cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Prime Tutor™

🌟Welcome to my channel🌟 If you stick with us in this channel, you will get very important lessons, brief notes✍️, study tips📔, useful practice questions❓, and other increasingly beneficial things. join my YouTube channel to get usefull videos

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
189
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#Update የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ፤ " ፈተና አንፈተንም " ያሉ ተማሪዎች በመደበኛው የፈተና አሰጣጥ በሚቀጥለው ዓመት ፈተና መውስድ  እንደማይችሉ አረጋግጠዋል፡፡ በግል መፈተን እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 948 ሺህ 322 ተማሪዎች ተመዝግበው ከ937 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ያልተፈተኑና በተለያዩ #አደጋዎች ፈተና ላይ ያልተቀመጡ፣ የወለዱ ተማሪዎች #ከአንድ_ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል። ከ2 ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የተማሪዎች ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር መገለፁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። ©tikvahethiopia
نمایش همه...
የ12ኛ ክፍል የናቹራል ተማሪዎች የፈተና ፕሮግራም ‼️ የ Social ተማሪዎች ጥቅምት 3 እና 4 ሙሉ ለሙሉ ከግቢ ሲወጡ የ Natural ተማሪዎች ከ ጥቅምት 5 ጀምሮ ወደ ግቢ ይገባሉ። በዚህ መሰረት 👇 🚩ማክሰኞ  08/02/15        ከ3:00 - 5:00 English        ከ9:00 - 12:00  Mathematics 🚩እሮብ  ከ 3:00-5:00 Aptitude               ከ 9:00 -11:00 Physics 🚩 ሐሙስ ከ 3:00 - 5:30 Chemistry                 ከ 9:00 -11:00 Biology 🚩አርብ    ከ3:00 - 5:00 Civics መልካም ዝግጅት ይሁንላችሁ። አድስ ነገር ካለ እናሳውቃለን 👏👏👏🙏🙏 @primetutor
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የዚህ Admission Card 👆 ባለቤት የሆንሽ ተማሪ ካርዱ ባስ ውስጥ ወድቆ ስለተገኝ በተከታዩ ስልክ በመደወል መውሰድ ትችያለሽ። 0910222366 ይህን መረጃ የተመለከታችሁ ሼር በማድረግ ተባበሩ። @tikvahuniversity
نمایش همه...
እባካችሁ አሽከርካሪዎች ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ! የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ትላንትና ሀሙስ በሰሜን ሜጫ ወረዳ በ " አምቦ መስክ " ቀበሌ አቅጣጫውን ከባህር ዳር ወደ ማርቆስ ያደረገ ሰሌዳ ቁጥር " አማ 17492 " የሆነ ተሽከርካሪ ወይም ኮስትር ተሽከርካሪ እና መነሻውን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ያደረገ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ጋር ግጭት ተፈጥሮ በተሳፋሪዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሷል። በአደጋው በአምስት ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከፈተናው የሚያግዳቸው አይደለም ተብሏል። የሰሜን ሜጫ ወረዳ ትራንስፖርት ፅ/ቤት ግጭቱ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት መፈጠሩን ገልጿል። በዚህ ወቅት ከአገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር ተያይዞ የትራፊክ መጨናነቅ ስላለ አሽከርካሪዎች በተገቢው ፍጥነት በማሽከርከር እራሳቸውን እና ተሳፋሪውን ከትራፊክ አደጋ እንዲታደጉ የሰሜን ሜጫ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አሳስቧል። ምንጭ፦ የሰሜን ሜጫ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ ቤት እና የሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን @tikvahethiopia
نمایش همه...
#እንድታውቁት መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መስከረም 26-28 ተጠቃለው  በመግባት መስከረም 29 ስለፈተናውና ተያያዥ ጉዳዮች በየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች ገለጻ የሚደረግበት ዕለት መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቆ ነበር። ሆኖም የእስልምና እምነት ተከታዮች መስከረም 28 የመዉሊድ በዓል አክብረዉ መስከረም 29/2015 ዓም እሁድ ጠዋት  መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸዉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። የፈተና እና ተያያዥ ጉዳዮች ገለጻ /Orientation/ ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እሁድ ከሰዓት በኋላ እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን የእምነቱ ተከታይ ተማሪዎችም ይህንን አውቀው በተጠቀሰዉ ሰዓት በመገኘት ገለጻ /Orientation/ እንዲከታተሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
نمایش همه...
የትምህርት ሚኒስቴር የብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ፦ (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር) - የፈተና ንክኪው በእጅጉ ተቀንሷል። - ከዚህ በፊት በፈተና አሰጣጥ ወቅት የነበረውን " የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ " የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም። - ተማሪዎች አንዴ ዩኒቨርሲቲ (ካምፓስ) ከገቡ በኃላ ከሌለው የውጪ ማህበረሰብ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አይኖራቸውም። ምንም ስልክ ወይም ሌላ የግንኙነት ነገር ይዘው አይገቡም። - ተፈታኝ ተማሪዎች ለ4 ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ እናበላቸዋለን ፣ እናጠጣቸዋል፣  እንከባከባቸዋለን ነገር ግን በፍፁም ከሌላው ዓለም ጋር አይገናኙንም። - ተማሪዎች ከሚነሱበት ቦታ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይሄዱ የክልል የፀጥታ ኃላፊዎች የፍተሻ ስራ ይሰራሉ፤ የክልል የፀጥታ አከላት ስራ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲ በር ላይ እስኪደርሱ ብቻ ነው ከዛ በኃላ ያለውን የፍተሻ እና ጥበቃ ስራ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ይሆናሉ። - ስልክ ይዞ አንድ ተማሪ ቢገኝ ስልክ ይቀማል ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ፈተናውን እንዳይወስድ ይደረጋል። - ተማሪዎች በምንም ሁኔታ ፈተና ከሚወስዱበት ግቢያቸው ውጭ መውጣት አይችሉም፤ ከማንም ጋር መገናኘት አይችሉም። - ከፍተኛ ዝግጅት እያደረግን ስለቆየን ችግር ይኖራል ብለን አናምንም። - በእስር ላይ ላሉ፣ በውጭ ላሉ የኮሚኒቲ ት/ቤቶች ፣ በፀጥታ ምክንያት ፈተናውን ለመውሰድ ለማይችሉ ሌላ ሁለተኛ ፈተና ተዘጋጅቶላቸዋል። በአንድ ወር ውስጥ ይሰጣቸዋል። የተፈጥሮ እና ሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በተለያየ ጊዜ መፈተናቸውን ተከትሎ ተመሳሳይ የሆኑ ትምህርቶች እንዴት ይሰጣሉ ? በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ላይ እንደተገለፀው የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት እና ኩረጃን ለመከላከል በ2ቱ ዙር ተፈታኞች መካከል ምንም አይነት ግኝኑነት አይኖርም። የመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ፈተናቸውን ጨርሰው ከወጡ ከቀናት በኃላ ነው ሁለተኛው ዙር ተፈታኞች የሚፈተኑት። ሁለቱም የሚወስዷቸው (የናቹራል እና ሶሻል) አንድ አይነት ትምህርቶች ላይ ጥንቃቄ ተደርጎ የተለያዩ ፈተናዎች ናቸው የተዘጋጁት። ተማሪዎች ስልክ ይዘው ባለመሄዳቸው ከወላጆቻቸው ጋር እንዴት ይገናኛሉ ? ትምህርት ሚኒስቴር ኩረጃን እና ስርቆት ለመከላከል ሲባል ተማሪዎች ወደ ሚፈተኑበት ተቋም ስልክ ይዘው መግባት እንደማይችሉ አሳውቋል። ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ፈታኞችም የፈተና ክፍሎች አቅራቢያ እና ፈተናው የሚሰጥበት አካባቢ ስልክ ይዘው መገኘት አይችሉም። በየዩኒቨርሲቲዎቹ አንድ አንድ ተወካይ የሚኖር ሲሆን በተወካዩ አማካኝነት ወላጆች ልጆቻቸውን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ይችላሉ። የህትመት ዝግጅቱ ምን ይመስላል ? የፈተናው ኮዶች ስንት ናቸው ? በአጠቃላይ የህትመት ዝግጅቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ጥንቃቄ የተደረገበት ሲሆን የፈተናው ኮዶች በፊት ከነበረው " 4 ኮድ " ወደ " 12 ኮድ " ከፍ ተደርጓል። ለወላጆች የተላለፈ መልዕክት ፦ ወላጆች ተማሪዎች ይዘው መሄድ የሌለባቸው ፣ እና ስለሚጠበቅባቸው ግዴታቸው አስገንዝበው መላክ አለባቸው።     @primetutor
نمایش همه...
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ፌደራል ፖሊስ ገልጿል። ፌደራል ፖሊስ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመቀናጀት ብሔራዊ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል። ፈተናው ከማንኛውም የፀጥታ ችግር ነፃ ሆኖ ተፈታኞች ያለምንም ስጋት ተረጋግተው መፈተን እንዲችሉ የፀጥታ መዋቅሩ ፈተናውን አጅቦ ለማጓጓዝ እና ጠንካራ ፍተሻዎችን ለማድረግ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገልጸዋል። @primetutor
نمایش همه...
#ብሔራዊ_ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኮማንድ ፖስት በፈተናው ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ፦ • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ • የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ • የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ • የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ • የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ • የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ሀላፊዎች እና የክ/ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ፦ - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ - ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ - ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ - አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ - ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተገልጻል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች አቅርበዋል። #የተፈታኞች_መብቶች_የሆኑት፡-  ➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው። ➭ በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው። ➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው። ➭ የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው። ➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው። ➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው። #የተፈታኞች_ግዴታ_የሆኑት፡- ➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት #ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት። ➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ  ሲመጣ  አንሶላ፣  ብርድልብስና  የትራስ  ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት። ➤ #ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት። #ለተፈታኞች_የተፈቀዱ_ነገሮች ፦ ➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ  ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት ➣ ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….) ➣ ገንዘብ (ብር) ➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ ➣ የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት) #ለተፈታኞች_የተከለከሉ_ነገሮች ፦ ⮕ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው። ⮕ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና  ሌሎች  ማንኛቸውም  ፎቶ፣  ምስል  እና  ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ  ዙሪያ  ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት  ወይም  መጠቀም  የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣  ሲጋራ፣  በሓኪም  ማዘዣ  የሌለው  መድኃኒት  (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ) ⮕ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ  45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡ ⮕ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ ሲሆን ፈተናው ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው ይፈተናሉ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ ያገኛሉ። (የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ) #tikvahethiopia @primetutor @primetutor
نمایش همه...
✅ Chemistry question Entrophy isAnonymous voting
  • Intensive
  • Extensive
0 votes