cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Amen Gospel Telegram Channel

#ሰዎችን #በክርስቶስ #ለክርስቶስ #ማድረግ #ነው 💥💥💥💥💥💥💥 #WELCOME TO OUR BLESSING CHANNEL 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ለበለጠ መረጃ +251941810160 ደውሉልን To our belssing telegram group https://t.me/+YcqErTQrE6M2NzFk Join as 🙏 https://t.me/helingjesus

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
943
مشترکین
+224 ساعت
+177 روز
+3430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

. ደሙ በመቃኔ °°°°°°°°°°°°°° ዘማሪት ምህረት ኢተፋ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° በአንተ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ ክብሬ (፯x) ሞገሴ ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ ደሙ ፡ በጉበኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ ሞት ፡ አለፈ ፡ ሄደ ፡ እራቀ ፡ ከእኔ ፡ ጋር የጌታዬን ፡ ደም ፡ አይቶ የኢየሱሴን ፡ ደም ፡ አይቶ (፪x) ሞት ፡ አለፈ ፣ ሞት ፡ አለፈ ሄደ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ የሞት ፡ መልአክት ፡ አያስፈራኝ ተሸፍኛለሁ ፡ አያገኘኝ (፪x) ዙሪያዬ ፡ ከደሙ ፡ ታጥሯል ያን ፡ ቅጥር ፡ አልፎ ፡ እንዴት ፡ ይገባል (፪x) ለጠላቴ ፡ የሃዘን ፡ ለእኔ ፡ የደስታ ፡ ቀን ፡ ነው ሞት ፡ እየገባ ፡ ያለው ፡ በጠላቴ ፡ መንደር ፡ ነው ይዙር ፡ እንጂ ፡ ዙሪያዬን ፡ እንደሚያገሳ ፡ አንበሳ ፍፁም ፡ አይቀናም ፡ አይችልም ፡ ከደሙ ፡ የተነሳ (፪x) ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ ደሙ ፡ በጉበኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ ሞት ፡ አለፈ ፡ ሄደ ፡ እራቀ ፡ ከእኔ ፡ ጋር የጌታዬን ፡ ደም ፡ አይቶ የኢየሱሴን ፡ ደም ፡ አይቶ (፪x) ሞት ፡ አለፈ ፣ ሞት ፡ አለፈ ሄደ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ በአንተ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ ክብሬ (፯x) ሞገሴ.  ✝️✟ መልካም የፋሲካ በዓል ✟✝️             ━   ━━⊱✿⊰━ ━ ━ ━        sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ            ▷ @jesusfollowing                 @jesusfollowers1                     ተባረኩበት🙏
نمایش همه...
በዘመናት መካከል ክንዱ የማይዝል፤ የፍጥረት ሁሉ አምላክ እና ጌታ የሆነው የናዝሬቱ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሲል በመስቀል ላይ ሞተ፤ ነገር ግን እንደ ሰው ሞቶ አልቀርም ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል። “ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።”   — ሉቃስ 24፥5 እንኳን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ           ✨ 𝐇𝐀𝐏𝐏𝐘 𝐄𝐀𝐒𝐓𝐄𝐑 ✨                 ✨ መልካም ፋሲካ✨      #Amen #Gospel
نمایش همه...
ዛሬ ማለዳ  እግዚአብሔር እንዲህ ተናገረ💥 ትንሳኤ ሆኖልናል 💥 ትንሳኤ ከክርስቶስ በተሰጠን እና  በተካፈልነው ህይወት በሞተው ከክርስቶስ ባልሆነው የኛ ማንኛውም ነገሮች ላይ የበላይ ሆኖ እኛን ከገዛ የትኛውም ነገሮች ፈቶ ለክርስቶስ ህይወት አስነስቶ ያቆመናል 💥ትንሳኤ በመብል በመጠጥ የሚናገኘው ህይወት አይደለም 💥ትንሳኤ ከክርስቶስ በተካፈልነው ደምና ስጋው የምናገኘው ዘላለማዊ ህይወት ነው 💥 የትንሳኤውን መንፈስ ስንካፈል አሮጌውን ነገር  ከህይወታችን ነቅሎ ያወጣዋል ፤  የጤንነት ችግር ካለ : ያለመከናወን : የተለያዩ የህይወታችን እንቅፋቶችን ነቅሎ ያወጣል።                 ✍️paster tesfahun
نمایش همه...
እንኳን #አደረሳችሁ!! ከትንሣኤ በኋላ ... እንኳን አደረሳችሁ መባባል ያለብን ስለ በዓል ሳይሆን ስለደረስንበት ዓለም ነው!! ... የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ #ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም #ደርሳችኋል!! ዕብራውያን 12፥²²-²⁴። ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ራሱ #ትንሣኤ ነው!! ከሙታን ወደ ተነሳው ወደ ኢየሱስ #ደርሳችኋል!! እንኳን #አደረሳችሁ!! ትንሣኤ በዓመት አንድ ቀን የሚጠበቅ በዓል ሳይሆን በየዕለቱ የሚያለመልም እና የሚያከብር ሕይወት ነው!! እርሱም፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!! ❝ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤❞ ዮሐንስ 11፥25። የትንሣኤን በዓል ሳይሆን ራሱን #ትንሣኤን ማለትም ኢየሱስን እናከብረዋለን!! እርሱን ደግሞ የምናከብረው በበዓል መንፈስ ሳይሆን በውስጣችን ባለው የትንሣኤ መንፈስ ነው!! ከሙታን የተነሳውን እያሰብን እና የትንሣኤውን ኃይል እየተረዳን በመንፈሱ ደስታ እንዋል!! መብላታችን፣ መጠጣታችን እና መልበሳችን እግዚአብሔርን አያስቆጣውም!! ዋናው ነገር የምናደርገውን ሁሉ ለእርሱ ክብር እናድርገው!! ክብር ሁሉ ለክብር አባት ለእግዚአብሔር ይሁን !! #Amen #Gospel
نمایش همه...
አንድ ወዳጅ ከመሞትህ በፊት ልትተዋወቀው የሚገባ አንድ ወዳጅ አለ። ይህ ወዳጅ አንተን መውደድ የጀመረው አንተ ከመወለድህ በፊት ነው። መኖር ሳትጀምር ያወቀህ፥ ሳታውቀው ያኖረህ፥ ሳትጠይቀው የኃጢአትህን ዕዳ የከፈለልህ፥ በነፃ ሕይወትን ሊሰጥህ እየጠበቀህ ያለ አንድ ወዳጅ ኢየሱስ!! ይህን አንድ ወዳጅ ስታውቀው ሰማይ ያውቅሃል። አንድ ኢየሱስን በመቀበል የእግዚአብሔር ስጦታዎችን ሁሉ ማለትም የኃጢአት ይቅርታ፣ ጽድቅ፣ የዘላለም ሕይወት፣ ልጅነት እና ክብር መቀበል ትችላለህ!! ኢየሱስ ይወድሃል!! ✍️messager kaleb
نمایش همه...
ወደ ኋላ የሚመልስ መንገድ የለም!! #ጀልባዎችህን አቃጥል!! የግሪኮች ጥንታዊ የጦር ዘመቻ ... መሪ ቃል "There is no turning back" የሚል ነበር። ወደፊት ለመሄድ ወደኋላ ሊመልሳቸው የሚችለውን ጀልባ ማቃጠል ይኖርባቸዋል። የጦር ሠራዊቱ ባሕር ካቋረጡ በኋላ ... የጦር ጀኔራሉ ... "ጀልባችሁን አቃጥሉ" ብሎ ያዛል። ወታደሮቹም ባሕር ያቋረጡባቸውን ጀልባዎች በገዛ እጃቸው ያቃጥላሉ። አሁን ወደኋላ የሚመልስ መንገድ እንደሌለ ግልፅ ሆነ። ቀጣይ ግባቸው ጦርነቱን ማሸነፍ ወይም መሞት ይሆናል። ይህን ካደረጉት ቄሳሮች ጁልየስ ቄሳር አንዱ ነበር። እኛም እንዲሁ ... የማንነት ለውጥ አድርገናል ማለትም በክርስቶስ በመሆን ከአዳም ታሪክ ተፋትተናል(2ኛ ቆሮ 5፥16-17)፤ መንግሥት ለውጠናል ማለትም ከጨለማው ስልጣን ወደ ሚወደው ልጁ መንግሥት ፈልሰናል(ቆላስ 1፥13-14)፤ በደም የተመረቀ መንገድ ውስጥ ነን፤ መንገዱ ወደኋላ አይመልስም!! ወደ መርከቡ [ወደ #ኢየሱስ] ስትገቡ ያላቃጠላችሁት ጀልባ በውጭ ካላችሁ አቃጥሉት - መርከቡ አስተማማኝ ነው!!! ✍️messager kaleb
نمایش همه...
#እንዳንወሰድ ❝ስለዚህ ከሰማነው ነገር ምናልባት #እንዳንወሰድ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል።❞ —ዕብራውያን 2፥1። እምነታችን የጀመረው ከሰማነው ሕያው ቃል ነው። (ሮሜ 10፥17) የእምነታችንን ንፅህና መጠበቅ የምንችለው በሰማነው እውነት በመደላደል ነው። የሚጠበቅብን ሌላ መስማት ሳይሆን በሰማነው በክርስቶስ ስር ሰደን መታነጽ ነው። (ቆላስ 2፥7) የዕብራውያን ፀሐፊ ... መጻፍ ሲጀምር ኢየሱስን የመጨረሻው የእግዚአብሔር አንደበት አድርጎ አቅርቦታል። ❝ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤❞ (ዕብራውያን 1፥2) እግዚአብሔር የተናገረን በልጁ ነው፤ እኛም የሰማነው ልጁን ነው። ፀሐፊው የጀመረውን አሳብ ሲጠቀልል ❝ስለዚህ ከሰማነው ነገር ምናልባት #እንዳንወሰድ ...❞ ብሏል። ይህ ማለት ከኢየሱስ እንዳንወሰድ እንጠንቀቅ። አሁን የኛ ሕይወት ልጁ በነገረን ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ከእርሱ ውጭ ላለመስማት መቁረጥ ይኖርብናል። ቅዱሳን ... የዕብራውያን ፀሐፊ ጭብጥ ወደ ፍጻሜ እንሂድ የሚል ነው። ምክንያቱም ከሁሉ የሚልቀው ኢየሱስ ስላለን እና የቀረን ወይም የጎደለን ስለሌለ ነው። #እንዳንወሰድ ... ማለት ትኩረታችን በሌላ ነገር ላይ እንዳይሆን፣ ዓይናችን ከኢየሱስ እንዳይነሳ፣ ሌላ ነገር ቀልባችንን እንዳይወስደው፣ ልባችን በሌላ ነገር እንዳይያዝ፣ ራሳችንን የሌላ ሆነን እንዳናገኘው፣ ተታለን ወይም ስተን እንዳንወድቅ ... አብልጠን እንጠንቀቅ!! ✍️messager kaleb
نمایش همه...
#ከአማኝ #ህይወት #መፅሐፍ #የተወሰደ ❤ ኢየሱስን ትታችሁ የምትሄዱት መንገድ አይኑር፤ እርሱ የሌለበት ነገር ሕይወት ኖሮት አያውቅም!! ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ... ''ኢየሱስን ወደጎን አድርጎ" የራስን ኑሮ ማደላደል ስለቀለላቸው ሰዎች እየሰማሁ ነው። ባለቀው ዓመት ብቻ ሦስት እህቶች በትዳር ምክንያት ወደ ሌላ ሃይማኖት መመለሳቸውን አስታውሳለሁ። በጊዜው የመጣልኝ አሳብ ''ኢየሱስን ትታችሁ የምትሄዱት መንገድ አይኑር፤ እርሱ የሌለበት ነገር ሕይወት ኖሮት አያውቅም" የሚል ነበር። ወገኖች ኢየሱስ ለእኛ ሲል ራሱን ትቷል፤ ራሱን ባዶ አድርጓል። ከእርሱ የሚቀድም ምንም ነገር የለም። ለጊዜው የነገሮች መቃናት ስሜት ይሰጥ ይሆናል፤ ዘግይቶ ግን የሚገባን ''ተራ ምርጫ" እንደ መረጥን ነው። በመጨረሻ ግልፅ ሊሆንልን የሚገባው ... ❝ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።❞ የሚለው ቃል የታመነ እንደሆነ ነው። —2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥13። ማለት እኛ ስለካድነው ... እርሱ ታማኝ መሆኑ አይቀርም! እኛ በእርሱ ላይ ያለን አቋም ቢለዋወጥ እርሱ ለእኛ ያለውን ልብ አይለወጥም!!                      ✍️messager kaleb
نمایش همه...