Ethio- Freshman Tutorial center
رفتن به کانال در Telegram
In here we provide reading tips and also different materials that will help you in achieving A+in your studies.
نمایش بیشتر831
مشترکین
-124 ساعت
-337 روز
-1130 روز
آرشیو پست ها
ክፍል 2
3. ምን ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባችሁ ወስኑ 💭💭
በመጀመሪያ ፈተናው የጽሁፍ ✍ነው ወይስ የተግባር👷♂👷? ወይስ ቃለመጠይቅ ነው የሚለውን መለየት ወሳኝ ነው። ሁሉም ዓይነት
ፈተናዎች የራሳቸው የሆነ የተለያየ አይነት አቀራረብ አላቸው። በምሳሌ አስደግፎ ማብራሪያ መስጠት የሚጠይቅ ዓይነት ፈተና
ከሆነ ከዚህ በፊት የተሠሩ ፈተናዎችን እያመሳከሩ ጥቂት ቦታዎች ላይ በትኩረት መዘጋጀት።
ምናልባት ፈተናው ምርጫ አልያም አጭር መልስ የሚፈልግ ዓይነት ከሆነ ቀለል ያለና አጠቃላይ መረጃዎችን ለመያዝ
መሞከር።
4. እቅድ ማዘጋጀት 📑
ምናልባት ነገሮችን ቦታ ቦታ ለማስያዝና እቅዴ ለማውጣት የምናጠፋው ጊዜ የባከነ መስሎ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን
እውነታው በተቃራኒው ነው። ምክንያቱም ምን ማጥናት እንዳለባችሁና መቼ ማጥናት እንዳለባችሁ እቅዳችሁ ይነግራችኋል።
ከዚህ በተጨማሪም ምን ያክል እንደተጓዛችሁ ለመመዝገብና ለመከታተል ይረዳል።
የትኞቹን ማስታወሻ ደብተሮች 📓መቼ መመልከት እንዲሆንባችሁ፣ የትኞቹን መጻህፍት 📚📚ለተጨማሪ ማብራሪያ እንደምትጠቀሙ
እንዲሁም የፈተና ጥያቄዎችን መቼ መለማመድ እንዲለባችሁ በእቅዱ ውስጥ ማስገባት ውጤታማ ያደርጋል።
እዚህ ጋር መርሳት የሌለብን ለእረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴም ቦታ መስጠት እንዳለብን ነው።
5. ከፋፍሎ ማጥናት 💾
የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንዴ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ
ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል።
ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን
መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች
ያመክታሉ።
6. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ 📝
የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚለት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን
መፈተን ውጤታማ ያደርጋል።
ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንደናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው አልያም
የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመዳየት ይረዳናል።
ለጓደኞቻችሁም ጠቃሚ ሊሆን ስለሚችል ማጋራት አትርሱ፡፡
@freshmanforall
@freshmanforall
@freshmanforall
For further inquiries inbox me at @Bet1y
