cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Book club

በዚህ ቻናል ላይ ቆየት ያሉ አዳዲስ በገበያ ላይ የሌሉ መጽሐፍት በ pdf የሚለቀቅ ይሆናል

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
4 507
مشترکین
+1224 ساعت
+637 روز
+54030 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

14/09/2016 የዕለቱ የወንጌል ክፍል ማቴዎስ 1:7-15 ሄዳችሁም፦ ‘መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች፡’ ብላችሁ ስበኩ። ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ። ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፥ ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና። “በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ። ወደ ቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ፤ ቤቱም የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይድረስለት፤ ባይገባው ግን ሰላማችሁ ይመለስላችሁ። ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። እውነት እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል..... የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ገላትያ 6:11-ፍጻሜ    እንዴት ባሉ ታላላቆች ፊደላት በእጄ እንደ ጻፍሁላችሁ እዩ። በሥጋ መልካም ሆነው ሊታዩ የሚወዱ ሁሉ እንድትገረዙ ግድ አሉአችሁ፥ ነገር ግን ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ብቻ ነው። በሥጋችሁ እንዲመኩ ልትገረዙ ይወዳሉ እንጂ የተገረዙቱ ራሳቸው እንኳ ሕግን አይጠብቁም። ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ። በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። በዚህም ሥርዓት በሚመላለሱ ሁሉ ላይ በእግዚአብሔር እስራኤልም ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን። እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ። ወንድሞች ሆይ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን። አሜን....                 1 ጴጥሮስ 4:12-17    ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ። ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ። ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤ ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር.....                     ሐዋ. ሥራ 4:31-ፍጻሜ        ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ። ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም። ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው። በመካከላቸው አንድ ስንኳ ችግረኛ አልነበረምና፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና፥ በሐዋርያትም እግር አጠገብ ያኖሩ ነበር፤ ማናቸውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር። ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ሌዋዊ ዮሴፍ የሚሉት ነበረ፥ እርሱም በሐዋርያት በርናባስ ተባለ ትርጓሜውም የመጽናናት ልጅ ነው፤ እርሻም ነበረውና ሽጦ ገንዘቡን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር አጠገብ አኖረው.... ምስባክ መዝሙር 115:6 ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር እግዚኦ አነ ገብርከ ገብርከ ወልደ ዓመትከ ትርጉም የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው አቤቱ እኔ ባሪያህ ነኝ ባሪያህ ነኝ የሴት ባሪያህም ልጅ ነኝ https://t.me/ethiobookclub2
نمایش همه...
3👍 2🤬 1
Repost from N/a
ሰው የሆነው ወልድ ብቻ ነው ማለትም አብ እና መንፈስ ቅዱስ ሰው አልሆኑም ማለት ነው እንጂ በማኀፀነ ድንግል ግን አላደሩም ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም በህልውና ሥላሴ የአንዱ አካል ባለበትና በደረሰበት ሁሉ የሁለቱም አካል አለና ወልድ በማኅፀን ሲያድር አካለ አብና አካለ መንፈስ ቅዱስም በማኅፀነ ድንግል አድረዋል፡፡ ወልድ በተለየ ግብሩ ተወላዲ ስለሆነ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደ ተወለደ በኋላ ዘመንም ከድንግል ማርያም ያለ አባት ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍስዋ ነፍስን ነሥቶ ሊወለድ በማኅፀንዋ ሲያድር፦ ድንግል ማርያም ምንም እንኳን ጽንዕት ብትሆንም እዚ ሐመልማል፣ እሱ መለኮታዊ እሳት ነውንዕኣ ዘ አብ ሊያጸናት በማኅፀንዋ ሲያድር፣ ምንም እንኳን ሊአብሔር ንጽሕት ድንግል ብትሆንም የበለጠ ጽድልት ብርህት ለማድረግ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በማኅፀንዋ አድሯል፡፡ ከ አብሲማዳኮስ መጽሐፍ የተቀነጨበ https://t.me/ethiobookclub2
نمایش همه...
Book Club2

በዚህ ቻናል ላይ ቆየት ያሉ አዳዲስ በገበያ ላይ የሌሉ መጽሐፍት በ pdf እና የየዕለቱ ግጻዌ የሚለቀቅ ይሆናል

👍 4
13/09/2016 የዕለቱ የወንጌል ክፍል ማቴዎስ 20:1-17 “መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና። ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው። በሦስት ሰዓትም ወጥቶ ሥራ የፈቱ ሌሎችን በአደባባይ ቆመው አየ፥ “እነዚያንም፦ ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ፡’ አላቸው። እነርሱም ሄዱ። ደግሞም በስድስትና በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ እንዲሁ አደረገ። “በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና፦ ‘ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ?’ አላቸው። ‘የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው፡’ አሉት። እርሱም፦ ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ፡’ አላቸው። “በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን፦ ‘ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፡’ አለው። በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። “ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። ተቀብለውም፦ ‘እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፥ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው፡’ ብለው በባለቤቱ ላይ አንጐራጐሩ። እርሱ ግን መልሶ ከእነርሱ ለአንዱ እንዲህ አለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ፥ አልበደልሁህም በአንድ ዲናር አልተስማማኸኝምን? ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን? ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይንህ ምቀኛ ናትን?’ “እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና”...... የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ኤፌሶን 6:1-10 ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና። መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት። እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው። ባሪያዎች ሆይ፥ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በልባችሁ ቅንነት በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ። ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምትገዙ በትጋትና በበጎ ፈቃድ ተገዙ፤ ባሪያ ቢሆን ወይም ጨዋ ሰው፥ እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት እንዲቀበለው ታውቃላችሁና። እናንተም ጌቶች ሆይ፥ ዛቻውን ትታችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፥ በእነርሱና በእናንተ ላይ የሚገዛው ጌታ በሰማይ እንዳለ ለሰው ፊትም እንዳያደላ ታውቃላችሁና.... 1 ጴጥሮስ 3:10-15 “ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤ የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።” በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብፁዓን ናችሁ፦ “ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥” ሐዋ. ሥራ 21:27-31 ሰባቱ ቀንም ይፈጸም ዘንድ ሲቀርብ ከእስያ የመጡ አይሁድ በመቅደስ አይተውት ሕዝብን ሁሉ አወኩና፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ እርዱን ሕዝብን ሕግንም ይህንም ስፍራ ሲቃወም ሰውን ሁሉ በየስፍራው የሚያስተምረው ሰው ይህ ነው፤ ጨምሮም የግሪክን ሰዎች ደግሞ ወደ መቅደስ አግብቶ ይህን የተቀደሰ ስፍራ አርክሶአል፥” ብለው እየጮኹ እጃቸውን ጫኑበት። በፊት የኤፌሶኑን ጥሮፊሞስን ከእርሱ ጋር በከተማ አይተውት ነበርና ጳውሎስም ወደ መቅደስ ያገባው መስሎአቸው ነው። ከተማውም ሁሉ ታወከ ሕዝቡም ሁሉ ተሰበሰቡ ጳውሎስንም ይዘው ከመቅደስ ውጭ ጎተቱት፥ ወዲያውም ደጆች ተዘጉ። ምስባክ መዝሙር 38:1 እቤ አአቅብ አፉየ ከመ ኢይስሐት በልሳንየ ወአንበርኩ አቃቤ ለአፉየ ሶበ ይትቃወሙኒ ኃጥአን ቅድሜየ                 ትርጉም በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ አልሁ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ https://t.me/ethiobookclub2
نمایش همه...
5👍 3
Repost from N/a
ሦስተኛው ኪዳን.pdf https://t.me/ethiobookclub2
نمایش همه...
🥰 1😡 1
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
የትንሣኤውና የዳግም ምጽአቱ ነገር አልገባ ብሎኝ ስኳትና ደሞዝ ጎሽም የተባለ ሰው ላይ ጣለኝና በመጽሐፉ ስለመሲሑ ስለትንሣኤ ስለኢትዮጵያ ትንሣኤ ስለዳግም ምጽአቱ አወጋኝ። አንዳንድ መጽሐፍ ለነፍስህ ሲስማሟት ይታወቅሀለው ለመብላት አይከብዱም... ጸሐፊው የአንድምታን ትርጓሜ ዳሶ ዳሶ የኢትዮጵያን ቅድስተ ቅዱሳን ያሳያል። ካገኘኸው አንብበው። ካጣኸው ዩትዩብ ላይ ደሞዝ ጎሽም ብለህ ፈለግ ፈለግ አድርገው ሐሳቡ ኮምኩም ይመስጥሀል። የአንድ ወንድማችን አስተያየት ነው
نمایش همه...
ርዕስ: የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች ደራሲ: ዶ/ር ዮናስ ላቀው አማኑኤል ሆስፒታል ብዙ የሚገመቱና የማይገመቱ ነገሮች ይከሰታሉ። https://t.me/ethiobookclub2
نمایش همه...
👍 1
Repost from N/a
ስለ የትኛው እናመስግን? በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር የሚወዳችሁ ወንድም እኅቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥንና ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡... እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደ እርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከኾነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡ ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊው ነገር ቢቀርም አይድልብንምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል?... አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡ (ማቴ.7፡11)፡፡ ለዚህም ነው ብፁዕ ጳውሎስ የማይረባውን ነገር ለምኖ እግዚአብሔር _ ጸሎቱን ያልሰማው! ለዚህም ነው የተወደደ : ሙሴ “ፊትህን አሳየኝ” ብሎ በለመነው ጊዜ ልመናውን ያልተቀበለው! ስለዚህ እኛም ጸሎታችን ባይሰ'ማ እንኳን እግዚአብሔርን እናመስግን እንጂ ተስፋ አንቁረጥ፡፡ ልል ዘሊል ኾነን ጸልየን ከኾነም ልል ዘሊልነታችንን አስወግደን እንጸልይ እንጂ ድኩማን አንኹን፡፡ እንደዚህ አድርገን ጸልየን ሳለ ጸሎታችን ባይሰ'ማ ግን አምላክ የሚያደርገው ኹሉ ለጥቅማችን ነውና በፍጹም አንዘን፡፡
نمایش همه...
11
Repost from N/a
ስለ የትኛው እናመስግን? በዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር የሚወዳችሁ ወንድም እኅቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥንና ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡... እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደ እርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከኾነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡ ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊው ነገር ቢቀርም አይድልብንምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል?... አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡ (ማቴ.7፡11)፡፡ ለዚህም ነው ብፁዕ ጳውሎስ የማይረባውን ነገር ለምኖ እግዚአብሔር _ ጸሎቱን ያልሰማው! ለዚህም ነው የተወደደ : ሙሴ “ፊትህን አሳየኝ” ብሎ በለመነው ጊዜ ልመናውን ያልተቀበለው! ስለዚህ እኛም ጸሎታችን ባይሰ'ማ እንኳን እግዚአብሔርን እናመስግን እንጂ ተስፋ አንቁረጥ፡፡ ልል ዘሊል ኾነን ጸልየን ከኾነም ልል ዘሊልነታችንን አስወግደን እንጸልይ እንጂ ድኩማን አንኹን፡፡ እንደዚህ አድርገን ጸልየን ሳለ ጸሎታችን ባይሰ'ማ ግን አምላክ የሚያደርገው ኹሉ ለጥቅማችን ነውና በፍጹም አንዘን፡፡
نمایش همه...
ግንቦት 12 በዚች ቀን የዓለም ሁሉ መምህር የሆነ የአበረ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አረፈ የአባታችን በረከት ይደርብን
نمایش همه...
9🥰 2🙏 1
ገዳም ሲኬድ ምን መደረግ አለበት? ከበረሃው ምስጢር መጽሐፍ የተቀነጨበ ወደ ገዳም ሲመጣ እርቃኑንና የሰውነት ክፍሉን የማያስቆጥር ልብስ እን አንዲህ ፀጉርን አንጨፍርሮ ሳይሆን ሴቷም በሻሽ ወንዱም በኮፍያ ፍያ ሸፍኖ የሚወራው መልካም መልካሙን፤ እየዘፈነ ሳይሆን እየዘመሩ ታድያ መዝሙሩ ውስጥ ዳንስ ያለበት ሳይሆን በእውነተኛ በተሰበረ ልብ የዛን ጻድቅ ወይ መልአክ ወይ የፈጣሪውንና የእመቤታችንን ቅድስናና ፍቅር እያሰቡ ከቻልን ከእንባ ንባ ጋር ካልሆነ ትህትና በተሞላ ልብ እየዘመሩ ነው፡፡ ልጆቼ ደግሞም በየገዳማቱ ሰው ሲሄድ አይተንና ደርሰን መጣን ለማለት ብቻ በቡድን `ን በመጓዝ አይደለም፤ በመጀመሪያ ሃይማኖትና ሃይማኖቱ የሚያዘውን ሥነ ሥርዐት መማር፣ መጠየቅ፣ ካለባበሳችን፣ ካነጋገራችን ጀምሮ እግዚአብሔር በኛ ደስ እንዲለው ትእዛዙን ማክበር ገዳምም ከደረስን በኋላ ከአባቶች ከእናቶች በረከት መቀበል የመጣንበት ነውና ማስቀደስ ትምህርቱን መስማት የገዳሙን ሕግ አክብሮ በሥርዐት ሆኖ የመጡበትን በዓል አክብሮ መመለስ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ሳያችሁ ወደ ገዳም የምትሄዱ ስላልመሰለኝ ነው የጠየኳችሁ ልጆቼ..... https://t.me/ethiobookclub2
نمایش همه...
4👍 2