cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ETHIO PLANET (ስነፍጥረት)

🌍ETHIOPLANET (ስነ ፍጥረት) 1,ስለ፦ክዋክብት planet ( space sience) 2,ስለ፦ኢትዮጵያውያን ሊቃውንቶች የስነ ፈለግ ጥበብ 3,ስለ፦አስገራሚው ኳንተም ፊዚክስ፣ጠልሰሞች 4,ስለ፦አስትሮይድ(astroied) belt 5,ስለ፦ ሳተላይት ቴክኖሎጂ(cyber security) 6,ስለ፦ አስገራሚው ግዕዝ ቋንቋ ሚስጥር 7,ስለ፦ኢትዮጵያውያን ጥበብ (astronomy book) ይቀላቀሉ👇👇

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
179
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ዓይንህን ግለጽ፤ ሀገርህን እወቅ፤ታሪከህን መርምር፤አንብበህ ስትጨርስ የሚሰማህን ጻፍልኝ ገነት ኢትዮጵያ ውስጥ የመሆኗ ምልክት ዕፀ ለባዊት አዳምንና ሔዋንን ተከትላ ከገነት መምጣቷ ነው? ዕፀ ለባዊት ከዓለም ላይ ካሉት ሃገራት ሁሉ ተከልላ የምትገኘው በጎጃም ክፍለ ሃገር ብቻ ነው፡፡ ይህች ዕፀ ለባዊት ሴቴና ወንዴ ፆታ አላት፡፡ በሳምንት ሰባት አይነት ባህሪ ታሳያለች፡፡ እንዲሁም በየቀኑ የምትቆረጥ ዕፀ ለባዊት በጥቅሉ 586 ገቢር አላት፡፡ በእያንዳንዱ ቀንና ሰዓት የምትቆረትበት ጥበብ የራሱ ልዩ ገቢር አለው፡፡ ሴቴዋ ዕፀ ለባዊት ሔዋን ከገነት ስትባረር ይዛት የመጣች ስትሆን እንደ ሴት የራሷ ብልት ቅርዕ አላት፡፡ በዚህ ሴቴ ብልትዋም(አፈ ማሕጸኗ) ወሩ በገባ በ27ኛው ቀን ለተከታታይ 7 ቀን ታለቅሳለች፡፡ የምታለቅሰው ወይም ከአፈ ማሕጸኗ(ብልቷ) የምታመነጨው ፈሳሽ ሲሆን የሚወጣው ፈሳሽም ከል(ደም) ነው፡፡ በትክክል የሰው ደም የመሰለ ቀይ ፈሳሽ ነው፡፡ ስትነግስም ሆነ ወሩ በገባ በ27ኛው ቀን የሚፈሳት ደም ውሎ ሲያድር ትል ይፈጥራል፡፡ ይህም ሴት በየ ወሩ ከአፈ ማዕፀኗ የሚፈሰውን ከል(ደም) ለማመልከት ነው፡፡ ይህች ዕፅዋት ‟ከጎጃም ውጭ የትኛውም ዓለም ላይ የለችም” ይላሉ አበው ጠቢባንና ሊቀ ሊቃውንት፡፡ ዕፀ ለባዊት ዓለም ላይ ካሉት የጥበብ ዕፅዋት ሁሉ ብቸኛዋና ባለ 586 ገቢር ዕፅ ናት፡፡ ዕፀ ለባዊት ጎጃም ውስጥ መኖሯን የዓለም የዕፅዋት ምርምር ሳይንቲስቶች ሁሉ ፈልገው ደርሰውባታል፡፡ ነገር ግን በእጃቸው ሊይዟትና ሊቆርጧት እንዲሁም በአይናቸው ሊያዩዋት አልቻሉም፡፡ እነሱ የደረሱበት በጎጃም ውስጥ መኖሯን ነው፡፡ ዕፅዋቷ ስትቆረጥ በጥንቃቄ ምስጢሩ በዕፅ አለቃ ምስጢር ካልሆነ በስተቀር እጅግ አስከፊና አደገኛ መሆንዋን እንጅ አውሮፓዊያን እስካሁን ባላጠፏት ነበር፡፡ ……ከሰባቱ አይነት ዕፀ ለባዊት በተለይ አንዷ ከኢትዮጵያ ምድር ውጭ አትገኝም፡፡ ሌሎች ስድስቱ ግን ይገኛሉ፡፡ ስድስቱ ማለት ከተፈጠረችበት ቀን ውጭ የምታሳያቸው የለባዊት ባህሪያት ማለት ነው፡፡ ….በዚህ በኩል ድንቅ አዲስ የዕጽዋት ምስጢር አለ……ይቀጥላል…. ምንጭ ገነት በኢትዮጵያ ናትን? ከበርባሮስ እስከ ሃኖስ ገጽ 2-3 ደራሲ ዝጋለ አያሌው
نمایش همه...
ዓይንህን ግለጽ፤ ሀገርህን እወቅ፤ታሪከህን መርምር፤አንብበህ ስትጨርስ የሚሰማህን ጻፍልኝ ከ4ኛው መጽሐፍ ከርታታው ባለቅኔ ሊቁ መሐሪ የኢትዮጵያን መልክአ ምድር ምስጢር እንዴት ሆኖ እንደተገለፀለት ገብቶኝ አያውቅም፡፡ በዚህ ሰዓት የምንገኘው አንድ ትልቅ በአረንጓዴ ደኖች እጅብ ብሎ በደመቀ እግዚአብሔር ዕፅዋትንና ተራራን ከፈጠረ ጀምሮ የሰው ልጅ በብዛት ረግጦት አያውቅም የሚባልለት ተራራ ስር ነበር፡፡ ይህን ተራራ ለብዙ ዘመና እንዴት የሰው እግር እንዳልረገጠው ደግሞ የሚታይ ምክንያታዊ ምስጢር አለው ይባልለታል፡፡ ሊቁ መሐሪ ከተራራው ስር ሆኖ ዓይኖቹን ፊት ለፊታችን እንደ ኮረዳ ጡት ቁልቁል የተንጠለጠሉ ቋጥኝኞች ላይ ያንከባልላቸው ጀመር፡፡ ተራራውን አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ወደ ግራ ግልምጥ እያደረገ ከንፈሩን ይመጥጣል፡፡ የማለዳዋ ፀሐይ እንደ ምድር ወገብ ደኖች ጥቅጥቅ ብሎ በረዣዥም ዛፎችና ቁጥቋጦዎች የታጀበውን ተራራ እንደ ማርያም መቀነት ሰባቱን የሠንደቃላማ ቀለማት ዘርግታበታለች፡፡ ተራራው ግን ለሊቁ መሐሪ እንጅ ለኔ በጣም ያስፈራል፡፡ ቁልቁል ወርዶ በላያችን ላይ የሚደረመስ ይመስላል፡፡ ሊቁ መሐሪ ሰላምታ ከሰጠኝ በኋላ ወደ ተራራው እንደምንወጣ ገለጸልኝ፡፡ በዚህ ድንቅ ተራራ ላይ አስገራሚ ምስጢራት አሉ፡፡ በዋናነት ወደዚህ ተራራ የተቀጣጠርነው በተራራው ወገብ ላይ ለሆድ ቁርጠት በሽታ መድኃኒት የምትሆን ዕፅዋት ከነ አጠቃቀሟ ሊያሳየኝ እንደሆነ ገለፀልኝ፡፡ በእርግጥ ይህን ጉዳይ እንዲገልጽልኝና እንዲያስተምረኝ ግፊት አላደርግም ብየ ነበር፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ እጠይቀው ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ የሚጠቅመኝ ነገር ካለ ያስተምረኛል ብየ ዝም ስለው ዝም ይለኛል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን በድፈረት እጠይቀዋለሁ፡፡ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ተንደርድሬ የምጠይቀውን ነገር ደርሶ ምስጢሩን አይገልጽልኝም፡፡ እኔም አሳየኝ ብየ እጠይቀውና ዝምታ ሲያበዛብኝ በቃ እሽ አይለኝም ብየ ዝም እላለሁ፡፡ በእርግጥ ለትውልድ የሚጠቅም ነገር ሳይተላለፍ ጊዜ እንዳይቀድመን ብየ እሰጋለሁ፡፡ እሱ ግን ዘመኑን ጠብቆ በራሱ ቀጠሮ ነገሮቹን በስክነትና በአስተውሎት እንድማር እያደረገ መሆኑ የገባኝ በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ ከርታታው ባለ ቅኔ፡፡ ወደ ተራራው አሻግረው የተተኮሱትን ዓይኖቹ ተራራውን ለሁለተኛ ጊዜ ከታች እስከ ላይ ገላመጡት፡፡ ከዚያም ዛቱበት፡፡ ተራራው ላይ የሆነ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ሊቁ መሐሪ ተራራውን አሻግረው ሲገላምጡት የቆዩ ዓይኖቹን ወደ እኔ መለሳቸውና ሊገልጽልኝ የፈለገውን ምስጢር እንዲህ አያለ ይዘረዘር ጀመር፡፡ “እየውልህ አሁን የምንወጣው ይህን ግዙፍ ተራራ ነው፡፡ ረጋ ብለህ ተከተለኝ፡፡ ምን አልባት አራዊቶች ይኖራሉ፤ሊተናኮሉን ከፈለጉ ረጋ ብለህ የማደርገውን ተከታተል” አለኝና ከተራራው ግርጌ ያለውን ዥረት ለመሻገር ጉዞ ጀመርን፡፡ ሊቁ መሐሪ እሱ ከፊት እኔ ከኋላ እየተከተልሁት ከተራራው ግርጌ ያለውን ወንዝ ተሻግረን ወደ ተራራው ሽቅብ ጉዟችን ቀጠልን፡፡ ወደ እዚህ ተራራ ሽቅብ ስንጓዝ በፍርሃትና በጭንቀት አይሉት ብቻ ውስጤ የሆነ የመረብሽ ስሜት ይሰማኝ ጀመር፡፡ ምክንያቱም ያልጠበቅሁት አስደንጋጭ አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ የእባቦች አስቀያሚ ድምጽ “ሲሰርርር ሲጥሲጥ ሲጥጥጥ” ይላል፡፡ ጎሬዛዎቹ/ጉሬዛዎቹ “ ኧኧ….ኧኧ” ይላሉ፡፡ በዚያ ላይ እኛን ስላዩ ነው መሰል በዛፎቹ ላይ ከወዲያ ወዲህ ይራወጡ ጀመር፡፡ የጦጣና የዝንጀሮዎቹ ድምጽም ከተራራው የገደል ማሚቶ ጋር እየተስተጋባ ይመለሳል፡፡ ከሁሉም በላይ ለእኔ ግን ፍርሃትን የፈጠረብኝ የእባቦች አስቀያሚ ድምጽ ነበር፡፡ ሊቁ መሐሪ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡እኔን ደግሞ የእባቦቹ ድምፅ ሰላሜን እየነሳኝ ተከትየዋለሁ፡፡ የእባቦቹ ድምፃቸው ብቻ ሳይሆን እባቦቹ በአካል ብቅ እያሉ በመንገዳችን ላይ እንደ አፍራና ጨው ተበተኑ፡፡ ይህን ትይንት የማውቀው በፊልም ነው፡፡ በአካል በእባቦቹ ተከብቤ አላውቅም፡፡ “ ሲርርር…ሲጢጢጢ…ሲርርር” እያሉ ሲሰቀጥጡኝ ቆም ብየ አካባቢውን ስቃኘው በቃ ቋጥኙንና ጫካውን ወረውታል፡፡ ወደ ግራ ዞር ብየ ስመለከት ከእግራችን ስር ሁሉ የሚሽሎከሎኩ ነበሩ፡፡ አቤቱ ደግሞ እርፍ የሚያካክሉ ወፋፍራም ቁንጮ ያላቸው እባቦች ናቸው፡፡ በጣምም ያስፈራሉ፡፡ ከገነት አዳምን ያባረረው እባብስ መልኩ ምን ይመስል ይሆን?.... “ሊቁ እነዚህ እባቦች ይናደፋሉ፡፡ እንዴት ነው ተራራውን የምንወጣው? እስቲ ተመልከት እግራችን ስር ሁሉ አሉ ኮ!” አልሁት የእባቦቹ ጉዳይ እጅጉን ስለ አሳሰበኝ፡፡ ሊቁ መሐሪ የኔ ግራ መጋባቴ ገርሞት “ቆይ አንዴ ተረጋጋ፤ቁም ” አለና በአፉ የሆነ ነገር “ኩትምትምትምትምምም ”ያደርግ ጀመር፡፡ የሆነ ጸሎት መሆኑ መሰለኝ፡፡ የእነሱ ነገር ምኑ ይታወቃል፤የአጋንንት ማባረሪያ ይሆናለ፡፡ እባብ ደግሞ በአብዛኛው በአጋንንት ወይም በአርዌ ሰይጣን ይመሰላል፡፡ ሊቁ መሐሪ ጥቂት እንደ አኩተመተመ የእባቦቹ ድምጽ በአንዴ ፀጥ አለ፡፡ መንገዳችንም ከእባቦቹ ተገለጠ፡፡ ከዚያም“ ሲርርርር ሲጥጥጥጥ” ሲል የነበረው የእባቦች አስቀያሚ ድምጽ ከአጠገባችን በአንዴ የውኃ ሽታ ሆነ፡፡ እኔም በጣም እየተገረምሁ ሊቁ መሐሪን “ትክ” ብየ ተመለከትሁት፡፡ “ ሊቁ ቆይ እባቦችን ምንድን ነው ያደረግኋቸው? እባቦቹ ወዴት ሄዱ? ኧረ ጉድ! አንተ ምን አይነት ጉድ የሆንህ ሰው ነህ?” አልሁት፡፡ ምንጭ፡- መክኑን በትር 4ኛው መጽሐፍ ደራሲ ዝጋለ አያሌው
نمایش همه...
ዓይንህን ግለጽ፤ ሀገርህን እወቅ፤ታሪከህን መርምር፤አንብበህ ስትጨርስ የሚሰማህን ጻፍልኝ ትኩር ብሎ ተመለከተኝና‟ የሙሴን መቃብር ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡” አለኝ፡፡ ‟አሁንም እንድትፈልግ ላደርግህ ነበር፡፡ ቆይ ግድ የለም ሌላ ፍለጋ እሰጥሃለሁ፡፡ የምትጠይቃቸው ቀሳውስቱም ይሰለቹኻል፡፡ እብድም ሊሉህ ይችላሉ፡፡ ብቻ አንተ እኔ የምነግርህን ስማ፡፡ በትክክል ስማ፡፡ እንግዲህ ናባው የሚባል ተራራ በእስራኤል ታሪክም ሆነ ተራራ የለም፡፡ ይህ ተራራ ሊሆን የሚችለው ጎንደር ውስጥ ነው፡፡ እኔ የሚሰማኝ እንዲህ ነው፡፡ የሚሰማኝ ብቻ ሳይሆን እውነትም ነው፡፡ አሁን የምነግርህ የሙሴና የክርስቶስ ምስጢር የኢትዮጵያን ህዝብ በአሁኑ ሰዓት አርሶ አደሩ ሸማች፤ከተሜው ሸማች ሀገሩ ጥጋብ የሆነበትን ምስጢር አያይዠ ነው፡፡ ሙሴ እስራኤል ሀገር የእስራኤልን ህዝብ ሲያስተዳድር ከቆየ በኋላ መሞቻው ጊዜው ሲቃረብ ወደ ተስፋይቱ ምድር ወደ ኢትዮጵያ መጣ፡፡ ከዛም ከአማቱ ከዮቶር አብ ጋር ይኖር ነበር፡፡ የዮቶርን በጎች በሚጠብቅበት ወቅት እግዚአብሔር ‟ ሙሴ ሙሴ ” መሞቻህ ደርሷል አለው፡፡ ሙሴም‟ ጌታ ሆይ! የአራት ዓመቱን ልጄን ትቼ እንዴት እሞታለሁ፤እሱንም ማን ያሰድገዋል? እባክህ ትንሽ ልቆይ” አለው፡፡ጌታም ሙሴን‟ ሙሴ ሙሴ ወደ ወንዙ ዳር ውረድ”አለው፡፡ ሙሴም ወደ ወንዙ ወረደ፡፡ ጌታም ዳግመኛ‟ ሙሴ ሙሴ የት ነህ?” አለው፡፡ ሙሴም‟ጌታ ሆይ ወደ ወንዙ ውረድ አላልከኝምን?” አለው፡፡ ጌታም‟እጅህን ወደ ወንዙ ውኃ ውስጥ ስደድ ” አለው፡፡ ሙሴም እጁን ወደ ውኃው ውስጥ ሰደደ፡፡ ጥቁር ድንጋይንም አገኘ፡፡ ጌታም‟ ሙሴ ሆይ! ምን አገኘህ ?” አለው፡፡ ሙሴም ‟ ጥቁር ድንጋይ አገኘሁ” አለ፡፡ ‟ ውሰድና እሱን ጥቁር ድንጋይ ከድንጋይ ጋር አጋጨው”አለው፡፡ ሙሴም ድንጋዩን ከድንጋይ ጋር ሲያጋጨው ድንጋዩ ከሁለት ተከፈለ፡፡ ሙሴም ከድንጋዩ መኻል አንዳች የክርስቶስን አስደናቂ ምስጢር አየ፡፡ ከድንጋዩ መኻልም አንዲት ትል አንዲት ቀጭን ዕፅ ስር ስትመጥጥ አየ፡፡ ጌታም ‟ ሙሴ ሆይ! እስቲ ምን አየህ” አለው፡፡ ሙሴም“ ጌታ ሆይ! አንተ ኃያልና ምስጢራዊ አምላክ ነህ፡፡ከውኃም ውስጥ ካለ ድንጋይ…ምንም ቀዳዳ ከሌለው ድንጋይም ውስጥ ሕይወትን ዘርተሕ ምግብንም በዚያ አኖርህ…” አለው፡፡ ጌታም ሙሴን‟ ሙሴ ሆይ! እና እንኳን የአንተን የወዳጄን ልጅ አሳዳጊና መጋቢ ሳላዘጋጅ ለሞት ተዘጋጅ እልሃለሁ፤ ፍጥረታትን ሁሉ በምስጢር ምግባቸውንስ ማን አዘጋጀላቸውና” አለው፡፡ ሙሴም ‟ ጌታ ሆይ! እባክህ እናቴን አሮጊቷን እናቴን ልቅበርበት እሷ እስከምትሞት እንኳን ተወኝ፤ደግሞም ኮ! ጌታ ሆይ ሞት ኮ እንዴት ይጨንቃል…ሞትኮ መራራ..በጣም መሪር ነው፡፡ እንደ ሞት ኮ መሪር የለም ’አለው፡፡ አናም እባክህ ልለምንህ አሮጊቷን እናቴን እስከምቀብር ጠብቀኝ” አለው፡፡ ጌታ ዝም ብሎ ተወው፡፡ ሙሴም በግ ሲጠብቅ አምሽቶ ወደ ናባው ተራራ ሲያቀና ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መቃብር ሲቆፍሩ አገኛቸው፡፡ ሙሴም‟ ቆይ እናንተ ደግሞ እነማን ናችሁ? ለሰፈሩ እንግዳ፤ለወንዙ ባዳ በዚህም አይቻችሁ አላውቅም፡፡” አላቸው፡፡ሙሴም አዲስ ሰዎች ስለመሆናቸው አጥብቆ ሲናገራቸው ‟ሂድልን አትረብሸን ” ብለውት ነበር፡፡ ሙሴም ‟እሽ ግን ማንን ልትቀብሩ ነው መቃብር የምትቆፍሩ? ለመሆኑስ ልኬት ይዛችኋል?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ ‟ እዚህ ቦታ እንዲቀበር የተነገረን ሰው ቁመቱም መልኩም አንተን ይመስላል፤እስቲ ግባና ለካልን” አሉት፡፡ ገብቶም ሲለካ ‟በደንብ ተንጠራራ” አሉት፡፡ ሙሴም በደንብ ተንጠራርቶ ሲተኛ መላእከ ሞት መጣና ወሰደው፡….. ምንጭ ገነት በኢትዮጵያ ናትን? ከበርባሮስ እስከ ሃኖስ ገጽ 45-47 ደራሲ ዝጋለ አያሌው
نمایش همه...
ንህን ግለጽ፤ ሀገርህን እወቅ፤ታሪከህን መርምር፤አንብበህ ስትጨርስ የሚሰማህን ጻፍልኝ ዕፀ ደማዊት “ደማዊት” የተባለችበት ዋና ምክንያት ምንድን ነው? የደም ህዋሱ ከተመጣጠነ የሰው ልጅ ምንም ነገር መሆን አይችልም፡፡ የዚኽች ዕፅት ዋና ስራ የጎደለውን የደም ክፍል እንዳይጎድልና ከፍ ያለውን የደም ክፍል ዝቅ በማድረግ ማመጣጠን ነው፡፡ የአባቶቻችን የሊቃውንቶች ምስጢር ብዙ ነው፡፡ ከዘመናት ባሻገር በባህላዊ መንገድ ሲመራመሩ ግብጦ ይተካታል ተብሎ ነበር፡፡ ግብጦ ግን ደም ግፊትን ዝቅ ማድረግ ብቻ ነው የሚችለው እንጅ ማመጣጠን አይችልም፡፡ ሊቃውንት ደማቸውን አመጣጥነው እረጅም አመት የሚኖሩት ሆስፒታል ገብተው ግልኮስ ተሰጧቸው አልያም ደም ተለግሶላቸው አይደለም፡፡ ይኽች ዕፅዋት ከፍ ያለውን የደም መጠንም ሆነ የደም ወገን ዝቅ ወዳለው የመቀየርና የማመጣጠን ተሰጦና ሃቅም አላት፡፡ እናም ስያሜዋ የተሰጠው ከዚያ ነው፡፡ ምንጭ፡- ገነት በኢትዮጵያ ‹ጓሮ› ናትን? ከኤረር ተራራ እስከ ሰማያዊ ኤረር ቁጥር 2 ገጽ 19 ደራሲ ዝጋለ አያሌው
نمایش همه...
ዓይንህን ግለጽ፤ ሀገርህን እወቅ፤ታሪከህን መርምር፤አንብበህ ስትጨርስ የሚሰማህን ጻፍልኝ ዘዌ ለዚህ ትውልድ ድህነት ትልቅ ትምህርት አለው፡፡ በውስጡ ብዙ ግራ የተጋባና መንገዱ የጠፋው ትውልድ አለ፡፡ የተሳሳተ ትራክ ላይ ያለም አለ፡፡ በጥበብ ስም የተሳሳተ የጥንቁልና ህይዎት ውስጥ ያሉ ነገሮች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ ዘዌ በጥቂቱ ከአራት በላይ ትርጉም አለው፡፡ 1.ኛ ዘዌ የምትባል ዕፅ አለች፡፡ ጥላዋን በእባብ ላይ ከጣለች እባብ ልፈስፍስ ብሎ ይሞታል፡፡ የእባብ ጠላት ናት፡፡ 2ኛ እመቤታችን ቅዲስት ድንግል ማርያም በዘዌ ትመሰላለች፡፡ የእባብ ጠላት የሆነውን ክርስቶስን ወልዳለችና፡፡ 3ኛ ኢየሱስ ክርስቶስም በዘዌ ይመሰላል፡፡ በሰምቀል ላይ ተሰቅሎ፤ከመቃብር ተነስቶ፤የሰው ልጅ ጠላት የሆነውን እባብ ሰይጣንን በነፋስ ዛንጁር ሰቅዞ ይዞ ሲኦልን ጠርጎበታልና የእባብ ጠላት ስለሆነ ዕፀ ዘዌ ምሳሌ ነውው፡ 4ኛ.ዘዌ ዕፅዋቷ ለተለያዩ ሀገር በቀል መድኃኒትነት ታገለግላለች፡፡ በዚያም ልክ ለክፋት የሚጠቀሟት ካሉ ለጥፋት ትሆናለች፡፡ ምንጭ፡ ዘዌ መጽሐፍ ደራሲ ዝጋለ አያሌው
نمایش همه...
በተመስጦ ውስጥ ከቆየ በኋላ“…..ስለ ሥነ ፍጥረት ያለህ እይታ እንዴት ነው አንድ ጥያቄ ነበረኝ በእርግጥ ሰዎችን ብትጠይቅ ሊያድበሰብሱብኽ ይችላሉ፡፡ ስነ ፍጥረትን እንዴት ትገልጸዋለኽ?” ሲል ጠየቀኝ፡፡ “ ማለቴ እንዴት ትገልጸዋለኽ ስትለኝ አልገባኝም! መቼ ምን ምን ተፈጠረ ለማለት ፈልገህ ነው ወይስ ምን ልትል ፈልገኽ ይሆን?” “ አዎ መቼ ምን ተፈጠረ የሚለውን ነው እንጅ ግን አንድ ከባድ ጥያቄ አለ፡፡ እስቲ ምን መቼ ተፈጠረ? ማለቴ ሥነ ፍጥረትን ታሪክ ስታነብ አወዛጋቢ ነገር ገጥሞኽ አያውቅም ወይ? ”አለኝ፡፡ “እኔ እንኳን አለማወቄ ስለሚበዛና ደካማ ስለሆንኹ ነው መሰል ሥነ ፍጥረትን የተምታታ ነገር አለው የሚል ሃሳብ ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ ምን አልባት 99ኙ ዓለማት በስነ ፍጥረት ታሪክ ስላልተዘረዘሩና ስለ እነዚኽ ዓለማትም የሚኖሩ መናፍስቶች የመናፍስት ጦርነት(ዣን ሸዋ/ጃን ሸዋ መጽሐፍ ላይ እንዳለው ነው፡፡ ስለነዚኽ መናፍስቶችና መኖሪያቸው እንጅ ስለ 99ኙ ዓለማት አፈጣጠር ምንም ነገር መናገር አልችልም፡፡ ስለሌሎች ስነፍጥረታት ግን መጽሐፍ ቅዱስን፤ስነ ፍጥረትን፤ቀለምንጦስና አክሲማሮስን እንዲኹም የገድለ አዳምን ታሪክ አለቅም፡፡ በዚኽ ታሪክ ውስጥ እኔ ካለማወቄ የተነሳ ስህተት አይታየኝም፡፡ ስህተት ቢሆንም ስለማላውቀው አወዛጋቢ ሊሆንብኝ አይችልም፡፡ ስህተት ነው ትክክል ነው ለማለት ኮ! ማወቅና ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ እንግዲኽ እነዚህን ታሪኮች ይዠ ብሳሳት ስህተቱ በሙሉ የኔ ላይሆን ይችላል፡፡ ከኔ በፊት የነበሩ አባቶች ስህተት ይሆናል ማለት ነው፡፡”አልኹት፡፡ ምክንያቱም እኔ የማውቀው መጽሐፍ ቅዱሱንም ሆነ ታሪኩን ከአባቶቻችን በተቀበልነው መረጃ መሰረት ነው፡፡ ሊቁ መሐሪ ትኩር ብሎ ከአፌ የሚወጡትን ቃላት በአይኑ፤ከልቤ የሚመነጩትን ሃሳቦች በጭንቅላቱ እያልጎመጎመ “ እሽ እስቲ ስነ ፍጥረትን ከእሑድ እስከ ዓረብ በአጭሩ አስረዳኝ“ አለኝ፡፡ ለራሴ ይኽን ባላውቅም ባውቅም መሠረቴና መረጃ ምንጨ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ሸምድጄ ባለመያዜ ሊቆጣኝ ይሆን የሚል ጥርጣሬ ቢያድርብኝም የምችለውን በአጭሩ ልዘረዝርለት ተዘጋጀኹ፡፡ “እሽ እንግዲህ ዋና መሠረቶቼ እነዚህ የዘረዘርኀዋቸው መጻሓፍት ናቸው፡፡ የሥነ ፍትረትን ሁኔታ በአጭር ሳብራራው ከእሑድ እጀምራለሁ፡፡ እሑድ “እሑድ 24ቱ ሰዓታት እንደዚኽ ተከናውነዋል፡፡ 1ኛው ሰዓት አራቱ ባህሪያንና ሰማያት፤መላእክት፤ጨለማ ፈጠረ፡፡ አክሲማሮስ ግን እነዚኽን ከቅዳሜ ለእሑድ ንግ ሌሊት የተፈጠሩ ናቸው ይላቸዋል፡፡ ነገር ግን የስነ ፍጥረት ታሪክ ደግሞ በየ ሰዐቱ የተፈጠሩትን ይዘረዝራል፡፡ አራቱ ባሕሪያት ማለት ኃያልነት፤ፈታሒነት/ፈራጅ፤ መንጽሒነት/የሚያነፃ፤ ባዕልነት/ባለጸግነት ናቸው ይልና እነዚኽንም እያንዳንዳቸው በአራቱ መሰረታዊ ባሕርያት ኃያልነት(እሳትን)፤ፈታሒነት/ፈራጅ(ነፋስን)…መንጽሒነት/የሚያነፃ(ውኃን) ባዕልነት/ባለጸግነት(መሬትን) ምሳሌ ያደርጋሉ፡፡ ሥነ ፍጥረት ታሪክ ላይ የሰፈረውን ስዘረዝር በ2ኛው. ሰዓት መንበረ መንግሥቱን ፤በ3ኛው ሰዓት ጽርሐ አርያም ሰማይን፤4ኛው ሰዓት ሰማይ ውዱድን ፤በ5ኛው ሰዐት ኢየሩሳሌም ሰማያትን፤በ6ኛው ኢዮር ሰማይን ፤በ7ኛው ራማን ፤በ8ኛው ኤረርን ከፈጠረ በኋላ በ9ኛው በኢየሩስዓሌም ሰማያዊት በ10ኛው በኢዮራ ሰማይ ያሉትን በ11ኛው በራማ ሰማይ ያሉትን በ12ኛው በኤረር ሰማይ ያሉትን መላእክት ፈጠረ፡፡ ልብ በልልኝ መላእክት የተፈጠሩት ከመካከለኛው ሰማይ ላይ ጀምሮ ነው፡፡ መንበረ መንገስቱን ፈጥሮ ክዳን ጽረሐ አርያምን(ጠፈርን) ስለሰራ ጽርሐ አርያም ሰማይ ከሰማዮች ሁሉ በላይ መሆኑንም አንዘነጋም፡፡ ከዚያ በኋላ ቀሪ ሌሊቱን 12 ሰዓት ደግሞ በእያንዳንዱ ሰማያት ያሉትን መላእክት አለቆችንና እየቀባ የቤት አለቃ ለየ፡፡ ለምሳሌ በ3ኛው ሰዓት በኢየሩሳሌም ሰማያት ያሉትን መላእክት ቀባ የቤት አለቃ ለየ፤የአለቃ አለቃ ሰማልያልን/ዲያቢሎስን ሾመ፡፡ ወደ ሰኞ ሥነ ፍጥረት ስሻገር ምድር ውኃ ሞልታ አድራ ነበርና ከሦስት ከፍሎ አንዱን እጅ ሃኖስ ፤አንዱን እጅ ውቂያኖስ ፤አንዱን እንጅ ቀላያት፤አፍላጋት፤አብርሀት አድረጎ ፈጠራቸው፡፡ ማክሰኞ/ማግሰኞ ውኃዎቹ ከተሰበሰቡ በኋላ የምድር ቡቃያና ፍሬያት፤ገነትን፤ሲኦልን፤ብሔረ ብፁዓንን፤ብሔረ ሕያዋንን ፈጠረ፡፡ ግማሽ ዕፅዋትም ዓርብ ከተፈጠሩት ውጭ በዚህ ዕለት እንደተፈጠሩ ይናገራል፡፡ ረቡዕ ደግሞ ጨረቃና ፀሐይን ፈጠረና አንዱን ቀን እንዲመግብ አንዱንም ማታ ወይም ሌሊት እንደመግብ አደረገ….፡፡” እያልሁ ስዘረዝር “ እዚኽ ላይ አቁም ” አለኝ ኮስተር ብሎ፡፡ እኔም የሆነ ስህተት ያለ ስለመሰለኝ ለምን ? ብየ አልጠየቅኹትም፡፡ ትረካየን ያዝ አደረግሁትና አፍጥጨ እመለከተው ጀመር፡፡ ዝም ብሎ አፍጥጦ ፈገግ እያለ በአጣፋው እየመለሰልኝ ነበር፡፡ “ ያጣድፍህና ሮጠህ በራስህ ጊዜ መጠህ ወጥመዱ ስር አረፍህ፡ ያዛክራባህ….አይ አንተ ሰው ቂቂቂቂ እየሳቀ ነበር፡፡ አየህ በደፈናው ብጠይቅህ ችላ ልትለው ስለምትችል ግንዛቤህን ማወቅ ፈለግኹ፡፡ ግንዛቤህን ሳላይ ደግሞ ስለ ምጠይቅህ ነገር ብቁ መሆንና አለመሆንህን መለየት እችላለሁ ማለት ነው፡፡ ቢያንስ መልሱን ማግኘት ባትችል ጥያቄውን የመሸከም ብቃት አለኽ ማለት ነው፡፡ እሽ ተመልከት እስቲ ይኽን እሑድ የሥነ ፍጥረት ዕለት የተባለውን ሃሳብ ‘ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ፤ምድር ግን ባዶ ነበረች፤አትታይም ነበር፤የተዘጋጀችም አልነበረችም፤ጨለማ በውኋው ላይ ነበረ፤የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይ ይንሳፈፍ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ብርሃን ይኹን አለ፤ ብርሃንም ሆነ፡፡(ኦ.ዘ 1፡1-3) ’ይኽን ታምናለህ አይደል” አለኝ፡፡ “ አዎ ይህንማ አምናለሁ፡፡ ከዚህ በፊት እንደተከራከርነው ከነ መጽሐፈ ኔኖክና ከነ ኢዮብ በፊት የሙሴ መጻሐፍት ቀድመው መጻፍ የለባቸውም ብንልም ይህን አምናለሁ፡፡ ታሪኩም የእሑድ ስነ ፍትረት ታሪክ ነው፡፡”አልሁት፡፡ “ እሽ መልካም እና ወደ ጥያቄየ ልምጣ ማለት ነው?” በስስትና በፈገግታ ዓይን ዓይኖቼን እያየኝ ነው፡፡ ቀጥታ ፊት ለፊት ነው ውይይታችን፡፡ “ እንግዲኽ ሃቅሜ የሚችል ከሆነ ጥያቄውን ለመመለስ አምላኬንም እማፀናለኹ፡፡ የማልችለው ከሆነም እተዋዋለኹ፡፡ ጥያቄው ግን መሰረታዊና በሐቅ ላይ የተመሰረተ ቢቻል የሚታይና የሚዳሰስ አሳማኝና ምክንያታዊ ጥያቄ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ”አልኹት፡፡ “ እሽ የኛ ተጠያቂ ከቻልኽ ፈልገው፡፡ ጨረቀና ፀሐይ የረቡዕ ፍጥረታት ናቸው እያልኽ እየተረክኽ ….ጨለማ በውኋው ላይ ነበረ፤የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይ ይንሳፈፍ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ፡፡(ኦ.ዘ 1፡1-3)’ ጨረቃና ፀሐይ ሳይፈጠሩ ይኽ ብርሃን የት መጣ ትላለኽ? ምንጭ፡- ገነት በኢትዮጵያ ‹ጓሮ› ናትን? ከኤረር ተራራ እስከ ሰማያዊ ኤረር ቁጥር 2 ገጽ 207-210 ደራሲ ዝጋለ አያሌው
نمایش همه...
ዓይንህን ግለጽ፤ ሀገርህን እወቅ፤ታሪከህን መርምር፤አንብበህ ስትጨርስ የሚሰማህን ጻፍልኝ ……..‹‹በል አሁን ተከተለኝ የሆነ ቦታ ይዠህ ልገባ ነው” አለኝ፡፡ “ ሊቁ ቆይ ወደ የት ነው ይዠኸኝ የምትገባው ” አልሁት እየፈራሁ፡፡ ሊቁ“ ተከተለኝ….አንድ መንገድ ላሳይህ”..ቆጣ ብሎ “ ዝም ብልህ ተከተለኝ” አለ፡፡ እኔም ዝም ብየ ተከተልኹት፡፡ የገባነው ከዚያ ካሳየኝ ማዕከለ ገነት ተብሎ ከሚጠራው ቀበሌ ፊት ለፊት የሆነ ዋሻ ነበር፡፡ ያ ዋሻ ወደ ላይ ወደ አዴት ግንባር የሚወስድ ይመስላል፡፡ ሽቅብ ወደ ፀሐይ መውጫ ነው የሚጓዘው፡፡ ከዚህ በፊትም በዚህ አካባቢ ተራራ የማርሄር ፈረስ ይታይበታል ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ነው፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ “ አትፍራ” አለኝ፡፡ ሊቁ“ ቆይ ምን እሆነ ነው? ወደ የት እየሄድነ ነው?” አልኹት በመጨነቅ፡፡ “ አትፍራ ተከተለኝ…ቆይ መንግዱ ጨለመብኽ እንዴት?” አለ፡፡ “ እስካሁን አልጨለመኝም፡፡ ሊቁ አንዴ ቆም በል እስቲ…ቆይ ወደ የት እምንሄደው…ቆይ ይኽ ኹሉ ነጸብረቅ ከየት የመጣ ብርሃን ነው? ይኽ ማራኪና ቀዝቃዛ ውኃ አዘል ንፋስ ከየት የመጣ ነው” አልሁት፡፡ ወደ ውስጥ እየገባ ነው፡፡ ሊቁ “ ሃምሳ ሜትር አካባቢ እንደሄድኹ ሊቁ ጠፋኝ፡፡ ድምጽ የለም፡፡ ፈራኹ…በጨለማ የተዋጠ ቦታ ማገኝ መሰለኝ፡፡ ቀዝቀዛ ነፋስና ጉም አዘል ነፋስ በዝግታ ሽው ሽው ይላል…ዋሻ ውስጥ ኮ ነው፡፡ ሊቁ ሲጠፋኝ ቆሜ ፈራ ተባ ስል “ ተመለስ ሌላ ጊዜ እንገናኛለን” አለኝ፡፡ ቀስ ብየ ወደ ኋላ ዞሬ ተጓዝሁ፡፡ ወደ ገባሁበት በር ላይ ስደርስ ሊቁ ቁጭ ብሎ አገኘሁት፡፡ እኔ ደንግጫለሁ፡፡ “ተረጋጋ! ይህ መንገድ ወደ ደብረ ሊባኖስና ወደ ኤረር ተራራ እንዲሁም ወደ ግሽ አባይ ይወስዳል፡፡ ተመልከት እዚያ ጉም የጋረደው ተራራ ስርም የማርሄርና የዲማስ ፈረሶች የሚኖሩበት ቦታ ነው ይባላል፡፡ወደ ፊት ስትሄድ ደግሞ በጣና ጭርቆስ አድርጎ ወደ ደብር ቅዱስ ይወስዳል፡፡ እዚያ ሽቅብ የምትመለከተው ተራራ ላይ ቅኔ ቤት አሥራ አራት ዓመት ተምሪያለሁም ፡፡ አቋቋም ተምሬበታለሁ አስተምሪያለሁም፡፡ ” አለኝ በጣቱ እየጠቆመ፡፡ እንግዲህ ኢትዮጵያና ገነት ጓሮና ጉሮኖ ናቸው፡፡ ቅድም ረጋ ብሎ ሲነፍስ የነበረው የተመጠነ ነፋስ….አሁንም እዚህ ላይ ተቀምጠን ቀስ ብሎ የሚነፍሰው ነፋስ…..የመሬት ነፋስ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ገነት በኢትዮጵያ ጓሮ ናትን? ጓሮ….ብዙ ቁልፍ አለው፡፡ ወንዙ ከኢትዮጵያ ይፈልቃል፤ወደ ገነት ይገባል…እንደገና ገነትን አጠጥቶ ወደ መሬት ይመለሳል….ገነት በኢትዮጵያ ጓሮ እንጅ በዓለም ጓሮ አይደለችም፡፡ ቁልፉ ያለው ሆማ ገደሉ ላይ ነው፡፡ ግዮን ከመሬት ፈልቆ ወደ ገነት ገብቶ ገነትን አጠጥቶ ወደ መሬት የሚወርድበት ቦታ ቁልፍ አለ፡፡ የጓሮው ቁልፍ በዚያ በኩል አለ፡ ምንጭ፡- ገነት በኢትዮጵያ ‹ጓሮ› ናትን? ከኤረር ተራራ እስከ ሰማያዊ ኤረር ቁጥር 2 ገጽ 295-296 ደራሲ ዝጋለ አያሌው
نمایش همه...
Hello
نمایش همه...
የመጽሐፍት ጥቆማ! ለአላነበባቺኃቸው ብቻ የተለጠፈ፡፡ የዝጋለ አያሌው መጻሕፍት በብዙ አንባቢያን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ 1 - ገነት በኢትዮጵያ ናትን? ከበርባሮስ እስከ ሃኖስ 2 - ገነት በኢትዮጵያ ‹ጓሮ› ናትን? ከኤረር ተራራ እስከ ሰማያዊ ኤረር 3 - ዘዌ ሲሆኑ እንዲሁም በቅርቡ ‘መክኑን በትር’ የሚል መጽሐፉን ለንባብ ይበቃል፡፡ 📌 በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም ለንባብ በበቃው “ ገነት በኢትዮጵያ ናትን? - ከበርባሮስ እስከ ሃኖስ ” በሚል መጽሐፉ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎችን ጠይቆ መልሶችንም ጠንቅቆ በምክንያታዊ ማስረጃም አርቅቆ አስረድቷል። መጽሐፉንም በጥያቄ ጀምሮ በጥያቄ ጨርሷል። 📌 ይህ መጽሐፉ ልዩ ነበር፤ ስለምን ብትሉ ከራስ በጀመረ ምክያታዊ ምርምሩ ነው። መላእክት በዕለተ እኁድ ካለመኖር ወደ መኖር እንደመጡ መጀመሪያ የጠየቁት ጥያቄዎችን ነበር፤ ማን ነን? ከየት መጣን? ማን አስገኘን? ብለው ነበር፤ ትዕግስትን ገንዘብ አድርገው የጠየቁትም ብርሃን በላያቸው ሲመላ ብርሃኑ እውቀት ሆኗቸው በፍጹም ምስጋና አመስግነዋል። 👉 እኛም ከዚሁ ትምህርት ልንወስድ ይገባናል፤ ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ መልሱንም በትዕግስት መፈለግ ይገባናል ፡፡ 👉 ‘ገነት በኢትዮጵያ ናትን?’ መጽሐፍ በ21 ምዕራፎችና በ298 ገጾች የተከፈለ ሲሆን ከዳሰሳቸዉ አርዕስቶች ውስጥ፦ 💥 ስለ ገነት መገኛ ፍንጭ የምትሰጠው ዕፀ ለባዊት ተብላ ስለምትጠራው ዕፅ ምስጢር፤ ይህች የወንድና የሴት ፆታ ስላላት ዕፀ ለባዊት ተፈጥሮ፣ ዝርያ፣ መገኛ ታትቷል። 💥 ስለ መሴ የመሬት ዕርስት መነፈግ ምክንያት፣ እንዴትና ማን እንደቀበረው፣ 💥 በተፈጠሩበት ቦታ ምንም ሳይንቀሳቀሱ ስለቀሩ ፍጡራን፤ በተጨማሪም ተረፈ ምግብና ተረፈ መድኃኒትነት የሚያገለግሉ ዕፅዋት ዝርዝር በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ጥናቶች ተቀምጠዋል። 💥 ስለ ሰባቱ ሰማያት መገኛ፤ አስራ ሁለቱ ዞዲያክ ኮከቦች ምንነታቸውና ጥልቅ ምስጢራቸው 💥 ክርስቶስ ያስነሳው አልዓዛር መቃብር መገኛ ቦታ፤ እስራኤል? ወይስ ኢትዮጵያ? 💥 ከዘንዶ ራስ ላይ ጤፍ መቼ፣ የትና እንዴት እንደበቀለች 💥 ከዓለም ተደብቀው የሚገኙት ግሩማን ብሔሞትና ሌዋታን የት እንደሚገኙ እንዲሁም አቡነ ዘርዓ ብሩክ የት አግኝተው ጥርሳቸውን ቆጥረው እንዳስታረቋቸው፤ በሃገራችን በገጠራማው ስፍራ ‘ጦሮ’ ስለሚባለው አውሎ ነፋስ መነሻ ምክንያት፤ 💥 እንዲሁም ጅራታቸው የሚገኝበትን ውኃ ውጮቹ ሊመጡት ብለው ይሄን ካደረግን ዓለም ትጠፋለች ብለው ሁሉንም በምስጢር ይዘው እንደሄዱ በሚገርምና ሁላችሁም በምትደነቁበት ሁኔታ ተዳሷል። 💥 የዳይነሰር መጥፊያ ምክንያት፤ ከ290 ሚሊዮን ዓመት በፊት ጠፋ? ከገነት ጋር አብሮ ተሰወረ? ከሰማይ በተወረወሩ ከዋክብት ጠፋ? ወይስ በረሃብ አልያም በሌላ ፍጥረት ጥቃት ጠፋ? የሚለው በአጭሩ ተዳሷል። 💥 የፀሐይና የጨረቃ ግርዶሽ እውን ሊከሰት ይችላል ወይስ አይችልም? 💥 ገነትና አዳም በኢትዮጵያ ጎጃም ያስቀመጧቸው እውነታዎች፤ጎጃም አራራት ተራራ ስለሚገኘው የኖኅ መቃብርና የኖኅ ትውልድ ከተሞች እንዲሁም እግዚአብሔር በኢትዮጵያው ደብረ ዘይትና ናዝሬት ስለማስተማሩ 💥 አዳም በውኃ ውስጥ አርባ ቀን ከጸለየ አዳም(ሰው) አሳ ነውን? 💥 ገነት በሄኖክ፣ በኩፋሌና በዓለም አቀፍ ምሁራን እይታ 💥 ዓባይና ጣና ለ5000 ዓመታት ያልተቀላቀሉበት ድንቅ ምስጢር 💥 ገነት በኢትዮጵያ ጉያ! 👉በውስጡ ብዙ ምስጢራትን ይዟል ገዝታችሁ ብታነቡት ብዙ ምስጢራትን ታገኙባቸዋላችሁ። መንፈሳዊ ብርታትም ታገኙባቸዋላችሁ። መልካም ጊዜ!
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.