fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
925
مشترکین
+224 ساعت
+27 روز
+830 روز
آرشیو پست ها
ነሐሴ 12/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2018 ዓ.ም መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ ተማሪዎች ምዝገባ ስራ በሁሉም ትምህርት ቤቶች በዛሬው ዕለት ተጀመረ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በምዝገባውም በመደበኛ ትምህርት ዘርፍ 31 ሺህ 743 ተማሪዎች ለመመዝገብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት አስታውቋል። የወረዳው ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ኬኔ ዕድሜያቸው ከ5-6 ዓመት የደረሱ የቅድመ-አንደኛ ተማሪ ቅበላ ዕቅድ ወንድ= 3ሺህ 736 ሴት= 3ሺህ 311 ድምር= 7ሺህ 47 ተማሪዎች ለመመዝገብ መታቀዱን ጠቅሰው ከ1ኛ-6ኛ ክፍል ወ=13ሺህ 160 ሴ=11ሺህ 442 በጠቅላላው 24ሺህ 602 እንዲሁም ከ7ኛ-8ኛ ክፍል ወ=2ሺህ 376 ሴ= 2ሺህ 104 ድምር 4ሺህ 481 ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ወ=15ሺህ 536 ሴ=13ሺህ 546 ድምር 20 ሺህ 83 ተማሪዎች ይመዘገባሉ ያሉት ኃላፊዉ ከ9ኛ-12ኛ ወ=1ሺህ 374 ሴ=1ሺህ 287 በድምሩ 2ሺህ 661 ተማሪዎች ብሎም ከ1ኛ-12ኛ ክፍል ወ=16ሺህ 910 ሴ=14ሺህ 833 በጠቅላላው 31ሺህ 743 መደበኛ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ ተይዞ ወደ ተግባር መገባቱን አቶ አለማየሁ ኬኔ ገልፀዋል። ከዚሁ በተጨማሪም መሠረታዊ የተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርትን ምዝገባን አስመልክተው እንዳሉት ወ=1ሺህ 904 ሴ=2ሺህ 856 በድምሩ 4ሺህ 760 የብርሃን ተመዛኝ ተማሪዎች ወ=1ሺህ 856 ሴ=3ሺህ 200 በድምሩ 5ሺህ 56 ተማሪዎችን ጨምሮ የክህሎት ሠልጣኝ ተማሪዎች ደግሞ ወ=1 መቶ 70 ሴ=2 መቶ 50 በድምሩ 4 መቶ 20 ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ኃላፊው አስታውቀዋል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ በገደባኖ 1ኛ ደረካ ትምህርት ቤት ተገኝተው እንደገለጹት በትምህርት ዘመኑ የተያዘውን የተማሪ ቅበላ ተግባር ሁሉም አካል በባለቤትነት ወስዶ በመተግበር ማሳካት እንደሚገባው አሳስበዋል። የተለያዩ አደረጃጀቶች፣የትምህርት አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት አቀናጅቶ በመስራት በትምህርት ዘርፉ የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ሚፍታ አረቦ አክለው ገልጸዋል። አንዳንድ መምህራን በሠጡት አስተያየት የተማሪ ቅበላ ስራውን አጠናክሮ በማስቀጠል በወረዳ ደረጃ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ከወትሮ በላቀ መልኩ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ነሐሴ 11/2017 ዓ.ም 👉🏼‎የተማሪዎች ቅበላ ተግባር በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ማሳካት እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የፌዴራልና የክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከመረጣቸው ህዝብ ጋር የውይይት መድረክ አካሄዱ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎'በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ " በሚል መሪ ቃል በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የክረምት በጎ ፍቃድ የደም ልገሳ መረሃ ግብር በመሃል አምባ ከተማ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የመሀል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እና ከወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በጋራ ያዘጋጁት የክረምት የአጭር ጊዜ ስልጠና ተጠናቀቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የሐይማኖት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በመወጣት የሰላም እሴቶችን ለትውልድ ለማስረጽ የሚደረገውን ርብርብ ማገዝ እንዳለባቸው ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን የስነ-ምግባር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ከወረዳው የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኦፊሰር የጋራ የውል ስምምነት ገብተዋል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከጅማ ወለኔ ከተማ 1.2 ኪ.ሜ የውስጥ ለውስጥ መብራት ዝርጋታ እና የጥልቅ ጉድጓድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ወደ መብራት ለመቀየር 4 ኪ.ሜ የዝርጋታ ስራ እየተጠናቀቀ ይገኛል 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ጠቅላላ አመራር በወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት አደረገ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨

ነሐሴ 09/2017 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ ተግባር በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ማሳካት እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለፀዉኣው የወረዳው ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት የ2017 ዓ.ም የክረምት ተግባር አፈፃፀም እና የ2018 ዓ.ም የተማሪ ምዝገባ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በተካሄደበት ወቅት ነው። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ትምህርት ለአንድ አካባቢ ሁለንተናዊ ዕድገት የአንበሳውን ድርሻ ይጫወታል። ዜጎችን አሟጦ ወደ ትምህርት ማስገባት ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የተማሪዎች ቅበላ ተግባርን በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ማሳካት እንደሚገባ ጠቁመው በየደረጃው ያሉ አካላት በጋራ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል። የወረዳው ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ኬኔ የ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት የ90 ቀን ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 ዓ.ም የመደበኛና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ቅበላ ሠነድ አቅርበዋል። የተማሪዎች ምዝገባ ስራን በተያዘለት ጊዜ ሠሌዳ መሠረት ለማሳካት ቅንጅታዊ አሰራራችንን በማጎልበት ከወትሮ በላቀ መልኩ እንደሚሰሩ፣ የመምህራን ዕጥረት ችግር አቅም በፈቀደ መጠን ሊፈታ እንደሚገባ፣ የትምህርት ስብራትን ለመሻገር አፅንኦት ሰጥተን እንሰራለን፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ የሚሉት ተሳታፊዎች ካነሷቸዉ ሃሳብና አስተያየቶች መካከል ይጠቀሳሉ። የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ያሲን በመድረኩ በማጠቃለያቸው ውጤታማ ነው ብሎ መውሠሰድ ይቻላል ብለዋል። በመሆኑም በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በጉድለት የተነሱ ሃሳቦች ላይ የቀጣይ ዕቅድ አካል በማድረግ በባለቤትነት ወስደው ሊሠሩበት እንደሚገባ አሳስበዋል። አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው መንግስት የትምህርት ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ እገዛ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል። በአንፃሩ ከትምህርት ስብራት ፈጥኖ መውጣት እንደሚገባ ጠቅሰው በትውልዱ ላይ ሠፊ ስራ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል። አያይዘውም  የ2018 ዓ.ም መደበኛ እና መደበኛ ያልሆነ የተማሪዎች ቅበላ ተግባር በተያዘለት ጊዜ መሠረት ማሳካት እንደሚገባ አሳስበዋል። የወረዳው ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ኬኔ የውይይት መድረኩ ውጤታማና አበረታች ግብዓቶች የተገኘበት እንደነበር ጠቅሰው ግብዓቶችን ወስደን እንሠራለንም ብለዋል። በአንፃሩ የዘንድሮ ዓመት የተማሪ ምዝገባ ተግባራትንም ሆነ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙ አካላት የጋራ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የፌዴራልና የክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከመረጣቸው ህዝብ ጋር የውይይት መድረክ አካሄዱ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በውይይቱ ላይ የሃገር ሽማግሌዎች፣የሃይማኖት አባቶች፣ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በዚህ ወቅትም በኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ወይዘሮ ሳዲያ ተማም ባደረጉት መክፈቻ ንግግር እንዳሉት የህዝብ ውክልና ስራ ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ ለጥያቄዎች የተሰጡና ህዝብ በየደረጃው ላለው አስፈፃሚ አካላት መረጃ መስጠትና በክረምት ወቅት ባሉት የፌዴራልና በየደረጃው ያሉ ተቋማት የሚነሱ ተጨማሪ የህዝብ አስተያየቶችና ጥያቄዎች መቀበል ማስቻል የመድረኩ ዋና ዓላማ መሆኑን ገልፀዋል። ውይይቱ በተደረገበት ወቅትም ከመሰረተ ልማት ተደራሽነት ጋር በተያያዘ የመብራትና የኔትዎርክ ሽፋን፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድ ቀሪ ተደራሽ ስራዎች ቀበሌን ከቀበሌ፣ ቀበሌን ከማዕከልና ሌሎችም፣ የአስፓልት መንገድ ዝርጋታ ጥያቄ ከመሃል አምባ-ኢንጌ-ጅማ-አገና፣ ከተሞችን በሚፈለገው ደረጃ ማልማት እንደሚገባ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ዝርጋታ፣ የተገነቡ መንገድ ልማቶችን በተገቢው መከታተልና መጠገን ያስፈልጋል ያሉት ተሳታፊዎቹ የትራንስፖርት ስምሪት በተመለከተ ከመሃል አምባ-አረዳ፣ ከቱሉ ቦሎ-መሃል አምባ ላብነት የተነሱ ሲሆን  የመሃል የመሃል አምባ ከተማ አስተዳደርነት ጥያቄ ምላሽ ላይ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ፣ የግብርና ግብዓት ማዳበሪያ አቅርቦት ውስንነት ችግር እንደሚስተዋልና መፈታት እንደሚኖርበት በተጨማሪም የመንግስት ሠራተኞች የማዐጤመ አገልግሎት ተጠቃሚነት ጥያቄ ምላሽ በአፋጣኝ እንዲሰጠው፣ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች በሚፈለገው ደረጃ ሊቋቋሙ ይገባል የተባለ ሲሆን የማንነት እና የቋንቋ ጉዳይ ግልፀኝነት እንዲፈጠርባቸው በማንሳት የተጀመረውን የሠላምና ልማት ስራችንን ከብልፅግና መንግስት ጎን ተሰልፈን አሁን ካለበት ደረጃ በበለጠ መልኩ አቀጣጥለን እናስቀጥላለን የሚሉት ከተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች መካከል በዋናነት ተጠቃሾች ናቸው። የፌዴራል ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ወይዘሮ ሳዲያ ተማም በማጠቃለያ ወቅት እንደገለፁት የውይይት መድረኩ በርካታ ግብዓቶች የተገኙበትና ውጤታማ ነው ብሎ መውሰድ የሚያስችል ስለመሆኑ ገልፀው የብልፅግና መንግስት ህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚ ማድረግ ያስቻሉ ዘርፈ-ብዙ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በማከናወን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ሲሆን ልማቱ በቀጣይ ጊዜያት ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሚሆን በማንሳት ከውይይት መድረኩ የተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች ለሚመለከተው አካል ተደራሽ እንደሚደረጉም አስታውቀዋል። የክልልና የዞን ምክር ቤት አባል እንዲሁም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት አቶ ኸይሩ መሀመድ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ሲያነሳቸው የቆዩ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በተደረጉት ትግሎች ዉጤታማ ድሎች መመዝገባቸውን አውስተዋል። አክለውም ህዝቡ አንድነቱን አጠናክሮ በማጎልበት ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል። የክልልና የዞን ምክር ቤት አባል የሆኑት ወይዘሮ ነጅቢያ መህሙድ እንደገለፁት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታችን ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። አያይዘውም ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመቆም በሚዘረጉ ሁለንተናዊ ልማቶች ላይ በባለቤትነት ሊሳተፍ እንደሚገባው አንስተዉ ህዝቡ ያነሳቸውን ግብዓቶች ለሚመለከተው ተደራሽ እንደሚያደርጉና ለተፈፃሚነታቸው አፅንኦት ሠጥተው እንደሚከታተሉ ጠቁመው በአንፃሩ መላው ህብረተሰብ ከወትሮ በላቀ መልኩ አንድነቱን ማጠናከር ላይ ሊሠራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም 'በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ " በሚል መሪ ቃል በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የክረምት በጎ ፍቃድ የደም ልገሳ መረሃ ግብር በመሃል አምባ ከተማ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ " በሚል መሪ ቃል በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የክረምት በጎ ፍቃድ የደም ልገሳ መረሃ ግብር 26 ዩኒት ደም መሰብሰቡን የወረዳው ጤና ጽ/ቤት አስተወቀ። ክብር የሆነውን ደም በመለገስ የማይተካውን የሰው ህይወት በመታገድ በበጎነት ደም ልገሳ መረሃ ግብር ላይ የወረዳ አመራሮች፣የመንግስት ሠራተኞች እና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተሳፈዋል።

ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም የመሀል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እና ከወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በጋራ ያዘጋጁት የክረምት የአጭር ጊዜ ስልጠና ተጠናቀቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የመ/አ/ኮ/ኢ/ኮ ዋና ዲን ወ/ሪት ሰላማዊት ኡርባኖስ በስልጠናው ማጠቃለያ ወቅት እንዳሉት የመሀል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው ከነዚህም በICT ፣ በኮንስትራክሽን ፣ በጋርመንት፣ በፈርኒቸር፣ በአውቶሞቲቭ እና በሜካኔክስ ዲፓርትመንት በመደበኛ ፣በማታ እና ቅዳሜና እሁድ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው  በተጨማሪም የአጭር ጊዜ ስልጠና ቅዳሜ እና እሁድ ይሰጣል ብለዋል የዚህ አንድ አካል የሆነው የክረምት ስልጠና ከወረዳው ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በጋራ በመሆን በICT፣በካይዘን በኢንተርፕሪነርሺፕ ለተከታታይ ለ15 ቀን ስልጠና ሲሰጥ እንደቆየ ገልፀዋል ። የመ/አ/ኮ/እና /ኢ/ኮሌጅ ምክትል ዲን አቶ አ/ረዛቅ ሁሴን ባስተላለፉት መልዕክት የቴክኒክና ሙያ በራስ ፍላጎት ራሱን ማብቃት እንደሚገባ ጠቅሰው ሁሉም ቁጥራቸው 48 የሚሆኑ በየመስሪያ ቤቱ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች እና በየትምህርት ቤቱ ያሉ ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆን መቻላቸው ያወሱት ምክትል ዲን አቶ አ/ረዛቅ ሁሴን ስልጠናው ቀጣይነት ያለው በመሆኑ ሁሉም ስልጠና ፈላጊ መሰልጠን መቻል እንዳለበት መልዕክታቸው አስተላልፈዋል ። የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኸይሩ ዱግዳ በበኩላቸው ስልጠናውን መስጠት ያስፈለገው ተቋማት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን እርካታና አመኔታ ለማረጋገጥ ያለመ ስለመሆኑ ገልጸዋል። በንድፈ- ሃሳብ እና በተግባር ተደግፎ የተሰጠውን ስልጠና ከተለያዩ ሴክተሮች የተውጣጡ ባለሙያዎች በተሳካ መልኩ ማጠናቀቃቸውን ያወሱት ኃላፊው ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ ተጠቅመው ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው በማስገንዘብ መሰል ስልጠናዎች በቀጣይ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነም አስታውቀዋል።