Farankaa - ፈረንካ
رفتن به کانال در Telegram
The primary goal of this page is to enhance the financial literacy of Ethiopians by offering valuable insights on investment, banking, insurance, capital markets, and taxation.
نمایش بیشتر1 775
مشترکین
+124 ساعت
+67 روز
+1330 روز
آرشیو پست ها
1 775
Filannoo - Guyyaa 3ffaa
Hiriyoon koo sagalee naaf keennitanii na filattan cuufti keessan galatoomaa!
Kan hanga ammaatti sagalee naaf hin keenniinee maal eegaa jirtu ree?
LinkedIn irratti dorgommi goosa sadiin na filataniiru. sagalee keessan naaf keennaa!
1. LinkedIn Change maker of the year
2. Consistent Linkediner of the year and
3. Inspiring journey of the year.
liinkii gadi aanuu xuqaa na filadhaa.
https://lnkd.in/exw6nKic
1 775
Day 3...
Thank you all for voting for me so far!
ድምጻችሁን ለሰጣችሁኝ፣ ለመረጣችሁኝ ሁሉ ምስጋናዬ ትልቅ ነው።
እስካሁን ላልመረጣችሁኝ በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ድምጻችሁ ስለሚያስፈልገኝ ይሄንን ሊንክ https://lnkd.in/e2Sh-V3D አሊያም በፎቶው ላይ ያለውን QR code በመጠቀም ድምጻችሁን ትሰጡኝ ዘንድ እጠይቃለሁ።
___
I am honored to be nominated in three categories at the LinkedIn Changemaker Awards Ethiopia.
1. LinkedIn Change maker of the year
2. Consistent Linkediner of the year and;
3. Inspiring journey of the year
Please vote for me using the link https://lnkd.in/e2Sh-V3D or use the QR code on the picture
1 775
በሊንክዲን ላይ በተለያየ ጊዜ ከምለጥፋቸው ጽሁፎች በተጨማሪ በእዚሁ በሊንክዲን ላይ በቀረበልኝ ጥያቄ መሰረት፣
📚 Value event በአሜሪካ ኤምባሲ ውስጥ ከሚገኘው ከSatchmo American Center ጋር በመተባባር በ“Financial empowerment: Mindset, Smart Money Management, and Investment Strategies" ርእስ ላይ ባዘጋጀው የወጣቶች ስልጠና ላይ፣
📚 Aspire Consultancy ባዘጋጀው የ"Future Finance Leaders" የወጣቶች ስልጠና ላይ እንዲሁም፣
📚 Aspire consultancy ባዘጋጃቸው የካፒታል ገበያ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ Webinars ላይ በመሳተፍ፣
ማህበራዊ ግዴታዬን እና ኃላፊነቴን ለመወጣት ሞክሬአለሁ። ለወደፊቱም ኃላፊነቴን ለመወጣት እሰራለሁ።
በሊንክዲን የውድድር እጩነት በቀረብኩባቸው የሚከተሉት 3 ዘርፎች ላይ ከታች የተያያዙትን ሊንኮች በመጠቀም ድምጻችሁን ትሰጡኝ ዘንድ እጠይቃለሁ።
🗳 Change Maker of the Year
🗳 Inspiring Journey of the Year
🗳Consistent LinkedIner of the Year
https://surl.li/rcnzor
https://surl.li/hqxzxk
https://surl.li/pndckx
1 775
በሶስት ዘርፎች የዓመቱ የሊንክዲን ሽልማት ታጭቻለሁ። የሚመቻችሁ የሚከተለትን ሊንኮች በመጠቀም ድምጽ እንድትሰጡኝ እጠይቃለሁ።
Please Vote for me as Linkedner of the year using the following links;
https://surl.li/pndckx
https://surl.li/rcnzor
https://surl.li/hqxzxk
1 775
የሰው-ሰራሽ አስተውሎት /AI/ - በመተመማኛ ሰነድ /Lettet of Credit/ ለሚነግዱ ላኪዎች ጨዋታ ቀያሪ መሳሪያ!
___
የመተማመኛ ሰነድ (Letter of Credit) በዓለም አቀፉ ህግ፣ በUCP 600 የሚዳኝ ሲሆን በዓለም ላይ ካሉ ዋስትናቸው የተጠበቀ የክፍያ መሳሪያዎች መካከል አንዱ ነው። ይሁንና ይሄንን ዋስትና ለማግኘት ላኪዎች በመተማመኛ ሰነድ ህግ ውስጥ አንዱና ዋነኛ የሆነውን በUCP 600 አንቀጽ 5 ላይ የተጠቀሰ ህግ አክብረው መገኘት ይጠበቅባቸዋል።
ይህ ህግ በአጭሩ “Banks deal with documents—not goods.”
“ባንኮች ከሰነዶችን ጋር በተገናኘ እንጂ እቃን በተመለከተ ኃላፊነት የለባቸውም።” የሚል ነው።
ባንኮች በላኪው ባንክ በኩል የተላኩት ሰነዶችን በመተማመኛ ሰነዱ /LC/ እንዲሁም በማሻሻያዎች /Subsequent amendments/ ጋር በማገናዘብ አስመጪው የጠየቃቸው ሰነዶች እንዲሁም ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።
በሻጩ ባንክ በኩል ለክፍያ በቀረቡት የንግድና የፋይናንስ ሰነዶች እና በመተማመኛ ሰነዱ መካክል ትንሽ ልዩነት እንኳ ካለ ክፍያ ላይፈጸም ይችላል።
___
🔍 በሻጭ በኩል በቀረቡ ሰነዶችና በLC በተጠየቁ ሰነዶች መካከል የሚፈጠር ልዩነት ፈተና፣
በዓለም በተለያዩ ጥናቶች መሰረት ከፍተኛ መጠን ያላቸው ከLC ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ሰነዶች ለክፍያ በሚቀርቡበት ጊዜ በገዢው ባንክ /Issuing Bank/ ውድቅ ይደረጋሉ።
ከእነዚህ የክፍያ የላኩ ሰነዶች ውድቅ ከሚደረጉባቸው ምክንያቶች መካከል፣
• የእቃ ዓይነት በተለያዩ ሰነዶች ላይ ሲጻፍ የጎላ ልዩነት መኖር (ለምሳሌ በCommercial invoice ላይ “የህጻናት ጫማ” ተብሎ የተገለጸ እቃ በእሽህ ዝርዝር /Packing List/ ላይ “የህጻናት መጫወቻ” ተብሎ ቢገለጽ)፣
• የቀን ልዩነት፣ (ለምሳሌ የመተማመኛ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት የተዘጋጀ የንግድ ደረሰኝ ማቅረብ)፣
• ለክፍያ የተጠየቀው የገንዘብ ዓይነት መለያየት (ለምሳሌ በUSD እና በ Euro መገለጽ)፣ የተጠየቀው የገንዘብ መጠን መለያየት፣
• የተጫነው እቃ ዝርዝር ሁኔታ መለያየት (የቁጥር፣ የኪሎ ግራም፣ የጥራት ልዩነት)፣
• የገዢ ወይም የሻጭ ስም መለያየት፣
• በንግድ ደረሰኝ /Commercial Invoice/ እና Bill of lading /የመርከብ ጭነት ማረጋገጫ/ መካከል ልዩነት መኖር፣
_____
ይህ በላኪዎች ላይ ምን ዓይነት ችግር ሊፈጥር ይችላል?
• የክፍያ መዘግየት፣
• ተጨማሪ ወጪ (ለምሳሌ ገዢው የተፈጠረውን ልዩነት አልቀበልም፣ እቃውን አልረከብም ቢል የወደብ ኪራይ፣ ክፍያው ቢፈጸም እንኳ ከስህተት ጋር በተገናኘ እስከ 300 ዶላር የሚደርስ discrepancy fee)
• የተወዳዳሪነት መቀነስ
____
⚙️ የመተማመኛ ሰነዶችን ያለ ስህተት ማዘጋጀት ለምን አስቸጋሪ ሆነ ሌሎች ጥሰቶችስ ምን ምን ናቸው?
• ከመተማመኛ ሰነድ የክፍያ ስርዓት ጋር በተያያዘ የሚዘጋጁ ሰነዶች ቁጥር መብዛት (የንግድ ደረሰኝ፣ የጭነት ማረጋገጫ፣ የኢንሹራንስ ሰርተፊኬት፣ እቃው የተሰራበትን ሀገር ማረገጫ፣ ሰርተፊኬት የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፣ ምግብ ነክ ከሆነ ለሰው ተስማሚ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት፣ የእሽግ ዝርዝር፣ የክብደት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፣ እህል ነክ ለሆኑ ከተባይ ነጻ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና የመሳሳሉት)
• በመተማመኛ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱ ሌሎች ቅድመ-ሆኔታዎችን ለማክበር መቸገር (ለምሳሌ የመጫኛ ማረጋገጫው በመርክቡ ካፒቴን አሊያም በወኪሉ አለመፈረም)፣
• የUCP ህጎችን አለማክበር (ለምሳሌ በመተማመኛ ሰነዱ ላይ ከፋፍሎ መጫን የተከለከለ ቢሆንም ያንን ጥሶ ከፋፍሎ መጫን)፣
• በሰነዶች መካከል የይዘት ልዩነት መኖር፣
• በእጅ የሚደረግ የሰነድ አዘገጃከት ጊዜ የሚወስድና ለስህተት የሚዳርግ መሆኑ፣
____
🤖 ሰው ሰራሽ አስተውሎት አስመጪዎችን እንዴት ሊያግዝ ይችላል?
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ከመተማመኛ ሰነድን ሂደት በሚከተለው መንገድ ሊያግዝ ይችላል፣
📜 በእያንዳንዱ ሰነድ ውስጥ የተሰገሰጉትን ዳታዎች በመልቀም፣
📜 የተለቀሙትን መረጃዎች ከዋናው የመተማመኛ ሰነድና ከማሻሻያዎች ጋር በማነጻጸር፣
📜 ከUCP 600 ህግ ጋር መጣረስ አለመኖሩን በማረጋገጥ፣
📜 ስህተት ያለው ሰነድ ወደ ውጪ ለክፍያ ሳይላክ ወዲያው በመለየት፣
📜 በሰነዶች መካከል የተጣረሰ መረጃ ያለመኖሩን በማረጋገጥ (ለምሳሌ በመተማመኛ ሰነዱ እና በንግድ ደረሰኙ)፣
📜 ሰነዶችን በፍጥነት በማዘጋጀት የሰነድ ማቅረቢያ ወቅት ማለፍን /Late presentation/ በማስወገድ
___
የሰው ሰራሽ ለኢትዮጵያውያን ላኪዎች ምን ማለት ነው? ምን ይጠቅማቸዋል?
• ከስህተት የጸዳ የኤክስፖርት ሰነዳቸውን ለባንኮች በመሸጥ ክፍያቸውን በሰዓቱ በማግኘት የጥሬ ገንዘብ እጥረታቸውን ይፈታላቸዋል፣
• ከተጨማሪ ወጪ እና ከኮንትራት መፍረስ ጋር ከተገናኙ የህግ ክርክሮችን ወጪዎች ይታደጋቸዋል፣
• በዓለም አቀፍ ገዢዎች ዘንድ እምነትንና መልካም ዝናን ይፈጥርላቸዋል፣
• በዲጅታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የውስጥ አቅምን ይፈጥርላቸዋል፣ የውድድር የበላይነት ያጎናጽፋቸዋል፣
___
እንደ መውጫ...
📌የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሙያዊ ውሳኔን የሚተካ አይደለም። ይሁንና የተሻለ ውሳኔን ለመወሰን የሚረዳ መሣሪያ ነው።
📌በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን መጠቀም የሰውን ሚና ለመተካት የሚደረግ ውጊያ አይደለም። ዋነኛ ዓላማው የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከሙያዊ ልቀት ጋር በማስተሳሰር ፈጣንና ቀልጣፋ የንግድ ሂደትን ን ማረጋገጥ ነው።
📌ኢትዮጵያውያን ላኪዎች ይሄንን ዘመን አፈራሽ የቴክኖሎጂ ውጤት አስቀድሞ መተግበራቸው በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ በሰነድ አቀራረብ ላይ የሚፈጠርን መዘግየት ያሰስቀርላቸዋል፣ ተወዳዳሪነታቸውን ይጨምራል እንዲሁም ያልተፈለጉ ወጪዎችን ይቀንስላቸዋል።
1 775
በሊንክዲን የ"Consistent LinkedIner of the year category" በእጩነት ቀርቤአለሁ።
የሚመቻችሁ ብትመርጡኝ እና ድምጻችሁን ብትሰጡኝ ለሚቀጥለው የፓርላማ እጩነት ተነሳሽነት ትፈጥሩልኛላችሁ። ሊንኩን ከታች አያይዣለሁ።
https://changemakeraward.com/nominees?nomineeId=mnxmwo1yz_J2hPFipj
1 775
የእለቱ ትምህርት፣
ዕድሜአችሁ ምንም ያህል ቢሆን ሁሌም ወጣት ሳላችሁ በጀመርነው ኖሮ ብላችሁ መመኘታችሁ አይቀሬ ነው። ። ይሁንና ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወጣት የሆናችሁበት ቀን ነው።
-----
መልእክቱን ደግመው ያንብቡ!
1 775
Brazil authorized to sell meat products, other goods to Ethiopia, says official
By Reuters
ብራዚል የስጋ፣ የዶሮ እና የአሳማ ጨምሮ 17 ምርቶቿን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ፈቃድ አገኘች።
https://www.reuters.com/world/africa/brazil-authorized-sell-meat-products-other-goods-ethiopia-says-official-2026-04-07/
1 775
የግብር ከፋዩ Burden?
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሰራተኞች የጡረታ ክፍያን በውክልና ይሰበስባል። ይኸው ክፍያ ከእዚህ ቀደም በማኑዋል ይሰበሰብ ነበር። ብዙም የተፈጠረ ችግር አልነበረም።
ይሁንና በቅርቡ የአዲስ አበባም ከተማ አስተዳደር ገቢዋች ቢሮ ግብር ከፋዮች ወደ ኢ-ታክስ ሲስተም እንዲገቡ አድርጓል። ይሄ በዘመናዊ መልኩ ግብርን ማሰብሰብ የግብር ከፋዩን ጊዜ የሚቆጥብና የመንግስትን ገቢ በወቅቱ እንዲሰበሰብ ከማድረግ አንጻር ተገቢና ወቅታዊ ነው።
ይሁንና በእዚህ በታክስ ሲስተም ላይ ደንበኛው በወቅቱ ግብሩን አሳውቆና ከፍሎ እያለ በሲስተሙ ላይ በሚፈጠር ችግር ምክንያት የደረሰኝ በሰዐቱ አይላክም። የሚገርመው ደግሞ የኢ-ታክስ ሲስተሙ በላከው የE-Tax reference ቁጥር ተከፍሎ እያለ ሲስተሙ ግብር ከፋዩ ላይ ቅጣትና ወለድ የመያዙ ነገር ነው።
ከሁሉም ደግሞ እጅግ የሚገርመው የከተማ አስተዳደሩ የታክስ አመራሮች ሲስተሙ የፈጠረውን ችግር እና ቢሮክራሲ ወደ ግብር ከፋዩ የሚያስተላለፉበት መንገድ ነው።
አይበለውና በእዚህ መንገድ የታክስ ሲስተሙ ቅጣትና ወለድ ቢይዝ "እኛ ጡረታን በውክልና ስለምንሰራ ማመልከቻህን የግል ድርጅቶች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አስገባ" እያሉ ግብር ከፋዩን ለእንግልት ይዳርጋሉ። ይሄንን ስልጣን ኤጀንሲው ባይሰጣቸው እንኳ ከኤጀንሲው ጋር በመነጋገርና ውክልና በመውሰድ ችግሩን መፍታት ይችሉ ነበር። ይሁንና ችግሩን መፍታት የሚፈልግ አይመስልም።
በጣም የሚገርመው ነጋር ይሄንኑ አገልግሎት የፌደራል ገቢዎች የሚሰጥ ሲሆን በሲስተም ምክንያት የሚደጠር ችግር ካለ ችግሩን ወደ ግብር ከፋዩ ሳያስተላልፉ write-off ማድረጋቸው ነው። እንዴት ሁለት የግብር ሰብሳቢ አካላት የተለያየ አሰራር ሊኖራቸው ቻለ? ግብር ከፋዩንስ በአብሹም በድምብላሉም ማስጫነቅ ለምን አስፈለገ?
1 775
ከጠበቃ ሊያ ተረፈ ጋር በካፒታል ገበያ ህጎች ዙሪያ ያፈረግነውን ውይይት ታደምጡት ዘንድ እጋብዛለሁ።
https://youtu.be/AJGWEsHG3NE?si=MI4SVe7S1lyLW9t0
1 775
Insider trading/በውስጥ አዋቂ መረጃ መነገድ - የፈጠረው ጣጣ!
------
የቴክሳስ ሆውስተን ነዋሪ የሆነው የ42 ዓመቱ ታይለር ላውደን የእንግሊዙ BP Merger and acquisition Manager የሆነችው ሚስቱ BP ስለሚፈጽመው TravelCenters የተባለ ካምፓኒ ግዢ (Acquisition) ከአለቆቿ ጋር በስልክ ስትወያይ ይሰማል። በወቅቱ ሁለቱም በRemote ሥራቸውን ከቤታቸው እያከናወኑ ነበር።
BP በመላ አሜሪካ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ 280 ሬስቶራንቶች፣ ሱቆችና እና ሌሎች አገግልግሎቶች የሚሰጡ ቅርንጫፎች ያለውን Travels Centersን ለመግዛት የፈለገው የተቋሙን መረብ በመጠቀም የነዳጅ ችርቻሮውን ለማቀላጠፍ ባለመ ስትራቴጂ ነበር።
የስልክ ልውውጡን ሲያዳምጥ የነበረው ላውደን TravelCenters በBP መገዛቱን ተከትሎ የአክሲዮን ዋጋው እንደሚጨምር ስለገባው ጊዜም ሳይፈጅ የካምፓኒውን 46,450 አክሲዮኖች ገዛ።
የአሜሪካው የካፒታል ገበያ ተቆጣጣሪ የሆነው Securities and Exchange Commission /SEC/ ይሄንን የካምፓኒ ግዢ ዜና ለህዝብ ይፋ ያደረገው እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 16 ቀን 2023 ሲሆን ታይለር ይህ ዜና ለህዝብ ይፋ ሳይደረግ በፊት ግዢውን በመፈጸሙ ከፍተኛ ቅጣት የሚያስጥለውን የInsider trading ህግ ጥሷል።
ዜናው ለህዝብ በይፋ እንደተገለጸ የTravelCenters አክሲዮን የገበያ ዋጋ በአንዴ የ71% ጭማሪ አሳየ። ላውደንም ጊዜ ሳይፈጅ እጁ ላይ ያሉትን አክሲዮኖች በሙሉ በመሸጥ 1.76 ሚሊዮን ዶላር ትርፍ በእጁ አስገባ።
ላውደን ትርፉን ወደ ባንክ ሒሳቡ ካስገባ በኋላ ድርጊቱን ለሚስቱ አሳወቀ። ሚስቱ የፈጸመውን ወንጀል እንዳወቀች ፍቺ በመጠየቅ ቤቱን ጥላ የሄደች ሲሆን ጉዳዩን ወዲያውኑ ለSEC አሳወቀች። (እሷ ባታሳውቅም ከካምፓኒው ግዢ በፊት የተፈጸሙ የአክሲዮን ግብይቶች ላይ ምርመራ ስለሚደረግ ግዢው መፈጸሙ ይታወቅ ነበር)። ይሁንና ምንም እንኳ ወንጀሉን ለSEC ሪፖርት በማድረጓ ከህግ ተጠያቂነት ብትድንም ቀጣሪ ድርጅቷ BP በቸልተኝነት ከስሶ ከስራዋ አባርሯታል።
SEC የተፈጸመውን ጥሰት ጠቅሶ ክስ መሰረተ፣ ላውደንም ድርጊቱን በማመን በወንጀል የተገኘ የትርፍ ገንዘቡን ሙሉ ለሙሉ ከመመለሱም ባሻገር የወንጀል ክስ ተመሰርቶበታል።
--------
ይሄንን ታሪክ ያጋሯኋችሁ በቀላሉ ስለInsider trading ምንነት ንቃትን ለመፍጠር እንዲሁም ተቋማችሁን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ውስጥ ያስመዘገባችሁ፣ ለማስመዝገብ በሂደት ላይ ያላችሁ እንዲሁም የካፒታል ገበያው ተዋናዮች ትምህርት እንድትወስዱበት በማሰብ ነው።
-------
ምስል ChatGpt
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
