cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ያልታተሙ ገፆች✍

✍️ ዝም ብሎ መፃፍ(እያገናዘቡ) ዝም ብሎ ማንበብ (እያሰቡ!)❤️

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
194
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Someone said: ከፍቶክ ደብሮህ ከጎንህ ሚሆን ሰው ከሌለህ or ልትነግራቸው ፈልገክ ማስቸገር ነው ፣ መረበሽ ነው ብለህ ካሰብክ u have no friends ልክ ነው መሰል.........
نمایش همه...
“እውቀት ውቃቢ አይደለም ሰው ላይ ዘሎ አይሰፍርም እናንብብ ንባብ ምክንያታዊ አሳቢ እንድትሆን ያደርግሃል!!" ❤️
نمایش همه...
#ስለወንዶች… (ከፊያሜታ) • ወንዶችን ፍቅር ማስያዝ ደስ ይለኛል። ወንዶችን ፍቅር ማስያዝ ቀላል ነው። እንዴት መሰለህ? መጀመሪያ ሳገኘው ልክ ስፈልገው የኖርኩት ሰው አስመስዬ የልብ ልብ አሰጠዋለው። ግልፅ እሆንለታለሁ። ፍቅር አሳየዋለሁ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለጥቂት ሳምንታት አልለየውም። ሳላየው ውዬ አላድርም። ሌላ ሴት እንዲያይ ወይም አሳብ እንዲኖረው ጊዜ አልሰጠውም። እንዲለምደኝ አደርገዋለሁ። ደሙ ውስጥ እገባለሁ። ወንድ ሞኝ ነው፥ ውሻ ነው። ቶሎ ይለምዳል። የለመደኝና ደሙ ውስጥ የገባሁ መሆኔን ካወቅሁ በኋላ ገሸሽ ላደርገው እጀምራለሁ፥ ዛሬ አይመቸኝም፥ ነገ አይሆንልኝም ማለት አመጣለሁ፥ ካመረረ እሔድለታለሁ። ብሔድለትም የመንፈስ እረፍት አልሰጠውም። በፊት የማውቃቸውን ወዳጆቼን ስም እየጠራሁና ዝናቸውንና ደግነታቸውን፣ ኃይላቸውንና ወንድነታቸውን እያነሳሁ አስቀናዋለሁ። (355) ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠ #ስለሴቶች… (ከፀጋዬ) • ሴቶች መቼም ጥሎባቸው ላንድ ሰሞን ቀርቶ ላንድ ቀንም ባጋጣሚ ዝም ካሏቸው ተንቀው የተረሱ ስለሚመስላቸው ያኮርፋሉ። ዘላለም ተንከባከቡን የሚሉ ፍጡራን ናቸው። (151) መቼም ሴቶች ሲባሉ አስር፣ አስር ጊዜ ካልማሉላቸውና ካልተገዘቱላቸው የተወደዱ አይመስላቸውም። (153) ናቃቸው ይከተሉሃል። ከመጡ አክብረህ ያዛቸው ይወዱሃል። ውደዳቸው አርካቸው ግን አትመናቸው። (166) ሴቶች ፈልገውኝ ቢመጡም እኔ ፈልጌ እንዳመጣኋቸው አድርጌ ነው የምይዛቸው። ሴት ልጅ ከኔ ጋር ሆና ኩራትና ክብር እንዲሰማት አፈልጋለሁ። ሴት ልጅ በፍቅር ቀርቶ በጥልም ቢሆን መከበር አለባት የሚል ፅኑ አምነት አለኝ። (255) ሴቶችን አልለማመጣቸውም። እልክ መግባትም አልወድም። የማታዳምጠኝ ከሆነ ጥያት መሄድ ብቻ ነው የማውቀው። (348) በቀጠሮ ሴቶችን አምስት ደቂቃ መጠበቅ ግዴታ ነው፣ ይገባል። አስር ደቂቃ መስጠት ጨዋነት ነው። ከዚያ በላይ መቆየት ነው ግን ሞኝነት ነው። (349) • ፊያሜታና ፀጋዬ በበዓሉ ብዕር፣ ኦሮማይ
نمایش همه...
#ያንድ_ሰሞን_ፍቅር 👫🥀🌷 ያን ሰሞን ••• ቀርበህ ስታወራኝ በጨዋታ በቀልድ ከብሶት ወጥቼ ከድብርቱ መንገድ ሀሳብ የለሽ ሁኜ ስቂያለሁ ከልቤ የደስታን ቡልኮ ካካሌ ደርቤ ያን ሰሞን ••• 🌹 ለኔ ያለህ ክብር ፍፁም ትህትና የጨዋነት ለዛህ ላየህ ስታስቀና በማሰብም ሆነ ወዲህ በመጨነቅ አቻህም አልነበር ጎኔን በመጠየቅ ያን ሰሞን •••• 🌹 ፅዶች ከበዙበት ሰፊው መናፈሻ በሀሴት ፈክቼ ልክ እንደ ፈንዲሻ ፍቅር በማሾክሾክ መውደደ ስታወጋኝ የነገውን ጉዞ በተስፋ ስትሞላኝ ከቅፍህ ገብቼ ተንተርሼ አንተኑ ተመኝቼ ነበር ባልመሼ ስል ቀኑ ያን ሰሞን ••• 🌹 ወክ እያደረግንም ስሼኜኝ ወደቤት በጨረቃ ታጅበን በንፋሱ ፉጨት ምነው በረዘመ መንገዱ በራቀ እንዲሁ ስንጓዝ ጎህ በፈነደቀ እያልኩ በውስጤ ብዙ ጎጉቻለሁ በቃ ያንን ሰሞን ላየኝ አስቃለሁ ያን ሰሞን ••• 🌹 አንተነትህ ገዝፎ መውደድህ በርትቶ አቅሜን ሲያዳክመው በፍቅርህ እረቶ እስከ መጨረሻው ላደርግህ የራሴ አቀድኩህ ከልቤ ለብቼኛ ነፍሴ ከዛም እኔነቴን የሴትነት ልኬን ሰጠሁህ ፈቅጄ አሳልፌ እራሴን ያን ሰሞን ••• 🌹 ክርና መርፌ አይነት ባንድ ተጣበቅን ቅፅበት መደብ ልፊያ በላብ ተጠመቅን ባአፍታ ጥብብቆሽ በደቂቆች እልፈት እርካታን ጎበኜን የስሜቱን ግለት ከዛ ቀን በዃላ ••••🚶‍♂ እሱ ብልጥ ሆነ እኔዋ ተላላ የማቀው ወዳጄ ከቦታው ወረደ መቀዝቀዝ ጀመረ እያለም በረደ የቆለለው ክብሬም ሳይቆይ ተናደ ጨዋታና ቀልዱም እንደጉም ተነነ መደወሉም ቀረ አብሮነት መከነ ይወደኛል ያልኩት ለብቻዬ ትቶኝ ከሌላ መነነ ❣ ለካ ሁሉም ነገር ነበር የውሻሼት ያንድ ሰሞን ፍቅር የገላ ፍላጎት ያኔ ሁሉም በቃኝ ስተቴም አነቃኝ ቢረፍድም ግን ገባኝ ውስብስብ መሆኑ የዚህ አለም መንገድ ኗሪም እንደበዛ ሳይመጣ የሚሄድ ዛሬ ብቻዬን ነኝ 🤷‍♀ አሁን ስላብሮነት አልጓጓም በጭራሽ የሚያስጀምር እንጂ የለምና አስጨራሽ #ሼን ✍
نمایش همه...
ከሰው ያልተወለደ ሰውን አይወክልም። (አዳምና ሔዋን ከሰው ስላልተወለዱ እኛን አይወክሉም።) ዳዊት ጸጋዬ ?
نمایش همه...
(እያለቀስኩ) እልፍ ህፃናትን - የታቀፋ ደጆች "ዳቦ ግዛልኝ" በሚሉት ፊደላት - አፍ የፈቱ ልጆች ጌም ፍለጋ ሳይሆን አንድ ብር ፍለጋ - የተዘረጉ እጆች በሞሉባት ሀገር - ችጋር በወረሳት ምን ይሉት ፈሊጥ ነው ❝ፈገግ በል❞ ብሎ - ሰውን ፎቶ ማንሳት ¯¯¯¯¯¯¯ ምስል አላበጅም ህሊናዬን ሽጬ - ራሴን እየወቀስኩ ይልቅ ፈጠን በል - አንሳኝ እያለቀስኩ 21/02/2015(📍4 ኪሎ) ✍🏾Trident
نمایش همه...
እሱን ፡መሆን ፡ቢያምረኝ ተይ ፡ አትፍረጅብኝ፡ ማሪኝ ፡ ግድ የለሽም ፡  ይቅር ፡ በይ ፡ እናቴ የመከዳት ፡እሾህ ፡አይኔን ፡ጓግጦት ፡ብሳብ ፡በደረቴ፥ የዉሸት ፡በትርሽ ፡አጥንቴን ፡ሰብሮት መቅነየን ፡አፍስሼ ፡ትቢያ ፡ላይ ፡ብንፏቀቅ፥ የክህደት ፡የጦርሽ ፡ልቤን ፡ወግቶት ፡ዉሃ ፡እና ፡እሳት ፡ቢፈልቅ፥ በአህያ ፡መንጋጋ ፡ሺህ ፡የጣልኩ ፡በሀሰት ምላስሽ ፡ከአርያም ፡ሲኦል ፡ስወድቅ፥ አላውቀውም ፡ብለሽ ፡ዶሮ ፡አልጮህ ፡ቢለኝ ፡ሺህ ፡ጊዜ ፡ብጠይቅ፥ በማሰብሽ ፡ብፈርስ ፡በመርሳትሽ ፡ብናድ ስመሽ ፡በመሸጥሽ ፡ብጋጥ ፡ብደቅ፥ ይቅር ፡በይ ፡በማርያም ፡ተይ ፡አትፍረጅብኝ ፥ ተስሜ ፡ከመሸጥ ፡እሱን ፡መሆን ፡ቢያምረኝ ።         በዘረ-ሠናይ           @Zeresenayy
نمایش همه...
የማይጠይቅ ሕዝብ አያውቅም! ------------- ሀገር ቢፈላሰፍ ይሰለጥናል! የማይፈላሰፍ ህዝብ ጉዞው የሗሊት ነው! ----------------- በሃሳብ የመጠቀ በፍልስፍና የረቀቀ በጥያቄ የጠለቀ ትውልድ ማፍራት ይገባናል። ራሱን የሚጠይቅ፣ ዓለሙን የሚጠይቅ፣ ተፈጥሮን የሚጠይቅ ትውልድ መልስ አያጣም። ፍልስፍና ፀጉርን ማንጨባረሪያ ሳይሆን ኣዲስ ሃሳብን ማፍለቂያ መሆኑን የሚያረጋግጡ ብልሆችን ማምረት ግድ ይለናል። በስካርፍ ሳይሆን በሃሳብ ሰይፍ አዕምሯቸውን የሚያስውቡ ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ንቁ፣ ሚዛናዊ፣ መርማሪ ወጣቶችን ለማብቀል የፍልስፍናን ችግኝ በየቤቱ ማፍላት ይጠበቅብናል። ኑሯቸውን መማረሪያ ሳይሆን ራሳቸውን መመርመሪያ የሚያደርጉ ችግሮቻቸውን የሚያጠኑ ብልሆችን መፍጠር ወሳኝ ነገር ነው። ሶቅራጦስ ጨቅጫቃዋ ሚስቱን ዛፕቴን አልፈታትም። ይልቁንስ በጭቅጭቋ ዓለምን ይመለከት ነበር። ለዚህ ነው 'ይቺን ነዝናዛ ሚስትህን ላንተ አትመጥንህምና ለምን አትፈታትም?' ሲሉት:- "ዓለምን በእሷ ነው የማውቀውና አልፈታትም" ብሏቸዋል። ከማይመች ነገር ላይ የሚመች ነገር መውሰድ፤ ከክፋት መልካም ነገር ማውጣት፣ ከስህተት ትክክለኛውን ነገር ማወቅ የፍልስፍና ልብ ላላቸው ብቻ የሚቻል ነው። ነገር ግን መፈላሰፍ መስሏቸው ራሳቸውን የሚጥሉ፣ ወገናቸውን የሚንቁ፣ የሃገራቸውን ባህል፣ ሃይማኖትና ታሪክ የሚያብጠለጥሉ፣ በጨዋነት ሃሳቦቻቸውን የማይገልፁ እነዚህ ፍልስፍና በደረሰበት ያልደረሱ ሃሳዊ ፈላስፎች ናቸው። ሃሳብ የሌላቸው መፅሀፍ ብቻ ተሸክመው የሚዞሩ ገልቱዎች ለራሳቸው የማያውቁ ድንዝዞች ናቸው። የልጆቻችን ዓለም እንደኛ ዓለም እንዳይበላሽ ጠያቂ እናድርጋቸው። የእኛን ያረጀና ያፈጀ አስተሳሰባችንን አንጫንባቸው። በነፃነት ያስቡ ዘንድ መንገዱን እንክፈትላቸው። ተቃራኒ ሃሳብ የማያስደነግጠው ትውልድ እንፍጠር! #ጠያቂዋሞጋቿፈላስፋነኝ @yaltatemu_gesoch
نمایش همه...
አለቃ ገ /ሀና ከጎንደር አዱ ገነት አፄ ምኒልክ መናገሻ ለደጅ ጥናት ሰንቀው በወረሀው ፆም አካባቢ ይጓዛሉ። ጥናት ወደ ቤተ መንግስት የወጡ ማታ ወደ ማደሪያቸው እየተመላለሱ የወረሀውን ፆም ጨርሰው ፍስክ ሲገባ ወደ ጠጅ ቤቶች ጎራ እያሉ መልከስከስ ይጀምራሉ። የያዙት ደረቅ ስንቅ አልቆ ወደ ማርትሬዛቸው ምንዘራ ጀምረዋል። ወርሀ ግንቦት ገብቶ ክረምቱ ሊጀምር ሲል ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረባቸው --ደጅ ጥናቱን ትተው ወደ ጎንደር ማቅናት ወይም እየተሟጠጠች ያለችውን ኪሳቸውን የሚያደልቡበት መንገድ መፈለግና ክረምቱን አራዳ ማሳለፍ፤ ደጅ ጥናቱንም መቀጠል። ታዲያ አንዷን የጠጅ ኮማሪት መሳም ከጀመሩ ቀኖች ተቆጥረዋል። አንድ ምሽት ግን ተንኮል አዘጋጅተው ኖሮ እሆን ብለው እዳሪያቸውን ሳይወጡ አብረው ይተኛሉ። ከሥራ በኌላ (ከመሳሳም በኋላ) እንቅልፍ መጥቶ የምኝታ ጓደኛቸውን እየረፈረፈ ሳለ፤ አለቃ ቀ .. ሰ . ስ ብለው ከጠፍር አልጋው እራቅ ብለው ይኮሱና ይዘውት ወደ አልጋው ቀ --ሰ --ስ ብለው ይጋደማሉ። ከዚያ የምኝታ ጓደኛቸውን (የጠጅ ቤቱን) ባለቤት መቀመጫ አካባቢ አብሰው የቀረውን ባካባቢው ያልከሰክሱታል። ሊቆዩ አስበው ሽታው ስላስቸገራቸው ሴትዮዋን መቀስቀስ ይገባሉ። ምነው ብለው ሲነቁ ሽታው እያድቀሰቀሰ የሚያመራው ወደሳቸው ጉያ መሆኑን የተገነዘቡ ኮማሪት። አለቃን። ስለፈጠረዎ በማሪያም ይዠወታለሁ። የሚፈልጉትን ሁሉ አደርጋለሁ። ከመሀላችን እንዳይወጣ ማለት። ደጅ ጥናቱንም ቢሆን እስከሚሳካልዎ እዚሁ ከኔ ጋር መቆየት ይችላሉ አሏቸው። አለቃም አይዞሽ ምንም ችግር የለም ያለ ነው። አትሰቀቂ ብለው ያረጋጓታል። በዚህ አስባብ አለቃ ወደ ጎንደር ሳይዘልቁ ክረምቱን ያለምንም ችግር ያሳልፋሉ።በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ደጅ ጠኙ ሁሉ ምኒልክ ግብር ሲገባ እሳቸውም ይገኛሉ። በመገኘታቸው የተገረሙ አፄ ምኒልክም "እንዴ አለቃ እዚህ ምን ስትበላ ከረምህ? " ብለው ሲጠይቋቸው ህ ..ም ብለው "አሬን ስበላ ከረምሁ።"ብለው መመለሳቸውን ሰምቻለሁ። @yaltatemu_gesoch
نمایش همه...
I want you to know that when I give you my heart, hope you accept all the broken pieces and keep them safe with you, and I know that there will be some missing pieces too, but I hope you do not mind. I will come vulnerable, soft, and breakable, but I hope you accept me as I am. I will write you silly love poems with all the words know and hope you will smile whenever you read them, just like do whenever I think about you. On some days you will find me sitting next to you, and I'll still be so far away, and I hope that on those days you will hold my hand a little tighter, and hug me a little longer. On some days I'll be upset with you, but I hope that on those days you will try to talk to me even more. Probably there will be days when we will have a fight, maybe not talk to each other the entire day, but I hope that at night when we sit at the dinner table, and I offer you a slice of cake with my hands, I hope you do not refuse. I hope you will take the entire cake and smack it on my face and laugh out loud saying this is how we make up. I promise I won't mind. Instead, I will kiss you with my cream covered lips and we will choose a different flavour for the next time. On the days when make you cry, hope you remember all the times when I made you laugh too. I hope you will forgive me for my mistakes, and if a day comes when you think that I do not love you anymore, I hope you will remember that I wrote you this letter before we even met, and that if needed, I'll write you a thousand more.     
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.