LEARN TECH ||ethiopia ®
رفتن به کانال در Telegram
We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share
نمایش بیشتر1 495
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-107 روز
-5530 روز
آرشیو پست ها
'ሙሽሪትን ማን ገደላት?'
(ኑዕማን ኢድሪስ)
ለስራ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ ሶዶ እየሄድኩ ነው 🚖 ድርጊቱ የተፈፀመው ከዛሬ 5 አመት በፊት ነው።
ሰርጉ 8 ቀን ቀርቶታል አብሹ፣ ቀሪቦ/ቡቅሪ፣ እህል ፈጨታው ባብዛሀኛው ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ነው።
ሰአዳ ልታገባ ቀናቶች ይቆጠራሉ እጮኛዋ ከድር በአካባቢው ወግ ልማድ መሰረት ማድረግ ያለበትን የጆሮ፣ የጣት ወርቅ ና ልብስ የመሳሰሉ ነገራቶች ተገዝተው ጨርሰዋል።
ሰአዲ ሚዜዎቿ ጋር ለሰርጉ ወይባ በመሞቅ ቅቤ መቀባት ከጀመረች ሰነባብታለች። አምሮባታል!
ሰአዳ ድሮም ምን ይወጣላታል?። ያ ፈረንጅ የሚያስንቅ ቅላቷ፣ ቀጥ ብለው በቆመው አፍንጫዋ፣ መሬት ሊደርስ በሚያቃጣው ፀጉሯ ፣ መስታወት በሚያስንቀው ተረከዟ ይበልጡን ፍክት ብላ ጨረቃ መስላለች።
ዘመድ አዝማድ ከየቦታው መሰባሰብ ከጀመረ ሰነባብቷል። ዛሬ ግን ያልተጠበቀ ሰው ብቅ አለ ሙህዬ። ሙህዬ ሁሌ ክላሽ፣ ጠመንጃ እና ጩቤ ከእጁ የማይጠፋ በሁሉ የሚፈራ አከባቢዉ ላይ አለ የሚባል ጀግና (በአካባቢው አጠራር ሽፍታ) ሲሆን ለሰአዳ ደግሞ አጎቷ ነው። ሙህዬ ትክክለኛ ስሙ መሀመድ ሲሆን ስሙን ያቆላመጡት በፍራቻ ይሁን በውዴታ አይታወቅም።
ዛሬ ለየት ያለ ቀን ነበር ሰርግ'ማይደል! ሁሉም ተሰብስበው ጨዋታ እያፈኩ፣ ልጆች እየጨፈሩ ሰፈሩ ድምቅ ብላል። ምሽት 1 ሰአት ተኩል ገደማ "እርርርርርርርይ" የሚል ድምጽ ተሰማ። ከርቀት ነበር። ጩኸቱ እየቀረበ መጣ፤ ሁሉም እየሮጠ ወጣ አንዲት ወጣት ቀሚሷ በደም እርሷል መሬት ላይ ተዘርራለች ሁሉም የሚያዩትን ማመን አቃታቸው። አንገቷ ላይ ያለው ደም መሬቱን ሞልቶታል። ሁሉም የሚያደርገውን አያቅም። እሪታው እየሞቀ ቀለጠ።
ሰአዳ ነበረች። ሙሽሪት ተደፍራለች ከዛም በአሰቃቂ ሁኔታ ተገላለች። ለደስታ የተሰበሰበው ዘመድ አዝማድ በመደናገጥ፣ በሀዘን ፣ በቁጭትና ግራ በመጋባት የሚያደርገውን አያቅም።
ሙሽሪትን ግን ማን ገደላት? የሁሉም ጥያቄ ነበረ!
ከሳምንታት ቡሀላ.....
ሁሉም ሰከን አለ ሀዘኑ ከልብ ባይወጣም ቁጭቱ ቢያንገበግብም ነገር ግን ማን ገደላት የሚለው ጥያቄ አሁንም እንደቀጠለ ቀናቶች ተቆጠሩ። የሁሉም ሀዘን ይለያያል። እንዴት ይሆኑ ይሆን የእጮኛዋ፣ የእናቷ ና አባቷስ ነገር?
ከሁሉም ግን ሀገር ያንቀጠቀጠው ሚኒሾች ሳይቀር የሚፈሩት ሙህዬ እንዴት ተደፈረ? እንዴት ተናቀ? የሚለው ሀሳብ በማሰላሰል እንቅልፍ ያጣው አጎቷ ግን ሀዘኑን ዋጥ አድርጎ በብዙ መንገድ ነገሩን በማጣራት ያላረፈው ሙህዬ አንድ ወሬ ከሳምንታት ቡሀላ ጆሮው ይገባል። «ይገለኛል ብየ ፈርቼ እንጂ አውቀዋለሁ» ብላለች አሉ ሰሚራ ሲል ጓደኛው ይነግረዋል።ሰሚራ የሟች ሙሽሪት አንደኛ ሚዜና የልብ ጓደኛ ናት።
ይህን ጊዜ ነበር ከነበነረበት ብድግ ብሎ ጊዜ ሳያጠፋ የተነሳው። "ሰሚራ የ ሰአዳ እናት እየጠሩሽ ነው" ትንሹ ወንድሟ ነገራት።
ሰሚራ በልጅነት እግሯ የሟች ጓደኛዋን እናት ጥሪ አክብራ ጊዜ ሳታጠፋ ነበር የሄደችው። ቤት ስትደርስ እማማ ዚነት ነጭ ጋቢያቸውን አጣፍተው በሀዘን ኩርምት ብለው ቤታቸው በር ላይ ባለ መደብ ላይ ቁጭ ብለዋል። «እታለም ጠራሁኝ» ስትጠራቸው እንደዚህ ነው። «አዎ ልጄ ነይ'ስኪ» ትንሽ ካወሩ ቡሀላ «እስኪ ልጄ ለሰአዳየ የገዛችሁትን ጥሎሽ አምጭልኝ እንግዲህ እኛ ጋ ምን ይሰራል እንመልስለት» አሉ ከአይናቸው እንባ ዱብ ዱብ እያለ። "ሳጥኑ ውስጥ ነው?" ብላ ከጠየቀች ቡሀላ ለማጣት ወደ ጓዳ ገባች። ብዙ አልቆየችም በሩ ተዘጋ። ሙህዬ ነበር የሰአዳ አጎት ኮስተር ብሎ "ቁጭ በይ"
"እሺ ጋጋጋሼ ምን አጠፋሁ? " አለች በድንጋጤ
"አበባን ማን ነው የገደላት? "
"እኔንጃ" ብላ መለሰች። መሳሪያውን ካስቀመጠበት አነሳ "አሁንስ አትናገሪም? "
"ይገለኛልኮ አስፈራርቶኛል"
"ካልነገርሽኝ አንቺ እንዳስገደልሻት ነው። እኔ ነኝ የምገልሽ" መሳሪያውን አቀባበለው።
"እሺ እሺ ጋጋሼ እነግርሀለሁ ሰይድ ነው"
"እ? "
ወሬዋን ቀጠለች "ሰይድ .. ሰይድሳ የሸሆቹ ልጅ! ያሳ መጀመሪያ ጠይቆ አይሆንም ለሱ አንሰጥም፤ አይሆናትም ተብሎ የተከለከለው።
"የሸሆቹ ልጅ? እኮ እሱ እኔን ንቆ? እዚሁ ሰፈርማ የሚውለው ተይ እንዳታሳስቺኝ? ድሮምኮ ቃልቻ ልጅ አይወጣለትም አባቱ ኪታብ ይዘው ሀገር ያቀናሉ እሱ መሳሪያ ተሸክሞ መንደር ለመንደር ቡና እየጨለጠ ሴት ያባልጋል። አላወቀኝማ!" አለ በቁጣ።
እሱ መሆኑን ካረጋገጠ ቡሀላ እሱን መከታተል ጀመረ ብዙ አልቆየምቡና ሊጠጣ ሲገባ አገኘው።
መሳሪያውን አጠገቡ ላለው ጓደኛ ያዝ አለውና እሱ ያለበት ቤት ገባ።
ከዚህ ቡሀላ ሙህዬ (የሟች አጎት) እንዲህ ሲል ነገረኝ!
«ሰይድ(ገዳይ)ቆሎ እየቆረጠመ ወሬውን ያፈካል።
ሰላም ብየ ገባሁኝ። ፈገግ ሲል ፈገግ አልኩለት።
እየሰረቀ ያየኛል።
እንደማውቅ አያውቅም፣ መሳሪያ እንዳልያዝኩ ስላወቀ ትንሽ ተረጋግቷል። 'ፊቱ ያለውን ቆሎ ልዘግን ተነሳሁ። አጠገቡ ስደርስ ዘልዬ አነቅኩት እንደተያያዝን ጓደኛየ ዘሎ ገባልኝ። መሳሪያውን ተቀበልኩት አውቶማቲክ ነው የለቀኩበት። ከጭንቅላቱ ጀምሬ እስከ ቆ*ጡ። ሰውነቱ ለሁለት ተከፍሎ ሳየው ነው የረካሁት።
...
ወላሂ ያኔ ነው ከልቤ የተደሰትኩት»
ፊቱ ላይ የደስታ እና ኩራት ይነበብበታል። ይህንን ታሪክ ከ 5 አመት በፊት አካባቢ እስር ቤት ያገኘሁት ጀግና ና ትሁት ሰው ሙህዬ ነገረኝ።
◉◎◦ ማሳሰቢያ ፦ ይህ ታሪክ ሁሉም እውነተኛ ነው! ◦◎◉
አልቋል
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
THE RED RIVALRY!የማንቸስተርን የቅርብ ጊዜ አሰልጣኞች የሚበላው ቀዩ ጦርነት ! ትሪቡን ስፖርት
በፍቅር ይልቃል
ያዳምጡ JOin 👇
https://t.me/addlist/GQL25GSkxHw3ODM0
ስማኝ ይሄን ቤተሰብ እውነተኛ ወንድ ከሆንክ ብቻ ተቀላቀል ካልሆነ አኛ ለልፍስፍስ ቦታ የለንም
እውነተኛ ወንድ💪💪💪
ማየት ማመን ነው።እታች የተዘረዘሩት ቻናሎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ምርጥ ቻናሎሎች ናቸው። የሌለው ነገር የለም ፊልም,ሙዚቃ,እግር ኳስ, በቃ የሌለ ነገር የለም እና ምን ትጠብቃላችሁ አሁኑኑ ተቀላቀሉ እንጂ !!!
Add your channel @slimshady_Lp
ቤቲንግ እየተበሉ ከተሸገሩ አሪፍ ቻናል ላስተዋውቅዎ 100℅ Sure የሆነ ቻናል ነው እኔ ከምነግራችሁ ገብተችሁ እዩት!!!
ዳናይትን ማይወድ ሰው አለ ግን??
ለማንኛውም ለዳናይት አድናቂዎች የተከፈተ አዲስ ቻናል ስለሷ እና ስለሌላ ታዋቂ ሰዎች ሚያወራ ቻናል
አሁኑኑ ተቀላቀሉ ገብታችሁ ማትወጡበት ቻናል ነው
