cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኖላዊት

"ጥሩ"ነትን በ "ልክ" ሳይሆን "ልክ"ን በ"ጥሩ" እንመዝን

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
630
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ +"+ +ባለንበት ዘመን አሳዛኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የቅዱሳኑ ስማቸው ከነሥራቸው መዘንጋቱ ነው:: ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደማቸው እንዳልፈሰሰ: አጥንታቸውም እንዳልተከሰከሰ ይሔው አስታዋሽ አጥተው ስማቸውም ተዘንግቶ ይኖራል:: +አንዳንድ ንፉቃን ደግሞ ከዚሁ ብሶ ጭራሹኑ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስለ ክርስቶስ ትታ ስለ ቅዱሳኑ ብቻ ትሰብካለች ይሉናል:: +በእጅጉ ከሚያሳዝኑኝ ነገሮች አንዱ የቅዱሳን ሐዋርያት (የ120ው ቤተሰብ) መዘንጋት ነው:: ከ120ው ቤተሰብ የአብዛኞቹ ስም በመዘንጋቱ: ሊቃውንቱም ዝምታን በመምረጣቸው "ያሶን: አርስጦስ: አፍሮዲጡ: ቆሮስ . . . እያልን የ72ቱን አርድእት ስም ስንጠራ ግር የሚለው ዓይነት ትውልድ ተፈጥሯል:: +እስኪ እንዲያው ቢያንስ ሐዋርያትንና ዐበይት ቅዱሳንን እናስባቸው:: አስበናቸው የሚጨመረልን እንጂ የሚጨመርላቸው የለምና:: +ዛሬ የምናስበው ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው:: ጌታችንን ከጥምቀቱ በኋላ ተከትሎ ለ3 ዓመታት ከእግሩ ሥር ቁጭ ብሎ ተምሯል:: ከጌታችን ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: +ለብዙ ጊዜ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ተመላልሶ ሰብኳል:: በመከራውም ተካፍሎታል:: ታላላቆቹ ሐዋርያት ሰማዕትነትን ከተቀበሉ በኋላ ለመጣው አዲስ ክርስቲያን ትውልድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በቃል የሰማውን አስተላልፏል:: +ወንጌልን ስለ ሰበከላቸው አሕዛብ ብዙ ጊዜ አስረው ይደበድቡት: ያንገላቱት ነበር:: አንዳንድ ጊዜም እሳት እያነደዱ ያቃጥሉት ነበር:: ፈጣሪው ግን በተአምራት እያዳነው ከርሱ ጋር አልተለየም:: +ከከተማ ወጥቶ በዱርና በእስር ቤቶች ብዙ ነፍሳትን: ሽፍቶችንም ሳይቀር ወደ ክርስትና ማርኳል:: ቅዱስ ያሶን ለረዥም ዓመታት ሰብኮ በመልካም ሽምግልና አርፏል:: ❖ ንግሥት ወለተ ማርያም ❖ +ዳግመኛ በዚህ ቀን ኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቡርክት ወለተ ማርያም ትታሰባለች:: +ወለተ ማርያም ማለት የደጉ አፄ ናኦድ ሚስት: የአፄ ልብነ ድንግልና የቅድስት ሮማነ ወርቅ እናት ናት:: በንግስትነት በቆየችባቸው ዘመናት (ከ1487-1500 ዓ/ም) የረሃብ ጊዜ በመሆኑ ብዙ ሕዝብ አልቆ ነበር:: +ቡርክት ወለተ ማርያም ከጾምና ከጸሎት ባሻገር የተራቡትን በማብላት ብዙዎችን ታድጋለች:: የንጉሡን ቤተሰብ ወደ መልካም ክርስትና በመምራትም የተመሰገነች ነበረች:: በዚህ ቀንም አርፋ ተቀብራለች:: ❖አምላካችን ከቅዱሳኑ በረከት አይለየን:: ❖ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት አንዱ) 2.አባ ብሶይ ሰማዕት 3.ቅዱስ አውሳብዮስ ቀሲስ 4.ቡርክት ወለተ ማርያም ንግሥት (የዐፄ ልብነ ድንግል እናት) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም 2፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3፡ ካህናት ዘካርያስ ወስምዖን 4፡ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5፡ አባ ዜና ማርቆስ 6፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት 8፡ ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ ++"+ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው . . . እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ:: +"+ (ሉቃ.10:17) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/nolawitm
نمایش همه...
ኖላዊት

"ጥሩ"ነትን በ "ልክ" ሳይሆን "ልክ"ን በ"ጥሩ" እንመዝን

“ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምስሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” (ቅዱስ እንድርያስ ዘቀርጤስ)
نمایش همه...
✝. ክርስቶስ ተንስዓ እሙታን . በዐቢይ ኃይል ወስልጣን . አሰሮ ለሰይጣን . አግአዞ ለአዳም . ሰላም . እምይእዜሰ . ኮነ . ፍስሐ ወሰላም ✝ መልካም የትንሳዬ በዓል አመሰግናለሁ።
نمایش همه...
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት ፪ ❖ ❖ ግንቦት 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ኢዮብ +"+ +የትዕግስት አባት ቅዱስ ኢዮብ በቅዱስ መጽሐፍ ላይ እንደተመለከትነው ያልተፈተነበት ነገር የለም:: ሐረገ ትውልዱም ከአባታችን አብርሃም ይመዘዛል:: *አብርሃም ይስሐቅን *ይስሐቅ ኤሳውን *ኤሳው ራጉኤልን *ራጉኤል ዛራን *ዛራ ኢዮብን ይወልዳሉ:: +ቅዱስ ኢዮብ የነበረው እሥራኤል በግብፅ በባርነት ሳሉ ነበር:: ኢዮብ ይሕ ቀረህ የማይሉት ባለጠጋ: ደግና እግዚአብሔርን አምላኪ ነበር:: የኢዮብ ደግነት የተመሰከረው በሰው (በፍጡር) አንደበት አልነበረም:: በራሱ በፈጣሪ አንደበት እንጂ:: +በዚህ የቀና ጠላት ዲያብሎስ ግን ኢዮብን ይፈትነው ዘንድ ከአምላክ አስፈቀደ:: ጌታችን የጻድቁን የትዕግስት መጠን ሊገልጥ ወዷልና ሰይጣን ኢዮብን በሐብቱ መጣበት:: በአንድ ጀምበርም ድሃ ሆነ:: እርሱ ግን ፈጣሪውን ባረከ:: +ሰይጣን ቀጠለ:- የአብራኩን ክፋዮች (ልጆቹን) አሳጣው:: ኢዮብ አሁንም አመሰገነ:: +በሦስተኛው ግን ሰውነቱን በቁስል መታው:: ቁስል ሲባል በዘመኑ እንደምታዩት ዓይነት አልነበረም:: ከሰው ሕሊና በላይ የሆነ አሰጨናቂ ደዌ ነበር እንጂ:: ጻድቁ የአንድ ወጣት እድሜ ያሕል በመከራው ጽናት እየተሰቃየ ገላውን በገል ያከው ነበር::ከአፉ ግን ተመስገን ማለትን አላቁዋረጠም:: +በመጨረሻም ሰይጣን በሚስቱ መጣበት:: "እግዚአብሔርን ተሳደብ" አለችው:: እርሱ ግን መለሰ:- "እግዚአብሔር ሰጠ: እግዚአብሔርም ነሣ: ስሙ የተባረከ ይሁን::" +ከዚሕ ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር ሰይጣንን ከጎዳናው አስወገደው:: ጤናውን: ሐብቱን: ልጆቹን ለኢዮብ መለሰለት:: ካለው እድሜ ላይ 140 ዓመት ጨመረለት:: ጻድቅና የትዕግስት ሰው ቅዱስ ኢዮብ በ248 ዓመቱ በዚሕች ቀን ዐረፈ:: =>እግዚአብሔር አምላክ ከጻድቁ ትዕግስትና በረከት አይለየን:: ❖ግንቦት 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ (የትእግስት አባት) 2.አባ ቴዎድሮስ ሊቀ ምኔት (የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙርና የአቡነ አረጋዊ ጉዋደኛ) 3."22" ሰማዕታት (የአባ ኤሲ ማሕበር) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ 2፡ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 3፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ 4፡ ቅዱስ አቤል ጻድቅ 5፡ አባ ጳውሊ ገዳማዊ 6፡ አባ ሕርያቆስ ዘብሕንሳ ++"+ ወንድሞች ሆይ! የመከራና የትዕግስት ምሳሌ የሆኑትን በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያትን ተመልከቱ:: እነሆ በትዕግስት የጸኑትን ብጹዓን እንላቸዋለን:: ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታቹሃል:: ጌታም እንደፈጸመለት አይታቹሃል:: ጌታ እጅግ የሚምር: የሚራራም ነውና:: +"+ (ያዕ. 5:10) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
نمایش همه...
ዮም_ፍስሐ_ኮነ ዮም /ፍስሐ ኮነ/(2) በእንተ ልደታ ለማርያም በባርነት ሳለን ፍስሐ ኮነ ኃጢአት በአለም ነግሳ ፍስሐ ኮነ በድንግል መወለድ ፍስሐ ኮነ ቀረልን አበሳ ፍስሐ ኮነ እግዚአብሔር መረጠሸ ፍስሐ ኮነ ልትሆኚው እናቱ ፍስሐ ኮነ ይኸው ተፈፀመ ፍስሐ ኮነ የዳዊት ትንቢቱ ፍስሐ ኮነ አዝ____ የሔዋን ተስፋዋ ፍስሐ ኮነ የአዳም ዘር ህይወት ፍስሐ ኮነ የኢያቄም የሐና ፍስሐ ኮነ ፍሬ በረከት ፍስሐ ኮነ ምክንያተ ድኂን ፍስሐ ኮነ ኪዳነምህረት ፍስሐ ኮነ ድንግል ተወለደች ፍስሐ ኮነ የጌታዬ እናት ፍስሐ ኮነ አዝ____ በሔዋን ምክንያት ፍስሐ ኮነ ያጣነውን ሰላም ፍስሐ ኮነ ዛሬ አገኘነው ፍስሐ ኮነ በድንግል ማርያም ፍስሐ ኮነ የምስራች እንበል ፍስሐ ኮነ ሀዘናችን ይጥፋ ፍስሐ ኮነ ተወልዳለችና ፍስሐ ኮነ የአለም ሁሉ ተስፋ ፍስሐ ኮነ መዝሙር ዘማሪ ፍቃዱ አማረ @mahibermedanialemzebonga @mahibermedanialemzebonga
نمایش همه...
✝. ክርስቶስ ተንስዓ እሙታን . በዐቢይ ኃይል ወስልጣን . አሰሮ ለሰይጣን . አግአዞ ለአዳም . ሰላም . እምይእዜሰ . ኮነ . ፍስሐ ወሰላም ✝ መልካም የትንሳዬ በዓል አመሰግናለሁ።
نمایش همه...
"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው። በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።" የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን https://t.me/nolawitm
نمایش همه...
ኖላዊት

"ጥሩ"ነትን በ "ልክ" ሳይሆን "ልክ"ን በ"ጥሩ" እንመዝን