fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ግጥም

ግጥም

رفتن به کانال در Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

نمایش بیشتر
5 623
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+97 روز
+12030 روز
آرشیو پست ها
#አልሞትም ስሚ እኔ በዚህ አለም ፤ብዙ ብሰቃይም አንድ ሀሙስ የቀረዉ ፤መስየ ብታይም አምሮቴን ሳላገኝ ፣ ሱሴን ሳላከትም ከመሬት ከርስ ዉስጥ ፤ ገላየን አልከትም አልሞትም ማንም ባልደፈረዉ መንገድ ሳላከትም እንደ ንጉስ አይዙር ግማሽ ቀን ሳልነግስ በጠገበዉ ሳልስቅ፣ለራበዉ ሳልደግስ አልሞትም ዝማሜን ሳላዉቅ ያንደበቴን ግድብ ዙፋን ላይ ሳልሸና ጌቶችን ሳልሰድብ ከድሀዉ ሳላብር ካገሬዉ ሳልወግን ከምድር በረከት ድርሻየን ሳልዘግን አልሞትም ስሚ ልቤ እንደምኞቱ ቢያገኝ እንደምርጫዉ ያላማየ ማብቂያ አንቺ ነሽ መቋጫው እና አገሬን ለቅቄ ልብሽ ላይ ሳልከትም በዉብ ከንፈርሽ ላይ ከንፈሬን ሳላትም አልሞትም።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ በእዉቀቱ ስዩም

#ተመኘሁሽ እንዳሁኑ ሳይሆን፣ የተፈጥሮ ዉበት መዓዛ ጠረኑን፣ ሁሉን ወሰድሽበት በራስሽ ወዘና፣ሁሌም የምትፈኪዉ ቻፕስቲክ፣ሊፕስቲክ፣ኮስሞቲክስ ማታዉቂዉ የት ሄድሽ ሄዋኔ.....???! ፍቅርን ባንደበትሽ፣ የማታስመስይዉ ከልብሽ የሚፈልቅ፣ፈገግታ ምትቸሪዉ የተጠና ቃላት፥ከአፍሽ የማይወጣ ገና በዓይን ጥቅሻ፥ቀልቤን በአንችማጣ እኔ እኮ እንደዚህ ነኝ፥ብለሽ ማትፎክሪ በገፅሽ ድንቅ ፀዳል፥ከሩቅ የምትጠሪ ፀባይና ዉበት፣የተሰጠሽ ላንቺ በሁሉ ነገርሽ፣ለሰዉ ምትመቺ የት ሄድሽብኝ  ሄዋኔ.....???! ካለሽበት ልምጣ፣ አንዴ ተዋወቂኝ ሁለንተናነትሽን፣ ባክሽ ለእኔ ስጭኝ የምትፈልጊዉን፣አይነት ወንድ ልሁንልሽ የእኔ መሆንሽን ልወቅ፣ብቸኛ አልሁንብሽ ካንች ጋራ ሁኘ ፣  ፍቅርን ላጣጥመዉ ያለሽበት ቦታ፣መገኛሽ ከየት ነዉ..???!!     'ካሁኑ ናፈቅሽኝ'         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ       ✍🏽 B.J

#ሰው_ማልመድ_ይከብዳል! ሰው ማመን ብጀምር አምናን እረስቼ፣ የደረሰብኝን ሁሉንም ዘንግቼ፣ ዘንድሮም ደገመኝ ጣለኝ ሰው ማመኔ፣ እኔም አልተማርኩኝ ወይ አልል ለምኔ፣ ጀርባ ይሰጡኛል ፊት ግን ይነሱኛል፣ ልቤን ይሰብሩና ፈጥነው ይርቁኛል፣ ሳልጠራቸው መጥተው ተመልሰው ሄዱ፣ እነ ወረት ዜማው መርጋት መች ለመዱ፣ ለካስ መስሎኝ ነበር እኔ የምገፋቸው፣ ከጀርባ በመቆም የወዘወዝኳቸው፣ እነርሱ ዘንድሮም አይረጋ ልባቸው፣ ለቅቤ የማይደርሱ የቸኮሉ ናቸው፣ ሳይላኩ ወዴት፣ ሳይጠሩም አቤት፣ ብለው ይመጡና ሄዱ ሳይሸኙ፣ እንደጠዋት ጤዛ ቀን ላይ ላይገኙ፣ እኔስ መስሎኝ ነበር ሰው ማልመድ ያቃተኝ፣ እንደቀትር ጥላ ስቀርብ በመራቅ ስርቀው ቢቀርበኝ፣ እንኳን እኔ ፍጡር ተፈጣሪን ላለምድ፣ ልባችን ደንድኗል ፈጣሪ እንኳን ቢወርድ፣ ሰው አልምድ አትበሉኝ ሰው ማልመድ፣ ይከብዳል፣ አንድ ክንድ ሲቀርቡት አርባ ክንድ ይርቃል!!!         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

#አይደለም_ምኞቴ… ባገኘሁት ሰበብ እጭንሽ ስር መግባት መጭመቅ ዳሌና ባት ነፍስያን ጨቁኖ በስሜት መግባባት፤ አይደለም ምኞቴ…. እንደ ኮርማ በሬ እላይሽ ላይ መውጣት ፍትወቴን ማስታገስ ግለቴን መወጣት እነዚህን ሁሉ … አላስብም ጭራሽ አላስብም ቅንጣት፤ ልንገርሽ አይደለ? የመንፈሴን መሻት የልቤን መመኘት ከነፍስሽ ዜማ ጋ ዜማየን መቃኘት፤ የደማ ስሜቴን … በሀሳቦችሽ ማከም በቃሎችሽ መግራት ከጎንሸ ቁጭ ብዬ… ምትዪኝን መስማት ሚሰማኝን ማውራት፤ አየሽ … ካካላችን በፊት ነፍሳችን ከጋለ ከልባችን ግድም ፍቅር ከበቀለ አልስገበገብም … ገላሽ ላይ ደርሳለሁ ገላሽ ሁሌም አለ! አዎ … አስገድጄሽ ሳይሆን ፤ ፍቅሬ አሸንፎሽ ገላሽን ስትሰጪኝ ያኔ ነው እንደ ማር የምትጣፍጪኝ!         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ እዮብ ዘ ማርያም መነሻ ሀሳብ :- በዕውቀቱ ስዩም!

#ልንገርሽ_ጨረቃ በገጣሚ ብዕር በስንኝ ቋጠሮ በዜማ ቀማሪ በድምጽ እንጉርጉሮ እየተሞላቀቅሽ በአፍቃሪ ደብዳቤ በሰአሊ ቀለም በሸራ ላይ ድቤ አሞጋሽ ሲበዛ በስምሽ ዘማሪ ፀሀይ ልሁን አትበይ ጨረቃ ተይ ፍሪ ደራሲ ነው እንጂ ብዕር አንጠፍጥፎ በሰው ህሊና ላይ ያተመሽ አግዝፎ ሰአሊው ነው እንጂ ውበትሽን አድምቆ የሌለሽ ማንነት ከፀሀይ ላይ ሰርቆ ገጣሚ ነው እንጂ በስንኝ ቋጠሮ ዜመኛው በዋሽንት በድምጽ እንጉርጉሮ አንቺን ያገዘፉሽ በሌለሽ ከፍታ በምናብ አስውበው በፍቅረኞች ኩታ የተራ ተራ ነሽ ልንገርሽ ጨረቃ ፀሀይ ትበልጣለች እጅግ ብዙ ልቃ በአሞጋሽ ግርግር በዘፋኝ እስክስታ በጨለማ አድናቂ ሲሰጥሽ ከፍታ ፀሀይ ነኝ አትበይ አቅምሽን እወቂ በሰው ህሊና ላይ ገዝፈሽ አትድመቂ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

"ከጎራው ዘልቄ ፣ እስኪ ልነጋገር ያለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር ሕንጻ መች ሆነና ፣ የድንጋይ ክምር የእኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና ፣ የድንጋይ አጥር የእኔ ውብ ከተማ ፣ የእኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ ፣ የሌለው ድንበር ሕንጻው ምን ቢረዝም ፣ ምን ቢጸዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ፣ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው ሰው ካልሸተተ ፣ ምንድን ነው ውበቱ ?"         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በዓሉ ግርማ

#ታገስ_ተስፋ_አትቁረጥ እኩል ተሰልፎ ከብርቱካን ማሳ እንቧይ ከደረሰው እጣውን ሲያነሳ ፈተናው ነውና የህይወት ጎዳና ሌላ እጣ መሞከር መፋቅ እንደገና እንቧይ በማግኘቱ ህይወትን ከመርገም ነገን እያሰበ  ተግቶ መደጋገም ዛሬ በሞከረው ነገን ከማጨለም ሌላ ሰልፍ ፈልጎ እድልን ማለምለም ለወርቅ ተሰልፎ መዳብ የወሰደ ተስፋውን ሰንቆ እየተራመደ በትጋት ጎዳና ዘወትር የሚተጋ አይቀርም ይወስዳል አለው የወርቅ ዋጋ ግዜው ሊያስተምረው መዳብ እየሰጠ የትግስቱን ውጤት በእንቁ እየለወጠ የጥረቱን ፍሬ ያጭዳል አዝመራውን ዛሬን በመታገስ ከሰራ ነገውን!!!         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

#አትፅናኝ ሞትን አንመልሰዉ፣ እናውቃለን አይሸሽ ስንት ጥፍራም ኀዘን አይተናል መሰለሽ! ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማቀይር አምነን ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤ ዳሩ ታውቂዋለሽ። አቀጣጡ ክፋት፤ አመጣጡ ም‘ፃት፤ ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰዉ ምን ይባላል ይኼ፣ ባንቺ የደረሰዉ?! ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ? እኩይ ነዉ እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ። በእድፋም ጥፍሩ፣ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘን መፅናናት መመኘት፣ ምንድነዉ መማፀን? ምንድን ነዉ ዕንባ አባሽ? ምንድን ነዉ ማገገም? ዕንባሽን ማድረቂያ፣ አልሰጥሽም ማ‘ረም። እሪ በይ! ቢል በይ! ኩርምት በይ–ዋኔ! ላንቺ መፅናናትን፣ አልመኝም እኔ። ወይኔ በይ! ወዮ በይ! ተይ አልልም ጭራሽ፤ አለመፅናናት ነዉ፣ አንቺን የሚያፅናናሽ! የሚገርም አይነት ጽሑፍ፣ ለዛውም የግጥም ጽሑፍ ማንበብ እንዲህ ከፍ ያደርጋል ለካ!         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ      ✍ መዘክር ግርማ

#ጠመንጃ_ወይ_ብዕር? ሀሳብ ጉልበት ኖሮት ጠመንጃን ካልረታ ብዕር እውቀት ወልዶ ትጥቅን ካላስፈታ ምኑ ነው መሰልጠን? የቱ ነው ጀግንነት? ሚዛኑ ልኬቱ የሰው ሰው ማንነት!!! መነጋገር ሸሽቶ እውነትን ደብቆ አንዱ ያንዱን ስራ አጣጥሎ ንቆ መድረሻው ወዴት ነው? የስኬቱ ምስጢር? ሀገርን ካልመራ እውቀትና ብዕር!!! የቱ ነው መሰልጠን?  የቱ ነው መደንቆር? ጠመንጃ ወይ ብዕር?  ሀገር የሚያሻግር? ሀሳብ እየሸሹ ጉልበት መለካካት ሀቁን እንጋፈጥ ይኼ ነው ቂልነት።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

#እንዲህ_ይመስለኛል ከእለታት አንድ ቀን ስም እየተሰጠ ለፍጥረታት ሁሉ እየተመረጠ አንድ ሰው መጥቶ መድረክ ላይ ቆመና ”አባት” ነህ ተባለ ምግባሩም ታየና ከዛም ባለተራ አንዲት ሴት ብቅ አለች ”እህት” ነሽ ተብላ እሷም ተሰየመች ደግሞ አንዱ ሲመጣ እሱም ደርሶት እጣ ”ወንድም” ነህ ብለውት ከመድረኩ ወጣ ”አክስት፣አጐት፣አያት” ሁሉም ጥሪ አገኙ እንደ ምግባራቸው በስሞች ተቀኙ፤ በስተ መጨረሻ አንዲት ሴት ብቅ አለች በመልካምነቷ ከኋላ የቀረች ፣ ስም አውጭውም ያኔ በጣም ተጨነቀ ስሟን ምን እንደሚል ፍፁም አላወቀ፣ ”ተናገር! ተናገር!” ብለው አጣደፉት አንድ ስም ስለሷ መናገር አቅቶት ጭንቀት ሲበዛበት አንዲት ቃል አምልጣ ”እ…” ሲል ተሰማች ከፀጥታው በልጣ፤ ስም ሳይገኝላት ይህ በእንዲህ እያለ ስም ማውጫው ዳቦ አልቆ ትሪው ተሰቀለ፣ ከዛም ”ማን ናት?” ሲባል ያች መልካሟ ሴት '' ’እ’ ናት ” ብለው አሉ ስም ሳይገኝላት ስም አውጭውም ሰምቶ ዝም ስላላቸው መስሏቸው ቀጠሉ የተቀበላቸው እንጂማ ቢሞከር ምግባሯን ለመስፈር ስንት ስም ተጠርቶ ምን ይበቃት ነበር።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ሰብለወንጌል ወርቁ

"ጾም" የመጣ ግዜ ልባችን ተሰብሮ ሆነን በትካዜ፤ እህል ሳንቀምስ ማር ጣፋጭ ሳንልስ፤ ተግተን እንጾማለን ቁርስ ምሳ ዘለን መክሰስ እንወዳለን፡፡ ፀሎታችን ሰምሮ ይደርስ ዘንድ እርሱ ቁርስ ምሳ ዘለን ይቅርብን መክሰሱ፡፡         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ      ✍ እዮብ ዘ ማሪያም

#ይነጋል ታድለሻል ቢሉም፣ የ13 ወር ፀሀይ፣ የ13 ወር ፀጋ ብርሀንሽ ተሰርቆ፣ ሲጨላልም እንጂ፣ መች አየን ሲነጋ? ተፈጥሮ ቸር ሆና፣ ሰማይዋ ባይነጥፍ፣ ምድሯ ቢለመልም፣ ከልጆቿ ልብ ውስጥ፣ ፍቅር ሲጎድል ነው፣ ሀገር የምትጨልም!፣ "አረ ነግቷል" ቢሉ የታለ የነጋው? አዕላፋት ተቧድነው፣ በየጎጥ በመንጋው፣ ሰው ከነገ ይልቅ፣ ዛሬን እያሰጋው የታለ የነጋው? ታሪኩን እንዳይፅፍ፣ ትውልድ እጁ ታስሮ፣ በትላንቱ ሾተል ዛሬው ተሸንቁሮ፣ ባልኖረው ተካሶ፣ ባልሰራው ተዋቅሶ፣ ለፀብ መዶለቻ፣ ያ'ያቱን ስም ጠቅሶ፣ ላለፈው ሲናከስ ለመጪው ሳይተጋ፣ በምን ስሌት ይሆን፣ ትዉልዷ ጨልሞ ሀገር የምትነጋ? የህሊና መስታወት በጥበብ ሲፀዳ፣ ማስተዋል እንዳ'አደይ ፈክቶ ሲፈነዳ፣ መገፋፋት ሲቀር ፣መደጋገፍ ነግሶ አንዱ ማገር ሲሆን፣ ሌላኛው ምሰሶ፣ የአብሮነትን ሸማ ትዉልዱ ሲሸምን፣ ያኔ ነው ሀገሬ መንጋቷን የማምን።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በረከት በላይነህ

#ደረትና_እውነት የልጅነት ነገር ፤ ቴሜቴ ጨዋታ፤ ደረቴን ስትደቂ ፤ ደረትሽን ስመታ የነገርሽኝ ነገር ፤ ትላንት ስትከጂኝ ፤ትዝ ብሎኝ ነበር፤ እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ፤ ያ ሰውዬ ምን አለሽ ማታ? ብዬ ስጠይቅሽ ፤ በለጋ አንደበቴ ምንም ምንም ምንም አላለም ፤ ብለሽ የመለስሽው ፤ ከሆድሽ አይደለም ደግሞም አውቅሻለሁ ፤ ቅጥፈት ስታስቢ                            እንዳንች ቀጣፊ የለም ንገሪኝ በሞቴ ፤ ሳይቦዝዝ ቅላቴ፤ እቴ ሜቴ እያልኩሽ ፤ በተባ አንደበቴ ያ ሰውዬ ምን አለሽ ማታ? ብዬ 'ምጠይቅሽ፤  እውነት አምሮኝ እንጂ ፤ ቀንቼ እንዳይመስልሽ አየሽ... በውሸት ሀገር ላይ ፤ እውነት የሚናገር ውሸታም ይባላል ፤ በሀቀኞች ሰፈር ውሸት ተደጋግሞ ፤ ከእውነት ሚስተካከል፤                             ከእውነት 'ሚሳከር ፤ ረስተሽ ይሆን እንጂ ፤ የኛ ሀገር ነበር እውነቱን ከውሸት ፤            ውሸቱን ከእውነት ፤ ስላደባለቅነው ያንቺን የውሸት እውነት ፤                            እንዴት አምንሻለው? በውሸታም ሀገር እውነት ተናጋሪ                           ውሸታም ይባላል በውሸቶች ሀገር መሲህ ይሰቀላል እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ፤ ያ ሰውዬ ምን አለሽ ማታ? ምንም ምንም አላለኝ፤ ትዳርሽን ፈቶ ልውሰድሽ አለኝ በጨዋታ መሀል ፤ ቅር አለኝ መሠለኝ የልጅነት ነገር ፤ ቴሜቴ ጨዋታ ደረቴን ስትደቂ ፤ ደረትሽን ስመታ የነገርሽኝ ነገር ፤ እድሜ ተቀይሮ ፤ ጥለሽኝ ስትሄጂ ፤                          ትዝ ብሎኝ ነበር።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ       ✍ በረከት ታደሰ

#በሉ_መልሱልኝ!!? ግራ የገባውን  ቀኙ የጠፋበት ለተዘጋጀ ሰው እራሱን ለማጥፋት አድኑት ቢሏችሁ በተስፋ መልሱት ምንስ ብትሉት ነው የሚድን ከመሞት? የችግሩን ሰንኮፍ ነቅሎ የሚጥል ቃል ምረጡ ቢይሏችሁ ችግሩን ለማቅለል ምንድን ነው መልሳችሁ? ክፋትን የሚጥል ሟችን አጠንክሮ ሞትን የሚገድል! እራሱን ሊያጠፋ ለተሰናዳ ሰው የህይወት አዙሪት ግራ ቀኝ ለጠፋው የትኛው ምክር ነው ተስፋ የሚሰጠው ሰርስሮ ችግሩን ነቅሎ የሚጥለው በሉ መልሱልኝ ልጠይቅ መካሪ ለሆነበት ምስኪን ማውለቅ ባንገት ሱሪ የትኛው ቃል ሰብሮ ሞቱን ያሸንፋል? ከስር መሰረቱ ስቃዩን ያክማል።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

#እራሴንስ_እንዴት_ልመን? ላስታውስሽ አስብና ከሩቅ ላይሽ በትዝታ ብዙ አይደለም ላንዲት አፍታ ለቅፅበት እንደትንታ ፣እንደነጎድጓድ ብልጭታ አይመጣልኝም ሁነትሽ ጠፍቷል ምስልሽ ከአዕምሮየ የቱ ዝናብ አጥቦት ይሆን ጠረንሽን ከገላየ ድምፅሽን ከልቦናየ? ስንት ዘመን አብረን ስቀን ከድሚያችን ላይ ስንት ዓመታት ተሰጣጥተን ተሰራርቀን ያረፈብን የፍቅር ወበቅ ገሞራው ጫካ የሚያደርቅ ያሳለፍነው ብዙ ክረምት እሳት ቆፈኑን  የማይገፈው እንዴት ነው ያ ሁሉ ህይዎት በቀን ክንድ የሚራገፈው? "ነበረች ግን?"እያልኩ ነው ነበርሽ ግን ፈጥሬሽ ነው? እንዳ'ቧራ እንደብናኝ እፍ ሲሉት በቃ የለም? ቅዤት ይሆን አልነበርንም እኔና አንች በዚች አለም? ፍቅራችን ደንቆት ከተማው "ጉድ እኒህ ልጆች" አላለም? እቅፌ ውስጥ እንዴት ሟሟሽ? ቆይ ሞቃት ነበርሽ ቀዝቃዛ ሸካራ ነበርሽስ ለስላሳ ? እንዴት ቅንጣት ነገር ልጣ በጣት እንኳን የሚነሳ እንደ ህልም እንደዋዛ?! መቸ ነበር የመጣሽው መቸስ ነው መምጣት የተውሽው? ከየት ነበር የምትመጭው እንደፀሀይ የምትወጭው? እንዳልነበር እንዳልሆነ ምን ምድጃ ላይ ብጣድ ነው ስምሽ ሳይቀር ከነፍሴ ውስጥ ብን ብሎ  የተነነ ? ቀን ብቻ ነው ያረሳሳን ወይስ ትላንት ሙተን ሌላ ሰው ሆነን ተነሳን? ምን አወራን ምን አቀድን የቱን ክበን የቱን ናድን? ስንቱን  አድባር  ተሳልመን በየወንዙ ተማምለን ለምልክት ከረሳሁሽ ራሴንስ እንዴት ልመን?         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ አሌክስ አብርሃም

#አለሁ_እንደ_ሾላው በገዛ ጆሮና ፥ በገዛ አይኖችሽ ላይ ሙሉ ስልጣን ያለሽ ከቶ እንደምን አለሽ? አለሁ እንደ ሾላው እንደ ወፍ መነሻው እንደ ወፍ መሸሻው ጸሐይ እየሞቀ ከመተንፈስ በቀር፤ ሌላ እንደማይሻው፤ መኖር ብቻ ሲሆን ፥ የሰው ልጅ እቅዱ በሲኦል ቢኖርም፥ አይቀርም መልመዱ እኔም ከመበላት፥ መብላት ይሻል ብየ’ ‘ፍሪደም ‘ ቢርቀኝ፥ ፍሪዳየን ጥዬ ነጻነት ቢርበኝ፥ እየበላሁ እህል አለሁ ይህን ያህል ፡ ፡         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በእውቀቱ ስዩም

🎰 Welcome Bonus 1200% — Maczo Crypto Casino 🎮 Crypto exchange · Sports · Live casino — all in one place 💳 USDT instant dep
🎰 Welcome Bonus 1200% — Maczo Crypto Casino 🎮 Crypto exchange · Sports · Live casino — all in one place 💳 USDT instant deposit & withdrawal → https://tglink.io/067862fd84a46f

🎰 Welcome Bonus 1200% — Maczo Crypto Casino 🎮 Crypto exchange · Sports · Live casino — all in one place 💳 USDT instant dep
🎰 Welcome Bonus 1200% — Maczo Crypto Casino 🎮 Crypto exchange · Sports · Live casino — all in one place 💳 USDT instant deposit & withdrawal → https://tglink.io/6b0022970354a8

እ-ን--ለ-ያ--ይ ፈርዖን ሲያሳድድሽ ከጭንቅሽ ደርሼ-ከስቃይሽ መንደር፤ በተሰጠኝ በትር ባሕሩን ከፍዬ-ላሻግርሽ ነበር፤ ግን በትሬን አይተሽ ገራፊ አደረግሺኝ-በሕዝበ-አዳም መሐል፤ ለመፍረድ ማን ብሎት ሕዝቡም አንቺን ትቶ-እኔ ላይ ይጮሃል፤ ከጩኸቱም አልፎ አለንጋ እያነሳ-ሁሉም ሲያሳድደኝ፤ በትሬን ብልከው ባሕር አልከፍል አለ-ውሃውም ወሰደኝ፤ አወይ ይሄ በትር ያላንቺ ማይከፍል-ያላንቺ ማይሠራ፤ ከሞት አፋፍ ጥሎኝ ሊያጣላኝ ደርሷል ከፈጣሪ ጋራ፤ ከፈርዖን የሸሸ ያ እስራኤል ልብሽ-ዘመን የተሠጠ-ለግብፅ ባርነት፤ ምነው ላዳኝ ከፋ በትር ለታደለ ለኔ ለሙሴ ዕ'ምነት፤ እንግዲያው በይ ሂጂ ተመልሰሽ ጊቢ-ከፈርዖን ጉያ ስር፤ በትሬን ልመልስ ተስማምቶሻልና የግብፃዊው እስር፤ እንግዲያው በይ ሂጂ ባሕሩም ይንሳፈፍ ሕልውናው ይሙላ-ከእንግዲ'ም አልከፍለው፤ ፈጣሪንም ሄጄ ፈርዖኗን ማርላት-በባርነት መኖር-ደልቷታል ልበለው፤ ፍቅር የማያውቀው ያልታደለ ልብሽ-የግዞት ባርነት ሕይወት የለመደ፤ መሻገር መች ያውቃል በለበጣ መውደድ-ተንሳ'ፎ እየሄደ፤ እ-ን-ለ-ያ-ይ በቃ! ሂጂ እኔም ልሂድ ዳርሽን ያዢልኝ-እኔም ዳር ይዣለሁ፤ ዳግመኛ እንዳትመጪ በመካከላችን ባሕር አበጃለሁ፤ በትሬም ላንቺ ልብ ባሕሩን ለመክፈል ዳግም እንዳይነሳ፤ አርቄ እጥላለሁ እስከ ዘለ-ዓለሜ አንቺን እንድረሳ፤ ፈጣሪም ዳግመኛ እስራኤል ልብሽን ነፃ አውጣ ከሚለኝ፤ አልታዘዝክም ብሎ ሺኅ ጊዜ ይጣለኝ ሺኅ ጊዜ ይግደለኝ፤ አ-ል-ፈ-ል-ግ-ም በቃ! ዕምነት ተሸርሽሮ ፍቅር ተንጠፍጥፎ-ተደፍቶ ካበቃ፤ ስለማይታፈስ በሌላ የ'ምነት ቅል በንፁኅ ልብ ዕቃ፤ ተመለሺ ብዬ በመርዛምነትሽ ዳግመኛ አልቆሽሽም፤ አርደሺኛልና በምድርም በሠማይ ይቅር አልልሽም፤ ተወኝ ህሊና አሮን ተወኝ አትመልሰኝ አይተሃት የለም ወይ የእግዜር ቃል ስትሽር ልቧ ሲያሳንሰኝ፤ በደነደነ ልብ ፈርዖን አልሰማ ሲል ባርነቷን ለምዶ፤ ፈጣሪ ሲወዳት በትር አውርሶናል ከሠማይ አውርዶ፤ ግን ይኸው አይተሃል ከነፃነት ይልቅ ባርነት ሲጠማት፤ ፈርኦን ምን አጠፋ የገዛ ፍቃዷ ባሕር ካሠጠማት፤ ተዋት አቦ! ተዋት! ተዋት ህሊና አሮን ይልቅ እንለምነው በትሩን እንዲወስድ ፈጣሪ ኩሉ-ዓለም፤ ከሷ ሚሻው እምነት ክህደት ሸርሽሮታል ካኖረበት የለም፤ ፈርዖን ሲያሳድድሽ ከጭንቅሽ ደርሼ-ከስቃይሽ መንደር፤ በተሰጠኝ በትር ወደፊት ሰንዝሬ-ባሕሩን ከፍዬ-ላሻግርሽ ነበር፤ ግን በትሬን አይተሽ ገራፊ አደረግሺኝ-በሕዝበ-አዳም መሐል፤ ለመፍረድ ማን ብሎት ሕዝቡም አንቺን ትቶ-እኔ ላይ ይጮሃል፤ ይጩህ ምናለበት እኔ የታመምኩትን መች ደርሶ ታሞታል፤ በተዛነፈ ዓለም ድሮም በቀና ልብ ቅጣት ይበረታል፤ ይጩህ አቦ! ይጩህ! ይጩህ ያ ህዝብማ ጉሮሮ አድሎታል ልቦናው ተሠርቆ፤ ልብሽ ነው ሚገርመኝ ፈርዖንን ሚማጠን የኔን በትር ንቆ፤ ይስመርልሽ ሂጂ!... ጊዜሽን ጠብቂ አይደርስም መስሎሻል፤ ሌላ እስራኤል ልብ እንድታሻግሪ በትር ይሰጥሻል፤ ያም ሌላ እስራኤል ልብ እንዳንቺ ደንድኖ ፈርኦንን ሲማጠን፤ አስታውሺው ያን ጊዜ የስብራቴን ልክ የሕመሜን መጠን።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ልዑል ኃይሌ