fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
925
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+67 روز
+1130 روز
آرشیو پست ها
ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገ/ጉ/ወ/ወረዳ በ2017 ዓ/ም የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ78 ሺህ 70 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስጠቀም ህዝብና መንግስት ሊያወጣ ይችል የነበረውን 44 ሚሊዮን 568 ሺህ 395 ብር ማዳን መቻሉን የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በክረምት ወራት የተከናወኑ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ን በበጋ ወራት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተገልጿል። ጽ/ቤቱ የ2017 ዓ/ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያ እና የ2018 ዓ/ም የበጋ በጎ ፍቃድ መክፈቻ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት አከናውኗል። በዕለቱ የ2018 ዓ/ም የስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ ተካሂዶ ውሏል። በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸዉ እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የጀመሩት የበጎ አድራጎት ተግባር አሁን ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የእርስ በርስ ግንኙነት፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት ባህል ማጎልበት ያስቻለ ስለመሆኑ ጠቁመው በበጎ ተግባራት አማካኝነትም በወረዳችን በርካታ የማህበራዊ ችግር ያለባቸውንና ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ማስጠቀም እንደተቻለ በማንሳት በወረዳው የተያዙ የበጎ ስራዎች ተግባራት ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በተደረገው ርብርብ ወጣቶችና ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ባደረጉት እገዛ ሰፊ ቁጥር ያላቸውንና ማህበራዊ ችግር ያለባቸው ነዋሪዎችን ማስጠቀም ስለመቻሉ ገልጸዋል። አቶ ሚፍታ ሁሴን አክለውም በክረምቱ ወራት የተመዘገቡ ስኬቶችን በበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ በበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀው መንግስት እያደረገ ያለውን እገዛ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል አስታዉምውቀዋል። የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም በበኩላቸው የበጎ ፍቃድ ስራ ግዴታ ያልታከለበት፣ ዜጎች ከሰብዓዊነት አመለካከት ተነስተዉምው ነፃ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ እዉቀታቸውንና በጎ አመለካከታቸውን ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማት የሚያውሉበት ክዋኔ ነው ብለዋል። የበጎ ስራ በወረዳችን እንደ ባህል የተለመደበት ደረጃ ላይ መድረስ ችሏል ያሉት አቶ ሸምሱ መንግስት ለዘርፉ በሰጠዉ ልዩ ትኩረት “ በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል የ2017 ዓ/ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ውጤታማና ተጨባጭ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። በ17 የስምሪት መስኮች ላይ 39 ሺህ 655 ወጣቶች የተሳተፉ ስለመሆናቸው ያወሱት ኃላፊው ከ78 ሺህ 70 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስጠቀም ህዝብና መንግስት ሊያወጣ ይችል የነበረውን 44 ሚሊዮን 568 ሺህ 395 ብር ማዳን መቻሉን አብራርተዋል። አክለውም በ2018 ዓ/ም የበጋ በጎ ፍቃድ ስራ በ17 ዘርፎች 9 ሺህ 500 የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ 22 ሺህ ዜጎችን በማስጠቀም 8 ሚሊዮን 125 ሺህ 350 ብር ለማዳን መታቀዱን አስታውቀዋል። በየደረጃው የሚገኙ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸን አቅርበዋል። በመድረኩ ላይ የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ጀማል ናስር የ2017 ዓ/ም የክረምት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 ዓ/ም የበጋ ወራት እቅድ እንዲሁም የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አ/ረሂም ባልቻ የ2017 ዓ/ም የስፖርት ምክር ቤት ሪፖርትና የ2018 ዓ/ም የበጋ ወራት እቅድ አቅርበዋል። በምክክር መድረኩ ላይ በተካሄደው የስፖርት ምክር ቤቱ ጉባኤ አባላቱ ባደረጉት ሰፊ ውይይትና ምክር 3 ውሳኔዎችን አጽድቀዋል። ይኸውም 1ኛ የ2018 አመት የስፖርት ምክር ቤት በጀትን 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ሆኖ የጸደቀ ሲሆን 2ኛ የስፖርተኞች ውሎ አበል ቀደም ሲል ከነበረበት መሻሻሉን እና የምክር ቤቱን የ2017 ዓ/ም ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት የስራ ዘመን እቅድ በሙሉ ድምጽ ም/ቤቱ አጽድቋል። መድረኩን የመሩት የወረዳው ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳ ባስተላለፉት መልዕክት በክረምቱ ወራት በ17 የስምሪት መስኮች የተከናወኑ የበጎነት ማሳያ ስራዎች በልዩነት መመራት በመቻላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ በመሆን ተጠቃሚነታቸውን በተጨባጭ ማሳየት መቻሉን ጠቁመው በፓርቲው ልዩ ትኩረት ሰጪነት በ2018 ዓ/ም የበጋ በጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ በ17 የስራ ዘርፎች እቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቅሰው በየደረጃው የሚገኙ አካላት በክረምቱ የተገኙ ውጤቶችን በበጋ ወራትም ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። አቶ ሸምሱ ኢብራሂም በማጠቃለያቸው እንዳሉት በክረምቱ ወራት የበጎ ፍቃድ ስራ የተስተዋሉ ጉድለቶችን ለማረም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል። አያይዘውም በየደረጃው የመገኙ አካላት በበጎነት ያከናወኗቸዉ የበጎነት ማሳያ ስራዎች እውቅናቸው የላቀ ስለመሆኑ በመግለፅ በስፖርት ዘርፍ ያሉትን አማራጮች አሟጦ በመጠቀም ማልማት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በመጨረሻም በበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ በየደረጃው ለሚገኙ የመንግት ተቋማት፣ቀበሌዎችና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የተዘጋጀላቸውን የምስጋና ምስክር ወረቀት ከእለቱ ተጋባዥ አንግዶች ተቀብለዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የተቋማት ህብረት ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው። ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎"ከመስፈንጠር ከፍታ ወደ ላቀ እምርታ"በሚል መሪ ሃሳብ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የፐ/ ሰርቫንት የ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል። ‎መድረኩ የበጀት አመቱን አፈጻጸሙን ጠንካራና ደካማ ጎን በመፈተሽ በቀጣይ ወራት በትኩረት ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ከአባላት ጋር ውይይት ይካሄዳል። በኮንፍረንሱ የብልጽግነና ቤተሰብና ህብረቱ አመራሮችና አባላት የሚሳተፉ ሲሆን ለቀጣይ ተልዕኮዎች አባላቱንና አመራር አቅም በመፍጠር ዝግጁ ለማድረግ የሚካሄድ ይሆናል።

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "አንድም እናት በደም እጦት ምክንያት መሞት የለባትም! በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ እለት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እና የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ከሆሳና ደም ባንክ ጋር በመቀናጀት "አንድም እናት በደም እጦት ምክንያት መሞት የለባትም" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በመሀል አምባ ከተማ የወረዳ አመራሮች፣የመንግስት ሠራተኞች እና በጎፈቃደኛ ወጣቶች በማስተባበር 28 ዩኒት የደም ልገሳ ተደረገ።

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም የትምህርት ስብራትን ለመሻገር የሚደረገውን ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለጸው የወረዳው ት/ቤቶች ፅ/ቤት የ2017 ዓ/ም የትምህርት ሴክተር አመታዊ ጉባኤ መድረክ ዛሬ በተካሄደበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅትም የወረዳው ት/ቤቶች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ኬኔ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው እንዳሉት መንግስት የህብረተሰቡን የትምህርት ጥራት ለልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የትምህርት ተሳትፎ ለማሻሻል የሚያስችሉ ስልቶችን በመቀየር ሰፊ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል። አክለውም የውስጥ እና የውጭ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተለይተው በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ አለማየሁ ከገጠመን የውጤት ስብራት ፈጥኖ መውጣት እንዲቻል የተማሪ መጠነ መቅረት መጠነ ማቋረጥና መጠነ ቆይታ መሻሻል ላይ ሁሉም በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው መንግስት አዲስ ፍኖተ ካርታ በመንደፍ የትምህርት ሁለንተናዊ ለውጥን ለማረጋገጥ አፅንኦት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አቶ ሚፍታ ሁሴን ይህንን መነሻ በማድረግ በወረዳው እየተከናወኑ ባሉ የትምህርት ልማት ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበበት እንደሚገኝ ጠቅሰው በጉድለት የተስተዋሉ ውስንነቶች ላይ በመነጋገር የጋራ መግባባት ላይ መድረስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመድረኩ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ኬኔ 5ቱን የትምህርት ኢኒሼቲቭ እንዲሁም የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ አህመዲን ሰኢድ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አቅርበዋል። የመምህራን እጥረትና የትምህርት ግብዓት አቅርቦት ችግር፣ ምቹና ማራኪ ትምህርት ቤቶች ከመፍጠር ረገድ ውስንነቶች መኖራቸውን በውይይቱ ወቅት ተሳታፊዎች ካነሷቸዉ ሃሳብና አስተያየቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱናቸው። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ለተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን መንግስት ለዘርፉ ውጤታማነት እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ እገዛ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው ሁሉም አካላት ተቀናጅቶና ተደራጅቶ በመስራት የትምህርት ስራውን ማሻገር እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል። አቶ አለማየሁ ኬኔ በበኩላቸው ከመድረክ የተገኙ ግብዓቶችን በመድሰድ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሰራ ጠቁመው በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የአመራርነት ማናቸዉን በአግባቡ በመጫወት በትምህርት ዘርፍ የተያዙ ግቦች ለማሳካት የሚደረገውን ርብርብ ማገዝ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመጨረሻም በ2017 በጀት አመት በተለያዩ ዘርፎች የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ርመምህራን፣የጽ/ቤት ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀላቸውን የገንዘብና ሠርተፍኬት ከእለቱ እንግዶች አማካኝነት ተበርክቶላቸዋል።

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም የጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት የ2017 አመታዊ የትምህርት ጉባኤ ፕሮግራም በመሀል አምባ ከተማ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እና የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየው ኬኔ የእንኳን ደህና መጣቹ መልእክትና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አህመዲን ሰኢድ የ2017 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2018 በጀት አመት ዋና ዋና እቅዶች አቅርበዋል። በጉባኤው ላይ የወረዳ አመራሮች፣የ፣የቀበሌ ሊቀመንበሮች ፣ርዕሰ መምህራኖች፣የትምህርት ቤቶች ወተመህ አካላት፣የጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ የህዝብ ክንፍ አባላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ። ዝርዝር መረጃዎች ተከታትለን የምንደርሳቹ ይሆናል!!!