ኦርቶዶክስ መዝሙር(Ortodox Mezmur)
رفتن به کانال در Telegram
በእንግድነቴ አገር ሥርዐትህ መዝሙር ሆነችኝ።መዝ-118:54 ሸር በማድረግ ተባበሩን👇👇👇 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21
نمایش بیشتر7 406
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-227 روز
-4230 روز
آرشیو پست ها
☦️መልካሙ ገበሬ☦️
ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ
ለስልሶላት ነበር ሃይማኖት መሬቱ
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ስርዓቱ
ተነቅሎላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ
አዝ=====
ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች
ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ
ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ
አዝ=====
ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት
ጠባቂ መልዐኳ ተማጸነላት
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት
ታፈራ እንደሆነ ለዓመት እንያት
አዝ=======
ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች
ቀሲስ ዳዊት ፈንታዬ
✝️ከወደዱት✝️ሼር ያድርጉት↗️
https://t.me/OrtodoxMezmur121
✞ ማርያም_ድንግል_ለባሲተ_ሞገስ
ማርያም ድንግል ለባሲተ ሞገስ
ልጅሽ ስለሆነ መድኃኒት ለነፍስ
ከጠፋበት ቦታ ልቤን ይመልስ
ግርማ ያለሽ ድንግል ስምሽ ተወደደ
ዓለሙ በሙሉ ለክብርሽ ሰገደ
ጉድፍ ቢሞላበት በይፀዳም ሕይወቴ
ከእቅፍሽ አታውጪኝ ድንግል እመቤቴ
አዝ----------------
ትውልድ ይጠራሻል ብፅዕት እያለ
ድንግል የት ይገኛል አንቺን የመሰለ
የጨነቀው ሁሉ ሰአሊ ለነ ብሎ
መልስ ያገኝብሻል ልቡን ላንቺ ጥሎ
አዝ----------------
የዚህ ዓለም ገዢ ወጥመድ ሳይጥለኝ
የስጋ ፈተና ሳይጠላልፈኝ
የሰላሙን መረብ ወደኔ ጣይና
ለልጅሽ ልገዛ ዛሬም እንደገና
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
https://t.me/OrtodoxMezmur121
✞ ማርያም_ድንግል_ለባሲተ_ሞገስ
ማርያም ድንግል ለባሲተ ሞገስ
ልጅሽ ስለሆነ መድኃኒት ለነፍስ
ከጠፋበት ቦታ ልቤን ይመልስ
ግርማ ያለሽ ድንግል ስምሽ ተወደደ
ዓለሙ በሙሉ ለክብርሽ ሰገደ
ጉድፍ ቢሞላበት በይፀዳም ሕይወቴ
ከእቅፍሽ አታውጪኝ ድንግል እመቤቴ
አዝ----------------
ትውልድ ይጠራሻል ብፅዕት እያለ
ድንግል የት ይገኛል አንቺን የመሰለ
የጨነቀው ሁሉ ሰአሊ ለነ ብሎ
መልስ ያገኝብሻል ልቡን ላንቺ ጥሎ
አዝ----------------
የዚህ ዓለም ገዢ ወጥመድ ሳይጥለኝ
የስጋ ፈተና ሳይጠላልፈኝ
የሰላሙን መረብ ወደኔ ጣይና
ለልጅሽ ልገዛ ዛሬም እንደገና
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
✝️የኔ መሃሪ ✝️
የኔ መሀሪ ሁሉን መርሻዬ
ሁሉን መርሻዬ
እንደ ህልም አልፏል ትናንትናዬ
ባንተ ጌታዬ...(2)
አዝ.....
አዳፋው ልብሴ ከነፃ
ከእዳ ከፈታኝ በነፃ
የፅድቁ ባሪያው ሆኛለው
ሳገለግለው ኖራለው።
የእንባ ዘለላን ያቀፈው
አይኔም እልልታ ተረፈው
ደልዳዩ መዳፍ ደርሶሎኝ
ተራራው ሜዳ ሆነልኝ።
አዝ.....
አይኖቼን ከጉድ ጋርዶልኝ
ክንዶቼን በእጁ ይዞልኝ
ከእግሬ በታች ነው ወጀቡ
አሁን ታይቶኛል ወደቡ።
ሰላም ይነፍሳል ዙሪያዬ
እረፍት ሆኖልኝ ጌታዬ
የባረከኝን ባርኬ
ተለወጠልኝ ታሪኬ።
አዝ.....
ብርሃንህ ገፏል ድቅድቁን
በልቤ ተክሏል ሰንደቁን
ተቆጣጥሮኛል መውደዱ
መንገዴ ሆኗል መንገዱ።
ያበቃው ነገር ቀጥሏል
ጭንቄ በሞቱ ተሰቅሏል
የእየሱስ ሆኜ ምን አጣሁ
ሁሉን በስሙ ተወጣሁ።
አዝ.....
እንደኔ ማንን ታግሷል
ይቅርታ ፍቅሩን አልብሷል
ማይገባኝን አድርጎ
ያሳለፈልኝ ሸሽጎ።
መልካም ነው ለኔስ መልካም
ፀጋው ያገዘኝ ስደክም
ሞትኩኝ ስል ምህረት ደርቦ
አቆመኝ በህይወት አስዉቦ።
ዘማሪ ገ/አምላክህ ደሳለኝ
https://t.me/OrtodoxMezmur121
✞ በመከራ ጽና ✞
በመከራ ጽና በመከራ ጽና በፈተና ጽና
ለጊዜው ነው እንጂ ሁሉም ያልፋልና /፪/
አዝ ========
ኢዮብ ተጨነቀ በጣም ተማረረ
በመከራው ብዛት ትዕግስትን ተማረ
ልጅ የሌለው ሆነ እጣንብረቱን
በመከራ ጸና አልካደም አምላኩን
አዝ ========
መፈተን መልካም ነው ያነጣል እንደወርቅ
በመጨረሻው ቀን በክብር እንደትደምቅ
አንዱን ሳትሻገር ሌላው ቢገጥም
በሕይወት ዘመንህ መከራው ያንተው ነው
አዝ ========
ከአምላክህ ተስማማ እራስህን አዋርድ
በቃሉ ተመራ እንደፈቃዱ ሂድ
ዋጋህ ከአምላክ ዘንድ በሠማይ አለና
በርታ ክርስቲያን ሆይ በመከራ ጽና
ዘማሪት ፋሲካ መኮንን
✞ ኒቆዲሞስ
ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር (፪)
በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምሕር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትሕትና ተዋርዶ አደረቀ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ
ከመቅደሱ አንቀጽ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
መዝሙር
ዲያቆን ቀዳሜጸጋ