918
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+27 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
ጥር 17/2018 ዓ.ም
የኦሮሚያ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን የሚያገናኘው የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ክቡር የክልላችን ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው።
የመንገድ ፕሮጀክቱ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ ሲሆን 81.1 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል። የመንገድ ግንባታውን የቻይናው ሁናን ሁንዳ አከናውኖታል። ሀገር በቀሉ የተባበሩት የምህንድስና አማካሪዎች የግንባታውን ጥራት በመቆጣጠር እና በማማከር በኩል ተሳትፏል። ለፕሮጀክቱ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በፌደራል መንግሥት ወጪ ተደርጎበታል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የኅብረተሰቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ከመኾኑም ባሻገር፣ በርካታ ማኅበራዊ እና ምጣኔ-ሃብታዊ ጠቀሜታዎችን ያበረክታል።
ጥር 14/2018 ዓ.ም
ጠንካራ የሴቶች ልማት ህብረት በመፍጠር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህን ያስታወቀው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘሬ ቀበሌ የእናቶች ቀን ( የአንትሮሽት) በዓልና የ3ኛ ዙር የሞዴል ልማት ህብረት ምርቃት እንዲሁም ከአየነ ምደር ነጻ ቀበሌ በተመረቀበት ወቅት ነው።
የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ መህዲ እንኳን የእናቶች ቀን ( የአንትሮሽት) አደረሳቹ በማለት አንትሮሽት እናቶች ከስራ አርፈው በልጆቻቸው እንክብካቤ የሚደረግላቸውና የሚደሰቱበት ዕለት በመሆኑ በተገቢው ሊከበር እንደሚገባ ገልጸዋል።
ጠንካራ የሴቶች ልማት ህብረት በመፍጠር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ወ/ሮ ፈትያ መህዲ አክለው አስታውቀዋል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለተለካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፈታ አረቦ በመርሃ ግበሩ ተገኝተው እንደገለጽት ብልጽግና ፓርቲ ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው የእናቶች የምስጋና ቀን ከማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አስተዋጽኦው ባለፈ ለሴት ልጅ መብትና ነፃነት ክብር የሚያጎናጽፍ ባህላዊና ታሪካዊ መሆኑን ገልጸዋው።
የወረዳው ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ ጉልላት በበኩላቸው የእናቶች ቀን ( የአንትሮሽት) እንኳን አደረሳቹ በማለት እለቱ ከጥንት ዘመን ጀምሮ የሴቶችን ክብር የሚዘክርበት ድንቅ ባህል መሆኑን ገልጸው
አሁን ላይ በዘመናዊ መልኩ በየ ዓመቱ በፈረንጆቹ ማርች 8 የሴቶች ቀን ብለን የምናከብረውን በዓል ማለት እንደሆነ አንሰተው በዓሉን በቀጣይ በወረዳ ደረጃ እንደሚከበር አስገንዝበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ በሴቶች ልማት ህብረት የተሰሩ የጓሮ አትክልት፣የዶሮ እርባታ እነዲሁም መጸዳጃ ቤት ጉብኝት የተደረገ ሲሆን የጎልማሳ ትምህርት እየተመሩ የሚገኙ እናቶች የማንበብና የመጻፍ ተግባር አቅርበዋል።
በመጨረሻም ለሴቶች ልማት ህብረት አባላት የምስክር ወረቀት በመስጠት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
***
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 52ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በሥራ ላይ ያለው የጉምሩክ አዋጅ ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ በመሆኑ፣ የአዋጁን ድንጋጌዎች ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ጋር ለማጣጣም፣ በአገራችን እያደገ የመጣውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ለመደገፍ፣ እንዲሁም ሕጋዊ ንግድንና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ይቻል ዘንድ የማሻሻያ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በማሻሻያ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል አዋጁ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው ለኢንቨስትመንት ስለሚሰጥ የታክስና ቀረጥ ማበረታቻ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላላቸውና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው፣ እንዲሁም ከፍተኛ ካፒታል ለሚጠይቁ የኢንቨስትመንት መስኮች በሥራ ላይ የሚውለውን ካፒታል ከግምት ውስጥ የሚያስገባና በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል፣ ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡
3. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ ፖሊሲው በኢንተርፕረነርሽፕ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ቀጣይነት ኖሯቸው ለሀገራዊ የልማት ግቦች ስኬት ሚናቸውን እንዲወጡ፣ የፈጠራ ባህልን ለማጎልበትና እሴትን ለመጨመር የሚያስችል ምቹ የኢንተርፕረነርሽፕ ሥነ-ምህዳር ለመገንባት እንዲቻል ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል፣ ፖሊሲው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ከጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡
#PMOEthiopia
ጥር 12/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር የ2018 በጀት አመት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በዛሬው እለት ተጀምሯል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር የበጀት አመቱ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ይገኛል።
በመድረኩ በ2018 በጀት አመት እስካሁን የተከናወኑ የ6 ወራት እቅድ አፈፃጸሞች በተቋም የስራ ኃላፊዎች ሪፖርት እያቀረቡ ነው።
በመድረኩ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ አባይት ተግባራት ተገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፈታ ሁሴን እንዲሁም የወረደው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን!!!
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የሚገኙ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦች ተገቢውን እንክብካቤና ጥበቃ በማድረግ ለቱሪስት ምቹ እንዲሆኑ መሰራት እንዳለበት ተገለፀ ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለፀው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ባህል ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ''አገርህን እወቅ ''በሚል መሪ ቃል በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የቱሪስት መስህብ ስፍራ በተጎበኙበት ወቅት ነው።
የገ/ጉ/ወ/ወ/ባ/ቱ/ፅ/ቤት የቱሪዝም መስህብ ባለሙያ አቶ ተኢ ነስሩ ጉብኝቱን አስመልክተዉ እንደገለፁት በወረዳችን ከ19 በላይ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦች መኖራቸውን ጠቅስዉ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር የሚፈልጉ ዋሻዎች ፣ጥብቅ ደኖች ፤ፏፏቴዎች ፤እድሜ ጠገብ መስጂዶች እና ቤተ ዕምነቶች ጥበቃ እና እንክብካቤ በማድረግ ለጎብኚዎች ምቹ ማድረግ እንደሚገባ አስታዉቀዋል።
በዘው እለት በወረዳው ከመንግስት ሰራተኞች የተውጣጡ የአገረህን እወቅ ክበብ አባለት በጉብኝቱ መሳተፋቸውን ባለሙያው አክለው ገልጸዋል።
በዕለቱ ጉብኝት ከተደረገባቸው የቱሪስት መስህብ ስፍራ አንዱ የአርባን ዋሻ ሲሆን ስለ ዋሻው ማብራሪያ የሰጡት የአከባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ አ/ራሂም ናስር የአርባን ዋሻ የቀድሞ አባቶች ጣሊያን ኢትዮጵያን ስትወር ፤የአፄ ዘራያቆብ ስራዓት በመቃወም እንደ ምሽግ ይጠቀሙት እንደነበረ እና ኢማም አህመድ ግራኝ እስልምናን ለማስፋፋት ወደ አከባቢው በመጡበት ወቅት እንደ ምሽግ ይጠቀሙበት እንደ ነበረ ጠቅሰው
አርባን ዋሻ ተፈጥሯዊ ዋሻ መሆኑ ተናግረው በወንዝ ዳርቻ የሚገኝና ዋሸው ሰው መግቢያ በር 5 ሜትር ርዝመት ያለውና የውስጥ ክፍሉ ከመሬት 2·2 ሜትር ከፍታ ሲኖረው የውስጥ ለውስጥ ርዝመቱ ከ85 ሜትር በላይ ሲረዝም የጎኑ ስፋት ደግሞ ከ20—30 ሜትር ስፋት ያለው መሆኑ ጠቅሰው የአርባን ዋሻ አሁን ላይ ሰፊ መሰረተ ልማት እንደሚያስረልገው እና ለጎብኚዎች ምቹ ከማድረግ አንፃር በሰፊው ከተሰራበት አካባቢያችን ስም እንደሚያስጠራ ተናግረዋል ።
የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ባለሙያ የሆኑት አቶ ፋሪስ ጥንታዊ የሰኢድ ከቢር ሃሚድ መስጂድን ለጎብኚዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በጉብኝቱ ላይ ሲሳተፉ ያገኘናቸው ወ/ሪት መህዲያ ረሻድ ከዚህ በፊት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚዘገበው ውጪ በአካል የማየት እድል እንዳልነበራቸው ገልጸው አሁን በአካል ቦታው ድረስ ተገኝተው በማየታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ሐቅስው
የወረዳችን የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ማህበረሰቡ እያወቃቸው እንዲመጣ የበለጠ ተደራሽ እንዲሆን በሁሉም የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች መጠበቅ እና መሰረት ልማት በማሟላት በወረዳች ውስጥ ያሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ቅርሶች ማስተዋወቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በዕለቱ የተጎበኙት ስፍራዎች ጎምራ ቀበሌ የሚገኘው የአርባን ዋሻ ፤የአዞ ተንጠልጣይ ድልድይ እና ዘልዋን ሰፋቶ የስይድ ከቢር ሀሚድ ጥንታዊ መስጂድ ሲሆኑ ከየሴክተሩ የተወጣጡ የመንግስት ሰራተኞች በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።
