሮግራሙ ታዳሚ ይሁኑ ስንል ጥሪያችን ነው ለበጠመረጃ :  በ 0983704604/0973538955 ሀሎ ይበሉን።  እዲሁም በቴሌግራም ፔጃችን  https://t.me/HiraEslamicMidea ይጎብኙን። እንዲሁም በ ሂጅራ ባንክ እና በ ዳሽን ባንክ በሁሉም ቅርንጫፍ ትኬቶቻችንን ማግኘት ይችላሉ አልያም ይንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ https://ticket.hijradigital.com/ ከፍለው ሲጨርሱ በ ሂራዕ ቦት ይመዝገቡ ለ ተመራቂ ተማሪ @sebah_islamic_org_bot አደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል ያለን ውስን ቦታ ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ።
نمایش همه...
⛰Hira Muslim student's Medi@🏔

ይህ ቻናል የሙስሊም ተማሪዎች ድምፅ ነው!! ꧁﷽꧂ ባለንበት ተጨባጭ በተለያዩ ረዕሰ ጉዳዮች ላይ እንመካከራለ እስካሁን በጣም ደስ የሚሉ አስተማሪ ፁሁፎችን አቅርበናል በአላህ ፍቃድ ከዚህ በኋላም ይቀጥላል። # ተከታታይ ታሪኮች # የመፅሀፍ ግብዣ # የጥያቄ ውድድር # የጀምዓው መልዕክት # የውይይት ረዕሶች የመሳሰሉት በዚህ ቻናል ይለቀቃል ለውይይት→

https://t.me/HiraMuslimstudent

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ እንኳን ደስ አላችሁ ሂራዕ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የመለያያ የምርቃት ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ይታወቃል በመሆኑም በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ ለተማሪዎች ለ ወላጆች እንዲሁም ለታዳሚዎች በቀላሉ ባሉበት ሆነው ትኬት መቁረጥ የሚያስችሎዎን ሊንክ ያዘጋጀን መሆኑን ስናበስሮ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው ይሄንን ሊንክ https://ticket.hijradigital.com/ በመጠቀም በምትፈልጉት በ VVIP ተመራቂ ተማሪ ከሆኑ  OR VIP ምሳን አካቶ ፕሮግራም ለመታደም  NORMAL ፕሮግራምን ለመታደም በሚፈልጉት አማራጭ ትኬቶሽን ባሉበት ሆነው ይግዙ አልያም በአቅራቢያዎ በሚገኝ ሂጅራ ባንክ  በመሄድ ክፍያ መፈፅም የምትችሉብት ሁኔታን ያመቻቸን መሆኑን ልናበስርዎ እንወዳለን ይህንን በ አይነቱ ለየት ያለና በትላልቅ ዱዓቶች የታጀበውን እንዲሁም እስላማዊ አደቡን በጠበቀ መልኩ የተዘጋጀውን ፕሮግራም ይታደሙ ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ
نمایش همه...
Hijra Bank

Hijra Bank Ticketing System

Photo unavailableShow in Telegram
@Hira_Muslim_stu_ass_bot Yealen bota wesen selehone fetnew yemezgebu Edelu endayameltot.
نمایش همه...
👍 3
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ በባልደረቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡ ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነኝህ ቀናት ናቸው። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል: — عن جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رَضِيَ الله عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى الله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ". أخرجه البزار وصححه الألباني (صحيح الجامع ، رقم 1133). ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው » አልበዛር እና አልሐይሰሚይ ዘግበዉታል አልባኒም ሰሂህ ብለዉታል (ሰሂሁል ጃሚዕ 1133) عن ابن عباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: "ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر. قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء" أخرجه البخاري ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:‐ «በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል በነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል:‐ 1. ጾም፤ ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም) 2. ዚክሮችን ማብዛት፤ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ፣ ተክቢር፣ ተስቢህ(ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል። عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : "ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد" أخرجه احمد 7/224 وصحّح إسناده أحمد شاكر ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፤«ከእነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ስለዚህ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል አህመድ ሻኪርም ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል። ከተክቢር አደራረግ መካከል፤ الله أكبر ، الله أكبر لا إله إلا الله ، والله أكبر ولله الحمد “አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሀ ኢለላህ ወላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ” የሚለው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ይዘቶች አሉት። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሊደረግ የሚገባው ይህ ተክቢር ብዙ ሰዎች ስለማይፈጽሙት እየተረሱ ካሉ ሱናዎች ማካከል ነው። ሰዎችን ለማስታወስ እና ሱናን ህያው ለማድረግ ድምጽን ከፍ አድርጎ ተክቢር ማድረግ ያስፈልጋል። ዓብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቡሁረይራህ በነዚህ አስር ቀናት ገበያ ወጥተው ተክቢራ ሲያደርጉ ሰዎችም እያስታወሱ ተክቢራ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል። ይህም፤ ሁሉም ሰው የራሱን ዚክር ያደርጋል ማለት ነው እንጂ ሰዎች እየተሰባሰቡ በአንድ ድምጽ ተክቢራ ያድርጉ ማለት አይደለም። ይህ መረጃ ያልተገኘለት ውድቅ ስራ ነው። 3. ሐጅና ዑምራ፤ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ የአላህ መልዕክተኛ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤ عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعته يقول: "الحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة" متفق عليه. ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡» ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል 4. ኡድሂያ በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደአላህ መቃረብ ነው። የሚከተሉት ነጥቦች አጠር ያለ ግንዘቤን የሰጣሉ፤ - ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ ሱናዎች መካከል ነው።የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረጉ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው። - ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ (ተቅዋ) ነው። - ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል። - ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል። - ወንድም ይሁን ሴት ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል ለኡድሂያ ይታረዱሉ። - የአላህ መልዕክተኛ እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ፣ የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም። - ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋርትም ይቻላል። - አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ለቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል። - ኡድሂያውን ለራሱ፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም። - በዒድ ቀን ኡድሂያን ለማረድ አስቦ የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም። ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህ በሀጅ ላይ ያሉ ሰዎችን የሚመሳሰልበት ነብያዊ ትዕዛዝ ነው። ይህ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው። እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም። የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸውና የቻልነዉን ሁሉ በመፈጸም ወደ አላህ መቃረብ ይገባል፤ የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ሰደቃ ማብዛት፣ ሱና ሰላቶችን ማብዛት፣ ቁርዓን መቅራት፣ ዚክር ማብዛት፣ ዱዓን ማብዛት…ወዘተ ያስፈልጋል። አላህ በነዚህ ወርቃማ ጊዜያት ከሚጠቀሙና አላህ ዘንድ መልካም ምንዳን ከሚያገኙ ጠንካራና ብልህ የአላህ ባሮች ያድርገን። ዝግጅት- አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
نمایش همه...
👍 2🥰 1
If u have any comment and suggestion drop here👇 https://t.me/HiraMuslimstudent
نمایش همه...
ሂራዕ የመዲሽ ሙስሊም ተማሪዎች ማህበር❤️

ይህ (ሂራዕ)የመዲሽ ሙስሊም ተማሪዎች ማህበር የቴሌግራም ፔጅ ነው።

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.