cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

በሰልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ ጽ/ቤት Mitto Woreda Public Communication

ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ ማድረስ ህዝብና መንግስትን ማገናኘት መረጃ አቅም ነው! Information is Power!

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
356
مشترکین
-124 ساعت
-57 روز
+130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ጠንካራ የፓርቲ ተቋም በመገንባት የፓርቲውን መሪነት ማረጋገጥና ሁሉንም ተግባራት በአደረጃጀት መፈፀም የፊት አመራሩ ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል-አቶ ቀድሩ አብደላ! የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የፓርቲውን የ2016 ዓ.ም አፈፃፀምና የ2017 ጠቋሚ ዕቅድ ከታችኛው መዋቅር ከተገኙ የፓርቲው አመራሮች ጋር ገምግሟል። በግምገማ መድረኩ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ ጠንካራ የፓርቲ ተቋም በመገንባት የፒርቲውን መሪነት ማረጋገጥና ሁሉንም ተግባራት በአደረጃጀት መፈፀም የፊት አመራሩ ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል። ፓርቲው በ2016 በጀት አመት በፓርቲው መሪነት በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ታቅደው መከናወናቸውን የገለጹት አቶ ቀድሩ በ2017 ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከ2016ቱ የላቀ እቅድ ታቅዷል ብለዋል። ይህንንም ለማሳካት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን አቀናጅቶ መስራት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል። የፓርቲያችንን መርህ፣ዕሳቤና እሴቶችን በአመራሩና በአባሎቻችን ከማስረፅ አንፃር ወጥነት ያለው ሊሆን ይገባል ያሉት የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቆም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ሙሀባ ሙስጠፋ ይህንን ሊቀርፉ የሚችሉ የአቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው መሰራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሸረፋ ሊገሶ በበኩላቸው ከአደረጃጀት ተግባራት ጋር በተያያዘ የአሰራርና መመሪያዎችን ጠብቆ ከመስራት አኳያ የሚስተዋሉ ጉድለቶች መታረም ኣለባቸው ያሉት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊው አቶ ሸረፋ ሌገሶ የአባላትን መረጃ አብዴት በማድረግ የጠራ የአባላት መረጃ ወደ ዳታ ቤዝ ማስገባት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የግምገማ መድረኩ በተግባር አፈጻጸማቸው የነበሩባቸውን ጉድለቶችን በመለየት ለቀጣይ በተሻለ ለመፈጸም የሚያስችል አቅም መቅሰማቸውን ተናግረዋል። ሰኔ 22/10/2016-ስልጤ ዞን ኮሙዩኒኬሽን።
نمایش همه...
የስልጤ የባሊቅነት ሴረ የ2016 ዮባጀ ዴረ በስልጤ ኣደ ጎዬ ተረሻን። ወራቤ፣ ሰኔ 22/2016 ቶ.እ (ስልጤ ዞን የመንግስት ተራከባት) የስልጤ ኣደ የባሊቅነት ሴረ የ2016 ባጀት ዘማን ዮባጀ ዴረ ሀውጄ በስልጤ ኣደ ጎዬ ተረሻን። የዞኒ ቡር አትንዳዳሪ የከድር አሊ፣ የዞኒ አደዋ ቱሪዝም መምረ ወሻይብ የናሲር ዶ/ር ይርዳው፣ የዞኒ አድል መምረ ወሻይብ የከዲር በረከት፣ የዞኒ ጎትለኜ ፍርድ ጋር ፕሬዝዳንት የአለሙ ነስሮ፣ ዮገሬትዋ ሱክት መምረ ወሻይብ የአብደለ ከድር፣ የዞኒ የአደ ባሊቅነት ሴረ ቂጨ ሙራሮይ ገራድ ዲሌቦ ገብሬዋ ገናሚ ሙራሮ የሜልቾይ ቦባጃይ ተዋሰዶን። ዮባጀ ዴራይ የዞኒ ቡር አቲንዳዳሪ የከድር አሊዋ የዞኒ ኣደኜ የባሊቅነት ሴረ ሙረ የገብሬይ ገራድ ዲሌቦ ተመራን። የዞኒ ቡር አቲንዳዳሪ የከድር አሊ ባክቾት አሳወኒሙ የስልጤ ባሊቅቸ የዳኝነት ሴረ ዩመተይ አድኖተከ አቁምሮት፣ ኣደ ፣ አፈከዋ ወግ ሺገከ ለመጪንት አትላልፎት ቡሪ ቀስድንከ በበሎት አጄረቦን። መንግስት ለስልጤ ኣደኜ የባሊቅነት ሴረ ገገከ አቀተለ ኢቃናነኮ ዋ ብለከ ያሻነኮ ኢንጀከ ታያገበ ኡግዠ ያሻነኮ ቡሪ አቲንዳዳሪ አትሬገጦን። ቦረዳም የውን በቀበሌ ያሉ የመንግስት ቃምቸ የባድ ባሊቅቸ ለባድ ወገሬትዋ ሽፍት ያለይሙይ አትዋጫት በጀረቦት ኡግዠኒሙ በጠቀለ ሀለት አቆሚሮ ቀጥሎት ያለቢሙኮ የከድር አሊ አዋለኮን። ኢንኩምንገ ባሊቅቸ ኣደኒሙ፣ ወግ ሽገኒሙ ታክማምቶት በድባየ ለሀቅ ዋ ለአድል ሊቃኑ ኢትጌባነምኮ ቡር አቲንዳዳሪ የከዲር አሊ አጄረቦን። በዞኒ ኣደኜ የባሊቅነት ሴረ ሙረ የገብሬ ገራድ ዲሌቦ በፊልኑም ሊኢቀደ የናሩይ መንግስትቸ ለባሊቅነት ሴራይ ኤት አዮቡይ የናረኮ አቻሎኔ አኩ ባለነቢ ሃለት መንግስት ያሺያነይ ኡግዠ በትቂበሎት ሀቀ አራክቦት አለቢነ በበሎት አቆመሮኔ ኤወዶን። በሜልቾይ ይነዛኒ የባሊቅቸ ሁንዱሉለ ከውነ ሪፖርት በዞኒ ኣደዋ ቱሪዝም ቡሪ ወሻይብ በናሲሪ ዶ/ር ይርዳው አቀረቦኔ ወባጀ ተረሼቢያን። ባሊቅቸ በሪፖርቲ ባሎ ያቡ ቲዮን የወረዳዶዋ ከተመ መትንዳደራሮ በሉሌም የስልጤን ኣደ ኢዶራን ብል በትቂራቀሮት ጦናቲ ሱተ ዮነ ዮጫነኮ ቢዢ ብልቸ የትረሱኮ ተጬቀማን። በሉሌም የደበሰጥራይ ደመ ያቅኖት ከውን ሰርቀዋ ተላጎት ሂንኩም ጅረዋ ገናም ጢፈ በዳኞት ሄራት ታለቆተከ በቡርከ ቴወዳን። መንግስት ቲኢቀዳይ በጠቀለ ሀለት ኡግዠ ያሻነኮ ባሊቅቸ ያቻሉ ቲዮን ሂታሚ ቁሚሮት ያለቢምኮ አቆመሮ ኤወዶን። በድባያም ተኦለ ጊቻቾ ያለይ የባሊቅነት ሴረ ባቁምሮት የታለቁ ሉላሉሌ ጢፍቸ ቢሮት ተኦለ ጊቻቾ ያለይ አድጋቦትዋ ተቻቦረት የጠቀለ ኢቆምራነኮ ተረሶትከ በዴራይ በፈትከ ነቃኔ ተዋለካን።
نمایش همه...
#የሪጀ ነቶ ለትቅራቀሮት ኢትረሶን የትቃጠባት ሉክትቸ: https://youtube.com/watch?v=RgMPU-_BTbw&si=UDS9_POxVyttysa1
نمایش همه...
#የሪጀ ነቶ ለትቅራቀሮት ኢትረሶን የትቃጠባት ሉክትቸ:

#የሪጀ ነቶ ለትቅራቀሮት ኢትረሶን የትቃጠባት ሉክትቸ:- አጎበር በሱኩተ በድጋለሎት ዋ ቡንፉቾ ዋ በሉላሉሌ ኤትቸ የቴለሉ መይቸ ባፊሶት ሪጀ ኢጠፋነኮ አሶት። በራጀ ነቶ የቴንዜ ሰብ በቀሊሎከ ሲለጦት ያቀትላን ሎነኮ አመሰቢ አፊየ ጣበ ኢንጃ'ንግሬ ተይብል ቦክት በሂዶት ባፊየ ሉባምቸ ኢቶቦን ደዋውቸ በሱት በቴወደይ ኬሶ በውሰዶት ተነቶይ ሲለጦት ያቀትላን። የሪጀ ነቶ በሱት ተክታተላት በላሱኒ ፈንቸርችሬ በባሊ ሩሀ ያትቄብጣን ለመውት ኢዳርጋን ነቶ ሎነ ኤት የሪጀ መልከትቸ የታንዙቡይ ማንም ሰብ ቦክት አፊየ ጣበ በሂዶት መርመረ አሶትዋ ታከሞት ያትኬሻን። ሚቶ ወረደ መትራከቤ
نمایش همه...
ትኩረት ለወባ ወረርሽኝ .... 🦟🦟‼️ ወባን መከላከልና መቆጣጠር ከእኔ ይጀምራል ..... ስለ ወባ በሽታ ምን ያክል ያውቃሉ ....👇 1. ወባ ምንድን ነው? ወባ በጥገኛ ተሕዋሲያን ምክኒያት የሚመጣ በሽታ ነው። የበሽታው ምልክቶች፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ማላብ፣ራስ ምታት፣ የሰውነት መጓጎል፣ማቅለሽለሽና ማስመለስ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ምልክቶቹ ከ48 እስከ 72 ሰዓታት እየቆዩ በድጋሚ ይታያሉ። ይህን የሚወስነው ግለሰቡን ያጠቁት/ቋት ተሕዋሲያን ዓይነትና በበሽታው ተይዘው የቆዩበት ጊዜ ነው። 2. ወባ የሚተላለፈው እንዴት ነው? 2.1.የወባ ተሕዋሲያን ፤ፕላዝሞዲያ ተብለው የሚጠሩ ባለ አንድ ሴል ፍጥረታት ሲሆኑ ወደ ሰው ደም ውስጥ የሚገቡት አኖፊሊስ በምትባለው ሴት ትንኝ ንክሻ አማካኝነት ነው። 2.2. አንድ ሰው የበሽታው ተሸካሚ በሆነች ትንኝ አማካኝነት ወባ ሊይዘው ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ አንዲት የወባ ትንኝ በበሽታው የተያዘን ሰው ደም በምትወስድበት ወቅት የወባ በሽታ አምጪ ተሕዋሲያኑ ወደ ወባ አምጪዋ ትንኝ ይተላለፋል። ከዚያም የወባ አስተላላፊዋ ትንኝ ተሕዋሲያኑን ሌላ ጤነኛ ሰው በምትነድፍበት ወቅት ታስተላልፋለች። 2.3. ተሕዋሲያኑ የሰው ልጅ ጉበት ሴሎች ውስጥ በመግባት ይራባሉ። 2.4. በጉበቱ ውስጥ ያሉት ሴሎች ሲፈነዱ ተሕዋሲያኑ ይወጡና የግለሰቡን ቀይ የደም ሴሎችን ይወርራሉ። ከዚያም ተሕዋሲያኑ በቀይ የደም ሴሎቹ ውስጥ መዛባታቸውን ይቀጥላሉ። 2.5. ቀይ የደም ሴሎቹ በሚፈነዱበት ጊዜ ተሕዋሲያኑ ይወጡና ሌሎች ቀይ የደም ሴሎችን ይወርራል። 2.6. በቀይ የደም ሴሎቹ ውስጥ የሚካሄደው ይህ ዑደት ይቀጥላል። ቀይ የደም ሴሎቹ በፈነዱ ቁጥር በበሽታው የተያዘው ሰው የወባ በሽታ ምልክቶቹ ይታዩበታል። 3. ራሳችንን ከወባ በሽታ መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው? ወባ በተደጋጋሚ በሚከሰትበት አካባቢ የምንኖር ከሆነ * በኬሚካል የተነከረ የአልጋ አጎበር በአግባቡ መጠቀም * ቤት ውስጥ የሚረጭ የተባይ ማጥፊያ መጠቀም * በመኖሪያ ቤትዎ የወባ አስተላላፊ ትንኝ በምሽት ወደ ቤት ውስጥ እንዳትገባ ቀዳዳዎችን መድፈን * በምሽት ውጪ ሥራ የሚሰሩ ከሆነ ሰውነትዎን ሙሉ ለሙሉ በልብስ መሸፈን *ቤትዎ ፀረ ወባ ኬሚካል ማስረጨትና ከተረጨ በኋላ እስከ 6 ወር ግድግዳውን አለመለቅለቅ *የወባ አምጪ ትንኝ ምቹ የመራቢያ ሙቀት ስታገኝ ከ24 እስከ 48 ሰዓት ባለ ጊዜ ውስጥ ስለምትፈለፈል በቤትዎ ዙሪያ ማንኛውም ለትንኝ መራቢያነት አመቺ የሆኑ ቦታዎች( የታቆሩ ውኃዎች፤ የቆጮ ግንድ፤ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ ስባሪዎች፤ የመኪና ጎማ) ማፋሰስ * በህመም ወቅት የታዘዘ መድሃኒት ሙሉ ዶዝ ጨርሶ መዋጥ ወባ በተደጋጋሚ ወደሚከሰትበት ቦታ ለመሄድ ያሰቡ ከሆነ ፦ *ጉዞ ከመጀመሪዎ በፊት ወቅታዊ የወባ መረጃ ለማግኘት ይሞክሩ * እዚያ በምትቆዩበት ወቅት፤ ወባ በሚከሰትበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚናገሩትን ምክሮች ተግባራዊ አድርጉ። * በበሽታው ከተያዙ በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ሞክሩ። የበሽታ ምልክቶች የሚታዩት ተሕዋሲያኑ ወደ ሰውነትዎ ከገቡ ከአንድ እስከ አራት በሚሆኑ ሳምንታት ውስጥ እንደሆነ ማወቅ ይኖርቦታል። ማድረግ የምትችሏቸው ተጨማሪ ነገሮች 1. በመንግስት የጤና ተቋማት አማካኝነት በሚሰጡ የጤና እንክብካቤ ፕሮግራሞች ተጠቀሙ። 2. መድኃኒት መግዛት የሚኖርብዎ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ቦታዎች ብቻ መሆን አለበት።( የጥራት ደረጃው ዝቅተኛ የሆነ ወይም ተመሳስሎ የተሰራ መድሃኒት በሽታው ቶሎ እንዳይድን ስለሚያደርግ ለሞት ያዳሪጋል!
نمایش همه...
ጠንካራ የፓርቲ ተቋም በመገንባት የመንግስት ተግባራትን ለማሳለጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ። *********** ሚቶ፤ሰኔ-20/2016 ዓ.ም.(ሚቶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን)በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት "ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ግንባታ ለጠንካራ መንግስት መሠረት ነው"በሚል መሪ ቃል የ2016 በጀት ዓመት የ12 ወር የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸምና የ2017 በጀት ዓ.ም.የዕቅድ ዝግጅት መድረክ ተካሂዷል። የውይይት መድረኩን የመሩት የሚቶ ወረዳ ዋናአስተዳዳሪ አቶ ሰባሃዲን ሎባ በሁሉም የልማት ዘርፎች የመንግስት ተግባራት በተገቢው እንዲሳለጡና ጠንካራ መንግስት ለመገንባት የፓርቲ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ጠንካራ የፓርቲ ተቋም መገንባት ከፍተኛ ሚና ስላለው የነበሩ ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ ተግባር ለመፈጸም አቅዶ መስራት ይገባል ብለዋል። ዋና አስተዳዳሪው አክለውም እንደ ወረዳ ከዕዳ ወደ ምንዳ ስልጠና ማግስት ጀምሮ ከመንግስትና ከፓርቲ ዕቅዶችና ግብ አኳያ ሲታይ በሌማት ትሩፋት ፣በገግ ለገግ ፣ በስራ ፈጠራ፣ በግብርና ልማት ፣ በትምህርትና ካጎራባች ህዝቦች ጋር ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት መገንባት መቻላችን ተስፋ ሰጪ ውጤት የታየበት በመሆኑ በቀጣይ በወረዳችን በሁሉም ዘርፍ ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ የበታች አመራሩ ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል። የሚቶ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፎሌ ሞሳ በበኩላቸው ከቀበሌ እስከ ወረዳ ማዕከል ያሉ ሁሉን ማህበራዊ መሠረቶች የነበሩባቸውን ጉድለቶች በተገቢው ለይቶ በማረም  ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቀጣይ የተሻሉ ተግባራትን ለመፈጸም ከወዲሁ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል ብለዋል። መድረኩ ላይ በወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በሆኑት በአቶ አክመል ኮርማ የቀረበውን የውይይት ሰነድ መነሻ በማድረግ ባለፉት 12 ወራት የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ውይይቶችን በማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል። የወረዳው አመራሮች፣የሁሉም ቀበሌዎች እና የፐብሊክ ሰሪቪስ የመሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢዎች፣የቀበሌ የፊት አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት መድረኩ ላይ ተሳትፈዋል። በመጨረሻም በአፈጻጸማቸው ፊት ለወጡ የቀበሌ የመሠረታዊ ድርጅቶች እንዲሁም የመንግስትና ፓርቲ ተግባራትን አቀናጅተው በማከናወን ውጤታማ ለሆኑ ቀበሌያት  የምስክር ወረቀትና ዋንጫ ተበርክቶላቸዋል። በዚህም መሰረት:- 1ኛ.ሸፎዴ ዳባር ቀበሌ (ለፈረጃት የመሠረታዊ    ድርጅቶች)  2ኛ.ሚቶ 01 ቀበሌ (መንደር 5)(ፈረጃት የመሠረታዊ ድርጅቶች)  3ኛ.ሚቶ 01ቀበሌ (መንደር4) (አፍራን የመሠረታዊ ድርጅቶች)  4ኛ.ኤደነባ አጋዎ ቀበሌ (መሀል አዴነባ የመሠረታዊ ድርጅቶች)
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.