fa
Feedback
Addis Ababa Police Official

Addis Ababa Police Official

رفتن به کانال در Telegram

📈 تحلیل کانال تلگرام Addis Ababa Police Official

کانال Addis Ababa Police Official (@addispolice) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 17 936 مشترک است و جایگاه 12 275 را در دسته اخبار و رسانه‌ها و رتبه 1 933 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 17 936 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 28 سپتامبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 286 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 24 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 17.75% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 12.08% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 183 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 167 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 12 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“Addis police”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 29 سپتامبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته اخبار و رسانه‌ها تبدیل کرده‌اند.

17 936
مشترکین
+2424 ساعت
+2027 روز
+28630 روز
آرشیو پست ها
በተለምዶ "ትፍታ" የተባለውን የማታለል ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። *** አዲስ አበባ፤ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ አብዱልራዛቅ አገዢ፣ ግዜያለሁ ተሻገር፣ ይተያሁ ምንተስኖት እና አብዲ መሐመድ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን የፈፀሙት መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረደ 7 ልዩ ቦታው ግዮን መድኃኒት ቤት አካባቢ ከቀኑ 6:00 ሠዓት ገደማ ነው ። አንድ የቻይና ዜግነት ያላቸው ግለሠብ ከቸርችል ወደ መስቀል አደባባይ በእግራቸው እየተንቀሳቀሱ እያለ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አብዱልራዛቅ አገዢ የተባለው ወደ ግለሰቡ ቀርቦ ምራቅ የተፋበት ሲሆን በመቀጠልም ልጠርግልህ በማለት ከለበሰው ጃኬት ውስጥ አይፎን pro max 17 ሞባይል የዋጋ ግምቱ 360ሺ ብር የሚያወጣ ይዘው የሠሌዳ ቁጥሩ ባልታወቀ ቪትስ ተሽከርካሪ ከአካባቢው ተሰውረዋል። የግል ተበዳይ የተፈጸመባቸውን ወንጀል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የለገሃር አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው አቤቱታቸውን አቅርበዋል። ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ ላይ ባደረገው ክትትል አንድ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ውስጥ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3B83359 አ/አበባ በሆነ ቪትስ ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። ሞባይሉን ለማስመለስ በተከናወነ የምርመራ ተግባር አብዱልራዘቅ አገዢ ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ላይ በተደረገው ፍተሻ ንብረቱን በምሪት ማስመለሱንና በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ  ከለገሀር አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የሰውን እንቅስቃሴ እየተመለከቱ  ምራቅ እየተፉ ልጠርግልህ በማለት የስርቆት ወንጀል የሚፈፅሙ አንዳንድ ግለሰቦች መኖራቸውን ህብረተሰቡ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በንብረቱ ላይ በቂ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል። * ዘገባ፦ ዋና ሳጅን ደጀኔ ኡልፋታ * ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦ በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial? በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/ በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage, Serve with Compassion! 🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

photo content
+4

የማታለል ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ *** አዲስ አበባ፤ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ገደማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ደሳለኝ ሆቴል አካባቢ ነው፡፡ ተከሳሾች ካሳሁን አለሙ ፣ እንዳለው ቸኮል እና ትሚዝ ቢያሳዝነው የተባሉ ሲሆኑ በተጠቀሰው ቦታ ላይ አንድ የኩባ ዜግነት ያላቸውን የግል ተበዳይ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 51708 ኮሮላ ተሽከርካሪ በመያዝና የሠሌዳ ቁጥሩ እንዳይታይ በመፋቅ በግል ተበዳይ ላይ ምራቃቸውን በመትፋትና ይቅርታ በመጠየቅ የጠረጉ በመምሰል ከኪሳቸው ውስጥ የዋጋ ግምቱ 97ሺህ ብር የሚያወጣ አይፎን 13 ስልክ በመስረቅ ተሰውረዋል፡፡ የግል ተበዳይም የተፈፀመባቸውን ወንጀል የዜጎች ተሳትፎ መተግባሪያ Citizen Engagemnet Application EFPApp በመጠቀም ለፖሊስ ሪፖርት አድርገዋል፡፡ በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የምርመራና የክትትል ቡድን ወንጀሉ የተፈፀመበት ቦታ በመሄድ ተገቢውን ማስረጃ በማሰባሰብ ባከናወኑት የምርመራ ተግባር ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው መቻሉን የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል ምርመራ ም/ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ኤፍሬም አለሙ ገልጸዋል። ተጠርጣሪዎች በተያዙበት ወቅትም ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑንም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ ህብረተሰቡ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችን ከመደበኛው የፖሊስ የመረጃ ስልኮች በተጨማሪ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ ጥቆማዎች ሊበረታቱ ይገባቸዋል ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጥቆማ የመስጠት ባህሉንም ማጠናከር እንዳለበት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ * ዘገባ፦ ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ * ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦ በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial? በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/ በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage, Serve with Compassion! 🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

photo content
+4

የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም መጠናቀቁን የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡ *** አዲስ አበባ፤ መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የ2019 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ከኃይማኖት አባቶችና አመራሮች፣ ከአስተዳደር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡ በመስቀል አደባባይ በነበረው ደመራ የማብራት ስነ ስርዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቲዮስ 3ኛ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚነስትር ሸዊት ሻንካ፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳትና ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቂ የጸጥታ ኃይል በመመደብ እንዲሁም ህብረተሰቡን አጋዥ በማድረግ በተከናወኑ ተግባራት በዓሉ ኃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በሠላም ማክበር ተችሏል፡፡ የዘንድሮ የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የተለመደውን ትብብር በማድረጉ በተለይ ደግሞ መላው የፀጥታ አካላት ድካማቸውን ተቋቁመው  ኃላፊነታቸው በትጋት በመወጣታቸው በዓሉ ፍፁም ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማድረግ ተችሏል፡፡ ህብረተሰቡ ላደረገው ትብብር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ መላው የፀጥታ አካላት አመራርና አባላት የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡  በሚቀጥለው ሳምንት መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም በአዲስ አበባ የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በማግስቱ በቢሸፍ ከተማ የኢሬቻ ሆራ አርሰዲ በዓላት እንደሚከበሩ የጸጥታ ግብረ ኃይሉ አስታውሶ በዓላቱ በሠላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን አቅርቧል፡፡ * ዘገባ፦ ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ * ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦ በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial? በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/ በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage, Serve with Compassion! 🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

photo content
+6

የአዲስ አባባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያው ለአመራር እና አባላት ልጆች የትምህርት እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ። *** አዲስ አበባ፤ መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ድጋፉ የተደረገው በዋና ጠቅላይ መምሪያው ስር ከሚገኙ ዋና መምሪያዎች እና ከወረዳ ፖሊስ መምሪያዎች ለተውጣጡ የአመራርና አባላት ልጆች ነው። ድጋፉን የሰጡት የዋና ጠቅላይ መምሪያው የሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ ሲሆኑ ተቋሙ ከህግ ማስከበር ተልዕኮው ባለፈ በልማት እና በጎ አድራጎት ተግባራት ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ደብተር እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት አባሉን ለማገዝ እና የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናቶች ተገቢውን እውቀት እንዲቀስሙ መንከባከብ እና መደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል። ህፃናቱም ትምህርታቸውን በስርዓት መከታተል እንዳለባቸውም ምክትል ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ መልዕክት አስተላልፈዋል። ድጋፉ የተበረከተላቸው ወላጆች በበኩላቸው ዋና ጠቅላይ መምሪያው አባላቱን በተለያየ መልኩ መደገፉ ለሕዝብ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያነሳሳና ይበልጥ ተቋማዊ ፍቅርን የሚፈጥር ከመሆኑም ባሻገር የወላጆችን ችግር የሚያቃልል፣ ህፃናት ተማሪዎችን የሚያበረታታ ስለሆነ መሰል ድጋፎች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል። * ዘገባ፡- ዋና ሳጅን አምሳሉ መብራቴ * ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦ በፌስቡክ:- https://www.facebook.com/Addisababapolice በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial? በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/ በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage, Serve with Compassion! 🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

photo content
+6

photo content
+9

በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ አደንዛዥ አፅ አከማችተው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዋሉ *** አዲስ አበባ፤ መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተጠርጣሪዎቹ ወ/ት ኤልሳ ማንደፍሮ እና አቶ ማስረሻ ማንደፍሮ ሲባሉ ወንጀሉን የፈፀሙት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ገዳም ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው። ተጠርጣሪዎቹ በሚኖሩበት መኖሪያ ቤት ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ እንደሚያከፋፍሉ እና እንደሚሸጡ ከህብረተሰቡ ለፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የፍርድ ቤት የመበርበሪያና የመያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ባደረገው ብርበራ ለሽያጭ የተዘጋጁ በነጭ ወረቀት የተጠቀለሉ 75 ጥቅልል አደንዛዥ እፅ ተገኝቷል፡፡ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝም ገልጿል፡፡ አደንዛዥ ዕፅን መጠቀም ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መንስኤ መሆኑን አፅንኦት የሰጠው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከሱስ ነፃ የሆነ ትውልድን ለመፍጠር ህብረተሰቡ እያደረገው ያለው ትብብር የሚመሰገን በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብሏል፡፡ * ዘገባ፡- ሳጅን ፍሬወይኒ ገ/ጻዲቅ * ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦ በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial? በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/ በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage, Serve with Compassion! 🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

photo content
+4

የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰጪ ቡድን በበዓል ወቅት የሚያጋጥሙ አድጋዎችን ለመከላከል በሚያስችል አግባብ ውይይቱ አደረገ። *** አዲስ አበባ፤ መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ከመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓላት ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከል በሚያስችል ሁኔታ ላይ ከተለያዩ ተቋማት ከተውጣጡ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰጪ ቡድን አባላት ጋር አራት ኪሎ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት አዳራሽ ውይይት ተደረገ፡፡ በዓላቱ ያለ ንም የአደጋ ስጋት በሠላም ተከብረው እንዲውሉ የአደጋ ምላሽ ሰጪ ቡድኑ ራሱን ንቁ አድርጎ መስራት እንደሚጠበቅበት በአዲስ አበባ ፖሲስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ፍስሃ ጀምበሩ ገልጸዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የቡድኑ አባላት ታች ያለውን ሰራተኛ በአግባቡ ማሰማራት እና በዓሉን ለሚያከብረው ምዕመናን አደጋን ተከላክለው እንዲያከብሩ በቂ ግንዛቤ መስጠት ይጠበቅበታል በማለት ተናግረዋል።ቡድኑ በበዓሉ ወቅት አደጋን ለመከላከል የሚስፈልጉ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በአግባቡ መሟላታቸውን የማረጋገጥ ስራ እንደሚጠበቅበት ኃላፊው አንስተዋል። ስራው በጥብቅ ዲሲፕሊን መከናወን እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከመንገድ ደህንነት ጀምሮ የሚያጋጥሙ ለአደጋ ስጋት ይሆናሉ የተባሉ እንቅፋቶችን አደጋ ምላሽ ሰጪ ቡድኑ ለሚመለከተው መስሪያ ቤት በማሳወቅ ወዲያው እንዲስተካከል ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት። በማታም ሆነ በቀን ቡድኑ በቅርበት እየተገናኘ ለመፍትሄዎች መነጋገር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በሌላ መልኩ ሊፈጠሩ ይችላሉ የተባሉ ችግሮችን በመለየት በስነ ልቦና ዝግጁ ሆነን እንሰራለን ያሉት ተሳታፊዎች ለዚህ ስራ በትራንስፖርት፣ በመብራት አገልግሎት፣ በግንኙነት ረገድ፣ በጤና አጠባበቅ፣ በቀይ መስቀል፣ በውሃ አቅርቦት እና በመሳሰሉት በኩል የራሳቸውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን የየተቋማቱ  ተወካዮች አረጋግጠዋል። ወንጀል እንዳይፈጸም የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እንዲሁም ሌሎች የጸጥታ አካላት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውም በመድረኩ ተነስቷል። ስራው ሲሰራ የዓዓት ጉዳይ አፅንኦት ሊሰጠው እንደሚገባ የተጠቆመ ሲሆን እንቅስቃሴዎች የህብረተሰቡን የበዓል አከባበር ወግ እና ባህል ባከበረ መልኩ መሆን ይገባልም ተብሏል። * ዘገባ፡- ም/ሳጅን መልካሙ ዜና * ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦ በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial? በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/ በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage, Serve with Compassion! 🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

photo content
+2

photo content
+9

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የመስቀል ደመራ በዓል ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር በሠላም እንዲከበር በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ። *** አዲስ አበባ፤ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በመርሀ ግብሩ ላይ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር የኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ይደነቁ ጌቱ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ የፖሊስ ዋና መምሪያው ከፍተኛ አመራር እና የወንጀል መከላከል አባላት እንዲሁም የአስተዳደር አካላት ተገኝተዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የመስቀል ደመራ እንዲሁም የኢሬቻ በዓላት እንዲሁም በህዝብ ዘንድ በታላቅ ጉጉት የሚጠበቀው የመንግስት ምስረታ በሠላም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የፀጥታ አካላቱ በጋር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት በሀገራዊ ምክክር ወቅት እንዲሁም በ2018 ዓ/ም በነበሩ ኩነቶች ላይ እኩይ አላማቸውን ማሳካት ያቃታቸው ቡድኖች አሁንም የአደባባይ ኩነቶችን ለማወክ አቅደው ሊንቀሳቀሱ ስለሚችሉ እጅ ለእጅ በመያያዝ ህልማቸውን ማክሸፍ ይኖርብናል ብለዋል። መንግስት በ24/7 ያለ ድካም ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን የተሻለች ሀገርን እየገነባ ይገኛል እኛም ለሠላምና ፀጥታው በትጋት በቁርጠኝነት ልንሰራ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል። በክፍለ ከተማው በተመረጡ ቦታዎች፣ ህዝብ በሚበዛባቸው፣ በየአካባቢው እንዲሁም በአብያተ ክርስቲያናት የሚደመሩ ደመራ ቦታዎችን ፍተሻና አሰሳ ስራዎች ተከናውኗል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው ለፌደራል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአድማ መከላከልና መቆጣጠር የሬጅመንት 6 አመራርና አባላት፣ ለሠላም ሰራዊት፣ ለደንብ ማስከበር አባላት እንዲሁም ለኦሮሚያ ፖሊስ፣ ለሸገር ከተማ አስተዳደር ለኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ጋቸና ሲርና (ሠላም ሰራዊት)፣ እንዲሁም ለሚሊሻ አባላት በመስቀል ደመራ እና በኢሬቻ የአደባባይ በዓል በፀጥታ አጠባበቅ ዙሪያ የስራ መመሪያ ሠጥተዋል። ሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ በበዓላት ወቅት እርስ በእርስ በመረዳዳት እንዲሁም በደመራ ወቅት ተቀጣጣይ ነገሮች ተቀላቅው እንዳይገቡ፣ በኤሌክትሪክ መስመር አካባቢ እንዳይደመር ከመቆጣጠር በተጨማሪ በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ከወትሮ በተለየ መልኩ ጥንቃቄ በማድረግ እራሳቸውን እና ንብረታቸው ሊጠብቁ እንደሚገባ በዝግጅቱ ላይ የተገኙ አካላት መልዕክታቸውንአስተላልፈዋል። * ዘገባ፦ ዋና ሣጅን አዳነ ደስታ * ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦ በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial? በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/ በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage, Serve with Compassion! 🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

photo content
+7

photo content
+9

photo content
+9

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የሲ ኤም ሲ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በስራ አፈፃፀማቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ አመራርና አባላት እንዲሁም ድጋፍ ላደረጉ አካላት እውቅናና ምስጋና ሰጠ። ***      አዲስ አበባ፤ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በመርሀ ግብሩ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ንግስቲ አባዲ፣ የወረዳ 8 አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ዳንኤል ቡራዩ እና የሠላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ሸዋረጋ ሲሳይ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። የሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ም/ኮማንደር በላይነሽ ቢራራ ባደረጉት ንግግር ለፖሊስ መምሪያው እደሳ እንዲሁም በየቀጠናው ላሉ የቀጠና አስተባባሪ የፖሊስ አባላት ተደራሽነታቸው ይበልጥ የጎለበተ እንዲሆን ህብረተሰቡን በማወያየት፣ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ ሰባት ሞተር ሳይክል  ገዝተው አስረክበው አገልግሎት እየተሰጠበት ይገኛል ብለዋል፡፡   አመራርና አባላቱ በቁርጠኝነት የዋና ጠቅላይ መምሪያውን ተልዕኮ በማስፈፀም ረገድ እየሰሩት ያለውን ስራ ለማበረታታት የተሰጠው የምስጋና ሰርተፍኬት በቂ ባይሆንም ተነሳሽነትን ለመፍጠር እንደሆነ ተናግረው በቀጣይ የሚከበሩ ታላላቅ ህዝባዊ በዓላት በሠላም እንዲያልፉ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ተወካይ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ዳንኤል ቡራዩ የአካባቢው ነዋሪ በቁርጠኝነት በመነሳት የፖሊስ ቢሮ ደረጃው የጠበቀ መሆን እንዳለበት በማሰብ ካላቸው በመቀነስ እራሳቸው አስተባባሪ በመሆን የሰሩት ስራ እጅግ የሚበረታታ በመሆኑ ይህ ጠንካራ ትብብርና ጥምረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ኢንስፔክተር ከበደ አደሬ በበኩላቸው የፀጥታን ስራ ከህብረተሰቡ ጋር በጥምረት በመስራት አመርቂ ውጤት እንደሚገኝ በዚህ ፖሊስ መምሪያ የቢሮ ማስፋፊያ ግንባታ አይተናል ብለዋል፡፡   ትብብሩ ለቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት የተደረገላቸውን የምስጋና ስጦታ ይበልጥ ጠንክረውና ተበረታትተው እንዲሰሩ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።     ህብረተሰቡም በየአካባቢ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት ‹‹ እኔ ለሰፈሬ  ፖሊስ ነኝ ›› በማለት ቅጥር ጥበቃ በመቅጠር እንዲሁም አካባቢያቸውን እየወጡ እየጠበቁ የፀጥታውን ስራ በማከናወን እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም መልዕክት ተላልፏል። * ዘገባ፡- ዋና ሳጅን አዳነ ደስታ * ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦ በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial? በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/ በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage, Serve with Compassion! 🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

photo content
+7