cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የፍቅር 💖 ጎጆ

💖👱‍♀ፍቅረኛሽን ምን ማለት ትፈልጊያለሽ ጣፋጭ የሆኑ የፍቅር መልዕክቶች እኛ ጋር ይገኛሉ 👱‍♂ የ ፍቅር ኬሚስትሪ😍💔 ካየሁት 👀 አስገራሚ ከሰማሁት 👂👂 መሳጭ ☝ ካነበብኩት 📚📚 አስተማሪ ማንኛውንም Comment እና ጥያቄ ካለችሁ በዚህ አማካኝነት ይፃፉልን 👇👇 👇 @lastBOYYYY

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
324
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ልጅ እያለሁ "የሞተ ሰው ዕንባ ፣ዝናብ ነው”ተብዬ፣ ዝናብ መርገጥ አቆምኩ፤አልቅሰሻል ብዬ። ይኸው... (ክረሞቱን በሙሉ) ሊያካፋ ሲጀምር፣ ውስጡን ሲከፋፍት፣ ደመና እንደሽንቁር፣ ከፍቶሽ ይመስለኛል ፣ ሰማዩ ሲጠቁር ከፍቶሻል መሰለኝ! 🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘 🙏🙏🙏 ሼር ቻናላችንን ይቀላቀሉ ◦◦✧join 👇👇👇👇👇 .. @habtamu39 @habtamu39 @habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
አንቺ በመሆንሽ የሰው ዘር መገኛ የአጥንቱ ስባሪ የደሙ መፍለቂያ ኑሪልን ክበሪ የጀግኖቹ ምድር ቅድስት ኢትዮጵያ ክፉ አይንካሽ ንገሽ ውጪ ተመንደጊ ከከፍታ ማማ ደሙን ለገበረው ምልክቱ ሆነሽ ሰደቅ ቀለም አርማ ከቶ አናፍርም ባንቺ ዘላለም ብንኮራ ደም የፈሰሰበት ይመስክር ተራራ አንክድሽ አንጠላሽ ያ ሁሉ ደም ፈሶ ለክብርሽ ነውና ምኒሊክ የወጋ ፍም እሳቱን ጎርሶ እኔም የሱ ልጅ ነኝ የሀገር ዘበኛ የሀገር ጠበቃ ነፍጥ የመዘዝኩ ለት አንድ ብቻ ሆኜ ለሺ ምበቃ እኔም የሱ ደም ነኝ ለወገኔ ነዋሪ ብቻዬን ጀግኜ "ሺ"ዎችን አስፈሪ ደመ ቁጡ ነኝ የኮስትር አሽከር የእነ አብዲሳጋ የነኩኝ ጊዜ ባለመትረይዝ ግራ ማጋባ በጦር ስዋጋ ትጥቅ አስፈቺ ነኝ በቁጣ ብቻ በአጭር አለንጋ ያገር ጠባቂ የወገን ጋሻ የቁርጥ ቀን ልጅ የሀዘን መርሻ አዎ ክንዱዋ ነኝ ለቅድስቲቷ ግንባሬን ሰጪ ለነፃነቷ እንኳን ለአፍሪካ እና ለመላው የጥቁር ህዝብ ለሆነው ለአድዋ በአል አደረሳችሁ 🙏🙏🙏 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ◦◦✧join 👇👇👇👇👇 .. @habtamu39 @habtamu39 @habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
نمایش همه...
sticker.webp0.45 KB
ለካ ሀገር ማለት፣ ሜዳ ሸንተረሩ ወንዙ ሸለቆ ነው ፣ ከሰው ጋር ተዳምሮ ሀገርን ሚሰጠው፤ ለካ ሀገር ጥቅሙ፣ የማነንትን ጥግ ስሜትን ይለካል፣ ከዛም ቀስ እያለ፤ ሀገር ሲተነተን የሰው ልጅ ይሆናል። ተፃፈ፡ በማርያማዊት፣ ሀይለማርያም። @KAL1y 🙏🙏🙏 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ◦◦✧join 👇👇👇👇👇 .. @habtamu39 @habtamu39 @habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
نمایش همه...
የአድዋዋ ጀግና #ጣይቱ ለጣሊያናዊው መልእክተኛ እንዲህ ብለው ነበር የላኳቸው —————————////—————— "እኔ ሴት ነኝ ጦርነትን አልወድም:: ነገር ግን ሀገሬ እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ። ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ፡፡ እግሩን ለጠጠር፣ ደረቱን ለጦር አስጥቶ፣ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ፣ ለአፈሩ፤ ክብር ለብሶ፣ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ፡፡ ሂድ ! የኢትዮጵያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው። ሂድ! ባሻህ ጊዜ ተመለስ፤ ተሰናድተን እንጠብቅሀለን ። ያንተን ወንድነት፣ የጣይቱንም ሴትነት ያን ጊዜ እናየዋለን፡፡ ሂድ! መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ" እቴጌ ጣይቱ (ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ) ።።።።።።።።።።።።። ♪የቀፎ ንብ ሲቆጣ ስሜቱ ከፊት ሆና መራችው ንግስቱ ወይ አለና ስትጠራው ጣይቱ ወይ ሳልላት ብቀር ያኔ እኔን አልሆንም ነበር እኔ 💚💛❤️ሀበሻ ነን የእምየ ኢትዮጵያ ሙሽሮች💚💛❤️[ 🙏🙏🙏 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ◦◦✧join 👇👇👇👇👇 .. @habtamu39 @habtamu39 @habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
نمایش همه...
ሲበርደን ኡ ኡ ታ ሲሞቀን ኡ ኡ ታ ሲርበን ኡ ኡ ታ ስንጠግብ ኡ ኡ ታ ስንጠማ ጩኸት ስንጠጣ ጩኸት ስንፋቀር ጩኸት ስንጣላ ጩኸት በድለንም ለቅሶ ሲበድሉን ለቅሶ ግራ ግብት አለው እግዜሩ ጨርሶ 🙏🙏🙏 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ◦◦✧join 👇👇👇👇👇 .. @habtamu39 @habtamu39 @habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
نمایش همه...
.......? ♥️ ❤️እናቴ❤️ #ቢሆንልኝም ድካምሽን ብደክም ሸክምሽን ብሸከም ባዝልሽ በጀረባዬ ባቅፍሽ በጉያዬ ቢሆንልኝም........ ብሰጥሽ እድሜዬን ከኔ ላይ ቀንሼ አንቺ ጎልተሺልኝ ይዩኝ እኔ አንሼ ቢሆንልኝማ........... አንቺ እንዳረገዝሽኝ እኔም ባረገዝኩሽ በሆድ በጀርባዬ ሁለመናዬ ላይ አንቺን ባነገዝኩሽ ሁሌ እንድትፈኪልኝ ደስታ እኔ በሆንኩሽ ቢሆንልኝ እማ........ እንቅፋት እንዳይኖር በተደለደልኩኝ ምቹ መንገድ ሆኜ ብትረማመጂብኝ ህመምሽን ብወስድ ድካመሽን ብደክም አንቺ የቻልሽውን እኔ ግን ማልችለው መስሎ የታየሽን ስቃይሽን ሁሉ እኔ ላይ ብጥይው ቢሆንልኝ እማ...... የተመኘውት አንቺነትሽን ነው እናት ያሳኘሽ ልዩ ምስጥር ነው ቢሆንልኝ እማ...... መሆን ምፈልገው አንቺኑ ብቻ ነው። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 🙏🙏🙏 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ◦◦✧join 👇👇👇👇👇 .. @habtamu39 @habtamu39 @habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
نمایش همه...
.......♦️አሳና አሞራ♦️........ ከጊዜያት ብዛት ምንም ብንላመድ ከትውውቅ ጥልቀተ ወዳጅነታችን ምን እንኳ ቢገመድ በጠንካራ ገመድ መላመዱ አይሎ ቢሆንም መዋደድ በእኔና አንቺ መሀል ትልቅ ገደል አለ የሚያስቀር ከመንገድ ምክንያቱን በተረት ላስረዳሽ የኔ ውድ ከእለታት አንድ ቀን በሰማይ ሚኖረው በራሪው አሞራ ምግብ ለመፈለግ ሲወርድ ከተራራ ክንፉን እያማታ በተራ በተራ ድንገት ሳያስበው በፍቅር ተያዘ በውሃ ውስጥ ካለች ካንዷ አሳ ጋራ ከዚያም በየቀኑ አሳዋን ለማየት ቀዬውን ቀይሮ ወረደ ከመሬት አሳዋም በፍቅሩ ተልክፋ ኖራለች ድምፁን እንደሰማች ከባህር ወደ የብስ ቶሎ ትዘላለች ብሎም ከውሃ ውስጥ ለመውጣት ትሻለች ግና ምን ያረጋል ተፈጥሮ ሆነና ምንም ቢዋደዱ በመፋቀር ዳና አንድ ሆነው አይኖሩም አይቻልምና አሞራው ውሃ ውስጥ ለመግባት ቢሞክር አሳዋም መሬት ላይ ለመኖር ብትጥር ሁለቱም አንድ ላይ መሞታቸው አይቀር በዚህ የተነሳም አልሆንልህ ሲለው ማየት እንጂ መንካት እንደማይችል ሲያውቀው ፍቅሩን በልቡ አርጎ በረረ አሞራው ....... አሳዋም ሰረገች ከጥልቅ ከባህሩ እንደማይሆን ስታውቅ ከአሞራ ጋራ አንድ ላይ መኖሩ የእኔና ያንቺም ነገር እንዲሁ ነው በቃ በእጄ ሚያስገባሽ የለኝም ጠበቃ ኑሮሽ ከኑሮዬ ሀሳብሽ ካሳቤ ለየቅል ሆነና ልብሽና ልቤ እጅጉን አራቀሽ ከቅርብ ካጠገቤ የኔን አለም ጥዬ ወዳንቺ እንዳልመጣ ቀሊል እኮ አይደለም የኛማ ጋሬጣ እንግዲያው እኔማ አንቺን ባልጠላሽም ብዙ አትድከሚ እኔ አልሆንሽም ምንም ብንላመድ ብንቀራረብም አሳና አምራ ነን አንድ ላይ አኖርም !!! 🙏🙏🙏 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ◦◦✧join 👇👇👇👇👇 .. @habtamu39 @habtamu39 @habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
نمایش همه...
ፍርሃትና ናፍቆት "ሊመጣ ነው!" ሲሉኝ "የመቅሰፍት ጊዜ! የመከራ ዘመን!" "የት ደርሷል?" ስላቸው "ቀርቧል!" ብቻ እያሉኝ "መች ይመጣል?"ም ስል "ደርሷል!" ብቻ እያሉኝ ይኸው አርባ አመቴ፣ በፍርሃት አለሁኝ ወይ ዘመኑ መጥቶ ደቁሶ አልደቆሰኝ ፍርሃቱ፣ ፍርሃቱ፣ ፍርሃቱ ገደለኝ። "ሊመጣ ነው!" ሲሉኝ "የሰላም የደስታ-የጥጋብ ዘመን!" "የት ደርሷል?" ስላቸው "ተቃርቧል!" እያሉኝ "መች ይመጣል?"ም ስል "ተዳርሷል!" እያሉኝ ይኸው አርባ አመቴ፣ በናፍቆት አለሁኝ ወይ ዘመኑ መጥቶ በደስታ አላሻረኝ ናፍቆቱ፣ ናፍቆቱ፣ ናፍቆቱ ገደለኝ። 🙏🙏🙏 ቻናላችንን ይቀላቀሉ ◦◦✧join 👇👇👇👇👇 .. @habtamu39 @habtamu39 @habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
نمایش همه...
ለሁሉም ነገር ቃላት ሊኖረኝ አይችልም ግን እጠይቃለው ምላሹ ምንም ይሁን ምን ጥያቄዬን ይዤ መቀመጥ አልችልም ስሜቴን አልደበኩህም ምላሽህ ባያስደስተኝም ሁሉንም ነግሬሀለው ለምትለኝ ሁሉ እሺ ማለቴን እንደ አጉል የዋህነት እና ሞኝነት አትቁጠረው ሰው ነኝ እኮ እኔም እሰለቻለው ሁሉም ነገር ደግሞ በልክ ሲሆን ያምራል። የኔም እሺታ ቢሆን.....
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.