ግጥም
رفتن به کانال در Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
نمایش بیشتر5 645
مشترکین
+324 ساعت
+267 روز
+11930 روز
آرشیو پست ها
5 648
አሁን dogs ከፍሎናል። ቀጣዩ የሚሆነው ደግሞ #cats ነው።
ከአሁኑ ብትሰሩት ጥሩ ነው። ባለፈው ኖት ኮይን ቻናላቸው ላይ cats ወይስ dogs ብለው መፖሰታቸው ራሱ ሁለቱም ትልቅ ፕሮጀክት መሆናቸው ማሳያ ነው። አሁን የcats ተጠቃሚ ከ6 ሚልዮን በላይ አልፏል።
premarket ተጀምሯል። እንዲሁም ከሀምስተር ቀድሞ ሊስት እንደሚደረግ ተገምቷል። ጀምሩት
ለመጀመር 👉
t.me/catsgang_bot/join?startapp=6iSPwHBPIOWUBANt-AngK
5 648
እንዴው ያንተ ስራ እንዴው ያንተ ነገር
ምን ቃል ይገልጸዋል ከመደነቅ በቀር
አበቃልህ ሲለኝ ሰይጣን በሹክሹክታ
ፈጥነህ ትደርሳለህ እኔ እንደበረታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
#ጥላችን_አይደለም
በህይወት ጎዳና ፈጥነን ስንራመድ
ወይም በዝግታ በሀሳብ ስንሄድ
ስንቆም የሚቆመው ሲመሽ የማናየው
ጥላችን አይደለም ለካስ ሞታችን ነው!
የሚከታተለን በእርምጃችን መጠን
ስንፈጥን ስንዘገይ ሁሌ ሚከተለን
ጥላችን አይደለም የምስላችን ቅኔ
ሞታችን ነው ባይ ነኝ እንደገባኝ እኔ
ሲመሽ ተደብቆ ሲነጋ ተገልጦ
ስንተኛ ተኝቶ ስንሮጥ እሮጦ
የያዝነውን ይዞ ስንበላ በልቶ
ሁልግዜም አብሮን ነው ሞታችን አድብቶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
ሰላም ሰላም እንኳን ወደ ከእለታት channal በሰላም መጣችው በዚ channel ላይ የተለዩ አስተማሪና አስፈላጊ ከማንኛውም ሁኔታ መንጭቀው አውጥተው ወደ ራሳችን እንድናይና ቀና እንድንል የሚያደርጉ ፅሁፎች ይለቀቃሉ....
Join👉 https://t.me/shewitdorka
5 648
በቅን ሰው ልቦና በቅን ሰው አንደበት
ሲነገር ደስ ይላል ማርማር ይላል እውነት
በአስመሳዮች ምላስ መሀላ ሲሰደር
ሀሰት መሆኑን ነው የሌለው ቁምነገር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
በዚህ እድሜዬ ይሄ ቢገባኝ ብላ የምትፀፀትበት ነገር አለመኖሩ እጅጉን ይገርመኛል፣ ሰው እንዴት ቀድሜ ቢገባኝ ኖሮ ይሄ አይፈጠርም ነበር ብሎ ራሱን አይወቅስም?
ሀሴት እንደዚ ናት
አመለካከቷ፣ የልጅ አዋቂነቷ፣ ሀሳቧ ሁሌ ይገርመኛል ፣ ህይወቷን በቁጭት አትመራም ፣ አሁንን መኖር ከሁሉ ይበልጣል ሁሌ ትላለች፣
ያለፈው ስህተቴን ቀድሜ ባውቀው ኖሮ ምናልባት አሁን ላይ የህይወት አቅጣጫዬ ይዞር ነበር
ሁሉን ነገር በማወቅ ነው ምንረዳው ፣ ራስን ላጠፉት ነገር መውቀስ ትርፋ የህሊና ህመም ነው፣ ሁሉን ነገር እንድናውቅ አድርገን አልተሰራንም ፣ በመኖር ነው ምንረዳው፣ እኛን ያልነበሩ ጊዜዎች ላይ መንጠልጠል ትርጉም አልባ ነው፣ የሁሉም ጊዜያት ጀግና መሆን አይቻልም ትላለች
ክፋ ያላየ የሚመስለው ፈገግታዋን እያሳየች...
https://t.me/tenqesha43
5 648
በዚህ እድሜዬ ይሄ ቢገባኝ ብላ የምትፀፀትበት ነገር አለመኖሩ እጅጉን ይገርመኛል፣ ሰው እንዴት ቀድሜ ቢገባኝ ኖሮ ይሄ አይፈጠርም ነበር ብሎ ራሱን አይወቅስም?
ሀሴት እንደዚ ናት
አመለካከቷ፣ የልጅ አዋቂነቷ፣ ሀሳቧ ሁሌ ይገርመኛል ፣ ህይወቷን በቁጭት አትመራም ፣ አሁንን መኖር ከሁሉ ይበልጣል ሁሌ ትላለች፣
ያለፈው ስህተቴን ቀድሜ ባውቀው ኖሮ ምናልባት አሁን ላይ የህይወት አቅጣጫዬ ይዞር ነበር
ሁሉን ነገር በማወቅ ነው ምንረዳው ፣ ራስን ላጠፉት ነገር መውቀስ ትርፋ የህሊና ህመም ነው፣ ሁሉን ነገር እንድናውቅ አድርገን አልተሰራንም ፣ በመኖር ነው ምንረዳው፣ እኛን ያልነበሩ ጊዜዎች ላይ መንጠልጠል ትርጉም አልባ ነው፣ የሁሉም ጊዜያት ጀግና መሆን አይቻልም ትላለች
ክፋ ያላየ የሚመስለው ፈገግታዋን እያሳየች...
@tenqesha43
@eliyasshitahun
5 648
#የጠላ_ስባቱ
አንቺው ጠላ ጠምቀሽ አስክረሽ አስክረሽ
ትዳር ስጠይቅሽ ሰካራም አልወድም ለምን ትይኛለሽ?
የቀመምሽው አንቺ በብቅል በጌሾ
ሰካራም አይደለም ለካ አንቺ ነሽ ዋሾ
እርሱማ ይጠጣል የልቡን ሊናገር
ሰካራም ከሌለ መች ታምራለች ሀገር
ማስከር አይደለም ወይ የጠላ ስባቱ
አጠማመቅሽ ነው ያሶደደሽ እቱ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
ስለ fintopio የተወሰነ ማብራሪያ እና እንዴት መስራት እንችላለን የሚለውን ያላያችሁ ልጆች በዚህ ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ
እንዲሁም በአሁኑ ዙር የወርሀዊ ውድድር አራት ኢትዮጵያዊ ከ 1-50 ውስጥ መመልከት ችያለሁ በርቱ በዚህ ዙር ሁሉም ተፎካክሮ ማሸነፍ አለበት
እንዲሁም fintoopio ባለንበት ደረጃ token እየሰጠ ነው እና check አድርጉ
ለመጀመር 👉 https://fintop.io/77iZhSV
5 648
ስለ fintopio የተወሰነ ማብራሪያ እና እንዴት መስራት እንችላለን የሚለውን ያላያችሁ ልጆች በዚህ ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ
እንዲሁም በአሁኑ ዙር የወርሀዊ ውድድር አራት ኢትዮጵያዊ ከ 1-50 ውስጥ መመልከት ችያለሁ በርቱ በዚህ ዙር ሁሉም ተፎካክሮ ማሸነፍ አለበት
እንዲሁም fintoopio ባለንበት ደረጃ token እየሰጠ ነው እና check አድርጉ
ለመጀመር 👉 https://fintop.io/77iZhSV
5 648
ግዜ አንደበት ኖሮት ብሶቱን ቢናገር
ተበዳይ በሰው ልጅ እኔ ነኝ ይል ነበር
እራሳቸው ከፍተው ዘመን ለሚከሱ
ሰው ነው ተጠያቂ ነበር ግዜ መልሱ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
#ምኑንስ_ተኖረ
እንቅልፍ አልባ ሌሊት
ትርጉም የለሽ ህይወት
መግፋት ቢሰለቸኝ ዋ! አልኩ ለራሴ
ግራ ብትጋባ ብትጨነቅ ነፍሴ
ድሃ እንቅልፍ አግኝቶ ህልምን ካላለመ
ህይወት ትርጉም አጥታ ቀኑ ከጨለመ
ምኑንሰ ተኖረ ተመስገን ተብሎ
ነገን ለመናፈቅ የዛሬን አቅልሎ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
የዲጂታሉ ዓለም ልብን ተቆጣጥሮ
መነጋገር ቀረ ሰው ከሰው ጋራ አብሮ
ህሊናችን ዛሬ መርጦ ብቼኝነት
ማንም ከማን አይደል ቢኖርም አንድ ቤት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
#ተፈጥሮም_ያኮርፋል
በእኔና አንቺ ፍቅር ሲታጀብ የኖረው
ድንገት ብንቀርበት ጭር አለ ጎዳናው
አብረን ያረፍንበት ተቃቅፈን ያን ግዜ
ልማዱን ነፍገነው ውጦታል ትካዜ
የእኛ መኮራረፍ እንኳን ለኛ ቀርቶ
መርዶ ሆኖበታል ጎዳናው ተከፍቶ
በኔና አንቺ ኩርፊያ ተፈጥሮም ያኮርፋል
ከሰው በላይ አውቆን ከልቡ ለምዶናል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
#ወፊቷን_በሆንኩኝ!!
በራሴ ችሎታ ቤቴን በሳር ሰሪ
ሳልዘራ ሳላጭድ ቀለቤን ሰፋሪ
በእግዚአብሔር ቸርነት ሳልጨነቅ ነዋሪ
ወፊቷን በሆንኩኝ በሰማይ በራሪ!!!
ዶላር ሰማይ ነክቶ ብር መሬት ወድቆ
እያሉ ከመኖር በሁሉም ተጨንቆ
ምነው ወፍ በሆንኩኝ ከዛፍ ዛፍ በራሪ
ቀለብ የማይጨንቀኝ ቤቴን ብቻ ሰሪ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
ዛሬ በሰው ችግር በግፍ የምትስቁ
ቀን መጣሉ አይቀርም ይህነን እወቁ
ሞልቶልኛል ብሎ በጎደለው መሳቅ
አወይ ነገን መርሳት ወየው አለማወቅ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
