fa
Feedback
ግጥም

ግጥም

رفتن به کانال در Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

نمایش بیشتر
4 785
مشترکین
+1424 ساعت
+437 روز
+22830 روز
آرشیو پست ها
#ስጠብቅሽ_ልኑር! ቀናቶች ቢረዝሙ ቢቆጠሩ አመታት ግዜ ቢለያየን ቢያልፉብን ዘመናት ከልብሽ ባልጠፋም ከትዉስታሽ ጓዳ በስቃይ ታስሬ በናፍቆት ጎዳና ህልሜም ባይሳካ የሆዴን ባላገኝ በደስታየ ዘመን ባይተዋር ቢያረገኝ ግዴለም ችላለሁ ሁሉን ነገር ችዬ እጠብቅሻለሁ ልቤን አባብየ የሀሳብ በረዶ ይጥለቅ በአናቴ ይደንዝዝ አካሌ ይድከሙ ጉልበቴ አንገናኛለን እያልኩ በተስፋ ልጠብቅ እልፍ ግዜ ይለፍ ወዜ ሁሉ ይድቀቅ ምን ያደርግልኛል ካንች ወድያ ንሮ ፍቅርሽ ይበቃኛል የስንቅሽ ቋጠሮ በትዝታሽ ዋሻ እራሴን ደብቄ በምናቤ ስየ ፍቅርሽን ሰንቄ እጠብቅሻለሁ በተሰጠኝ እድሜ ባንች ናፍቆት ፍቅር ካልሞትኩኝ ታምሜ አዎ...ስጠብቅሽ ልኑር ሳለሁ በህይዎቴ ፍቅርም ባንች ይብቃኝ ይምከን ፍላጎቴ፡፡         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ቢታነፅ_ቢወቀር! እኔም አንድ ሰሞን ልክ እንደ ሰለሞን "ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል" እያልሁ አጨልሜ በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር! ከዚያ አንቺን አገኘሁ በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ መፈጠሬን ወደድሁ ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ "ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ! ለካስ... ጠቢብ ቢያስተምረው መከራ ቢመክረው አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር!         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ በእውቀቱ ስዩም

መልካም በዓል! ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ቃና.... ከዉበት እስረኞች... ጥቁር ፍቅር ይዞኝ በንስር አይኖቼ... ፍለጋ ጀመርኩኝ የጠፋዉን ስሜን... ልመልስ አልኩና ማጣጣም ስጀምር.. የህይወቴን ቃና ለኔ ወጥመድ ሁነዉ... ዛራና ቻንድራ ሚስቴ ጋር አጣሉኝ... ማን ያቅርብ እንጀራ.....         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#አንተም_እኔም_ተጓዥ አትግፋኝ ወንድሜ ፣ በከንቱ ጥላቻ፤ ለየትኛው እድሜ ? እንኑር በጡንቻ? ለኮንትራት ዓለም ፣ ባለቤት ለሌላት፤ ከፍቅር ቀንሰን የምን? መገፋፋት ? አንተም እኔም ተጓዥ ፣ በተራ ለጣቂ፤ ማን እንደሚቀድም ፣ አምላክ ነው አዋቂ ። ስትገፋኝ ስገፋህ ፣ አንዱ ላያሸንፍ፤ መጓተት ብቻ ነው ፣ ሌላ የለንም ትርፍ ። ለፍቅርም አይበቃ ፣ የተሰጠን አድሜ፤ እኔም ነኝ ወንድምህ ፣ አንተም ነህ ወንድሜ።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

#ልቤን_መልስልኝ ልትሄድ  ከሆነ  ላይቀር  መለየቱ ቢበቃኝ  ይሻላል  ባንተ  መጎዳቱ። ቀልብህ  ካላረፈ  እግረኛ  ሆነህ መጓዝህ  ካልቀረ  ከእኔ  መራቅህ ለምን  አስፈለገ  ልቤን  መስረቅህ?         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ወዴት_ተሰወሩ? በሳቃችን ዘመን አብረውን የሳቁ፣ ከእናንተ ውጪ ብለው ትላንት ያደነቁ፣ ሳቃችን ሲጠፋ መከራችን ነግሶ፣ በእህ! እህ! ሲተካ በሀዘን በለቅሶ፣ ወዴት ተሰወሩ? ምንስ ከለላቸው? የትኛው ተራራ የትኛውስ እርቀት ገዝፎ ጋረዳቸው ? በዙሪያችን ከበው በክብር ሸልመው፣ በንግግራችን ፣ በማያስቅ ስቀው! ለጥቅማቸው ሲሉ ትላንት ያገጠጡ መካራ ሲገጥመን ወዴት? ፈረጠጡ?! የሉም፣ አይታዩም! ምን ጉድጓድ ዋጣቸው?! የትኛውስ እርቀት ከእኛ ሰውራቸው? የሉም! የሉም! በቃ ዛሬ የሉም! ሳቃችን ከጠፋ ከቶ አይመለሱም!!          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

#ውሻ_ነበር_ያልሽኝ? ቃል ኪዳን ጠብቄ ለእምነቴ መኖሬን፣ ከራሴ ሰስቼ ላንች መታመኔን፣ ስትመሰክሪልኝ......! አቻ በሌላቸው በሁለት ቃላቶች፣ ስሜን ከፍ  አ'ረግሽው ውሻ ብለሽ ጠርተሽ። ላንች ውሻ ማለት ስድብ ቢመስልሽም፣ ማክበር እንደሆነ ፈፅሞ አልገባሽም። አዎ እኔ ውሻ ነኝ........! ጊዜ አይቼ ምቀርብ ድመት አይደለሁም፣ ለመጣ ለሄደው ጅራቴን አልቆላም። ቀዘቀዘ ብዬ ቤቴን አልቀይርም፣ ሲሰጡኝ ወድጄ ሲነሱኝ አልጠላም። አዎ እኔ ውሻ ነኝ...........።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ሀዘኑ_መች_ጠፋ!!! ማልቀስ አምሮኝ ነበር እንባ ከየት መጥቶ ሐዘን በልቤ ውስጥ ተርፎ ተከማችቶ ከዚህ ሁሉ ሀዘን በዝቶ ከተረፈው አንዲት ጠብታ እንባ ይቸግረዋል ሰው እባክህ እንባዬ መንታ ሆነህ ፍሰስ የታመቀው ውስጤ በጥቂት ይተንፍስ ሀዘኑ መች ጠፋ ከልባችን ጓዳ የራቀን ዘንድሮ እንባችን ነው ባዳ         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

በሔድክበት መንገድ አይኔን ጣል አድርጌ   በትዝታ መርከብ በሀሳብ ቀዝፌ አተን እያሰብኩኝ ጉጬን ተደግፌ እየጠበኩህ ነው         ትዛለህ ? ትተኸኝ ስትሔድ      እዳትከተይኝ ደግመሽ እዳትመጪ በሔድኩበት መንገድ       ብለኸኝ ስትሔድ ስላስጠነከከኝ እዳልከተልህ አሳስቶኝ እኳን ዞሬም እዳላይህ    ቃልህን አክብሬ አልተከተልኩህም    ባለህበት ቦታ ፍፁም አልመጣሁም     ነገር ግን  እጠብቅሀለሁ አለሁኝ እዛው  ነኝ  እጠብቅሀለሁ ሳልሆን እራስ ወዳድ ምናልባት ከመጣህ በሔድክበት መንገድ አይኔን ጣል አድርጌ   በትዝታ መርከብ በሀሳብ ቀዝፌ አተን እያሰብኩኝ ጉጬን ተደግፌ እጠብቅሀለሁ   በትዝታ መርከብ በሀሳብ ቀዝፌ እየጠበኩህ ነው ጉጬን ተደግፌ         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#አንድ_እንባ_ለሁለት_ስሜት ለሀዘን ለደስታ የእንባ ቋጠሮ ሲፈታ ከሁለት አይኖች ለሁለት ስሜት ለማዘን ወይ ለመደሰት በሳቅ ታጅቦ ወይም በለቅሶ በመንታ ጉንጮች ቁልቁል ፈስሶ ለመለያየት ለመገናኘት ብሶት ለመግለጽ ወይ ደስታ በሁለት ስሜት የሚምታታ እንባ አንድ ነው ግን ሁለት ስሜት በሀዘንም በደስታም " ና " ብለው የሚጠሩት።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

#እንዴት_ይሆን_ፍርድሽ? ጥቂት ታገሽ ሆዴ መንገዱን አሳብረሽ ማዶ ማዶ እያየሽ ብቻ ተስፋ አትቁረጭ ቁጭብለሽ ጠብቂኝ እንዳትሄጅ ተናደሽ እርሜን አረፈድኩኝ አንድ መሪ መ'ቶ መንገድ ተዘጋግቶ ወደዚ ሂድ ሲሉት ወደዛ ተመለስ ህዝቤ ተሰላችቶ ተስፋ ቆርጦ ሳለ እኔ ግን የኔ ማር ካንቺ ተቃጥሬ እንዴት እቀራለው ልሂድ ብዬ በግሬ እየመጣሁኝ ነው ፍቅርሽ ጉልበት ሆኖኝ ለመድረስ አንቺጋ አይንሽን ካላየሁ ነብሴም እረፍት የላት መንፈንፈሴም አትረጋ አይዞሽ የኔ ቆንጆ አልቀርም አልቀርም ጥቂት እንደሮጥኩኝ ቁሙ ባላቹበት ተብለን ብንቆምም ልቤ እየሮጠች ነው በፍፁም አታርፍም አቤት ክፉ ጊዜ አይ የቀን ጎዶሎ ባልጠበቅነው መንገድ ባላሰብነው ውሎ ደውዬ እንዳልነግርሽ ተዘግቷል ኔትዎርኩ አልበር እንዳሞራ ለዚህ አልታደልኩ አወይ የኔ ፍቅር ለጠባቂ ሴኮንድ ከሰአት በላይ ነው ይህንን አውቃለው ደቂቃ ዘግይተሽ በቀናት አስልቼም ተቆጥቼሻለው ብቻ የኔ አበባ ምን አሰበ ይሆን ምን ወሰነ ልብሽ ? ለጠዋት ቀጠሮ ማታም ሳልደርስልሽ በቃሽ የኔ ነገር ? ጠላሺኝ ወዳጄ እንዴት ይሆን ፍርድሽ ለቀረሁ ታግጄ ???         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#መልክአ_ሕይወት ቧልትን ከፈገግታ ሳቅን ከፌዝ ጋራ ባንድ ላይ ቀይጠን፥ አቅልመን በጥብጠን በሐዘን ባሕር ላይ ፥ ብናንቆረቁርም ባሕሩ ሰፊ ነው፤ መልኩን አይቀይርም::         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በእውቀቱ ስዩም

FRESH mek money በጥሩ ገንዘብ ማድረግ መንገድ ይፈልጋሉ? እዚህ በአጭር ጊዜ የሚሰጡ ምክሮች, ማስተላለፊያዎች እና ፍላጎቶች ናቸው። ቅድሚያ፡ ዕቅድ, ትኩረት, ስራ እና ተመን ከፍ ማድረግ!
FRESH mek money በጥሩ ገንዘብ ማድረግ መንገድ ይፈልጋሉ? እዚህ በአጭር ጊዜ የሚሰጡ ምክሮች, ማስተላለፊያዎች እና ፍላጎቶች ናቸው። ቅድሚያ፡ ዕቅድ, ትኩረት, ስራ እና ተመን ከፍ ማድረግ! 🔥 እንዴት ገንዘብ መፍጠር ትችላለህ? 💰 መነሻ 🚀 #ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች

የአደይ ድራማን ማግኘት ተስፋ ይቆምበታል? ሙሉ ክፍልና በጥራት የተሞሉ አዲስ እና ተወዳጅ አደይ ድራማዎች በዚህ ቻናል ብቻ! አዲስ ክፍሎችን ፈጣን በፈጣን በቴሌግራም በመመልከት ይችላሉ። አትሳኑ፣ አ
የአደይ ድራማን ማግኘት ተስፋ ይቆምበታል? ሙሉ ክፍልና በጥራት የተሞሉ አዲስ እና ተወዳጅ አደይ ድራማዎች በዚህ ቻናል ብቻ! አዲስ ክፍሎችን ፈጣን በፈጣን በቴሌግራም በመመልከት ይችላሉ። አትሳኑ፣ አሁኑኑ ይቀላቀሉ! #ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች

“1 ቀን ያህል ፈቃድ ያለው ነገር አለ? እኔ የገና አውቅልኝ፣ 00 ብር እንዴት ነው? መረዳት የምትፈልጉት አሁን አልቅሱ #ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች.
“1 ቀን ያህል ፈቃድ ያለው ነገር አለ? እኔ የገና አውቅልኝ፣ 00 ብር እንዴት ነው? መረዳት የምትፈልጉት አሁን አልቅሱ #ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች.

2018 የመግቢያ ፈተና ተሰፍተው? አንዴ የሚሰጥ የእሳት ፈተና ነው! ሰዓት ማጣት አትፈልጉ፡ መደበኛ የትምህርት ፕሮግራሞች፣ አስተማማኝ የፈተና ቅጅዎች፣ እና ድሆነታችሁን የሚቀድሙ መቻል በዚህ ላይ
2018 የመግቢያ ፈተና ተሰፍተው? አንዴ የሚሰጥ የእሳት ፈተና ነው! ሰዓት ማጣት አትፈልጉ፡ መደበኛ የትምህርት ፕሮግራሞች፣ አስተማማኝ የፈተና ቅጅዎች፣ እና ድሆነታችሁን የሚቀድሙ መቻል በዚህ ላይ ጠቃሚ ነዋ! አሁኑኑ ተመዝገቡ፣ ፈተናዎን ከጀመሩበት ይቅረቡ። #ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች

⚡️ Oroshop_seller_buyer በቀጥታ ያግኙ ⚡️ በዚህ ጣቢያ የዲጂታል አገልግሎቶች ሁሉ በቀላሉ እና በፍጥነት ይገኛሉ። ፍላጎት, መረጃ, እና ሙሉ እርዳታ - ከአንድ ቦታ በላይ ይሁን። 📲
⚡️ Oroshop_seller_buyer በቀጥታ ያግኙ ⚡️ በዚህ ጣቢያ የዲጂታል አገልግሎቶች ሁሉ በቀላሉ እና በፍጥነት ይገኛሉ። ፍላጎት, መረጃ, እና ሙሉ እርዳታ - ከአንድ ቦታ በላይ ይሁን። 📲 ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ፣ የሚያስፈልግ እቃ፣ የተለያዩ አገልግሎቶች። ✔️ ፈጣን እና ቀላል መግኘት። ⏳ የህይወትዎን ቀን ለቀጥታ አድርጉ። 💡 ለሙሉ እይታ እና አግኝተው ለመሆን እዚህ ጫነው 🚀 #ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች.

The Word Lab ቋንቋን እና አለምን በአስደናቂ የትምህርት ዕውቀት ያዩ። ቀላል ትምህርቶች, ምንጭ እና ጥንቃቄ ምክሮች፣ ትንሽ ማዕከላዊ ሐሳብ ያሉት ነገሮች ለመማር በግልፅ ሁኔታ ሁሉንም ይዘዋል
The Word Lab ቋንቋን እና አለምን በአስደናቂ የትምህርት ዕውቀት ያዩ። ቀላል ትምህርቶች, ምንጭ እና ጥንቃቄ ምክሮች፣ ትንሽ ማዕከላዊ ሐሳብ ያሉት ነገሮች ለመማር በግልፅ ሁኔታ ሁሉንም ይዘዋል። 🤓 ትንሽ ቀውስ፣ ማጠቃለያ፣ አስፈላጊ ቃላት፣ እና ማሰተኛ አሰሳ — ለቋንቋው ፍላጎት እርስዎን በማቀናበር ይጠቅመዋል። በእርግጥ ለመጀመር ዛሬ የትምህርት አሰሳ እንደት ነው? 📚 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይጎብኙ ✨ #ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች