918
مشترکین
+124 ساعت
+27 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
የካቲት 09/2018 ዓ/ም
ወጣቱ ስራዎችን ከማማረጥ ይልቅ ገበያ ላይ ባሉት የስራ አማራጮች በተገቢው በመሳተፍ እራሱን ቤተሰቡንና ሀገሩን ሊለውጥ ይገባል - አቶ ላጫ ጋሩማ
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ባለፉት ወራት በዞኑ ከ166 ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ የስራ እድል ለተሰማሩ ወጣቶች ማሰራጨት መቻሉ የዞኑ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡
"ክህሎት መር የስራ እድል ፈጠራ ለብልፅግናችን" በሚል መሪ ቃል የጉራጌ ዞን የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት የ2018 ዓ/ም የአንደኛ ግማሽ አመት አፈፃፀም በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዞኑ ስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት የወጣቶች የሥራ አጥነት ችግር በማቃለልና የህብረተሰቡ የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ በትኩረት ይሰራል፡፡
ወጣቶች የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የገበያ ክፍተት በመለየት ማምረት እንደሚጠበቅባቸው የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው አምራቾች በተለያዩ ከተሞች ምርቶቻቸውን የሚሸጡበት ሼድ በፍትሀዊነት ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑ አስረድተዋል።
ወጣቶች የዞኑ ማህበረሰብ ያካበተውን ጠንካራ የስራ ባህል እሴት በመጠቀም ጊዜያቸው፣ ጉልበታቸውና እውቀታቸው በማቀናጀት ለተሻለ ለውጥ ተግተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
አክለውም አቶ ላጫ በልየታ የተረጋገጡ ስራ ፈላጊ ወጣቶች በቂ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ በተለያዩ ጊዜያት የተሰራጨ ብድር በአጭር ጊዜ በመመለስ ለሌሎች ወጣቶች ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
በጉራጌ ዞን ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል በመፍጠር የዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ያሉት አቶ ላጫ ለዚህም የየአካባቢው ፀጋዎችን በተገቢው ለይቶ መጠቀም ላይ ያተኮሩ ስራዎች በስፋት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በበኩላቸው የስራ እድል ፈጠራ በተገቢውና በቅንጅት ከተመራ የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ችግር በመፍታት ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይቻላል።
በገጠር የሉ ባዶ መሬቶችን ለወጣቶች በመስጠትና በግብርና ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተጀማመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የጉራ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ያሲን የዜጎች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተለያዩ የስራ እድሎችን በመፍጠር አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
ይህንን ውጤታማ ተግባር በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል ስራ ፈላጊ ወጣቶች በመለየት በተለያዩ ዘርፎች ስልጠና እንደሚሰጣቸውም ገልፀዋል።
የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ለማነቃቃት እና ክፍተቶችን ለይቶ ለመሙላት፣ የገበያ ትስስር ለመፍጠር፣ እንዲሁም ውጤታማ የሆኑትን ለማበረታታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አቶ ሙራድ ገልፀዋል፡፡
የዞኑ ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በስራ እድል ፈጠራ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ሚና የላቀ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡
በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም ለማፈንና የተረጋጋች ሀገር ለመገንባት የስራ አጥ ቁጥር መቀነስ እንደሚገባ የተናገሩት ኃላፊው ያሉንን ጸጋዎችና አቅሞችን በመጠቀም ውጤታማ ተግባር ማከናወን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በዞኑ 92 ሺህ 358 ስራ ፈላጊ ወጣቶች የተለዩ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ከ166 ሚሊየን ብር በላይ ብድር በማሰራጨት ከ54 ሺህ በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡
የስራ እድል ፈጠራ ለማበረታታት የብድር አቅርቦት እና እዳ አመላለስ ስርዓት ማሻሻል ይገባል ያሉት አቶ ሙራድ ከዚህ ቀደም ከተሰራጨው ብድር 93 ሚሊዮን ብር ማስመለስ የተቻለ ሲሆን 137 ሚሊዮን ብር ማስቆጠብ ተችሏል ብለዋል፡፡
የካቲት 09/2018 ዓ/ም
የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ንግድና ገብያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ንግድና ገብያ ልማት ጸ/ቤት በ2018 በጀት አመት ሸማቹ ማህበረሰብ የገጠመውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አክሎ ገልጿል።
የወረዳው ንግድና ገብያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቀድሩ ነጋሽ በ2018 በጀት አመት ባለፉት 6ወራት እቅድ አፈፃፀም አስመልክተው እንደገለፁት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በችርቻሮ ምርቶች ላይ ያልተገባ ዋጋ በሚጨምሩና ጊዜ ያለፈባቸውን ምርቶች ይዘው በተገኙ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የገለጽት አቶ ቀድሩ ነጋሽ
የተከሰተወን የኑሮ ውድነት ለመቀነስ የገበያ ለማረጋጋት የተለያዩ የግብርና ምርቶችን እንዲሁም ሌሎችን የፋብሪካ ምርቶችን ጨምሮ ከሌላ ቦታ ለሸማቾ ማህበረሰብ እያቀረቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
ኃላፊው አክለው እንደገለፁት የህገወጥ ስራዎች ያለንግድ ፍቃድ ሲንቀሳቀስ የነበረ እንጨት ከነጋዴ ተወርሶ 65ሺህ ወደ መንግስት ካዝና ማስገባት መቻሉን ጠቅሰው ለ9መቶ 92 ነባር ነጋዴዎች የንግድፈቃድ ሰርተፍኬት በማሳደስ የእቀዱን 90 በመቶ የተፈጸመ ሲሆን አዲስ የንግድ ምዝገባ 28 ነጋዴዎች የንግድፍቃድ መስጠት እንደተቻለ አመላክተዋል።
የተከሰተወን የኑሮ ውድነት አስመልክተው አቶ ቀድሩ እንዳሉት የህብረተሰቡን ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ ማርካት ባይቻልም በተወሰነ መልኩ ችግሩን ለማቃለል በግብርና ምርቶችን እንዲሁም ሌሎችን የፋብሪካ ምርቶችን ጨምሮ ለማቅረብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ሁሉንም የሁለገቦች እና የሸማች ኅብረት ስራ ማህበራትን በማጠናከር እና ወደ ስራ በማስገባት የኑሮ ወድነት ችግርን ለመፈታት በተቋም ደረጃ ጥርት እንደሚደርግ አሳታወቀዋል።
በመጨረሻም የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ቀድሩ ነጋሽ ነጋዴው ማህበረሰብ የሚጠበቅበትን ግዴታ መወጣት እንዳለበትና ሸማቹ ማህበረሰብ ያላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎችን፣ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶችን እንዲሁም ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ሚዛኖችን በማጋለጥ ሁሉም የድርሻው እንዲወጣ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
