925
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+47 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላቹ!!!
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢንርጂ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ከዞን መዋቅሮች 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆን ችሏል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በተጨማሪም ሚድሮክ ኢንቨስትመነት ግሩፕ በወረዳው መሃል አምባ ከተማ ላይ ላስገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታዎች ከጉራጌ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢንርጂ መምሪያ የምስክር ወርቅት ተበርክቷለታል።
ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም
ሴቶችን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ በተጠናቀቀው በጀት አመት አበረታች ስራዎች መስራቱ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨
የሴቶች ውሳኔ ሰጪነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ መህዲ ገልጸዋል።
በ2017 በጀት አመት የሴቶችን የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሴቶች ልማት ህብረት እንዲደራጁ የተሰራ ሲሆን በበጀት አመቱ 23 ሺህ 880 ሴቶች በ796 የሴቶች ልማት ህብረት ማደራጀት መቻሉን ገልጸው 8 ቀበሌዎች በሞዴልነት ማስመረቃቸውን አስታውቀዋል።
ባለፈው በጀት አመት ለ250 ሴቶች የህግ ምክርና ድጋፍ መስጠት የተቻለ ሲሆን አገልግሎቱም የባልና ሚስት፣ የልጅ ቀለብ፣ የመሬት ይዞታ፣ ሁከትና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የተለያዩ ጥቃቶች ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን ኃላፊዋ አስታውቀዋል።
በወረዳው የሴቶች ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የግብርና ስራዎች ላይ በማሳተፍ ውጤታማ ስራ መሠረቱን የገለጹት ወ/ሮ ፈትያ መህዲ የሴቶች የቁጠባ ባህል እያደገ በመምጣቱ በበጀት አመቱ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ብር መቆጠብ የቻሉ ሲሆን የኢኮኖሚ አቅማቸው ይበልጥ እንዲዳብር በሌሎች የገቢ ማስገኛ ስራዎች እንዲሰማሩ ይሰራል ብለዋል።
የሴቶችና ህፃናት ውክልና ከማረጋገጥ አንፃር ሴቶች በአመራር ውሳኔ ሰጭነት ያላቸው ሚና እንዲጎለብት ማድረግ፣ የህፃናት ፓርላማ መቋቋምና ማጠናከር እንዲሁም ሴት ተማሪዎች በተለያዩ ክበባት ያላቸውን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መደረጉ ፅ/ቤቱ በበጀት አመቱ መከናወኑን ወ/ሮ ፈትያ መህዲ ተናግረዋል።
ለችግር የተጋለጡ ህፃናትና አቅመ ደካማ ሴቶች ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ሌላኛወ የፅ/ቤቱ ተግባር መሆኑን በመግለፅ ለ2 ሺህ 468 ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ፣ የአልባሳት፣ የገንዘብና የአስቤዛ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን 1,941,030 ብር በተለያዩ ሴክተሮች፣ በኃይማኖት ተቋማትና በግለሰቦች አማካኝነት በመሰብሰብ ድጋፍ መደረጉን ገለጸዋል።
በወረዳው የሚገኙ ሴት የመንግስት ሰራተኞች በተቋሞቻቸው ውጤታማ ስራ እንዲያከናውና ልጆቻቸው በአግባቡ መንከባከብ እንዲችሉ በአቅራቢያቸው የጡት ማጥቢያ ማዕከላት ከማስፋፋት አንጻር ውስንነት መኖሩን ጠቅሠው በተቋምቸው ደረጃ መዘጋጀቱን ያወሱት ኃላፊዋ ሌሎች ተቋማት ተሞክሮውን በመውሠድ በሴክተራቸው የህጻናት ማቆያ ሊያዘጋጁ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የሴቶችና ህፃናት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መከሰት፣ የሴቶች ውክልና እና ውሳኔ ሰጭነት ድርሻ አነስተኛ መሆን፣ ሴቶች በሚፈለገው መጠን የብድር ተጠቃሚ አለመሆን እንዲሁም በተለያዩ የወረዳው ክፍሎች አልፎ አልፎ ከወረዳውን ማህበረሰብ ባህልና ስነምግባር ባፈነገጠ መልኩ ሴት ልጆችን በማታለል ወይም በማስገደድ ጋብቻ መፈፀም የመሳሰሉት ችግሮች የሚያጋጥሙ መሆናቸውን በመጥቀስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት የሴቶችና ህፃናት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ወ/ሮ ፍትያ መህዲ በማስገንዘብ በ2017 የተመዘገቡ ውጤቶች ይበልጥ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
የትምህርት ጥራት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ የተቀረፁ 5 ኢንሼቲቮች ይፋ ሆኑ
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሁለተኛው የትምህርት ጉባኤ የትምህርት ጥራትን በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ የተቀረፁ 5 ኢንሼቲቮች ይፋ ሆኑ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )ኢንሼቲቮቹን አብስረዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በዚህ ወቅት እንዳሉት በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋሉ መሰራታዊ ችግሮችን በተለመደው አሰራር ብቻ መፍታት አይቻልም።
ለዚህም በክልሉ የትምህርት ጥራትን በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ የሚያግዙ 5 ኢንሼቲቮች መቀረጻቸውን ተናግረዋል።
የመጀመሪያው አንድ ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት በአንድ መንድር ኢንሼቲቭ ሲሆን ይህም በክልሉ በቅድመ 1ኛ ደረጃ ትራት ያለው ትምህርት በወጥነት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑም ጠቁመዋል ፡፡
2ኛው የንባብ ክህሎት ለትውልድ ኢንሼቲቭ ሲሆን ይህም የተማሪዎችን የንባብ ክህሎት በማዳበር የመማር ብቃትን ለማሳደግ ያስችላል ነው የተባለው፡፡
3ኛው የሒሳብ ትምህርት ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንሼቲቭ ሲሆን ይህም የተማሪዎችን የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራ ክህሎት ለማዳበር ያግዛል፡፡
4ኛው ዲጅታል ትምህርት ኢንሼቲቭ ሲሆን ይህም በክልሉ የትምህርት ዲጅታል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና አጠቃቀምን ለማሻሻል ያግዛል፡፡
5ኛው የትምህርት ቤት ሀብት ለትምህርት ጥራት ኢንሼቲቭ ሲሆን ትምህርት ቤቶች ያላቸውን ሀብት በአግባቡ ተጠቅመው ገቢ ማመንጨትና የትምህርት ማህበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላቸዋል ፡፡
ኢንሼቲቮቹ ከዘንድሮ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረጉ አቶ አንተነህ ጠቁመዋል።
ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከነሐሴ 01 ጀምሮ በከፊል ተዘግቶ የነበረውን የፍርድ ቤት አገልግሎት ዛሬ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በይፋ መደበኛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሰፊዩ ሱልጣን በስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው እንደገለፁት ላለፉት ሁለት ወራት ፍርድ ቤታችን በከፊል ዝግ ሆኖ ቆይቶዋል። በዚህ ወቅት የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብት እንዳይጣስ ጊዜ የማይሰጡ እና አስቸኳይነት ባህሪ ያላቸው የወንጀል እና የፍትሀብሄር ጉዳዮች ሲታዩ ቆይቶዋል።
በዛሬው ዕለት የሁለት ወር የዳኞች ዕረፍት ጊዜ ተጠናቆ መደበኛ ፍርድ ቤት ስራ በይፋ መጀመሩን ጠቅሠው ህብረተሰባችን ከዛሬ ቀን ጀምሮ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም ፍርድ ቤቱ የፍትህ ስርዓቱን ተደራሽ ለማድረግ ከመደበኛው ችሎት በተጨማሪም በስሩ ባሉት የኢንጌ፣የጅማ ወለኔ እንድሁም የእንደብዩ ተዘዋዋሪ ችሎቶች ቀድሞ በነበረው መርሃ ግብር መሰረት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት መልእክት
ዳኞችና መላው የፍርድ ቤቱ አጠቃላይ ሰራተኞች ቀልጣፋና ፍትሃዊ የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት በበጀት አመቱ የተሻለና ስኬታማ ስራ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በዛሬው ፕሮግራም ላይ የወረዳው ፍርድ ቤት ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በመንግስት ሰራተኞች የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የክረምት ወራት የእግር ኳስ ውድድር በባንኮች አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በፍፃሜ ጨዋታዉ ፋይናንስ እግር ኳስ ቡድን ከባንኮች የተገናኙ ሲሆን በመደበኛዉ 90 ደቂቃ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ተጠናቋል።
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት በባንኮች 5 ለ 4 በሆነ ውጤት ጨዋታውን አሸንፈው ውድድሩ ተጠናቋል።
በጫወታው ግቦቹን ለፋይናንሶች ታዬ ሀብቴ በ5 ኛው ደቂቃ ያስቆጠረ ሲሆን ለባንኮች ደግሞ የአቻነት ግቧን ደረሰ አበራ በ25 ኛው ደቂቃ ኳስና መረብ ማገናኘት ችሏል።
በውድድር ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም ለሻምፒዮኖቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ከዚሁ ውስጥም የእግር ኳስ ዉድድር፣ መረብ ኳስ፣ አትሌቲክስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ፓራ ኦሎምፒክና ሌሎች ስፖርታዊ ዉድድሮች እንደሚገኙበት አንስተዋል።
በዕለቱ ለኮከብ ተጫዋቾች፣ ኮከብ ግብ አግቢዎች፣ ኮከብ ግብ ጠባቂዎች፣ አሰልጣኞች እና ለውድድሩ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል።
ዉድድሩ በ5 ቡድኖች መካከል ሲካሄድ መቆየቱ ተገልጿል።
ጨዋታውን አ/ሰመድ አህመድ በመሃል ዳኝነት የመሩት ሲሆን ጂብሪል ሁሴንና አ/ሰላም በድሩ በመስመር ዳኝነት መርተውታል።
ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።
