cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ምስራቅ ጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ East Gurage Zone Justice Department

+251904202912

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
530
مشترکین
+224 ساعت
+97 روز
+3530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
የውሀ ቆጣሪ በህገ ወጥ መንገድ በማቅረብ ፣ በማከፋፈልና በመግጠም ወንጀል የተሳተፉ ተከሳሾች በእስራትና በገንዘብ ተቀጥተዋል። ድርጊቱ የተፈፀመው መጋቢት ወር 2015 ቡታጅራ ከተማ ውስጥ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ የመቂቾ አንደኛ ደረጃ መምህር ሲሆን ከቡታጅራ ከተማ ውሀ ልማት ፅ/ቤት እውቅና የሌለውን የውሀ ቆጣሪ በህገ ወጥ መንገድ በማስመጣትና በማከፋፈል ከማህበረሰቡ ገንዘብ በመሰብሰብ በተቋሙ ላይ ጉዳት በማድረሱ በከባድ አታላይነት ተከሷል። ሁለተኛ ተከሳሽ የውሀ ዝርጋታ ባለሙያ ሆኖ መስሪያ ቤቱ ቆጣሪ እንዲገጥም ትእዛዝ ሳይሰጠው ቡታጅራ ከተማ 05 ቀበሌ ውስጥ ቆጣሪው የገጠመ በመሆኑ ስልጣንን ያላግባብ በመገልገል ወንጀል ተከሷል። ጉዳዩን ሲያከራክር የቆየው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም የወንጀል ድርጊቱን መፈፀማቸው በማረጋገጡ ጥፋተኛ ብሏቸዋል። የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብሎ አንደኛ ተከሳሽ ባይከዳ ደበበ በ4 አመት ከ5 ወር ፅኑ እስራትና 2000 ብር የተቀጣ ሲሆን ሁለተኛ ተከሳሽ በድሩ ሀምዛ በ6 ወር ቀላል እስራትና 1500 ብር ተጥቷል። የትኛውም የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችን ህግን ባከበረ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ መምሪያው ያሳስባል።
نمایش همه...
👍 4
ክስ እና የክስ መልስ ማሻሻል ✍ የክስ ማሻሻያው የክሱን ወይም የመከላከያውን አቤቱታ በማብራራት ክርክሩን በተሻሻለ ሁኔታ የሚገልፅ እና ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚረዳ ሆኖ ከተገኘ በተከራካሪውቹ ጥያቄ ወይም በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ማንኛዉም አቤቱታ ሊሻሻል ይችላል(ቁ 91)። ✍ ማሻሻያው መከናወን ያለበት ከፍርድ በፊት ነው። አቤቱታው ሲሻሻል ፍ/ቤቱ ስለ ሚኪሳራው አስፈላጊውን ትዕዛዝ መስጠት አለበት። የክሱ መሻሻል ነገሩን በመጀመሪያ ከቀረበለት ፍ/ቤት ስልጣን በላይ ያደረገው ከሆነ የመጀመሪያ ፍ/ቤት ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ያስተላልፋል። ✍ ጉዳዩ የተላለፈለት ፍ/ቤትም የነገሩን መስማት ይቀጥላል። በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 91 መሠረት አቤቱታውን ለማሻሻል የሚቀርቡ አቤቱታዎች በተገቢው ሁኔታ መቅረብ አለባቸው፡፡ የአቤቱታ ማሻሻያ የሚፈቀደው የቀረበው አቤቱታ ፍ/ቤትን የሚያሳምን እንደሆነ ነው፡፡ ✍ የሚሻሻለው ነጥብ ምን እንደሆነ ባልታወቀበት የሚፈቀድ ከሆነ የክርክር ሂደትንም የሚያበላሽ ከመሆኑም በላይ ፍ/ቤትም ግራ-ቀኝንም ለበለጠ ወጪና እንግልት የሚዳርግ ነው፡፡ ✍ አቤቱታ ማሻሸል መብት ብቻ ሳይሆን ፍ/ቤትን የማሳመን ግዴታም አለበት፡፡ ሚስጥር አድርገው ይዘው ነጥቦቹ ባልተጠቀሱበት አቤቱታዬን ለማሻሻል እንድፈቀድልን በሚል የሚቀርበው ማመልከቻ አቤቱታውን የሚያበራራ ወይም ለትክክለኛ ፍትህ አሳጣጥ አስፈላጊ መሆን አለመሆኑን በምንም መልኩ ማወቅም አይቻልም፤ የሚፈቀድበትም አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡ አንድ ተከራካሪ ክሱን ለማሻሻል ወይም ክርክሩን ለመለወጥ ፍ/ቤትን ለመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን ፍ/ቤቱ ግን ጥያቄውን የሚቀበለው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ክስ የቀረበበትን ጉዳይ በይበልጥ ግልጽ የሚያደርገው ወይም ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት አስፈላጊ መሆኑን ሲያምን ነው፡፡ ✍ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማናቸውም ጊዜ ፍርድ ቤት ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዳ ከሆነ ክሱ እንዲሻሻልና ክርክሩ እንዲለወጥ ሊፈቀድ የሚችል እንደሆነ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 21 በመ.ቁ 104621 በሰጠው ውሳኔ የክስ ማሻሻያ ነጥብ ተለይቶ መታወቅ ያለበት መሆኑንና ክሱ የሚሻሻልባቸው ነጥቦች ተገቢነት መመርመር ያለበት የማሻሻያ ትዕዛዙ ከመሰጠቱ በፊት እንደሆነ የሰበር ችሎቱ በሰጠው ውሳኔ አስፍሯል፡፡ ✍ ከዚህ ውጪ የሚሻሻልበትን ነጥብ ሚስጢር አድርገው ይዘው በደፈነው አቤቱታዬን አሻሽዬ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ በሚል የሚቀርበው አቤቱታ በፍርድ ቤቶች የተለመደ ተከራካሪ ወገኖችን ለወጪና እንግልት የሚዳርግ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ደግሞ በሚቀርቡት የመከላካያ መልሶች ክፍተቶች ሲገለጹ ክሴን ላሻሽል በሚል አቤቱታ ያቀርባሉ፤ ይህ ደግሞ ተገቢ አይደለም፡፡    
نمایش همه...
 በህግ በተቋቋመ ባለስልጣን ወይም የስራ ግዴታውን በማከናወን ላይ በሚገኝ በአንድ የህዝብ አገልጋይ በሆነ ሰራተኛ ላይ ሲሆን ነው በማለት በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡ ነገር ግን  እነዚህ ሁኔታዎች በህጉ ልዩ ክፍል ለወንጀል ማቋቋሚያ ወይም ለቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች እንደሚሆኑ በተደነገገ ጊዜ የወንጀል ቅጣት ለማክበድ ሲል ፍ/ቤቱ ይህንኑ ሁኔታ ዳድም ምክንያት ሊያደርግ እንደማይችል ህጉ ይደነግጋል ፡፡ 4ኛ ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች የወንጀሎች መደራረብ እና ደጋጋሚነት የወንጀል ህጉ በአንቀጽ 60 ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመዋል የሚባሉት  ሁለት ወይም ከሁለት ሚበልጡ አንድ አይነት ወይም የተለያዩ ወንጀሎችን አከታትሎ ሲፈጸም  በአንድ ድርጊት በአንድ ጊዜ ሁለት ወይም ከሁለት ባላይ የሆኑ ህግ ድንጋጌዎችን በመጣስ  በአንድ ድርጊት ልዩ ልዩ ግዙፋዊ ውጤት የሚያስከትሉ ወንጀሎችን በመፈጸም ጣምራ ወንጀሎችን መድረግ  በአንድ የወንጀል ድርጊት ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሆኑ ሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ አንድ አይነት ጉዳት ያስከተለ እንደሆነ እንደ ልዩ ቅጣት መከበጃ ምክንያቶች የወስዳሉ፡፡ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 67 አንድ ሰው ደጋጋሚ ነው ሚባለው የተወሰነበትን የእስራት ቅጣት በሙሉ ወይም በከፊል ከፈጸመበት ወይም ይህ ቅጣት በይቅርታ ከቀረለት ቀን ጀምሮ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ መነሻ ቅጣቱ ስድስት ወር የሆነ ቀላል እስራት ሊያስቀጣ የሚችል አዲስ ወንጀል አስቦ የፈጸመ እንደሆነ እንደ ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት የሚያዝ ያሆናል፡፡ በአጠቃላይ ከላይ በህጉ ላይ ከተዘረዘሩት ውጪ ሌሎች ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ እና መክበጃ ምክንያቶች ሲገኙ እና ይሄንኑ ፍርድ ቤቱ የሚቀበል ሲሆን ለምን እንደተቀበለው በምግለጽ መያዝ እንደሚችል ህጉ ደንግጎ ይገኛል፡፡
نمایش همه...
የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ምክንያቶች የወንጀል ህግ አንዱ አላማ እና ግብ ወንጀል እንዳይፈጸም መከላክል ሲሆን ይህም ስለ ወንጀል ድርጊቶች እና ስለ ሚያስከትሉት ቅጣቶች አስቀድሞ በማሳወቅ ተፈጽመው በተገኙ ጊዜም ለሌላው ትምህርት እንዲሆን አሰተማሪ የሆነ ቅጣትን በመቅጣል አለማውን የሚያሰካ በመሆኑ የሚጣለውም ቅጣት ወጥነት፤ ትክክለኝነት፤ ተገማችነት፤ ምክንያታዊነት እና ፍታዊነት ያለው መሆን አለበት፡፡ ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ በ1996 የወጣው የወንጀል ህግ ቅጣትን ያሚያቀሉና የሚያከብዱ ምክንያቶችን ፤ሁኔታዎችን፤ አይነቶችን እና ፍርድ ቤትም ቅጣትን ሲጥል ግምት ውስጥ ማስገባት ስላለበት ሁኔታዎች ፤እንደ ቅጣት ማቅለያ እና መክበጃም ምክንያቶች ሊያዙ የሚገባ ምክንያቶችን እና ቅጣት በሚጥልበት ወቅት እንዴት ማስላት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በዚህ ጹሁፍ በወንጀል ህጉ ላይ ያተዘረዘሩትን የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ምክንያቶችን በዝርዝር የምናይ ይሆናል፡፡ የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ምክንያቶች በ1996 የወጣው የኢ.ፊ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ምክንያቶችን ጠቅላላ እና ልዩ የቅጣት የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ምክንያቶች በማለት በሁለት ያሚከፍል ሲሆን እነዚህም፡- 1ኛ ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች የወንጀል ህጉ አንቀጽ 82/1 ከ ሀ እስከ ሠ ባለው ስር የተለያዩ ሁኔታዎችን መነሻ በማድረግ የቅጣት መቅለያ ምክንያቶችን በዝርዝር የሚያስቀምጥ ሲሆን እነዚህም ሁኔታዎች የጥፋተኛውን ግላዊ ሆኔታ ፤የትምርት ደረጃ ፤የተጎጂውን አስተዋጾ፤ ወንጀሉን እንዲፈጽም ያስገደዱትን ምክንያቶች እና ሌሎች ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአምስት መቅላላ የቅጣት ማቅለያ ሁኔታዎች በመክፈል አስቀምጧ እነዚህም፡- ሀ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን እስካደረገበት ጊዜ ድረስ የዞትር ጠባዩ መልካም እንደ ሆነ እና ያጠፋውም በእውቀት ማነስ፤ ባለማወቅ ፤ በየዋህነት ወይም ባልታሰበ በድንገተኛ አጋጣሚ ሲሆን፡፡ ለ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው በተከበረ እና በግል ጥቅም ላይ ባልተመሰረተ ፍላጎት ሲሆን ውይም  ከፍ ባለ ሀይማኖታዊ፤ ሞራላዊ ወይም ማህበራዊ እምነት ተነሳስቶ እንደሆነ ሐ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን የፈጸመው ከፍተኛ ቁሳዊ እጦት ወይም የሂሊና ስቃይ ደርሶበት እንደሆነ  ከፍ ያለ አደጋ የሚያመጣ ነገር የተቃጣበት መስሎት እንደሆነ  መሰረት ያለው ፍረሃት አድሮበት እንደሆነ ወይም  ሊታዘዝለት በሚገባው ወይም በስልጣኑ ስር በሚያስተዳድረው ሰው ተጽኖ ምክንያት እንደሆ፡፡ መ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን የፈጸመው የተበደለው ሰው ጸባይ ከብርቱ ፈተና ላይ ጥሎት በከባድ ጸብ ቀስቃሽነት በአጸያፍ ስድብ ምክንያት ደም ከሚያ ፈላ ንዴት ፤ስቃይ ብስጭት ላይ ጥሎት እንደ ሆነ ወይም  ከፍ ያለ አስገዳጅነት ባለው ስሜትን በሚለውጥ ሁኔታ ወይም ምክንያት ባለው የመንፈስ ሁከት ላይ ሆኖ እንደ ሆነ ሠ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ካደረገ በኋላ የእውነት የተጸጸተ መሆኑ በተለይም በደል ላደረሰበት ሰው አስፈላጊውን እርዳታ ያደረገ እንደሆነ  ጥፋቱን በመገንዘብ ለፍትህ አካላት እርሱን የቀረበ እንደ ሆነ  የወንጀሉ ጥፋት ላደረሰው ጉዳት በተቻለው መጠን በመካስ መጸጸቱን በተግባር አሳይቶ እነደ ሆነ ወይም  ተከሶ ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ በክስ ማመልከቻ ላይ የተመለከተውን የወንጀል ዝርዝር በሙሉ ያመነ እንደ ሆነ በማቅለያነት ይያዝለታል በማለት የህጉ ድንጋጌ በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩት ሁኔታዎች  በህጉ ልዩ ክፍል ውስጥ በተለየ ድንጋጌ እነዚህ ሁኔታዎች ወይም ምክንያቶች በማቅለያነት በተመለከቱ ጊዜ ፍ/ቤቱ በድጋሜ እዚህን ምክንያቶች ቅጣቱን ለማቅለል በድጋሜ ሊጠቀምባቸው አይችልም፡፡ 2ኛ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ዝምድና እና የጠበቀ ወዳጅነት ይህ የቅጣት ማቅለያ በብዛት ጥፋተኛው በቀጥታ ወንጀል ላይ ሳይሳተፍ ነገር ግን ፤የቅርብ የስጋ ዘመዱን ወይም የቅርብ የጋብቻ ዘመዱን ወይም በተለየ ጥብቅ በሆነ ወዳጅነት የተሳሰረውን ሰውን ወንጀል ፈጽሞ እሱን ለቅጣት ፤ለውርደት ወይም ለከባድ አደጋ ላለማጋለጥ በማሰብ  ወንጀል መደረጉን እና ወንጀለኛውን እያወቀ ለፍርድ ባለስልጣን ያማስታወቅ ግዴታውን ያለፈጸመው እንደሆነ  መስጠት የሚገባውን እርዳታ ያልሰጠው እንደሆነ  ሀሰተኛ መግለጫ፤ ምስክርነት ወይም መረጃ የሰጠው እንደሆነ  ወንጀለኛው ከክስ ወይም ከቅጣት አፈጻጻም እንዲያመልጥ በመርዳት የወንጀል ህግን የሚቃረን ተግባር ያደረገ ሲሆን ነው፡፡ ፍርድ ቤቱም ዝምድና መኖሩን እና ምክንያቱ በቂ መሆኑን በማረጋጋጥ በመሰለው ቅጣቱን ያሚያቀል ሲሆን ዝምድናው ጥብቅ ሲሆን እና የተፈጸመው ወንጀልና የደረሰው ጉዳት አነስተኛ ሲሆን ወንጀለኛውን በማስጠንቀቂያ፤ በወቀሳ ወይም በነጻ ሊያልፈው እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን ጥፋተኛው የፈጸመው ወንጀል  በአገር ላይ በህግ መንግስቱ እና ህግ መንግስታዊ ስረዓቱ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች አለማሳወቅ ሲሆን  በመከላከያ ሰራዊት እና በወታደራዊ ግዴታዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን አለማሳወቅ ሲሆን እና  የመሸሸግ ወንጀል ሲሆኑ ዝምድና እና የጠበቀ ወዳጅነት መኖሩ እንደ ልዩ ቅጣት ማቅለያ ምክንያት እንደማይያዝለት በግልጽ ህጉ ደንግጎ ይገኛል፡፡ 3ኛ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች የወንጀል ህጉ አንቀጽ 84/1 ከ ሀ እስከ ሠ ባለው ስር የተለያዩ ሁኔታቶችን መነሻ በማድረግ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን በዝርዝር ያሚያስቀምጥ ሲሆን እነዚህም ሁኔታዎች የጥፋተኛውን ግላዊ ጸባይ፤ አመል፤ ሀላፊነት፤ ስልጣን፤ ወንጀል አፈጻጸም ሁኔታ፤ አደገኝነት እና የተጎጂውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአምስት መቅላላ የቅጣት ማክበጃ ሁኔታዎች በመክፈል የሚያስቀምጥ ሲሆን እነዚህም፡- ሀ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው -በከሐዲነት ወይም - በወስላተነት ፤ወራዳነት ወይም - መጥፎ አመልን በሚያሳይ ምቀኝነት ጥላቻ ስግብግብነት -መጥፎ ነገርን ለመስራት ወይም ስውን ለመጉዳት ፍጹም ፍቃደኛ በመሆን ፤ወይም -በተለየ ክፋት ወይም ጨካኝነት እንደ ሆነ ለ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው ስልጣኑን ተግባሩን ወይም የተጣለበትን እምነት ወይም ሀላፊነት ያለአግባብ በመገልገል እንደሆነ ሐ/ ወንጀለኛው በቀድሞ ጥፋተኝነቱ ፤ወንጀልን ማድረግ ሙያው ወይም ልምድ አድርጎ መያዙ፤ወይም  የወንጀሉ አፈጻጸም ዘዴ፤ጊዜ ፤ቦታና የአፈጻጸሙ አኳኋን፤በተለይም -በሌሊት ወይም በሽብር ወይም በሁከት ለአደጋ ሽፋን ወይም በጦር መሳሪያ ወይም በሌላ አደገኛ መሳሪያ ወንጀሉን በማድረግ የተለየ አደገኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ እንደ ሆነ መ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው ወንጀል ለመፈጸም በተደረገ ስምምነት መሰረት ሲሆን ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን ሲሆን  ወንጀል ለመፈጸም ከተቋቋመ ቡድን ጋር በመስማማት ወይም አባል በመሆን ይልቁንም እንደ ወንጀል ቡድን ሹም፤አደራጅ ወይም መሪ በመሆን እንደሆነ ሠ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው በዕድሜው፤ በጤንነቱ፤ በኑሮው ወይም በስራው ሁኔታ ልዩ ጥበቃ በሚያሻው ሰው ላይ በተለይም ለመከላከል አቅም በሌለው ፤መንፈሰ ደካማ ፤በሽተኛ ወይም የአካል ጉዳተኛ፤እስረኛ ሲሆን  በቅርብ ዘመዱ ላይ ወይም የበላዩ ወይም የበታቹ በሆነ ሰው ላይ ሲሆን
نمایش همه...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከባድ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጥቷል ድርጊቱ የተከሰተው በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ ውስጥ ሲሆን ተከሳሽ አቶ ከበበው ጣሰው በቡኢ ከተማ ልዩ ስሙ ቄራ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በቀን 28-08-2015 አ.ም ሟች አቶ ፈቀደ አታሎን ከኪሴ ገንዘብ አውጥተሀል በሚል ምክንያት በዱላ እና በመጥረቢያ ጭንቅላቱን ጨምሮ የተለያየ የሰውነት ክፍሉ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ አቃቢ ህግ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቶ ሲከራከር አቃቢ ህግ ምስክር አሰምቶ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱ ስለመፈፀሙ በማስረዳቱ ተከላከል ቢባልም የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ የመከላከል መብቱ ታልፎ በቀን 17-07-2016 በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ጥፋተኛ ብሎታል። በተከሳሽ በኩል አራት የቅጣት ማቅለያ ተይዞለት በ15 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል። የእለቱ የመምሪያው መልእክት፦ ተከሳሽ ጥቂት ሴኮንዶች መረጋጋት ባለመቻሉ የሰው ህይወት አጥፍቷል ፣ የራሱን ቀሪ ህይወትም በማረምያ እንዲያሳልፍ ሆኗል። መላው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ማህበረሰብ የወንጀልን አስከፊነት በመረዳት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችን ከስሜት በፀዳና ህግን ባከበረ መልኩ እንዲሆን ለማሳሰብ እንወዳለን። https://www.facebook.com/61552754727232/posts/pfbid02WMd7kTwGBmUjZUfGHeYUj1kWR5c2xokzv3APyaXiBMPMDUdUWRGaSxPmUuJQMbrjl/
نمایش همه...
New COM Regulations
نمایش همه...
የፌዴራል_ሰነዶች_ማረጋገጫና_ምዝገባ_አገልግሎት_543.pdf4.62 KB
544_የደን_ልማት_ጥበቃና_አጠቃቀም_የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት_ደንብ.pdf6.64 MB
542_ብሔራዊ_የእንስሳት_ጤና_ጥበቃ_ኢንስቲትዩት_ማቋቋሚያ_ደንብ_ማሻሻያ.pdf7.16 KB
ቀብድ እና ቅድመ ክፍያ ቀብድ (Earnest) ➡️ ቀብድ ማለት ውል ሲፈጸም የሚመለስ ወይም ከሽያጩ ገንዘብ (ከዋጋዉ) ላይ የሚታሰብ ገንዘብ ነው። ➡️ ተዋዋዮየች ቀብድ የተቀባበሉ እንደሆነ በመካከላቸው የሽያጭ ውል መኖሩን የሚያረጋግጥ ሲሆን ሻጭ ስምምነት ላይ በተደረሰዉ ዋጋ መሰረት ለመሸጥ ገዥም በዚያዉ ዋጋና የውል አፈጻጸም መሰረት ለመግዛት የጸና አቋም እንዳላው (ሁለቱም ወገኖቸ ቁርጠኛ መሆናቸዉን) የሚያረጋግጥ ነዉ፡፡  ቀብድ መሰጠቱ በማያከራክር ሁኔታ ውል መደረጉን እንደሚያረጋግጥ በፍትሀብሔር ሕጋችን በቁጥር 1883 ስር በግልጽ ተደንግጓል። ➡️ ቀብድ የመቀባበል ውጤት:- ውሉ የማይፈጸም ከሆነ የቀብዱን ገንዘብ የከፈለዉ ወገን የሰጠውን ገንዘብ ለሌላኛው ወገን በመተው ወይም በመልቀቅ ውሉን ለመሰረዝ መብት የሚያገኝበት ሲሆን ቀብድ ተቀባዩ የገንዘቡን እጥፍ በመክፈል ውሉን ለመሰረዝ መብት የሚያገኝበትን ውጤት የሚያስከትል ነዉ፡፡ ቅድመ ክፍያ ➡️ በፍትሀብሔር ሕጋችን ቅድመ ክፍያን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች የለም ማለት ባይቻልም ቅድመ ክፍያ በመክፈል የተፈጸመ ዉል በሚመለከት ልክ እንደ ቀብድ ራሱን የቻለ ክፍል ተሰጥቶት የቅድመ ክፍያ ምንነትና የሚያስከትለዉን ዉጤት የሚመለከት አንቀጽ በፍትሀብሔር ሕጋችን በግልጽ አልተደነገገም፡፡ ➡️ ቅድመ ክፍያ ማለት ውል ሲፈጸም ከሽያጩ ገንዘብ (ዋጋ) ላይ የሚታሰብ ከዋጋዉ ላይ በከፊል በቅድሚያ የተከፈለ ገንዘብ ነዉ፡፡ ➡️ ቅድመ ክፍያ ከቀብድ የሚለየው ከሽያጩ ዋጋ ላይ በከፊል ቅድመ ክፍያ በመክፈል የተደረገ ውል ገንዘብ ከፋዩ(ገዥ) በውሉ መሰረት ቀሪ ገንዘብ በመክፈል ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ውል በሚሰረዝበት ጊዜ ከዋጋው ላይ በቅድሚያ የተከፈለዉን ገንዘብ እንዲያስቀር ለሻጭ የፍትሀብሔር ሕጋችን መብት አይሰጠዉም። ➡️ በመሆኑም የተከፈለዉ ገንዘብ ቅድመ ከፍያ መሆኑ ከተረጋገጠ ውል ሲሰረዝ ገንዘብ ከፋዩ ገንዘቡን መልሶ የመዉሰድ መብት ያለዉ ሲሆን ገንዘብ ተቀባዩም የተቀበለዉን ገንዘብ የመመለስ ግዳታ ይኖርበታል፡፡
نمایش همه...
👍 1
" የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቃ አዋጅ " ምን ይዟል ? የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ናቸው ፡- 1. መስከረም አንድ ቀን የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል 2. የካቲት ሃያ ሶስት ቀን የአድዋ ድል በዓል 3. ሚያዚያ ሃያ ሶስት ቀን የዓለም የሠራተኞች (የላብአደሮች) ቀን 4. ሚያዚያ ሃያ ሰባት ቀን የአርበኞች (የድል) ቀን በዓል በተጠቀሱት ብሔራዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ይሆናሉ፡፡ የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ናቸው ፡- 1. የካቲት አስራ ሁለት ቀን የሰማዕታት ቀን 2. ሕዳር ሃያ ዘጠኝ ቀን የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊነት (የብሔር ብሔረሰቦች) ቀን በተጠቀሱት ብሔራዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ይሆናሉ፡፡ የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ኃይማኖታዊ በዓላት ናቸው ፡- 1. መስከረም አስራ ሰባት ቀን የመስቀል በዓል 2. በየአራት አመቱ የሚመጣው ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ ታህሳስ ሃያ ዘጠኝ ቀን የሚውለው የገና ወይም የልደት በዓል 3. ጥር አስራ አንድ ቀን የጥምቀት በዓል 4. የስቅለት በዓል 5. የትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል 6. የኢድ-አልአድሃ (አረፋ) በዓል 7. የመውሊድ በዓል 8. የኢድ አልፈጥር በዓል በተጠቀሱት ኃይማኖታዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ይሆናሉ። ይህ ገና ረቂቅ አዋጅ ሲሆን ገና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አልጸደቀም። ረቂቅ አዋጁ በም/ቤት ሲጸድቅና በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ነው የጸና የሚሆነው።
نمایش همه...
👍 1