cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Tomarit seliniya📝

Tomarit seliniya ... ምርጥ ግጥሞች, አጫጭር ሳቢ ታሪኮች ደስ ከሚያሰኙ አቀራረቦች ጋር ግጥሞችን እና ሌሎች ፁፎችን ለመላክ @AsktDr Follow me on tiktok @seliniya2

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
462
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-57 عوز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

፨፨፨ከዲያሪዋ የተዘረፈ፨፨፨ ክፍል አምስት(5) "እንዴት አመሸሽ sweety ያው እኔ ደናነኝ ብታይ ዛሬ ቆንጆ ቀን ነበር ማለት አጎቴ የሆነ ቦታ እንሄዳለን ብሎኛል አላልኩሽም ነበር እና የሆነ ቤት ይዞኝ ሄደ ብታይ በጣም ደስ የሚል ግዜ ነበረኝ በነገርሽ ላይ ይሄ ቦታ ለኔ ገጠር ቢሆንም ከዚ የባሰ ደግሞ በጣም ወጣ ያለ ቦታ አለ ። ቅድም እንደነገርኩሽ አዳሬ ሰላም አልነበረም የዛች አይጥ የአፍንጫዋ ቅዝቃዜ እስካሁን ይሰማኛል ታውቂያለሽ የማስታውሰው እንደህልም በብዥታ አደለም ልክ በእውኔ እንደተፈጠረ አይነት ነገር ነው የምር አሁን ድረስ ያስጨንቀኛል ። እና ጋሼ ፀበሉን ከረጨኝ በኋላ ቁርስ በላን በኋላ ካለንበት ትንሽ እራቅ ወዳለ ቦታ ሄድን በጣም ደስ የሚል አካባቢ ነው አረንጓዴ ነው በጣም ዝም ያለ የሚሰማው የወፎቹ ድምፅ እና በእርጋታ የሚንቆረቆር ምንጭ ነው ሰላም የሚሰጥ ቦታ ምነው "ልጄ ድርሰት መፃፍ ጀመርሽ እንዴ?" አለኝ ፈገግ አልኩ እና አይ ጋሼ ለምን እንደዛ አልክ አልኩት "ያው እያታሽ ጠለቅ ያለ ነው አለኝ "ተፈጥሮን የማስተዋያ አይን የተሰጣቸው እነሱ ብቻ ይመስል ሆ አልኩና በውስጤ ውይ ጋሼ እንዲሁ ቦታው ማርኮኝ ነው እንጅ የመድረስ ሃሳብ እንኳን የለኝም "በይ ልጅ እየረፈደ ነው ቶሎ ቶሎ እንሂድ" ሲለኝ ነቃ ብየ መራመድ ጀመርኩ ከዛ የሆነ ቤት ስንደርስ የኔ ልጅ ፀጉርሽን ሸከፍ አድርጊው እስኪ አለኝ ውይ በግድ ቀሚስ ማስለበሱ ሳያንስ አሁን ደግሞ ፀጉርሽን ሸክፊ ማለቱ ልክ አደለም አልኩ እና በውስጤ እሽ ብየ ፀጉሬን ወደኋላ እንደነገሩ ሸከፍኩት። ወደግቢው ስንገባ ደስ የሚል ምዓዛ ነው የተቀበለን ከበሩ ፊትለፊት የሆኑ እናት ሸራ ዘርግተው ጤፍ የጠራሉ ልክ ሲያዩን "ውይ ጋሻየ በሞትኩት እንደምን አደርክ ደናነህ እንዴት ናችሁ " እያሉ ወደኛ መጡ ጋሼ በፈገግታ "እቴትየ እንደምን አደራችሁ ደና አደራችሁ" አለና ጉልበታቸውን ስሞ ጉንጫቸውን ሰማቸው እና ወደ ቤት ገባን ያው የገጠር ቤት ስለሆነ ሁሉ ሙሉ ነው እያሉ ጠላውን ቆሎውን ቂጣውን አቀረቡልን ። ፊታቸው ላይ የማየው ፈገግታ ከልብ እንደሆነ ያስታውቃል "አንቺ .......ያ አባትሽ ሽፍታ ሁኖ ቀረ አደል?" አሉኝ እኔም አይ አብረን ልንመጣ ነበር እኮ አልኳቸው በውስጤ ወይ መምጣት😏 እያልኩ ትንሽ ቆይቶ ስንጠብቃኋቸው የነበሩት አባት መጡ ብታይ ቤብ ግርማ ሞገሳቸው በዛ ላይ እርጋታቸው ቀስ ብለው ነው የሚያወሩት ፂማቸው ወደታች እስከደረታቸው ቁልቁል የወረደ ነው ከትቁር ካባቸው ጋ በህብረት ሲታይ በተራሮች ምሃል እየተወረወረ የሚወርድ ፏፏቴ ነው የሚመስል ውይ ቤብ ሰው ሲያስል ሊያምር ይችላል 🙈? ብቻ እርጋታቸው ፣ ዝምታቸው ፣ እውቀታቸው እና ሲያወሩ ቃላቶቻቸው wow ለማንኛውም ግን የሆነ ጀልጋጋ ልጅ ዝምብሎ ሲያፈጥብኝ ነበር እኔስ የዋዛ መሰልኩሽ እንዴት እንደገላመጥኩት የሆነ ብቻ ደሞ እንደቁም ነገር ካንቺ ጋር ላወራበት አልፈልግም ........ ውዴ እየተጠራሁ ነው መሄድ አለብኝ ቻው እሺ ደና እደሪ እወድሻለሁ #ጦማሪት_ሰሊኒያ #ጦማሪት_ሰሊኒያ
نمایش همه...
👍 2🥰 1🤗 1
፨፨፨ ከዲያሪዋ የተዘረፈ ፨፨፨ ክፍል አራት (4) "በጣም የሚያስፈራ ድምፅ ፣ የማንኮራፋት አይነት >>>የሚወጣው ከዚ አስፈሪ ክፍል ውስጥ ይሁን ከውጭ ይሁን አላውቅም ። ድንገት ያ አስፈሪ ድምፅ ፀጥ አለ ያኔ ነው ልቤ ምን ያህል እየመታ እንደሆነ ያስተዋልኩት የምትርገበገብ እና የተጨነቀች ትንሽየ ልብ ድምፅ ያንን አስፈሪ ክፍል አናወጠው ከዛም እኔ ለመቆየት ብየ የምምገው አየር እና በመንቀጥቀጥ የማወጣው ትንፋሽ የልብ ምቴን ተከተለው ። አስጨናቂ ድባብ ኡፍፍ ልቤን ደከመኝ እጄን ወደልቤ አስጠግቼ ለመረጋጋት ሞከርኩ ግን ድንገት በጣም ቀዝቃዛ ነገር እጄን ነካኝ ትንፋሽ ያለው ነገር ነው እና ፀጉር ያለው ነገር ይመስለኛል እየገባኝ ሲመጣ አይጥ እጄ ላይ እየተራመደ እንደሆነ ገባኝ በዛ ቅፅበት ላንቃየ እስኪሰነጠቅ ድረስ ጩኸቴን አቀለጥኩት ከዛ በጣም በፍጥነት የሚራመድ ሰው ኮቴ ተሰማኝ ጩኸቴን ጨመር አድርጌ ማነው ? የት ነው ያለሁት? ፣ ማነው ወደዚ ያመጣኝ የሚሉ ጥያቄዎችን ጠየኩ ግን አሁንም የሚራመድ ሰው ድምፅ እንጂ ሌላ ቃላት አልተሰማኝም ። ስለዚ የሚመጣው ሰው እሩቅ ነው ማለት ነው አልኩ ግን ክፍሉ ድቅድቅ ያለ ጨለማ ውስጥ ምን እንዳለ እንኮን አላውቅም በድጋሚ ያ አስፈሪ አይጥ እግሬን ሲነካኝ ተሰማኝ አሁንም ክፍሉን በጩኸት አቀለጥኩት ግን በምሃል በጣም በሚስተጋባ ድምፅ አንቺ ትህትና ትህትና የሚል ድምፅ ሰማሁ አይኔን ስገልጥ አጎቴ ውሃ በኩባያ ይዞ አንዴ መፃፉን አንዴ እኔን ያያል ኡፍፍ ቅዠት ነበር አልኩኝ ለራሴ ተመስገን አልኩኝ እንዴት ነሽ ጓደኛየ አየሽ ምን እንደሆንኩ በጣም ነበር የጨነቀኝ ያልፋል ብየ እራሱ አልገመትኩም ነበር ውዴ ትንሽ ልረጋጋ እና ከአጎቴ ጋር እሄዳለሁ የሆነ ዘመድ ጋ ነው ምንሄደው ግን ቤብ የደርብሽ ( ያ ውሻ) ነገር በጣም አስጨንቆኛል ለማንኛውም ማታ በድጋሚ እናወራለን ደና ዋይሊኝ እሺ" አምላኬ ሆይ ይቺ ልጅ ምንድናት ቆይ ጭራሽ ህልሟን ሁላ ነው ዲያሪዋ ላይ ምትፅፈው ወይኔ እንደዚ ልጃጃል መጨረሻዋን ማየት ናፈቀኝ ለማንኛው ልተኛ
نمایش همه...
🔥 1👏 1
፨፨፨ከዲያሪዋ የተዘረፈ፨፨፨ ክፍል ሶስት(3) I think ካወራን ሶስት ቀን ሆነን አይደል ይቅርታ አድርጊልኝ እሺ ጓደኛየ ያው እንደምትገምቺው ድካም አለ በዛ ላይ ግርግሩ እሚገርምሽ ቤብ ምንም እየገባኝ አይደለም እኔ የመጣሁ ለሳምንት በጣም በዛ ቢባል ለሁለት ሳምንት ነው ግን አጎቴ የደስታው መጠን ለዘላለም የመጣሁ ያክል ነው ግርግሩ ያደክምሻል የምር ታውቂያለሽ ደግሞ እኔ ግርግር ሲበዛ ምን እንደሚሰማኝ ዝምብየ ያለጥቅም የተፈጠርኩ ያክል ይሰማኛል ከዚ ሰው ምሃል የኔ የምለው እና ከኔ ጋር የሚግባባ ባህሪው የሚስማማ እና ፈገግታየ ንዴቴ እና የማስመሰል ሳቄ የሚገባው ሰው ማነው ብየ እጠይቃለሁ እና መልሱ ደግሞ እራሴን ያሳምመኛል ብቻ ተይው ባክሽ ይልቅ የሆነ ሰው ናፍቆኛል "እገሌ" የምር የመጨረሻ የአይን ወጋችን አይረሳኝም እና የመጨረሻ ፁፍ የምር ግን የዛን ቀን ቻው እልሻለሁ ሲል ለቀልድ ቢሆንም ማለቱ አስደስቶኝ ነበር የእውነት እንደዛ ሲያደርግ አስቢው ስሚኝ ግን ፍቅር እዚ ጥሩ ግዜ ሚኖረኝ ይመስልሻል? እኔ ግን አይመስለኝም ግቢውን ብታይዎ የኛን compaund ነው የሚያክለው የጤፍ ገለባ፣ በሬ ፣ ዶሮ ፣ በግ እና ደግሞ ሰዎች ከግቢው የማይጠፉ ኗሪወች ናቸው እና ደግሞ በጣም ያስፈራኝ ነገር ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ "ደርብሽ" u believe honey ውሻ እኮ ነው እንደመጣሁ ካላቀፍኩዋት እና ከልሳምኳት ብሎ እንዴት እንደተገለገለ የምር እንዳትስቂ እንጂ ሽንቴን ልለቀው ነበር አንተነህ ጋ እንዴት እንደጮሁኩበት እና እሱ ደግሞ ምንድነው የሚያስጮህሽ ብሎ ይዞት በነበረው ዱላ ሊመታኝ ነበር😭😭 ቤብየ የዛን ቀን የተሰማኝን ስሜት ላስረዳሽ አልችልም ለማንኛውም ቤብየ ነገ እናወራለን እሺ አሁን ልተኛ ነገ የሆነ ቦታ እንሄዳለን እያለኝ ነበር አጎቴ ቻው እሺ ስለምትሰሚኝ እና ብቸኝነቴን ስለተጋራሽኝ አመሰግናለሁ ቻዎ ቻው እንደሚመስለው ይቺ ልጅ ቀበጥ ትመስላለች አሰብኩት ውሻው ሊጠመጠምባት ሲታገል እሶ ስትጯህ አንተነህ ሊመታት ሲል ብቻ አሰብኩት የሆነች ቀውስ ነገር ናት ግን ወጌሻ ያላየው ስብራት ያለባት ናት እስኪ እንግዲ ነገ ከስራ መልስ ደሞ አነባለሁ #ጦማሪት_ሰሊኒያ #ጦማሪት_ሰሊኒያ #ጦማሪት_ሰሊኒያ
نمایش همه...
👍 1🥰 1😁 1
፨፨፨፨ከዲያሪዋ የተዘረፈ፨፨፨፨ ክፍል ሁለት(2) "እንዴት ነሽ ቤብየ ያው ቤት እስከምደርስ እና እስከሚመሽ መጠበቅ ስላልቻልኩ ባስ ውስጥ ሁኜ ነው ምፅፍልሽ እንደምታቂው እረጅም ጉዞ ነው ። ምን ላወራሽ እንደቸኮልኩ ገብቶሻል አይደል😌 ከመስበው በላይ ነው የሆነው ብታይ አባቴ ጋ ባስ እስከሚሞላ ብለን ካፌ ውስጥ ቁጭ ብለን ነበር ያው እንደምትገምቺው ሁለታችንም አንገታችንን አቀርቅረን ከስልካችን ጋር የደራ ጭዋታ ይዘናል በምሃል አንደድንገት የፉጨት ድምፅ ሰምቼ ቀና ብየ ወደስልኬ ተመልስኩ ከዛ ግን ሳስተውል እኔ ና አንቺ የምናቀው ሰው ነበር ከዛ "ወይኔ አምላኬ የምር አደረገው እንዴ" ብየ ቀና ስል አልተሳሳትኩም እራሱ ነው🙈 "ምንድነው እንዲ የሚያስቅሽ"የሚል ከባድ ድምፅ😬 ለካ እሱን በማየቴ ስፈግ የአባቴን ካጠገቤ መኖር እረስቼው ነበር "አይ ምንም still know ሰው የቀልዳል " አልኩና ፈገግታየ ከስልኬ ወግ የመጣ እንደሆነ ለማስመሰል ሞከርኩ ከዛ በቆረጣ ቀና ብየ ሳየው ቻው በሚል እጁን አውለበለበልኝ ያው ምንም ማደረግ ስላልቻልኩ ባይኔ ብቻ ቻው አልኩት ግን አልገረመሽም ቤብ እንደቀልድ "ቻው ሳልልሽማ አልቀርም" ብሎ እኮ የምሩን ቻው አለኝ የሆነ ቀውስ ነገር ነው አይደል በቃ ቀሪውን በቃ ቤብ ለምሳ ልንወርድ ነው መሰለኝ ቻው እሺ በቃ እወድሻለሁ😊 ቆይ ይሄ ልጅ ግን ማን አባቱ ነው ??🤨 ብየ ሌላ ገፅ ላነብ ነበር ግን እንቅልፌ ሊደፋኝ ነው ስለዚ ብተኛ ይሻለኛል ገናለገና ማንነቱን ለማወቅ ብየ ልደፋ እንዴ ሆሆ #ጦማሪት_ሰሊኒያ #ጦማሪት_ሰሊኒያ #ጦማሪት_ሰሊኒያ
نمایش همه...
🤔 3🔥 1
፨፨፨፨ ከዲያሪዋ የተዘረፈ፨፨፨፨ ክፍል (1) "ላወራሽ ፈልጌ ነበር እናም በጣም ናፍቄሽ ነበር ግን ምንም አዲስ ነገር የለም መነሳት ፣ መተኛት ፣ መብላት ፣ መቀመጥ ህይወቴን የሞሉት "መ" ዎች ናቸው ግን ችግር የለውም አብረን መሆናችን እራሱ በቂ ነው ታውቂያለሽ ግን አንዳንዴ ሰው ብትሆኚ ባቅፍሽ እና ህመሜን ታክሚኝ ዘንድ ባለቅስ ደስ ይለኝ ነበር ስሚኝ ግን ነገ የማወራሽ ዜና እንደሚኖር እርግጠኛ ነኝ በቃ ነገ ጉዞ አለብኝ ሻወር ወስጄ ልተኛ .....እወድሻለሁ" ይላል እወነቱን ለመናገር ቀጣዩን ገፅ ለመግለጥ ብዙም አልጓጓሁም መብራቴን አጥፍቼ ማስታወሻውን ከትራሴ ስር ሸጉጬ ተኛሁ
نمایش همه...
🆒 4
00:27
Video unavailableShow in Telegram
እኛ ..........መንገዳችን ጠፍቶብን ኑሯችን ሁሉ መባዘን ሁኗል ለዛውም መልካም ነገር የመምረጥ እድል ኑሮን ፨መልካም ሰው መሆን ስንችል ከዲያብሎስ ጋር ተወዳጀን ፨በሰላም መድመቅ መዋብ ስንችል መንገዳችን ሁሉ በውጊያ የታጀበ እሩጫ ሁኗል ፨ከፈጠረን ተስማምተን ከፍ ብለን መብረር ስንችል ከሰውነት ዘቅተን እንደ ትንሽየ ነፍሳት መሬት ለመሬት እንርመጠመጣለነሰ ፨ ፨ ፨ ፨ የምር ግን ምን ሁነን ነው? #ጦማሪት_ሰሊኒያ #ጦማሪት_ሰሊኒያ
نمایش همه...
15.00 MB
😢 2🔥 1
አማን ይሁንልን ብለን እንጀምር እስኪ
نمایش همه...
🕊 3👍 2
Dawit_Tsige_Aman_Yihun_አማን_ይሁን_New_Ethiopian_Music_2018_Official.m4a1.40 MB
🔥 2
🌼🌼🌼🌼ተስፋ🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼 ሰውነት ሰው የሚሆነው ተስፋው ሲቀድመው ነው ፣ ፊት ለፊቱን የተስፋ ብርሃን ሲያፈካለት ምን እልባት ያለፈው አመታችን የኛም ነበር የኛም አልነበረም። የኛ አልነበረም እንዳንል በመከፋት ምሃል ሳናስበው የደስታ ሳግ አንቆናል ፣ ተስፋ በቋረጥንበት ስዓት ትዓምራዊ ሁነት አጋጥሞናል ፣ ያመነው ሰው ከጀረባችን ወግቶን ጥሎን ስሄድ የፈጣሪ ክንድ ድጋፍ ሁኖናል ፣ አለማችንን የሰጠነው ሰው አለመቻንን ይዞብን ሂዶ ባዶነትን ስንታቀፍ መፅናኛ ከወደለይኛው አምላክ አግንተናል ......የኛ ነው እንዳንል ልፋት እና ድካም ብቻ ታቅፈን እንዲሁ እንደባዘንን ቀርተን ይሆናል 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ግን አዲስ አመት ሁሌም አዲስ ተስፋን ይዞ ይመጣል አዲስ የመኖር ጉጉት ምን አለባት የምነሰማው ሁሉ ጥሩ አደለም ይሆናል ግን ወደፊታችንን የሚያውቀው ፈጥሮናል ብለን የምናመነው ነው ። መቼም ያለምክንያት አንድ ስዓት እንኳን አይጨመረንም 2016 ብለን እንድንቆጥር ያደረገን በምክንያት ነው አዲስ ቀናቷች እየጠበቁን ነው ዝግጁ ናችሁ?????? መልካም አዲስ አመት ቤተሰብ🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 #ጦማሪት_ሰሊኒያ #ጦማሪት_ሰሊኒያ
نمایش همه...
👍 1🤯 1
።።።።ፅሃይ ነበረችኝ።።።።። እኔ ገና ልጅ እያለሁ በጣም የምወዳት ፅሃይ ነበረችኝ፣ ሁልግዜም አወጣጦን ድምቀቷን ለማየት የምጓጓላት ፣ ሁልግዜም ፍካቷን የምናፍቅላት ። ግን ሳድግ ጮራነቷ አለፈ እና ንዳድነቷ ተንሰራፋ አይኔ እያየ የምወደው ብርሃኗ ጨረር ሁኖ አይኔን ወጋኝ ፣ብርሃኖ በዛና ሰቀቀኗ ባሰኝ፣ጊዜው በሄደ ቁጥር በሷ ላይ ያለኝን ተስፋ እና እምነቴን አጣሁኝ ☀️እመት ፅሃየ ምነው ምነው ብርሃንሽን ቀነስ አድርገሽ ወደቀድሞው ደስታችን ብንመለስ😒😒 #ጦማሪት_ሰሊኒያ
نمایش همه...
😢 4🥰 1