cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Al Qalam School

A smart person Knows what to say A wise person Knows whether or not to say it

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
695
مشترکین
+224 ساعت
+67 روز
+3630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

👍 2
የሳምንቱ አበይት መርሃግብሮች ከፊል ገፅታዎች በፎቶ 👉በተማሪዎች መካከል የተካሄደ      የስፔሊንግ ቢ ውድድር 👉የንባብ ሳምንት በሰልፍ      ሥነስርዓት ላይ 👉የሦስተኛው ሩብ ዓመት     የወላጅ-መምህር ክፍት የውይይት      መድረክ
نمایش همه...
👍 4
👍 3
👍 2
ለተከበራችሁ ወላጆችና አሳዳጊዎች በሙሉ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ። ከሰኞ፣ሚያዝያ 28/2016 እስከ ጁመዓ ፣ግንቦት 02/2016 ድረስ በትምህርት ቤቱ   የስፔሊንግ ቢ ውድድር እና የንባብ ሳምንት ይካሄዳል።ስለሆነም ልጆችዎን የተላከውን የእንግሊዝኛ ቃላት ሳያዩ በትክክል ፊደላትን ሳይገድፉ መናገርን ያለማምዷቸው፤ ስለንባብ ጥቅምም ገለፃ ያድርጉላቸው።ከሰኞ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ከቁርስና ምሳቸው ጋር መፃህፍትን ቋጥረውም ይላኳቸው። እንዲሁም እለተ ረቡዕ፣ሚያዝያ 30/2016  የ3ኛው ሩብ ዓመት የወላጅ-መምህር ክፍት የውይይት መድረክ እንደሚካሄድ በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን ከ 3:00-9:00 በተመቸዎ ሰዓት ተገኝተው በልጅዎ/ችዎ ሁለንተናዊ ስነምግባር እና የት/ት አቀባበል ዙሪያ ተነጋግረው ሪፖርት ካርድ መውሰድ እንደሚችሉ ከወዲሁ እናስገነዝባለን። ''ንባብን የሚያፈቅሩ እውቀትን የሚያፈቅሩ ናቸው!"        አልቀለም የልጅዎ ዓለም!!!
نمایش همه...
👍 6 1😢 1
🔔የአለማችን ታዋቂ ሰዎች       ስለንባብ ከተናገሩት ✅1 “ማንበብ ትልቅ ሀብትን ያጎናፅፋል። እስከዛሬ በአለማችን ላይ ስለተከሠቱ እና በሌሎች ሰዎች ስለተሰሩ ነገሮች በሙሉ ማወቅ የምንችለው ማንበብ ስንጀምር ነው።” (አብርሃም ሊንከን) ✅2. “በህይወቴ ማወቅ የምፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ መፀሀፍቶች ውስጥ አሉ። የኔ ምርጥ ጓደኛ ብዬ የምቀርበው ሰው ያላነበብኩትን መፀሀፍ “እንካ አንብብ” ብሎ የሚሰጠኝ ነው።” (አብርሃም ሊንከን) ✅4. “ዘወትር ባነበብኩኝ ቁጥር ውስጤ የነበረውና ያለው ትልቁ የመቻል አቅም ይቀሰቀሳል።”  (ማልኮምኤክሥ) ✅5. “የኔን የግል ህይወት ብቻ ሳይሆን በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን ህይወት መለወጥ የቻሉ ሀሳቦችን መተግበር የቻልኩት መፀሀፍ በማንበቤ ነው።” (ቤል ሑክሥ) 🌟6 “ለአንድ ሠው መፀሀፍ ስትሸጥ የሸጥከው ብዙ ወረቀቶችን፣ የተፃፈበትን ቀለምና ጥራዙን አይደለም። ለርሱ የሸጥክለት ዋናው ነገር ሙሉ የሆነ አዲስ ህይወትን ነው።”(ክርስቶፈር ሞርሌይ) 🔇7. “መፀሀፍትን በሚገባ ማንበብ ማለት በድሮ ዘመን ይኖር ከነበረ በጣም አስተዋይ ሰው ጋር መወያየት ማለት ነው።”(ሬኔ ዴካርቴሥ) ✅8. “ከየትኛውም ነገር በላይ ትልቁንና ከፍተኛውን ደስታ የማገኘው ሳነብ ነው።”(የፋሽን ዲዛይነሯ ቢልብላሥ) ✅9. “ማንበብ ከቻልክና አንዴ ማንበብ ከጀመርክ በቃ አንተ ነፃነት ያለህ ሠው ነህ።”(ፍሪድሪክ ዳግላሥ) ⭐️10. “አላዋቂነትንና ችኩልነትን የምንዋጋበት ብቸኛው ወሳኝ መሣሪያ ማንበብ ነው።”(ሌኖርድ ቤይንሥ ጆንሰን) ✅11. “ለአንድ ጨቅላ ልጅ መፅሐፍ እንዲያነብ ከማድረግ በላይ ልንሠጠው የምንችለው ትልቅ ሥጦታ የለም።”(ሜይ ኤለን ቼሥ) ✅12. “አንድ መፀሀፍ ባነበብን ቁጥር እዚህ ምድር ላይ በሆነ ቦታ ለኛ አንድ በር እየተከፈተልን ነው።”(ቬራናዛሪያን) (ፎቶ👉ቤተ መጽሀፍት በቻይና😮) https://t.me/dam76
نمایش همه...

SQ𝟑R የጥናት  ዘዴ ◾️የSQ3R የጥናት ዘዴ: ተማሪዎች በመማሪያ መጽሐፋቸው ውስጥ በጣም ጠቃሚ መረጃ የሆኑትን እንዲለዩ እና  እንዲይዙ የሚያግዝ የማንበብያ ቴክኒክ ነው። ◾️ SQ3R (ወይም SQRRR) የንባብ ግንዛቤ ሂደት አምስት ደረጃዎችን የሚያመለክት ምህጻረ ቃል ነው። ⓵ S- Survey: ሙሉውን መጽሐፍ ከማንበብ ይልቅ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በመዝለል እና በምዕራፉ ስር በተካተቱ አርእስት፣ ንዑስ ርዕሶች፣ ምስሎች ወይም ሌሎች ጎላ ያሉ ባህሪያት ላይ ማስታወሻ በመያዝ መጀመር። ⓶ Q- Question : በምዕራፉ ይዘት ዙሪያ ጥያቄዎችን መፍጠር። ለምሳሌ:- ይህ ምዕራፍ ስለ ምንድን ነው? ስለዚህ ጉዳይ አስቀድሜ የማውቀው ነገር ምንድን ነው? ⓷ R-Read : ሙሉውን ምዕራፍ ማንበብ መጀመር ከዚያም ከላይ ለፈጠርናቸው ጥያቄዎች መልስ መፈለግ። ⓸ R - Recite: አንድን ክፍል ካነበብን በኋላ ያነበብነውን በራሳችን ቃላት ማጠቃለል። ዋና ዋና ነጥቦችን ለማስታወስ እና ለመለየት መሞክር እና ከሁለተኛው ደረጃ ማንኛውንም ጥያቄዎች መመለስ። ⓹ R - Review : ምዕራፉን ከጨረስን በኋላ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ጽሑፉን መከለስ አስፈላጊ ነው። በመጨረሻም ከላይ በፈጠርናቸውን ጥያቄዎች እራሳችንን መጠየቅ እና በተጨማሪ ማንበብ ያለብንን ወይም የምንፈልገውን ማንኛውንም ክፍል እንደገና ማንበብ ነው።
نمایش همه...
👍 11 2