cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

پست‌های تبلیغاتی
11 595
مشترکین
-424 ساعت
-687 روز
+22930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ፕሬዝዳንት ማክሮን ፓርላማቸውን በተኑ፡፡ ማክሮን በተካሄደው የአውሮፓ ምክር ቤት ምርጫ ተቀናቃኛቸው ማሪን ለፔን 32 በመቶ የሆነ ከፍተኛ ድምጽ በማገኘታቸው ነው ፓርላማውን ለመበተን የተገደዱት፡፡ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ቀጣዩን ምርጫ ሰኔ 30 እንዲካሄድ ውሳኔ ማሳለፋቸውን የIndia Today ዘገባ አመልክቷል። 27ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለሶስት ቀናት የቆየውን ምርጫ ባሳለፍነው እሁድ አጠናቀዋል፡፡ @thiqahEth
نمایش همه...
👍 10😱 1
የእስራዔል የጦር ካቢኔ ሚኒስትር የነበሩት ቤን ጋንትዝ ስልጣናቸውን ለቀቁ፡፡ እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ፣ ጋንትዝ በጋዛ ጦርነት ዙሪያ ከጠ/ሚ ኒታንያ ጋር መግባባት ባለመቻላቸው ነው ከኃላፊነታቸው የተነሱት፡፡ ኒታንያሁ የጋንትዝን መልቀቅ ተከትሎ "እስራዔል የህልውና ጦርነት ውስጥ ናት፤ ጋንትዝ ዘመቻ የሚተውበት ወቅት አይደለም" ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ጽፈዋል፡፡ ከለቀቁ በኋላ ምርጫ እንዲደረግ የጠየቁት ጋንትዝ በጋዛ ጦርነት በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከኒታንያሁ ጋር የእስር ማዘዣ ይወጣባቸዋል ከተባሉት የእስራዔል ከፍተኛ ባለስልጣን አንዱ ናቸው፡፡ @thiqahEth
نمایش همه...
👍 27
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል 4 ታጋቾችን ስታስለቀቅ 274 ፍልስጤማውያንን ገድላለች ተባለ። ህፃናትን ጨምሮ 274 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጦር መገደላቸውን Scripp News ዘግቧል። ከሟቾች በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል ተብሏል። እስራኤል ከኑሰራት የስደተኞች ካምፕ አራት ዜጎችን ከእገታ ማስለቀቋን አስታውቃ ነበር። @thiqaheth
نمایش همه...
😢 27👍 22😡 7🤔 3
Photo unavailableShow in Telegram
የሁቲ ታጣቂዎች 11 የተ.መ.ድ ሰራተኞችን በቁጥጥር ማዋሉ ተገለጸ። ከታገቱት ውስጥ የቀድሞው የአሜሪካ ኢምባሲ ባልደረባ የነበረ ግለሰብ እንደሚገኝበት ተነግሯል። የየመኑ ታጣቂ ቡድን የእርዳታ ሰራተኞቹን ያገተበትን ምክንያት በግልጽ አልገለፀም። በአሜሪካ የሚመራው ጥምረት በቡድኑ ላይ በአየር ላይ ጥቃት የታገዘ ውጊያ እያካሄደ ይገኛል። #EuroNews @thiqaheth
نمایش همه...
👍 29😁 2
Photo unavailableShow in Telegram
የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጥቃት ደረሰባቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬድሪክሰን የአውሮፓ ህብረት በሚያካሂደው ምርጫ ለመሳተፍ እየሄዱ በነበረበት ወቅት በኮፐንሀገን አደባባይ ጥይት ተተኩሶባቸው ተመትተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሯ፣ ”በተፈጠረው ክስተት ደንግጠው ነበር” ሲል ያስታወቀው ጽህፈት ቤታቸው፤ የደረሰባቸውን አደጋና አሁን ያሉበትን ሁኔታ ግን አልገለጸም፡፡ ጥቃት አድራሹ ግለሰብ ወዲያውኑ በፖሊስ መያዙን የIndiatoday ዘገባ ያመላክታል፡፡ @thiqaheth
نمایش همه...
👍 25 4
Photo unavailableShow in Telegram
ፈረንሳይ ሚራጅ-2000 ጄት ለዩክሬን ልልክ ነው አለች፡፡ ፕሬዝዳንት ማክሮን የዩክሬን የጄት አብራሪዎች ወደፈረንሳይ መጥተው እንዲሰለጥኑ ለፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ግብዣ እንደሚያቀርቡላቸውም ተናግረዋል፡፡ ማክሮን፣ “በነገው እለት አዲስ የትብብር ምዕራፎችን መተግበር እንጀምራለን፤ የጄት አቅርቦቱንም እውን እናደርጋለን“ ብለዋል። ለአብራሪዎች የሚሰጠው ስልጠና ከ5 እስከ 6 ወራት እንደሚፈጅ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ምን ያክል ጀቶችን ለመስጠት እንዳሰቡ ግን አልገለጹም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን በትናንትናው እለት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ የሚያደርጉ የምዕራባውያን ሀገራት ላይ ጥቃት እንሰነዝራለን ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር፡፡ @thiqaheth
نمایش همه...
👍 27😡 14 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
“በእስራኤልና በሊባኖስ መካከል ሌላ የማይበርድ ግጭት እንዳይፈጠር እሰጋለሁ" - አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) በደቡብ ሊባኖስ የተኩስ አቁም እንድደረግ ጠይቋል። የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ “በእስራኤልና በሊባኖስ መካከል ሌላ የማይበርድ ግጭት እንዳይፈጠር እሰጋለሁ" ብለዋል። ዋና ፀሐፊው ይህን ማለታቸውን የገለጹት፣ ቃል አቀባያቸው ሰቴቨን ዱዳሪች በሰጡት መግለጫ ነው። ጉተሬዝ እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት ከሁለቱም ወገን በ100ዎች የሚቆጠር ህይወት መጥፋቱንና በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል፡፡ በጦርነቱ ከባባድ የጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆናቸውን GulfToday ዘግቧል። @thiqaheth
نمایش همه...
👍 22🔥 3 1😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የደቡብ አፍሪካ ገዥ ፓርቲ ጥምር መንግስት እንደሚመሰረት አስታወቀ፡፡ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ፣ “ሀገራችንን ወደፊት ለማራመድ የሚያስችለንን ጥምር መንግስት መመስረት እንድንችል ሌሎች ፓርቲዎችን ጋብዘናል" ብለዋል። በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉን ያካተተ ውህድ መንግስት ለመመስረት ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት አግኝተዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው ምርጫ ላለፉት 30 ዓመታት ሀገሪቱን እያስተዳደረ የቆየው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረንስ /ANC/ ፓርቲ የአብላጫ ድምጽ ማገኘት አልቻለም፡፡ #AnadoluAgency @thiqaheth
نمایش همه...
👍 13😁 2😡 1
Photo unavailableShow in Telegram
"ለዩክሬን ድጋፍ የሚያደርጉ ሀገራት ላይ ጥቃት እንፈጽማለን" - ፑቲን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ የሚያደርጉ የምዕራባውያን ሀገራት ላይ ጥቃት እንሰነዝራለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ፣ እነዚህ ሀገራት ዩክሬን በሩሲያ ለምትፈጽማቸው ጥቃቶች ከጎኗ በመሆን እገዛ እደረጉ ነው ብለዋል። በምዕራባውያን ሀገራት ላይ ጥቃት ሊያደርሱ ለሚችሉ ሦስተኛ ሀገራትም ቢሆን የሚሳዔል ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡ #Novinite @ThiqahEth
نمایش همه...
👍 70 14😁 6🔥 2😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
39 ፍልስጤማውያን በትምህርት ቤት ውስጥ እያሉ በእስራዔል ጥቃት ተገደሉ፡፡ እስራዔል በበኩሏ የሀማስ ኃይሎች ትምህርት ቤቱ ውስጥ ተደብቀው ነበር ብላለች፡፡ በኑሰይራት ስደተኞች ካምፕ ተፈናቅለው በትምህርት ቤት ውስጥ ከተጠለሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ውስጥ 39 የሚሆኑት እስራዔል ባደረሰችው ጥቃት ተገድለዋል፡፡ ትምህርት ቤቱ በተ.መ.ድ ስር የሚተዳደር መጠለያ ካምፕ ነበር። #AnadoluAgency @ThiqahEth
نمایش همه...
😭 94👍 13😢 4