916
مشترکین
+124 ساعت
-17 روز
+530 روز
آرشیو پست ها
መጋቢት 13/2018 ዓ/ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የሚደረገው የመራጮች ምዝገባ በዲጂታልና በመደበኛ ማንዋል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የምዝገባ ሂደቱ በተጠናከረ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል።
መጋቢት 12/2018 ዓ/ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች፣7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የወረዳው ነዋሪዎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ወደ መራጮች መመዝገቢያ ጣቢያ በመሄድ የመራጮች ካርድ እየወሰዱ ነው።
መጋቢት 11/2018 ዓ/ም
ለምርጫ የተመዘገቡ ዜጎች ቁጥር 18 ሚሊየን 556 ሺህ 337 ደረሰ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ ትናንት ባካሄደው የመራጮች ምዝገባ 18 ሚሊየን 556 ሺህ 337 ተመዝግበዋል፡፡
ቦርዱ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫን የመራጮች ምዝገባ በጊዜ ሠሌዳው መሠረት ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በማከናወን ላይ ይገኛል።
በዚህም እስከ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በማንዋልና በዲጂታል አማራጭ ባከናወነው የመራጮች ምዝገባ 18 ሚሊየን 556 ሺህ 337 መራጮች መመዝገባቸውን አስታውቋል።
ከተመዘገቡት መራጮች ውስጥ 10 ሚሊየን 133 ሺህ 639 ወንድ ሲሆኑ፤ 8 ሚሊየን 422 ሺህ 698 ሴት መሆናቸውን ቦርዱ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።
ቦርዱ ለመራጮች ምዝገባ አወዳድሮና ገለልተኝነታቸውን በፖለቲካ ፓርቲዎች አስተችቶ ያሰለጠናቸውን 187 ሺህ 28 የምርጫ አስፈጻሚዎች ማሰማራቱንም አስታውሷል።
(ኤፍ ኤም ሲ)
የዒድ ደስታ ለሁሉም፤ የዘካተል ፊጥር ድንጋጌና ማኅበራዊ ፋይዳ
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የረመዷን ፆም መጠናቀቅን ተከትሎ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የዒድ አል ፊጥር በዓልን ከማክበሩ በፊት ሊወጣው የሚገባው "ዘካተል ፊጥር" ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን የእስልምና አስተምህሮ ያዛል።
ይህ መልካም ተግባር ችግረኞች በዒድ ዕለት እጃቸውን ለልመና እንዳይዘረጉና የዕለቱ የደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ታስቦ የተደነገገ ሲሆን፣ በፆም ወቅት ለተከሰቱ ጥቃቅን ጉድለቶችም ማሟያ ሆኖ ያገለግላል።
ይህ የዘካ ዓይነት አቅም ባለው ማንኛውም ሙስሊም ላይ ግዴታ ሲሆን፣ በጾታም ሆነ በዕድሜ ሳይገደብ ለሁሉም የቤተሰብ አባላት መውጣት ይኖርበታል።
የዒድ ቀን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት የተወለደ ሕፃንም በዚህ ግዴታ ውስጥ የሚካተት ሲሆን፣ ለራሱና ለቤተሰቡ የዒድ ቀንና ሌሊት የሚበቃ ቀለብ ያለው ማንኛውም ሙስሊም ዘካውን የማውጣት ኃላፊነት አለበት።
ይህም ድሆችም ጭምር ተቀብለው ለሌላው የሚሰጡበትን ሁሉንም የሚያሳትፍ የልግስና ሥርዓት ይፈጥራል።
ለዘካተል ፊጥር የሚውሉ የእህል ዓይነቶች በአካባቢው ለቀለብነት የሚያገለግሉና ረዘም ላለ ጊዜ የማይበላሹ እንደ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ቴምርና ዘቢብ መሆን ይገባቸዋል።
መጠኑም በሐዲሥ በተቀመጠው ስፍር መሠረት ወደ ኪሎግራም ሲቀየር ለአንድ ሰው በአማካይ 2.5 ኪሎ ግራም ገደማ ሲሆን፣ ለምሳሌ 10 የቤተሰብ አባላት ያሉት ሰው 25 ኪሎ ግራም እህል ማውጣት ይኖርበታል።
ልዩ አንገብጋቢ ሁኔታዎች ካልገጠሙ በቀር ዘካውን በገንዘብ ማውጣት የማይመከር ሲሆን፣ በእህል ተለክቶ ለችግረኛ ሙስሊሞች ብቻ እንዲሰጥ በጥብቅ ይመከራል።
የዘካተል ፊጥር ትክክለኛ ጊዜ የረመዷን ወር ተጠናቆ የዒድ ሌሊት ከገባበት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዒድ ሶላት መጀመሪያ ድረስ ቢሆንም፣ ለሚሰበስቡ አካላት ለማድረስ እንዲመች አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ መስጠት እንደሚቻል ተገልጿል።
ይህ ሥርዓት ሙስሊሞች በረመዷን ያገኙትን መንፈሳዊ ጥንካሬ ወደ ተግባራዊ መረዳዳት በመቀየር፣ ማኅበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩበትና የበዓሉ ደስታ በሁሉም ቤት እንዲገባ የሚያደርጉበት ዋነኛው መንገድ ነው።
EBC
ሰበር መረጃ❗️
የ1447ኛው የሸዋል ወር ጨረቃ በሳውዲ አረቢያ ዛሬ ባለመታየቷ ኢድ አል ፊጥር በዓል መጋቢት 11/2018 ዕለተ አርብ ወይም ሸዋል 01/1447 ዓ.ል እንደሚከበር ተረጋግጧል።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ🙏
መጋቢት 09/2018 ዓ/ም
የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክትና ማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፓርቲውን የምርጫ ምልክትና ማኒፌስቶ ለክልሉ ወጣቶች የማስተዋወቅ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል።
የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)፣ ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ወጣቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማድረግ ከወጣቱ ጋር ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል።
በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራሮች፣ ወጣት አደረጃጀት አመራሮች፣ ከክልሉ ከሁሉም መዋቅር የተውጣጡ ወጣቶች ተገኝተዋል።
Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau
መጋቢት 08/2018 ዓ/ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ ተግባር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ጽ/ቤቱ ይህን ያስታወቀው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ዘርፍ እና "የመሬት ገጽታ አያያዝ ለተሻሻለ ምላሽ እና ትራንስፎርሜሽን" (CALM-PforR) ፕሮግራም የፊዚካልና ፋይናንሻል ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የውይይት መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።
የወረዳው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ሰማን እና የወረዳው ገጠር መሬት አጠቃቀም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስራጅ ደንበል አማካኝነት የ2018 የ6 ወራት የፊዚካልና ፋይናንሻል አፈጻጸም ቀርቦ ከቦርድ አባላት ጋር በመወያየት የተለያዩ አቅጣጫዎች ተቀምጧል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፋታ ሁሴን የተቀናጀ የግብርና ልማት እንቅስቃሴው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል የተፈጥሮ ሀብትን ማልማት፣ መንከባከብና መጠበቅ ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆኑንም ገልፀዋል።
ሁሉም weter shed በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግና አስፈላጊ ግብዓቶችን በማቅረብ፣ ለዜጎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን እንደ ፍራፍሬ፣ ቡና፣ እንሰትና መኖ ያሉ ተፈላጊ ችግኞችን በስፋት ለማዘጋጀት በትኩረት መሰራት አለበት ብለዋል።
አቶ ሚፋታ አክለውም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች ዘላቂ እንዲሆኑ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ያረጋገጠ የእንክብካቤ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ይህ ፕሮግራም የመሬት አቀማመጥን መሰረት ያደረገ ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ላይ እንደሚያተኩር በመሆኑ በአንዳንድ ቀበሌዎች የሚታዩ ጉድለቶችን በማረም የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አቶ ሚፋታ አስተውቀዋል።
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ በበኩላቸው ከመድረኩ የተገኙ ግብዓቶች ወስደው እንደሚሰሩ ጠቁመው ከአብይ ኮሚቴ አባላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
አቶ ከድር አክለውም በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች ባህር ዛፍ በንቅናቄ በማንሳት በሌሎች ምረቶች እንዲተካ በትኩረት ያሰራል በለዋል።
በመጨረሻም የ2018 የ2ኛው ሩብ አመት የCAKmp4 ፕሮግራም ድጋፍ ለንኡስ ተፍሰሶዎች ለሚከናወኑ ተግባራት IGA (የገቢ ማስገኛ ተግባራትን) ለንብ መንደር ምስረታ በተመረጡ በሁለት ንኡስ ተፍሰሶዎች ላይ ለሚከናወነ ውተግባር ከወዲሁ ትኩረት ሰጥቶ መከናወን እዳለበት አቅጣጫ በማስቀመጥ የተበጀተው በጀት ለታለመለት አላማ በማዋል እዲቺል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ እደሚቀጥል አቅጣጫ በማስቀመጥ የ2018 የሁለተኛ ሩብ አመት በጀት አብይ ኮሚቴ እና ቴክኔክ ኮሚቴ ገምግሞ አጽድቋል።
በመድረኩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ጨምሮ የአብይና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል።
መጋቢት 07/2018 ዓ.ም
ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ እያከናወናቸው የሚገኙ የክትትልና ቁጥጥር ተግባራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በዞኑ ምክር ቤት የህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የወረዳው አስተዳደር፣ ፖሊስ፣ ሰላምና ፀጥታ፣ ሚሊሻ ጽ/ቤቶችና የወረዳው ፍርድ ቤት አፈፃፀም የመስክ ምልከታ አደረገ።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጌታሁን ነጋሽ እንዳሉት ምክርቤቱ ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ እያከናወናቸው የሚገኙ የክትትልና ቁጥጥር ተግባራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
ምክር ቤቱ አቅዶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የተቋማት አፈፃፀም የመስክ ምልከታ ማድረግ ሲሆን ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ የህግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች አፈፃፀም በመገምገም ለተቋማቱ ግብረመልስ ይሰጣል ብለዋል።
እንደ አቶ ጌታሁን ገለፃ በተቋማቱ የሚስተዋሉ የአፈፃፀም ክፍተቶች ለመሙላት እና ውጤታማ የሆኑ ተግባራትን ማስቀጠል እንዲቻል ምክር ቤቱ ለሚመለከታቸው ተቋማት ግብረመልስ ከመስጠት በተጨማሪ ተገቢው የክትትልና ቁጥጥር ተግባራት ይከናወናሉ።
የወረዳው ህብረተሰብ በልማት ስራዎች በማሳተፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ስራዎች አበረታች በመሆናቸው በቀጣይም የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
አቶ ጌታሁን አክለውም ህብረተሰቡ የሚያቀርባቸው ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ሱሆን ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ የሚደረገው ጥረት መጠናከር አለበት ብለዋል።
በወረዳው የሚስተዋለው ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል እየተሰራ ሲሆን ቀጣይነት እንዲኖረው የክትትል ስራ መሰራት አለበት።
ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እየተፈጠረለት ሲሆን በወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህግ ጥላ ስር ከማዋል ጎን ለጎን ተጠርጣሪዎች በጊዜያዊ ማቆያ ሰብዓዊ መብቶቻቸውን ተጠብቆላቸው እንደሚቆዩ መደረግ እንዳለበት አስገዝበዋል።
በጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ፍርደኞች ወደ ማረሚያ ተቋም እንዲገቡ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ገለታሁን ተናግረዋል።
የፍርድ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ አበረታች መሆኑን የገለፁት ሰብሳቢው ዜጎች የፍትህ አገልግሎት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ የተዘዋዋሪ ችሎት ማዕከል ቁጥር ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም የተከፈቱ የክስ መዝገቦች በአጭር ጊዜ ውሳኔ የሚሰጥባቸው መሆኑ የሚበረታታ ሲሆን ከባህላዊ የዳኝነት ስርዓት ጋር በማስተሳሰር ይበልጥ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ይገባል ብለዋል።
ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው የወረዳው ህብረተሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድ፣ የኔትወርክ፣ የመብራት መሰረተ ልማት ለማስፋፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ገልፀዋል።
እንደተሳታፊዎቹ ገለፃ ባለሀብቱና ህብረተሰቡ በመንገድ ልማት እያደረገ ያለው ተሳትፎ አበረታች ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እንድሚቀጥል አስረድተዋል።
በወንጀል ተጠርጥረው በጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በወቅቱ ውሳኔ እንዲያገኙ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በወረዳው አገልግሎት እየሰጠ ላለው የተጠርጣሪዎቹ ጊዜያዊ ማቆያ የሚበጀተው በጀት በቂ ሬሽን ለማቅረብ የማያስችል በመሆኑ ሬሽን ለፍርደኞችና ጠያቂ ቤተሰብ ለሌላቸው ተጠርጣሪዎች ብቻ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ምክርቤቱ ያደረገው ድጋፍ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያነሳሳ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
መጋቢት 06/2018 ዓ.ም
🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በተቋም ግንባታ ፣በዜጎች ቻርተር ሰነድ እና በተገልጋይ እርካታ መርሆች ትግበራ ማንዋል ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በጉራጌ ዞን የመሀል አምባ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የ 6ወር አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ የ6 ወር ዕቅድ አተገባበር ዙርያ የቦርድ አባላት ውይይት አካሄዱ።
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የሚገኘው HLS አበባ ልማት ድርጅት አማካኝነት ለኤክስፖርት ገበያ
የተዘጋጁ የአበባ ምርቶች በምስል በከፊሉ
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
🎤 የመንግስት የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በማስተካከል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ ።
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
🎤 ጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የተወዳዳሪ እጩዎችን በይፋ አስተዋውቋል!!
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
🎤 በሳይንስና ቴክኖሎጂ የዳበረ ትውልድ በመፍጠር የሀገር ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በእንስሳት ሀብት ልማት የተጀመረውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከሼሽት ማዴ- አመቶ መንገድ የግሬደር የማሽን ስራ ተጀምሯል።
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
🎤 ባለፉት ዓመታት በተሰራው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለፀ።
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
🎤 የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞችን ደህንነት በመጠበቅ ፍትሀዊ የሆነ የዜጎች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ገለፀ።
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
🎤 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከጅማ አረዳ 11 ኪሎ ሜትር ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ እየተገነባ መሆኑን የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
