cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ህይወትን በግጥም 📜

☺☺እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ አስደሳች ህይወትን እና ስሜትን የሚገልጹ ግጥሞች ፣ወጎች ፣ታሪኮች፣ልብወለድ እንዲሁም የተለያዩ ጠቃሚና አስተማሪ ሀሳቦችን በፁሑፍ፣በምስል እና ትረካ ያገኛሉ 😍☺☺😍 ቻናላችንን ምርጫቹ ስላደረጋቹ እናመሰግናለን 🙏 😶😶😶ሁሉም ሰው ከልቡ ያለቀሰበት የሳቀበት በውስጡ ከትቦ ያኖረው የራሱ ታሪክ አለው

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
314
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+17 روز
+230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ተመልሰህ ዋጠኝ! ወይ ሞቃት አልሆንኩ ወይንም ቀዝቀዝ ያልኩ ለብ ባለ ህይወት ጌታዬን አስቸገርኩ አምላኬን አሳዘንኩ አንቅረህ ልተፋኝ ከአፍህ ላይ ደረስኩኝ አንዴ በጽድቅ ህይወት አንዴም በሃጢአት እየተመላለስኩ ነፍሴን ባስጨንቃት አንተንም ብበድል እባክህ ይቅር በል ተመልሰህ ዋጠኝ ፪× ከእቅፍህ አታስወጣኝ ታውቀዋለህና መሄጃ እንደሌለኝ አደራ ፈጣሪ ለጠላቴ ለእኔ አሳልፈህ አትስጠኝ ከእራሴ ጠብቀኝ። ✍ Betty @hiywotnbegetem @hiywotnbegetem @hiywotnbegetem @hiywotnbegetem
نمایش همه...
👍 6❤‍🔥 2
አቅም አጣው ጉልበት ወኔ እንዳልተውህ አይችል ጎኔ ፍቅር ፀጋ ነበር ሳውቀው ሠው ሁሉ ሲል የምሠማው ለኔ ግዜ ፀጋነቱን ትቶ እረስቶ ማጣት ሆነ ተበራቶ ልይዘው ስል የሚጠፋ ቀላል ሳለ የሚያስለፋ ፍቅር እና ፀፀት ቅጣት አንተን ማሠብ መብከንከኑ           ከ እረመጥ ነብሴን ጣላት ከእሳቶች በሚብሰው በናፍቆት           ተቃጠልኩኝ በ ብትንትን ሀሳቦችህ ሳትወስን           ተጎዳሁኝ ወይ አትወስን ወይ እኔ አልተው ሳክልኝም ተከሳተርክ ሁሌ ካ'ንተ           እመጣለው ነገሮችን አላስተውል ምንም ነገር            አይታየኝ ይሄ ጅሉ ሞኙ ልቤ ሁሌም አንተን            ሲያስታውሰኝ ላንተው📝ነው                                  ✍@koltafit 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱          @bewketuseyoum19          @bewketuseyoum19
نمایش همه...
نمایش همه...
BV Computer Repair

Call us 👇👇 📞 0931250190 📞 0704700190 📞 0937609277

በቅርቡ አዳዲስ አስቂኝ ቪዲዮዎችን John Tube ይጠብቁን https://youtube.com/watch?v=KEYmbH1oSA8&feature=shared
نمایش همه...

∙∙∙∙∙∙∙∙😔ልጅህ መባል ባዪገባኝም😔∙∙∙∙ ያለምኩት ቅንጦት ያለምኩት ደስታ በቤትህ ተኝቼ ከንተ ርቄ ሄጄ ቤቴንም ገምብቼ እኖርበት መስሎኝ ወልጄ ከብጄ እስከ ልጅ ልጆቼ ዓለም ጥሩ መስላኝ  እንደዛ ገምቼ አንተንም ላልሰማህ ልቤን አሸፍቼ ጥዬህ ስሄድ ፍቅርክን ገፍቼ ምነው እሺ አልከኝ ሳለው ታሳስቼ ምነው አልናፈኩህ ከ አይንህ ስር ጠፍቼ የምኖር መስሎህ ሁሉንም ረስቼ ? አልሆነማ አባ እደጁ በረደኝ ከ እቅፍህ ወጥቼ መርገም ደረሰብኝ ከቤትህ ጠፍቼ . . በዝቶ በሀጥአት መመላለሴ መች በርክቶልኝ የሰጠኸኝ ዉርሴ ክፋትንጅ ደግ አታወጣም ምላሴ እኔ ማነኝ እኔ ምንድነኝ አላውቅ ስለራሴ ስጋዬም ተራበ ተጨነቀች ነብሴ ብጮህ ከረፈደ ላዪሰማ ኪሴ በኔላይ ተጣብቃ የለበስኳት ልብሴ . . ስንት እንዳልበላሁ አማርጬ እስክጠግብ ቀለቤ ሆኖ አረፈ የእርያ ምግብ እሷኑን ስሻማ ስገጥም ግብግብ እንደ ዶፍ አወረዱብኝ አልቀራቸው ስድብ . . ተሳለቁብኝኮ እያሉ ወፍ ዘራሽ እንዴት ቀና ልበል እንደ ደጉ ወንድሜ እንደዛ አስቀዳሽ ህግህን አክባሪ እሱኮ ነው ታጋሽ አፈርኩኝ በእውነት አልፀለይኩም ጭራሽ በየትኛው አንደበቴ እላለው እማምላክ የት አለሽ . . ብቻ ልመለስ ወዳንተ ሌላው አልሆነኝም ያላንተ ብለፋም በረካም የለኝም እንደ ልጅነቴ እንደ አፍላነቴ ዛሬ ባትወደኝም ባሳዝንህም በክፉ ክፋት ቢጥለኝም አዉቃለሁ ታደርግልኝ ዘንድ ለእኔ አይገባኝም ክብሬን አንተን ስለተውኩ ክብርስ አይገባኝም ግና ምንም ብትጠላኝ ምንም ባትወደኝም እባክህ አባቴ ከ ባርያዎችህ እንዳንዱ ልኑር ልጅህ መባልንኳ ባዪገባኝም                                                                 ✍️𝒃𝒚 𝒅𝒆𝒎𝒔𝒊𝒔 @hiywotnbegetem @hiywotnbegetem @hiywotnbegetem
نمایش همه...
👍 4 1
አንበሳ ራበው አሉ ቀበሮን ጠርቷት "የምበላው ነገር አምጪልኝ አለበለዚያ አንቺን እበላሻለሁ" አላት ቀበሮም አህያ ጋር ሄዳ "አንበሳ ሊያነግስህ ይፈልጋልና እንሂድ" አለችው አህያም አንበሳው ፊት ዘውዱን ሊደፋ ቆመ አንበሳው አፈፍ አድርጎ ሊይዘው ሲል የአህያውን ጆሮ ቆረጠለት:: አህያውም እንደምንም ብሎ አመለጠ "ቀበሮ ሆይ! ለምን ዋሸሺኝ ? አስበልተሺኝ ነበር እኮ" ብሎ ሲጠይቃት "ተው እንጂ አትሳሳት! አንበሳው እኮ ጆሮህን የቆረጠልህ ዘውዱን ሲደፋልህ ጆሮህ እንዳይከለክለው ሊያመቻችልህ ብሎ ነው:: በል አሁን ተነስ እንሂድ" ብላ አስማማችው አህያ በቀበሮዋ ሀሳብ ተስማምቶ ወደ አንበሳው ተመለሱ አንበሳው ግን አህያውን በድጋሚ ሊይዘው ሲሞክር ጭራውን ቆረጠለት ግን እንደምንም አመለጠው "በድጋሚ ሸወድሺኝ! አንበሳው እኮ ጭራዬን ቆረጠኝ" ሲል ጮኸባት "ተው እንጂ አትሳሳት! አንበሳው እኮ ጭራህን የቆረጠልህ የንግስና ወንበርህ ላይ ስትቀመጥ እንዳይቆረቁርህ ነው:: በል ተመልሰን እንሂድ" ብላው አግባባችው አሁን ግን አህያው አላመለጠም:: አንበሳው አፈፍ አድርጎ ያዘው አንበሳውም ቀበሮዋን "ጥሩ ስራ ነው የሰራሺው:: በይ እንግዲህ ከሆድ እቃው: ከአንጎሉ: ከጉበቱ: ከሳንባው: ከልቡ እየመተርሽ አጉርሺኝ! " ሲል አዘዛት ቀበሮውም እንደታዘዘችው አድርጋ ነገር ግን ልቡን እና አእምሮውን ራሷ ሰልቅጣ አጣጣመችው አንበሳውም "ልቡ እና አእምሮውስ የታለ?" ሲላት "ጌታዬ አንበሳ! አህያው ልብ እና አእምሮ ቢኖረው ኖሮ ጆሮው እና ጭራውን ቆርጠኸው ተመልሶ አይመጣም ነበር እኮ" ስትል መለሰችለት አንበሳውም "እሱን እንኳ ልክ ነሽ" በዘመላዕክ እንድሪያስ የቀረበ!!
نمایش همه...
👍 2
#አይገኝም : : በህይወት ጎዳና፤ ሳንል ጎንበስ ቀና፤ ያለ እንቅፋት ያለ እሾ፤ አይገኝም የድል እርሾ። #ሄኖክ_ብርሃኑ @yeneeyita
نمایش همه...
🍲🍲ድስት ቢቀያየር 🥘🥘 ተመሳሳይ ቅመም ውስጡ አየጨመሩ አንድ ሆኖ ሳለ ሂደት አሰራሩ ወጥ ጣፈጠ አሉን ድስት አየቀየሩ : : እሺ ይሁን ግድ የለም እያወቁ ማለፍ ለኛ አዲስ አይደለም እያልን ለራሳችን ደጋግመን በመንገር ባይጣፍጥም በላን የሰጡንን ነገር ይሻለናል ብለን ባዶ ሆድ ከማደር:: : : ዘንድሮ ግን ተዉት ሆነናል ፆመኛ ስንት ቀን አለፈን በልተን ሳንተኛ : : ነገሩ እንዲህ ነው የመጣው ለውጡ መምረር ሲጀምረን የሚሰጡን ወጡ በጣም ከባድ ሲሆን አላምጦ መዋጡ መስዋት በመክፈል ፈልገን ቅያሪ ሾመን አስቀመጥን አዲስ ምግብ ሰሪ : : ሹማምንቶቹማ ስንቱን አፍዘዉት የሚሰራውን ወጥ መስለው ሚያሻሽሉት መቅመስ በሚል ሰበብ በጉርሻ ጨረሱት ሰዉን በረሃቡ በጠኔ ሊደፉት:: ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.