cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሕይወት

አንዳንዶቹ ሲሞቱ ይወለዳሉ። ሌሎቹ ደሞ ሲወለዱ ይሞታሉ። በዚ ቻናል ከተለያዩ መፅሀፍቶች, ቻናሎች የመሠጡንን እና ያስተምራሉ ያልናቸውን እናጋራለን።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
194
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
👉ሰዎች በድክመትህ ላይ መሰልጠን ይፈልጋሉ ስለዚህ ድክመትህን አታሳያቸው!!! 👉በሚስጥርህ ሊቆጣጠሩህ ይፈልጋሉ ስለዚህ መወራት እና መደበቅ ያለበትን ሚስጥር ለይ!!! 👉በደካማ ጎንህ ፣ በጎዶሎኽ ላይ ምርኩዝ ሆነውህ ይገባሉ ግን የተደላደልክ ፣ የተመቸህ ሲመስልህ ምርኩዙን ጥለው ይፈጠፍጡሃል! ደካማ ጎንህን ምትገልጥለትን ሰው ልብ በል!!! የሰው ፍጥረት ሑሉ አንድ ነው ማለት አይደለም ፤ ይህን ማለት በሰው ላይ ያለንን እምነት መሸርሸርም አይደለም!!! ግን በሰውነት ቆዳ የተሸፈነ ከሰውነት የጎደለ ማንነት ሊኖረን ስለሚችል ራስን ከጥቃትና ካላስፈላጊ ሕመም መጠንቀቅ መቻል አለብን!!!
نمایش همه...
እርሳስ የሆነ ነፍስ ይስጠን ከእለታት አንድ ቀን አንድ ህፃን አያቱ ደብዳቤ ስትፅፍ ይመለከታል። እናም አያቱን እንዲህ ሲል ይጠይቃታል “አያቴ ይህ የምትፅፊው ደብዳቤ ስለኛ ነው? እኔ እና አንቺ ስላደረግነው ነገር?” አያቱም መልሰው “አዎ ልጄ የምፅፈው ስለ አንተ ነው፣ ነገር ግን ከምፅፈው ፅሁፍ ይበልጥ የምፅፍበት እርሳስ ትልቅ ትርጉም አለው፤ አንተም ስታድግ እና ትልቅ ሰው ስትሆን እንደዚህ እርሳስ እንድትሆንልኝ እመኛለው “ አሉት የልጅ ልጃቸውን ቁልቁል እየተመለከቱት። ህፃኑም አያቱ በጨበጡት እርሳስ ላይ ምንም አዲስ ነገር ባለማየቱ ግራ ተጋብቶ “አያቴ አሁን የያዝሽው እርሳስ ከሌላው እርሳስ በምን ይለያል” አላቸው፤ አያቱም ቀጥለው “አየህ ልጄ፤ ሁሉም ነገር እንዳመለካከትህ ይለያል፤ ይህ እርሳስ አምስት ድንቅ ባህሪዎች አሉት አንደኛው ይህ እርሳስ ያለ እጅ መፃፍ አይችልም፤ አንተም ምንም ድንቅ ተዓምር መስራት እና መከወን የምትችል ሰው ብትሆንም እጅ የሚሆንህ ፈጣሪ ከሌለ ዋጋ የለውም።ስለዚህ ፈጣሪን ፍራ የእጁን ፍጥረቶች አክብር። ሁለተኛው እንደምታየኝ እፅፍ እፅፍና እርሳሱ ሲዶለዱም አረፍ እልና በመቅረጫ እቀርፀዋለው፤አካሉን ያጣል ግን ይበልጥም ሹል ይሆናል። ሰውም ቢሆን በህይወቱ ብዙ ውጣ ውረዶች ያጋጥሙታል፤መሳልም መውደቅ መነሳቱም ህመም አለው ግን ፈተናውም ሲያልፍ ይበልጥ ሹል ይሆናል ማለት ነው። ሶስተኛው ደግሞ ልጄ….. ይህ እርሳስ በማንኛውም ሰዓት የምሰራውን ስህተት በላጲስ አጥፍቼ እንዳስተካክል እድል ይሰጠኛል። ይህ ማለት በህይወታችን የምንፈፅማቸውን ስህተቶች ማስተካከል ነውር አይደለም፤አንድ ውድቀት ሲያጋጥመን ከሱ ተምረን የተሻለ ድንቅ ሰው ማድረግ፤ ይልቁንም እራሳችንን እያረምን እረጅም መንገድ እንድንጓዝ ይረዳናል። አራተኛው ድንቅ ባህሪ ደግሞ፤ የዚህ እርሳስ ታላቅነት ያለው የውጪ አካሉ ላይ ማለትም እንጨቱ ላይ ሳይሆን፤ ውስጡ የተቀበረው ቀጭን ነገር ላይ ነው። ሰውም ቢሆን እንደዛው፤ሁሌም ቢሆን ታላቅ ነገር የሚሰራው ውስጣችን ያለው ነገር ነው። ውስጣችን ልዩ ሃይል አለው ታምር መስራት ያልታየውን የመፍጠር ድንቅ ብቃት አለው። እናም ልጄ ለውስጥህ ሰላም እና ደስታ ትኩረት ስጥ።ሁሌም የአሸናፊነት መንፈስ ይኑርህ። ውስጥህ መልካም ነገር ከሌለ መልካም ነገር ማድረግ ይሳንሃል። አምስተኛው ምን መሰለህ ልጄ….. ይህ እርሳስ በተፃፈበት ቁጥር ምልክት ይተዋል። አንተም እንደዛው…..በህይወት ጎዳና ስትጓዝ ምልክትህን መተውህ አይቀርምና በኑሮህ የምትወስናቸውን ነገሮች ሁሉ አስተውል።የሰው ልጅ ሁሉ አሻራ የተለያየ ነው አንተስ ምንድነው አሻራህ?ምን ምልክት ዘላለም የአንተ የሆነ ምን አለህ?.ሁሌም ይሄን መልስ። የመጨረሻው አየህ ልጄ እስራሱ ሲዶለዱም ይቀረፃል በዚህም ሂደት ቁመቱ እያጠረ እያጠረ ያልቃል ስለዚህ እርሳሱ ጥሩም ፃፈ መጥፎ ማለቁ አይቀርም እኛ ሰዎችም ከዚች አለም ማለፋችን አይቀርም መልካም ሰርተን እንለፍ እኔ አርጅቻለሁ አንተም እንደኔ አርጅተህ ማለፍህ ስለማይቀር ሁሌም መልካም ሰርተህ እለፍ።አሻራህን በድንቅ መልካም መሬት ላይ አንፅ! @be_MOTIVATEDPERSON
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ሁሉም እንስሳት እና አዕዋፋት ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ወደ መጠለያቸው ገብተው ዝናቡን ያሳልፋሉ ንስር የሚባለው አዕዋፍ ግን ዝናብ ሲዘንብ ራሱ ከ ደመና በላይ ማለትም ከዝናቡ በላይ እየበረረ ከዝናብ ራሱን ይከላከላል ::
نمایش همه...
Repost from FANOS BOOKS
"ፕሮፌሰሩና ባለጀልባው" አንድ ፕሮፌሰር በባሕር ላይ ለመዝናናት ጀልባ ተከራይቶ መጓዝ ይጀምራል፡፡ ፕሮፌሰሩም ባሕሩ ጸጥ ስላለባቸው ከባለ ጀልባው ጋር አንዳንድ ነገር ለምን አልወያይም ብለው ወደ ሰማይ አቅንተው ከዋክብትን ካዩ በኋላ ጀልባ አከራዩን "አንተ ሰው ስለ እነዚህ በባሕር ውስጥ ስለሚኖሩ አሳዎች አሳ ነባሪዎች ምን ያህል ታውቃለህ?" ይሉታል፡፡ ባለ ጀልባውም "አይ ፕሮፌሰር ምንም አላውቅም" ይላል። ፕሮፌሰሩም «ይህን ካላወቅክ የሕይወትህን 1/4ኛ አጥተሐል »ይሉታል፡፡ ጥቂትም እልፍ እንዳሉ በባሕሩ ላይ ያሉትን እጽዋት እያዩ«አንተ ሰው ስለ ሥነ እጽዋት ምን ያህል ታውቃለህ ?» ይሉታል ፡፡ ባለ ጀልባውም ከቀዘፋ ተግባሩ መለስ ብሎ « ጌታዬ ምንም አላውቅም እኔ ጀልባ እያከራየሁ ቤተሰቤን ብቻ ነው የማስተዳድረው ምንም ያልተማርኩ ተራ ምስኪን ሰው ነኝ ይላቸዋል » አለ፡፡ ፕሮፌሰሩም እንግዲያውስ «ይህን ካላወቅክ አሁንም ከሕይወትህ 1/4ኛውን አጥተሃል ይሉታል። » ቀዛፊውም ግማሽ ሕይወቱ በምሁራዊ አስተሳሰብ ተቀንሶበት ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ፕሮፌሰሩም በዚህ ሳያበቁ «አንተ ሰው ስለ ስነ ሥነ-ከዋክብት ምን ያህል ታውቃለህ?» ይሉታል። ባለጀልባውም "እንዴ ፕሮፌሰር እኔ እዚህ ባሕር ውስጥ አጠገቤ ስላለው ስለ አሳ ስለ አሳ ነባሪ ያላወቅኩ እንዴት ሰማይ ወጥቼ ስለ ከዋክብቱ ላውቅ እችላለሁ? እኔ የማውቀው ነገር የለም።" ይላቸዋል። ፕሮፌሰሩም እንግዲያውስ «ይህን ካላወቅክ አሁንም ከሕይወትህ 1/4ኛውን አጥተሃል ይሉታል። » ባለ ጀልባውም አይ ይህቺን የቀረችኝን 1/4 ኛዋን ሕይወቴን እንዳይጨርሷት ብሎ ቶሎ ቶሎ ወደ ባሕር ዳርቻው ሲቀዝፍ ሐይለኛ ማእበል መጥቶ ጀልባዋን ሊገለብጣት ይታገል ጀመር :: ባለ ጀልባውም ከመገልበጥ ለማዳን ሞክሮ ሞክሮ አቃተው ከአቅሙ በላይ ሲሆንም በማእበሉ መሐል ሆኖ ፕሮፌሰርን ጮክ ብሎ " ፕሮፌሰር ስለ ዋና ምን ያህል ያውቃሉ?" አላቸው። ፕሮፌሰሩም "ምንም አላውቅም።" አሉት። ባለጀልባውም እያዘነ "ፕሮፌሰር እንግዲያውስ ሙሉ ሕይወትዎትን አጥተዋል።" ብሎ እየዋኘ ወጣ፡፡ ፕሮፌሰር ግን ሰጥመው ቀሩ፡፡ @fanos_books_official
نمایش همه...
አየህ ይች ሀገር ህዝብ አላት! ሰው ግን የላትም! እንጨት ብቻውን ቆሞ ቤት አይሰራም! ማገር ያስፈልገዋል፡፡ ህዝብም ብቻውን ሀገር አይሆንም፡፡ አንድነትን የሚጠብቁ ካስማዎች ያስፈልጉታል፡፡ የዚች ሀገር ካስማዎች እነ ቴዎድሮስ፣ እነ ሚኒሊክ አሁን የሉም፡፡ አንተ እነሱን መሆን አትችልም? ራዕያቸውን ብትጋራ ግን እነሱን ትተካቸዋለህ፡፡ እነሱን ለመተካት ደግሞ ግዴታ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መሆን አይጠበቅብህም!.....›› (ቃለ ዲዲሞስ፣ ዴርቶጋዳ) @amba88
نمایش همه...
የሰውን ፍጥረት ገል አፈር፤ሸክላ አብዝቶ ይመስለዋል! ሸክላውም ካፈር ይጸነሳል፤ቅርጹን ይዞ ይወለዳል ፤ በሳት እየተፈተነ በብቃት ያድጋል ፤ ለራሱ ኖሮ ሌሎችን ሲያበላና ሲያጠጣ ይቆያል ፤ ከዛም ባንዲቷ ዕለት በእርጅናም ሆነ በድንገት ተሰብሮ ወደ ታነጸበት ግብዓት ይመለሳል!!! ግን በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ሕሊና ፤ በራስ መመራት ፤ ለውጥ እና የመሰሉት ነገሮች ይገኙበታል። ያ ደግሞ በሰውነት ጸንቶ ለመቆም ዋናው መሠረት ነው። ታዲያ ስንቶቻችን እንሆን ራሳችንን ምናዳምጠው? ስንቶቻችን እንሆን በስሜት ሳይሆን በማመዛዘን የሕሊናችንን ልክነት የምንገልጠው? ስንቶቻችን እንሆን በተገቢው ሕይወት ውስጥ የምንገኝ???
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
• ልጅ ዮናታን ሙሴ /ኪያ ይባላል ‼️ ገና በልጅ እድሜው ነበር , ሚስኪን ደሀ እናቱን ለመርዳት በዲሽ ስራ ተሰማርቶ ሲያግዛት የነበረው ! ዛሬ ላይ ግን ይሄ ገና የ 18 አመት ህፃን አልቻለም ! የነበረበት የስኳር ህመም ተባብሶ ሁለቱ ኩላሊቶቹ Fail አስደርገውበታል ! ይባሱን ብሎም ሁለቱ አይኖቹን እየጋረደበት ጭምር ለኩላሊት እጥበት እንኳን ብር አጥቶ በጣም በስቃይ ላይ ይገኛል ! • ወዳጄ ምትጠቀመው Telegram ' youtube ' Tiktok ' facebook ይሄን መረጃ ለማድረስ /SHARE ለማድረግ ለመረዳዳት እንኳን ካልሆነ ብተወው ነው ሚሻልህ ‼️ • በቻልነው እንረዳዳ ! ለመልካምነት ሰአት አይመረጥም ! ላንተ ትንሽ ምትለው ለሌላው የህይወት ዋጋ አለው ! እባካችሁን ለመልካምነት 1 ጊዜ እንኳን አናመንታ ! • የቻልነውን እናድርግ የሀገሬ ልጆች " ሀዘኔታ ብቻውን አያድነውም ! 1000114377388 - ገነት ሀይሉ የእናቱ Bank Ac ነው ! 0941561516 - የእናቱ ስልክ ነው ‼️
نمایش همه...
በዕንባቸው ጠብታ ውስጥ መልካቸውን ይመለከቱ ነበር.. "...ከዚህ በፊት ሰዎች ፊታቸውን በመስታወት ተመልክተውት አያውቅም ነበር። ከዛ በፊት... ጦረኞች በጦራቸው ፍላፃ ውስጥ መልካቸውን ይመለከቱ ነበር። ሴቶች በገንቧቸው ውስጥ ወይም ውሃ በሚቀዱበት ሻንኩራ ውስጥ ቁልጭ ቁልጭ የሚለውን ፊታቸውን ይመለከቱ ነበር። የወለዱትም በልጆቻቸው ዓይን ውስጥ ዓይናቸውን ይመለከቱ ነበር። የተገፉትም ሰዎች በዕንባቸው ጠብታ ውስጥ መልካቸውን ይመለከቱ ነበር።... ዛምራ (ይስማዕከ ወርቁ ገፅ 33-34) @leywo
نمایش همه...