925
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+67 روز
+1130 روز
آرشیو پست ها
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
የሴቶች ልማት ህብረት ውጤታማ ስራዎችን ይበልጥ በመጠናከር የሴቶችና ህፃናትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሠራ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽህፈት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የወረዳው ሴ/ህ/ጉ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ1 ኛ ሩብ ዓመት የወረዳው የሴቶች ስትሪንግ ኮሚቴ የውይይት መድረክ ዛሬ ተካሄዷል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ፈቲያ መህዲ ለመድረኩ የተዘጋጀ ዕቅድ አፈጻጸም ሰነድ አቅርበው ጥልቀት ያለው ውይይትና ምክክር ተደርጓል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪና የሴቶች ስትሪንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደገለፁት በየደረጃው የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ተሳትፏቸውን በማሳደግ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መስረት እንደሚገባ ገልጸዋል ።
ጠንካራ የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት በመፍጠርና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎን ለማሳደግና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላትና የሴቶች ልማት ህብረት የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት አስተዋጽኦ የላቀ ሚና እንደለው አስረድተዋል።
ሁሉም የእስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በቋሚነት ቀበሌ በመያዝ ሊደግፉ እንደሚገባ እንዲሁም ሁሉም የመንግስት ተቋማት የጡት ማጥቢያ ክፍል ማዘጋጀት እንዳለባቸው አቶ ሚፍታ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፈቲያ መህዲ በበኩላቸው የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀቶችን በየቀበሌው የተቀናጀ ልማት ህብረቱ የተደራጀና ሁሉንም ሴቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ በቀጣይ ትኩረት እንደሚሻ ተናግረዋል ።
በተለይም የሴቶች እና ህፃናት ደህንነት በማስጠበቅ ሁለተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ብቻ አይደለም ያሉት ወይዘሮ ፈትያ መህዲ በየደረጃው የሚገኙትን የሴቶችን ልማት ህብረት የመጠናከር የሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ኃላፊነት መሆን ይገባል ብለዋል።
የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በውይይታቸው ወቅት እንደገሉት የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችንና የጉልበት ብዝበዛዎች መከላከል እንደሚገባ ጠቅሠው ለዚህ ደግሞ የሁሉም አባል ሴክተሮች ቅንጅት ወሳኝ እንደሆነ ተነስቷል።
ኮሚቴው በተለይ የሴቶች ልማት ህብረትን በማጠናከር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ ይገባል የተባለ ሲሆን በግብርና፣ በትምህርት፤ በቁጠባ፣ በጤና እና መሰል ዘርፎች ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላክተዋል፡፡
ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አማካኝነት የ2018 ዓ.ም የበጋ እግር ኳስ የውስጥ ለውስጥ ውድድር ለመጀመር የእጣ ድልድል ስነ ስርዓት እንዲሁም የውድድሩ መመሪያ እና ደንብ ላይ ውይይት በዛሬው እለት ተካሂዷል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የ2018 ዓ.ም የበጋ እግር ኳስ የውስጥ ለውስጥ ውድድር በአቂዎች 17 ቡድኖች በሁለት ክላስተር የሚደረግ ሲሆን ማለትም በጅማ ክላስተር እና በገደባኖ ክላስተር በአዋቂዎች ውድድሩ የሚደረግ ይሆናል።
በውይይት መድረኩ ላይ የሁሉም ቡድን አሰልጣኝና አንበሎች እንዲሁም የውድድሩ ስነ ስርዓት ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም እንዳለት ስፖርት ዕድገት እንዲኖረውና የላቀ ችሎታ ያላቸውን ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትና እንዲሁ ጥሩ ስነምግባርና ስፖርታዊ ጨዋነት የተላበሱ ስፖርተኞችን ለማፍራት ትልቅ ፋይዳ ያለው ውድድር መሆኑን ጠቅሠው ቀጣይ በሁሉም ስፖርት ዓይነት ወረዳውን የሚወክሉ ተተኪዎች የሚለይበት ውድድር መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ሸምሱ አክለውም ሁሉም ተወዳዳሪ ቡድኖች ፍጹም በሆነ ስፖርታዊ ጨዋነት በመላበስ እንዲወዳደሩ ጠቅሠው መመሪያ እና ደንቡን በተገቢው በማውቅ እንዲሁም በመተግበር ረገድ ሊያግዙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የጽ/ቤቱ የስፖርት ተሳትፎና ውድድር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ታዬ ሃብቴ ለ2018 ዓ.ም ለበጋ ወራት ለውድድር የተዘጋጃ መመሪያ እና ደንብ አቅርበው
ባለድርሻ አካላት በጥልቀት ውይይትና ምክክር ተደርጎበት ጸድቋል።
በጅማ ክላስተር በአዋቂዎች 7 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን፦
በምድብ አንድ
1. ጅማ ለቻቻልነ
2. ኢንጌ አልኑር
3. ጅማ ተስፈኞች
4. ኢንጌ በምአሊ
በምድብ ሁለት
1. ከንተዋት መጣናን
2. ኢንጌ ወገሬት
3. ጅማ አድ ለሁነ በመሆን ተደልድለዋል።
በገደባኖ ክላስተር 10 ቡድኖች በተመሳሳይ በሁለት ምድብ የእጣ ድልድል ስነስርአት የተካሄደ ሲሆን
በምድብ 1
1. መከዞ
2. ጨፌ
3. ኮምበል
4. ጎራ
5. ቤተል
በምድብ ሁለት
1. ኡትዮ ተስፋ
2. አዴ
3. ለጋይ አለልቱ
4. ኦቼ
5. መሀል አምባ በመሆን ተደልድለዋል።
በዚህ መሰረት የ2018 ዓ/ም የበጋ ወራት የውስጥ ለውስጥ የእግር ኳስ ውድድር የፊታችን እሁድ ማለትም በ ጥቅምት 30/02/2018 ዓ/ም ከ4 ጀምሮ የመክፈቻ ፕሮግራም የሚካሄድ ሲሆን በገደባኖ ክላስተር መከዞ ከ ኮምበል የመክፈቻ ጨዋታ 5 ሠዓት ላይ ይደረጋክ ይህንን ጨዋታ የወረዳችን ማህበረሰብ በሙሉ መሀል አምባ ጨፌ ሜዳ በመገኘት እንድትመለከቱ ሲል የወረዳው ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት ጥሪውን ያስተላልፋል።
የታዳጊዎች ውድድር በሚቀጥለው ሳምንት የእጣ ድልድልና ውድድር የሚጀመር መሆኑን ከመድረኩ ተመላክቷል።
ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም
በክልሉ ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ለዜጎች ክህሎት መር የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ቢሮው የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ4 ወር አፈፃፀምና በአዳዲስ እሳቤዎች እንዲሁም የሪፖርት ስርዓት ላይ የተዘጋጀ የስልጠናና ግምገማ መድረክ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የክልል ፣የዞንና የልዩ ወረዳ የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የሰራ ሀላፊዎችና ባለሞያዎች እየተሳተፉ ነው።
የቢሮው ምክትልና የገጠር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ተመስገን ሀይሌ እንደገለፁት በክልሉ ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ክህሎት መር የስራ ዕድሎችን ለዜጎች ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የስራ ዕድል መፍጠር ራስን ከመቻል ባለፈ በግለሰብ፣ በቤተሰብና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ ተመስገን የገጠሩን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በፖለቲካ ፣በማህበራዊና በኢኮኖሚው የተረጋጋ ማህበረሰብ በየአካባቢው ለመፍጠር ለዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በበቂ ሁኔታ መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ወጣቶችን በአዳዲስ የሪፎርም እሳቤዎች ማሰልጠንና ማላመድ ይገባል ያሉት ሀላፊው በአደረጃጀትም ሆነ ከአደረጃጀት ውጭ የሚፈጠሩ ስራዎችን የመለየት፣ የመከታተልና የመደገፍ ስራ መጠናከር እንዳለበትም አሳስበዋል።
በኢንተርፕራይዞች የብድር ስርጭት እና አመላለስ ላይ ያሉ ውስንነቶች በመቅረፍ ኢንተርፕራይዞች በማሸጋገር ዘርፉን ውጤት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
መድረኩ በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን በመለየት በሪፎርም ስራዎች እና የመረጃ አያያዝ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በስልጠና በመሙላት በቀጣይ ጠንካራ ስራ መስራት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጉራጌ ዞን የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙራድ ያሲን መንግስት ለዜጎች በገጠርና በከተማ በርካታ የስራ ዕድል መፍጠር የሚያችሉ ሪፎርሞችን ቀርፆ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዘርፉ የሚታዩ የመብራት ፣ኢንተርኔት እና ሌሎች የመሠረተ ልማት ማነቆዎች ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው የወጣቶችን የክህሎት እና አቅም ክፍተት ለመሙላት በቅንጅት መስራት ይገባልም ብለዋል።
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
የተጀመረውን የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ተጠየቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የ2018 ዓ/ም 1ኛ ሩብ አመት የዜጎች ቻርተርና የህዝብ ክንፍ የውይይት መድረክ ዛሬ አካሂዶ ዉሏል።
የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባስ ለሙ ከህብረተሰቡ ተሰብስበው ለተቋማት ተደራሽ የሆነ ግብረ-መልስ እና የጽ/ቤቱ ልማት ዕቅድ ባለሙያ በዛሽ መህዲ የ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በውይይት መድረኩ ከተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች መካከል ተፈጻሚ እየሆነ ያለው ፈጣን ቀልጣፋና ውጤታማ የህዝብ ግንኙነት ስራ የሚበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው፣ ለህዝብ ግንኙነት ፎካል ፐርሰኖች ወጥ ስልጠና ቢሰጥ የተሳለጠ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራ መስራት እንደሚያስችል ያነሱት ተሳታፊዎቹ ተቋሙ የህዝብ አስተያየቶችን ሰብስቦ ግብረ-መልስ በማዘጋጀት በተሰጡ ሃሳቦች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር በመነጋገር ችግሮች የሚፈቱበትን አግባብ አስመልክቶ እየተሄደበት ያለዉ ርቀት ለውጥ የታየበት በመሆኑ ቀጣይነቱ ላይ መሰራት እንደሚኖርበት በማንሳት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻዎች ተቋሙን በግብዓትና የሰው ሀይል በማገዝ የተሰጠውን ሀላፍትና በአግባቡ መወጣት እንዲችል የድርሻቸውን ሚና ሊያበረክቱ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አባስ ለሙ በማጠቃለያቸው ከውይይት መድረኩ የተሰጡ ግብዓቶች የቀጣይ ዕቅድ አካል ተደርጎ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።
የተጀመረውን የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ጠቅሠው
በየተቋሙ ያሉ የህዝብ ግንኙነት ፎካል ፐርሰኖችና መላው የመንግስት ሰራተኞች በተገቢው በመቀናጃት የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ወደ ህዝብ አይንና ጆሮ በማድረስ የህዝብ ግንኙነት ስራውን ማሳለጥ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ከ5 መቶ 22 ሺህ ብር በላይ ወጪ የመማሪያ መጽሐፍት ለገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በወረዳው በሚገኙ የጉልባማ አባላት በተሠበሠበ ገቢ 3060 ከ 1ኛ-8ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍት
522,213 ብር የጨረሠ በዛሬው እለት ድጋፍ መደረጉን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ለተግባራቱ መሳካት የበኩላቸውን እንደሚሰሩ ገልጸው ውይይቱ ተጠናቋል።
በንቅናቄ መድረኩ ላይ የኮሌጁ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም አጠቃላይ ከወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል።
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
የመሃል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ያሉበትን የግብዓትና የሰው ሃይል በማሟላት ተፈላጊውን የትምህርትና ስልጠና አገልግሎት መስጠት እንዲችል በየደረጃው የሚገኙ አካላት እገዛ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው ኮሌጁ የነባር እና የአዲስ ሰልጣኞች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ “ቴክኒክና ሙያ ትዉልድ መገንቢያ" ዛሬ ባካሄደበት ወቅት ነው።
ተቋሙ በትምህርትና ስልጠናዉ ዘመን የነባር ሰልጣኝ ቅበላ ዕቅድ 147 በማቀድ 62 ሰልጣኞችን የተቀበለ ሲሆን አዲስ ሰልጣኝ ቅበላ ዕቅድ 415 ክንዉን 26 ላይ ይገኛል።
የኮሌጁ ዲን ወ/ሪት ሰላማዊት ኡርባኖስ የ2018 ዓ/ም ማስፈጸሚያ ዕቅድ ባቀረቡበት ወቅት በመደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ የስልጠና መስኮች ዜጎችን ተቀብሎ በማሰልጠን የዘመኑን ዕቅድ ማሳካት እና የክህሎት ልማት ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ለስራ ዕድል ፈጠራ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር የመድረኩ ዓላማ መሆኑን ጠቅሰው ኮሌጁ ለወጣቶች ክህሎት መር ስልጠናዎች በመስጠት የስራ እድል ባለቤት ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ተማሪዎች ወደ ኮሌጅ መጥተው የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል የሁሉም የኮሌጁ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች እና የወረዳ አመራሮች የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የ2018 ነባር ተማሪዎች ስልጠና የተጀመረ ቢሆንም በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰልጣኞች እስካሁን ያልተመዘገቡና ስልጠና ያልጀመሩ በመሆኑ የቀሩበትን ምክንያት በመለየት ፈልጎ የማምጣት ስራ ለመስራትና ከአዲስ ሰልጣኝ ቅበላ ጋር በተያያዘ ምዝገባ ከተጀመረ የቆየ ቢሆንም እስከ አሁን መጥቶ የተመዘገበው ቁጥሩ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ሁሉም በየወረዳውና በከተማ እና በቀበሌዎች በመንቀሳቀስ የተማሪ ቅስቀሳ በማድረግ ወደ ኮሌጅ የማስገባት ስራ እንዲሰራ አሳስበዋል።
የንቅናቄ መድረኩን የመሩት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሰን እንደገለጹት በሁሉም አካባቢዎች የተሳካ የተማሪ ልየታ በማድረግ ተፈላጊውን የምዝገባና ትምህርትና ስልጠና መስራት እንደሚገባ በመግለጽ የወረዳው መንግስት ለኮሌጁ እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መመሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርገማ እንዳሉት የተቋሙ አመራርና ማኔጅመንት አካላትን ጨምሮ በየደረጃው ያለው አመራር ያሉትን አማራጮች አሟጦ በመጠቀም የተማሪ ቅበላውን ማሳካት እንደሚገባ ጠቅሰው የዞኑ መንግስት ተቋሙን በግብዓትና መሰል ጉዳዮች ለማገዝ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት አቶ አብድረሂም ርዳ በበኩላቸው ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስራ ፈጣሪ ዜጎች የሚፈሩበት ብቻ ሳይሆን ስራ ወዳድ ፣ ትጉህ ፣ከዘመኑ ጋር በተገቢው የተዋሃደና ሀገር ተረካቢ ዜጎች የሚመረትበት ታላቅ ሙያ ያሉት አቶ አ/ረሂም ተቋሙን የተጣለበትን ተልእኮ እንዲወጣ ለማድረግ እንደወረዳ የምንቆጥበው ምንም ሀብትና ጉልበት የሌለ መሆኑን ገልፀዋል።
በመጨረሻም አቶ አ/ረሂም ችግሩ በጣም አሳሳቢ በመሆኑ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የቅስቀሳና የግንዛቤ ስራ እንደሚሰራ ገልፀው ከነዚህም መካከል ከዞንና ከወረዳ ደጋፊ አመራሮች ጋር በቅንጅት በመሆን በወረዳና በቀበሌዎች ተከታታይ የንቅናቄ ስራዎች እንደሚሰራ፣ ከአሰልጣኞችና ነባር ሰልጣኞችን በማሰማራት አዳዲስ ሰልጣኞች ቀስቅሶ የማምጣት ስራ እንደሚሰራ አሳውቀዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ለተግባራቱ መሳካት የበኩላቸውን እንደሚሰሩ ገልጸው ውይይቱ ተጠናቋል።
በንቅናቄ መድረኩ ላይ የኮሌጁ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም አጠቃላይ ከወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል።ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም

ጥቅምት 27/2018.ም
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሃል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የነባርና አዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ ማሳካት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሃል አምባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሠን፣
የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምረያ ኃላፊ አቶ
የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳን ጨምሮ የወረዳው ጠቅላላ አመራሮች፣
የመሃል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
አመራርና ባለሞያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ!!
ዝርዝር መረጃ ተከታትለን እናደርሳለን።
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ ነው!!
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ወደ ስራ ከገባ በኋላ ለተገልጋዮች ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ከበደ ሻሜቦ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ባለ ጉዳዮች ጊዜያቸውና ገንዘባቸው ሳይባክን ምቹ አገልግሎት እንዲያገኙ አስችሏል፡፡
ከዚህ ቀደም ህብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት ወደተለያዩ ተቋማት ለአላስፈላጊ ወጪ ይዳረግ እንደነበር አስታውሰው፥ አሁን ላይ በአንድ ጣሪያ ስር የተቀናጀና ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በክልሉ በሁሉም አገልግሎቶች ላይ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣና ችግር ፈቺ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ተገልጋዮች ክፍያ የሚፈፅሙበት በዲጂታል ሥርዓት መኖሩ ሙስናና ብልሹ አሰራርን የሚያስቀር መሆኑን ገልጸው፥ ህብሰረተሰቡ ወደ ማዕከሉ በመምጣት ያለ ተጨማሪ ወጪ እና እንግልት ፈጣን አገልግሎት በአንድ ቦታ ማግኘት ይችላል ብለዋል፡፡
ሰባት ተቋማት በማዕከሉ እንደሚገኙና 20 ያህል አገልግሎቶች ለማህበረሰቡ እየተሰጡ ሲሆን፥ በቀጣይ በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወደ 60 ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በክልሉ በአምስት ከተሞች ለማስፋት እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
FBC