cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ethio medstar/ኢትዮ ሜድስታር /ስለ ጤናዎ ይወቁ

በየጊዜው ስለጤናችን መረጃ የምናገኝበት ቻናል ነው! አባል እንሁን!❤️ ማሳሰቢያ- ይህ ስለጤናችን መረጃዎችን ለመስጠት እንጂ ህክምናን ለመተካት ታስቦ የተዘጋጀ አይደለም!! ይህ ቻናል ህክምናን ቶሎ ለማግኘት እንጂ ለመዘግየት ምክንያት መሆን የለበትም!! ሀሳብ፣ ጥያቄና አስታየት ካላችሁ 👉 @etBahH 👈 የዩትዩብ ቻናል👇👇 https://www.youtube.com/@ethiomedstar8690

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
797
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

♦️ ታይፎይድ/የአንጀት_ተስቦ ♦️ ክፍል_ሁለት 🥰 ውድ አባላት ባለፈው ሳምንት   💥 ስለ ታይፎይድ በሽታ ምንነት ፣   💥ከታይፈስ ጋ ስላላቸው ልዩነት፣   💥 ስለ መተላለፊያ መንገዶቹ  ማንሳታችን ይታወሳል ስለምርመራዎቹ ና ስለ ህክምናው የሚያትተው የመጨረሻ ክፍል እንሆ 🚩 የታይፎይድ_ምርመራዎች 🚩 👉 አንድ ሰው በትክክል በታይፎይ ተጠቅቷል የሚባለው ከደም፣ ከሰገራ፣ ከሽንት ፣ ከመቅኔ ፣ ከቆዳሽፍታ ላይ የሚወሰድ ናሙና ውስጥ ታይፎይድ የሚያመጣው ባክቴሪያ salmonella typhi ሲገኝ ነው። ይህም ናሙና ውስጥ ያለውን ባክቴሪያ ለመራባት ምቹ በሆነ ቦታ በማስቀመጥ የሚለይ ምርመራ ሲሆን culture (ካልቸር) ይባላል። ይህ መንገድ ውድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብዙ ቦታ የሚገኝ አይደለም። 👉 አሁን እኛ ሀገር በብዛት የምንጠቀመውና በብዙ ሀገራት ዘንድ ከቆመ ብዙ ጊዜ የሆነው የዋይዳል ( widal test) ነው። በዚህ ምርመራ ሰው በእርግጠኝነት ታይፎይድ አለበት ማለት አይቻልም!! ታይፎይድ ታሞ ነበር ወይ ደሞ አሞት ሊሆን ይችላል ማለት ግን ይቻላል። ምክንያቱም ይህ ምርመራ የሚያሳየው ለባክቴሪያው መልስ የሚሆን ፀረ ባክቴሪያ(antibody) ሰውነታችን እንዳመረተ ብቻ እንጂ ባክቴሪያው ይኑር አይኑር የሚናረው ነገር የለም። ስለዚህ ከዚህ በፊት ታይፎይድ ታሞ የነበረ ሰውና አሁን ፍፁም ጤነኛ የሆነ ሰው  ቢመረመር posetive ሊሆን ይችላል። ይህ ብቻም አይደለም አብዛኞቻችን ከአናኗር ባህላችን አንፃር ባንታመምም ለዚህ ባክቴሪያ ብዙ ጊዜ ተጋልጠናል ፤ ሰውነታችንም ፀረ-ባክቴሪያ ማምረቱ አይቀሬ ነው ስለዚህ ይህ ምርመራ አብዛኞቻችን ጋ ቢሰራ posetive ነው ማለት ነው። 👉 ከዋይዳል ምርመራ ይልቅ የፀረ ባክቴሪያ ምርመራ መጠን(antibody titer) ቢሰራ በሽታውን በመግለፅ ደረጃ የተሻለ ነው። እንደህመሙ ደረጃ ተጨማሪ ምርመራዎችም ሊያስፈልጉ ይችላሉ 🚩 ህክምናው 🚩 👉 ታይፎይ በጊዜና በአግባቡ ታከመ ሙሉ ለሙሉ የሚድን በሽታ ነው። አለመታከም ከሚያስከትላቸው የጤና ጠንቆች አልፎ ሕይወትን ሊቀጥፍ ይችላል። የሀኪም የታዘዘሎትን መድሀኒት በትክክል ይውሰዱ። 🚩 የታይፎይድ_መድሀኒት_መላመድ 🚩 👉 ይህ ባክቴሪያ ከዕለት ዕለት የታይፎይድ ፍቱን መድሀኒት የተባሉትን የመድሀኒት ዘሮች እየተላመደ በመምጣቱ ለህክምና አልበገርም እያለ ይገኛል። በዚህም የተነሳ ገዳይነቱ በእጥፍ እንዳይጨምር ደሀ ሀገራት ራስምታት ሆኗል። 🚩 ለመድሀኒት_መላመዱ_ምክንያት 🚩 💥 ባልተረጋገጠ ምርመራ ታይፎይድ እየተባለ በየቦታው መድሀኒቱ መሰጠቱ፤ 💥ሰዎች መድሀኒቶቹን ያለ መድሀኒት ማዘዣ ከየፋርማሲው እየሸመቷቸው ስለሆነ፤ 💥 ሰዎች ትንሽ ለውጥ ሲያዩ ተሽሎኛል ብለው መድሀኒቱን ጨርሰው አለመውሰዳቸው በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። 🚩 መከላከያ_መንገደች 🚩 ⚠️  ከሽንት ቤት መልስ እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ፤ ⚠️ ምግብ ከመመገባችን ከማብሰላችን በፊት በደንብ መታጠብ ⚠️ በተቻለ መጠን ከቤት ውጪ አለመመገብ ⚠️ እቤት ውስጥ የታመመ ሰው ምግብ እንዲያበስል አለማድረግ ⚠️ አትክልቶችን ቅጠላቅጠሎችን በደንብ አጥቦ መመገብ ⚠️በምንም ምክንያት ከሽንትቤት ጋ ግንኙነት ያላቸውን ውሀዎች ለመጥነት አለመጠቀም ⚠️ ውሀዎችን አፍልቶ/አክሞ መጠቀም ⚠️ ታፎይድ በሽታ በጣም የበዛበትና የተለመደበት ቦታ ሲጓዙ ፀረ ታይፎይድ ክትባት ይከተቡ(ክትባቶቹ መሉ ለሙሉ የመከላከል አቅም ባይኖራቸውም) ስለ ታይፈስ በሌላ ጊዜ እንመለሳለን 💥👉 ሁላችንም (የጤና ባለሙያዎች፣ ሰፊው ህዝብ፣ ፋርማሲ ቤቶች) ሀላፊነታችንን በመወጣት የታይፎይድን መድሀኒት መላመድ እንከላከል!! ሁላችንም ለታፎይድ በሽታ መድሀኒት መላመድ ተጠያቂዎች ነን!! ዋናው_ነገር_ጤና ሀሳብ አስታየት ካላችሁ ላኩልን! ኢትዮሜድስታር የናንተ ነው!!   ቴሌግራም ቻናል  👇 https://t.me/ethiomedstar facebook page https://www.facebook.com/profile.php?id=100086078512805 ቴሌግራም ግሩፕ 👇👇 https://t.me/+ifm_wiqB_6kzZTY0 youtube channel https://youtu.be/hLem0L0gOTY
نمایش همه...
Ethio medstar/ኢትዮ ሜድስታር /ስለ ጤናዎ ይወቁ

በየጊዜው ስለጤናችን መረጃ የምናገኝበት ቻናል ነው! አባል እንሁን!❤️ ማሳሰቢያ- ይህ ስለጤናችን መረጃዎችን ለመስጠት እንጂ ህክምናን ለመተካት ታስቦ የተዘጋጀ አይደለም!! ይህ ቻናል ህክምናን ቶሎ ለማግኘት እንጂ ለመዘግየት ምክንያት መሆን የለበትም!! ሀሳብ፣ ጥያቄና አስታየት ካላችሁ 👉 @etBahH 👈 የዩትዩብ ቻናል👇👇

https://www.youtube.com/@ethiomedstar8690

🔰 ስለ_ጡት_ካንሰር  🔰 እንድታውቁት... 💥 በአለም ደረጃ ሴቶች ላይ በብዛት ከሚከሰቱ ካንሰሮች  በገዳይነቱ የሚገዳደረው የለም። 💥 በየዓመቱ ግማሽ ሚሊየን የሚሆኑ ሴቶች በዚህ ካንሰር ይሞታሉ ይህ ማለት በአለም በየደቂቃው  የአንዲት ሴት ሕይወት በጡት ካንሰር ምክንያት ይነጠቃል ማለት ነው። 💥 በአሜሪካ በተደረገ ጥናት ከ 8 ሴት አንዷ በሕይወት ዘመኗ በዚህ ካንሰር መጠቃቷ አይቀርም። 💥 ጥቂት ቢሆንም ወንዶችም በጡት ካንሰር ሊጠቁ ይችላሉ።(1%) 💥 ቶሎ ብሎ የታወቀ/በጊዜ የተለየ/ የጡት ካንሰር ከ90 % በላይ ሙሉ ለሙሉ የመዳን እድል አለው። 💥 የጡት ካንሰር ምንም በአይን የሚታይ ምልክት ላያሳይ ይችላል። 💥 የብብት ፍርንትት ማበጥ/መጠን መጨመር፣  ጡት ላይ የሚከሰት እብጠት፣ የጡት ቆዳ /የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መሰርጎድ፣ የጡት ቆዳ መቀየር(መቅላት ፣ መቁሰል፣ የብርቱካን ልጣጭ መምሰል/ጠቃ-ጠቆ ያለው ቆዳ/ )፣የጡት ህመም፣ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ፣ ከምታጠባና ከወላድ ሴት ውጪ ያለ ማንኛውም የጡት ፈሳሽ ፣ የሁለቱ ጡቶች በቅረፅ/ በመጠን አለመመሳሰል ዋና ዋና የጡት ካንሰር ምልክቶች ናቸው። 💥 አብዛኛው የጡት ካንሰር ከ 40 ዓመት እድሜ በላይ የሚታይ ሲሆን በቤተሰብ የመጣ ከሆነ ግን ከዚያ ቀድሞ ሊከሰት ይችላል።   💥 ከአልኮልና ከሲጋራ መቆጠብ ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፣ ከልክ በላይ ውፍረት ካለ መቀነስ፣ የሆርሞን መተኪያ ህክምናዎችን/hormone replacemet therapy/ አለመጠቀም፣ መውለድ፣ የወሊድ ቁጥርን መጨመር ተጋላጭነትታችንን የሚቀንሱ መንገዶች ናቸው። 💥 የራስ ለራስ ምርመራ/self examination/  እና ማሞግራፊ /mamography/ ለቅድመ ካንሰር ምርመራ/screening/የሚያገለግሉ ሲሆን የናሙና ምርመራ/FNAC/፣ MRI ፣ አልትራሳውንድና ሌሎች ምርመራዎች ካንሰሩን ለማረጋገጥና ደረጃውን ለማወቅ ያገለግላሉ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የአደራ መልዕክት 📌 ውድ እህቶቻችን/እናቶቻችን ቢያንስ በወር አንዴ ጡታችሁን በራሳችሁ መርምሩ፣ አስተውሉ፣ ፈትሹ  -ይህ የጡት ካንሰር ምልክቶችን በጊዜ ለማግኘት/ለማወቅ ከፍተኛ እስተዋፅኦ አለው። 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆                                          ምንጭ- WHO                                                     -myoclinic.org 💥 ዋናው ነገር ጤና 💥 🥰ይጠቅማል ብለን ካሰባብን ለወዳጆቻችን እናጋራ! 🥰ይህን በማድረጋችን ቢያንስ የአንድ ሴትን በጡት ካንሰር ምክንያት የመሞት ዕድል እናስቀር ይሆናል።                                          🥰ቤተሰብ ይሁኑ🥰 ጥያቄ ሀሳብ አስታየት ካለ ይላኩልን። ቴሌግራም ቻናል👇 https://t.me/ethiomedstar የቴሌግራም ግሩፕ 👇 https://t.me/+ifm_wiqB_6kzZTY0 facebook-👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100086078512805 Youtube channel- 👇 https://youtube.com/@ethiomedstar8690
نمایش همه...
Ethio medstar/ኢትዮ ሜድስታር /ስለ ጤናዎ ይወቁ

በየጊዜው ስለጤናችን መረጃ የምናገኝበት ቻናል ነው! አባል እንሁን!❤️ ማሳሰቢያ- ይህ ስለጤናችን መረጃዎችን ለመስጠት እንጂ ህክምናን ለመተካት ታስቦ የተዘጋጀ አይደለም!! ይህ ቻናል ህክምናን ቶሎ ለማግኘት እንጂ ለመዘግየት ምክንያት መሆን የለበትም!! ሀሳብ፣ ጥያቄና አስታየት ካላችሁ 👉 @etBahH 👈 የዩትዩብ ቻናል👇👇

https://www.youtube.com/@ethiomedstar8690

🌟 የቆዳ_እንክብካቤ 🌟 👉 የቆዳ አይነታችንን ማወቅ ቆዳችንን ለመጠበቅ ጉልህ ሚና አለው። ለቆዳችን የምንሰጠው እንክብካቤ እንደየቆዳችን አይነት የተለያየ በመሆኑ ሁላችንም የራሳችንን የቆዳ አይነት መለየት ይኖርብናል። 👉 በዚህ ቪዲዮ ለሁሉም የቆዳ አይነት አስፈላጊና ተስማሚ የሆኑ ጤናማ ልማዶችን አጋራችኋለሁ። 👉 እነዚህን ጠቃሚ ልምዶች በመተግበር ቆዳችንን ከመላላጥ፣ በብጉር ከመጠቃት፣ ከመሸብሸብ ና ከመቁሰል እንከላከል ! የሚከተለውን ሊንክ ተጭናችሁ ተመልከቱ👇👇 👉👉 https://youtu.be/VYvYytS6-JI?si=QXen-9P3p3PCXH81 👈👈👈👈 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ስለ ጤና ነክ ጉዳዎች ያሻችሁን የምትጠይቁበትና የጤና መረጃ የምታገኙበት👇 ♨️ኢትዮሜድስታር የናንተ ነው🙏♨️ የዩትዩብ ቻናል👇👇 https://www.youtube.com/@ethiomedstar8690 👇👇👇👇👇👇👇👇 ቴሌግራም ቻናል https://t.me/ethiomedstar 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/+ifm_wiqB_6kzZTY0 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@michael.habtee?_t=8egaPijGUhJ&_r=1 የፌስቡክ ገፅ👇👇👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100086078512805
نمایش همه...
ማወቅ ያለብን የቆዳ እንክብካቤ ጠቃሚ ልምዶች/ tips on skin care

#የቆዳ አይነታችንን ማወቅ ቆዳችንን ለመጠበቅ ጉልህ ሚና አለው። ለቆዳችን የምንሰጠው እንክብካቤ እንደየቆዳችን አይነት የተለያየ በመሆኑ ሁላችንም የራሳችንን የቆዳ አይነት መለየት ይኖርብናል። 👉 በዚህ ቪዲዮ ለሁሉም የቆዳ አይነት አስፈላጊና ተስማሚ  የሆኑ ጤናማ ልማዶችን እጋራችኋለሁ። 👉 እነዚህን ጠቃሚ ልምዶች በመተግበር ቆዳችንን ከመላላጥ፣ በብጉር ከመጠቃት፣ ከመሸብሸብ ና ከመቁሰል እንከላከል ! #ሰን ስክሪን #ሰን ብሎክ #ሜካፕ #የራስምታት #የብጉር መፍትሔ #ለቆዳ ህክምና #የቆዳ መሸብሸብ #sunscreen #sunblock #ethiopia #ethiopianmusic #ethiopianyoutubers #ጤናችን #about_health #ethiopiantiktok #ዶንኪቲውብ #yebetesebchewata #ጤና ሚኒስትር #የጤና ቻናል

♨️የራስ_ምታት ♨️ 👉 ኢትዮሜድስታር በዚህ ሳምንት የአብዛኛው ሰው ችግር ስለ ሆነው የራስ ምታት በአጭሩ ይዳስሳል። 👉 ራስምታት በጣም የተለመደና የአብዛኛው ሰው ችግር ሲሆን ማንኛውም ሰው በህይወት ዘመኑ  ቢያንስ አንዴ ከራስምታት እንደማያመልጥ ጥናቶች ያመለክታሉ።        🚩ስለ ራስምታት አይነቶች        🚩 ስለ መንስኤዎቹ        🚩ስለ ህክምናው እና       🚩ስለ አደገኛ የራስ ምታት ምልክቶች የሚከተለውን ሊንክ ተጭናችሁ ተመልከቱ 👇👇👇👇    https://youtu.be/RYPen0n6mPw?si=BTDROM2Z6_rt-9oN  
نمایش همه...

Photo unavailableShow in Telegram
ውድ የኢትዮሜድስታር አባላት እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን🙏 ❤መልካም በዓል !❤ ወዳጆቻችንን ወደዚህ ህብረት በመጋበዝ ጤናቸውን እንዲጠብቁ ስለጤናቸው እንዲያውቁ እናድርግ 🙏🙏 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ስለ ጤና ነክ ጉዳዎች ያሻችሁን የምትጠይቁበትና የጤና መረጃ የሚያገኙበት👇           ♨️ኢትዮሜድስታር የናንተ ነው🙏♨️ የዩትዩብ ቻናል👇👇 https://www.youtube.com/@ethiomedstar8690 👇👇👇👇👇👇👇👇 ቴሌግራም ቻናል https://t.me/ethiomedstar 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/+ifm_wiqB_6kzZTY0 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@michael.habtee?_t=8egaPijGUhJ&_r=1 የፌስቡክ ገፅ👇👇👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100086078512805
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ውድ የኢትዮሜድስታር አባላት እንኳን ለ መውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🙏 ❤መልካም በዓል !❤ ወዳጆቻችንን ወደዚህ ህብረት በመጋበዝ ጤናቸውን እንዲጠብቁ ስለጤናቸው እንዲያውቁ እናድርግ 🙏🙏
نمایش همه...
♨️ የወንዶች_የወሲብ_ያለማድረግ_ችግሮች ♨️ 👉 የግብረ ስጋ ግንኙነት በሰዉነታችን ዉስጥ አራት ዋና የስርአት  ቅንብር ዉጤት ነዉ። የደም ስር  ፣ የነርቭ  ስርአት፣ የሆርሞኖችና የአእምሮ ዉህድ ዉጤት ነዉ። ከነዚህ የአንዱ ወይም ከአንድ በላይ ችግሮች  የተለያዬ የወሲብ ችግሮችን ያመጣሉ። 👉 የብልት መቆምና እንደቆመ ለግንኙነት ለሚያስፈልግበት ጌዜ መቆየት በዋናነት ወደብልት በሚሄድ የደም ስር በደም መወጠር የሚከሰት ሲሆን የነርቭ መልእክቶችና የሆርሞኖች መልእክቶች በየአእምሮ መልእክቱን የመተንተን ዉጤት ይወሰናል። ስለሆነም የግብረስጋ ግኑኙነት በዋናነት የሚደረገዉና የሚቆጣጠረዉ በእምሮችን ክፍል ነዉ ። 👉 በወንዶች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የወሲብ ችግሮች ሶስት አይነት ናቸዉ። 1-የብልት የግብረስጋ ግንኙነት በሚፈለገዉ ግዜ ያለመቆም (erectile dysfunction) በወነዶች ላይ ከሚከሰቱ ችግሮች ዋንኛዉ ሲሆን እድሚያቸው ከ20-75 አመት በሆኑት ላይ ከ6ሰዎች በአንዱ ላይ ይከሰታል(16%) ችግሮቹ የሚከሰቱበት ምክንያቶ፦ ዉፍረት ፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የልብ የደም ስር ችግሮች ፣ የተወሰኑ መድሀኒቶች (ለድባቴ የሚወሰዱ: ለደም ግፊት የፈንገስ መድሀኒቶች) የስነአእምሮ ሁኔታ ፦የድባቴ ፣ የዉጥረት፣ የፍራቻ ችግሮች የነርቩ ችግሮች፦ ስትሮክ ፣የጀርባ ጉዳቶች ፣ የህብለሰረሰር  ችግሮች የሆርሞን መዛባት ፦የስኳር በሽታ ፣ የወንድ ሆርሞን (ቴስቴስትሮን) እጥረት 2- የፍላጎት መቀነስ ወይ አለመኖር (diminished libido) በተለይ እድሜ እየጨመረ በሚመጣበት ወቅት የመከሰት ሁኔታ ይጨምራል። 3-የመርጨት ችግሮች (በፍጥነት መርጨት: በመዘግየት ወይ ያለመርጨት ችግሮች ሊሆኑ ይችላሉ) - abnormal ejaculation በፍጥነት መርጨት (premature ejaculation ) ከሶስት ወንዶች በአንዱ ላይ ሊከሰት ይችላል። በሴቷ ብልት ዉስጥ በተለይ ከ60ሰከንድ በታች ከተረጨ ችግር እንዳለ ያመለክታል። 👉 ይህ ችግር በወንዶች ላይ ከፍተኛ ዉጥረትና የተስፋ መቁረጥ ችግሮች በማምጣት ወንዶችን ከግብረስጋ ግንኙነት መራቅን ብሎም ከትዳር መፋታትን ያስከትላል። 👉 የችግሮችን መንስኤ በማወቅ በህክምና ባለሙያዎች ሊረዱ ስለሚችሉ ያማክሩ ። ዶ/ር ዘለቀ ከበደ ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ና የህብረተሠብ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ (MD, MPH, gyn-obs specialist) © via Hakim page
نمایش همه...
♨️ *ጥያቄዎቻችሁ ♨️ 👉 በዚህ ሳሞንት ኢትዮሜድስታር የናንተ የ ተከታታዎቹን ጥያቄዎች  መልስና ማብራሪያዎች በአጭሩ ይዞ ቀርቧል። 🚩ስለ ጨጓራ ህመም 🚩 ስለ ደም ማነስና ስለ ደም ግፊት የተነሱ ጥያቄዎች  መልስና ማብራሪያ ሊንኩን ተጭናችሁ ተመልከቱ 👇 https://youtu.be/-pcbKp5VBrs
نمایش همه...
ስለ ጨጓራህመምና ና ስለ ደም ግፊት የተነሱ ጥያቄዎች / questions on Gastritis and Hypertension /

👉 በዚህ ሳሞንት ኢትዮሜድስታር የናንተ የ ተከታታዎቹን ጥያቄዎች  መልስና ማብራሪያዎች በአጭሩ ይዞ ቀርቧል። - ስለ ጨጓራ ህመም - ስለ ደም ማነስና ስለ ደም ግፊት የተነሱ ጥያቄዎች  መልስና ማብራሪያ #የጨጓራ_ህመም #የደም_ግፊት #የደም_ማነስ #ጤናችን #ቀይ_የደም_ህዋስ #ማቅለሽለሽ #ማስመለስ #ጤና_ነክ #tena #health #gastritis #anemia #hypertension #Ethiopia

♨️ *ጥያቄዎቻችሁ ♨️ 👉 በዚህ ሳሞንት ኢትዮሜድስታር የናንተ የ ተከታታዎቹን ጥያቄዎች  መልስና ማብራሪያዎች በአጭሩ ይዞ ቀርቧል። 🚩ስለ ጨጓራ ህመም 🚩 ስለ ደም ማነስና ስለ ደም ግፊት የተነሱ ጥያቄዎች  መልስና ማብራሪያ ሊንኩን ተጭናችሁ ተመልከቱ 👇 https://youtu.be/-pcbKp5VBrs   ውድ አባላት ጥያቄዎችን ቀተቻለ ፍጥነት በግልም ሆነ  በ ኢትዮሜድስታር የቴሌግራም ግሩፕ ወዲያው የሚመለሱ ሲሆን  ለሌሎች ይጠቅማሉ ብለን ያሰብናቸውን ጥያቄዎች በድጋሜ እዚህ እናቀርባለን። -በቅድሚያ ለዚህ ቻናል አዲስ የሆናችቸቹ    ተጋብዛችሀል    -like , share invite  በማድረግ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ድምፅ ትሆኑ ዘንድ የሁልጊዜ ጥርያችን ነው አብራችሁን ቆዩ የመጀመሪያው ጥያቄ - እናቴ በተደጋጋሚ ጨጓራ ያማታል /ብዙ ጊዜ ታክማለች አንዳንዴ ግን ይነሳባታል - አሁን ደሞ የበላችው ነገር ሁሉ ያስመልሳታል መፍትሔ ጥያቄውን ቀጥታ ከማነታችን በፊት  ስለጨጓራ ህመም ትንሽ ነገር ልጠቁማችሁ የጨጓራ ህመም በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ሲሆን በታዳጊ ሀገራት ላይ H.pylori የሚባል ባክቴሪያ ዋነኛውን ምክንያት ይይዛል። - የጨጓራ ህመም  የተለያዩ መገለጫዎች አሉት -የደረት ላይ ማቃጠል፣ መለብለብ - የመፋቅ ስሜት - ማቅለሽለሽ - የምግብ አለመፈጨት ስሜት - በተደጋጋሚ ማጋሳት / ሆድ መንፋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው - በጨጓራ ባክቴሪያ ምክንያት የመጣ የጨጓራ ህመም ባክቴሪያው ከሰውነት ላይ እስካልተወገደ ድረስ በተደጋጋሚ እየተነሳ ጤናን ማወኩ የማይቀር ነው። - ስለዚህ ማንኛውም የጨጓራ ህመም ያለበት ሰው በዘፈቀደ anti- አሲድና የህመም ማስታገሻ  ከመውሰዱ በፊት የዚህን ባክቴሪያ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል ምክንያቱም በተለምዶ ለ ጨጓራ ህመም የሚሰጡት መድሀኒቶች ጊዚያዊ መፍትሔ እንጂ ባክቴሪያውን በማጥፋት ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጡ አይደሉም። ስለዚህ ውድ ጠያቂያች  ታማሚዋ  ከዚ በፊት የጨጓራ ባክቴሪያ ምርመራ አድርገው የማያቁ ከሆነ ምርመራ አድርገው ባክቴሪያው በሰውነት ውስጥ ከተገኘ ባክቴሪያውን ለማጥፋት ለ2 ሳምንታት የሚሰጠውን መድሀኒት እንዲወስዱ እንመክራለን። -ይህም Eradication therapy ይባላል    ሌላው  ማቅለሽለሽና አንዳንዴም ማስመለስ የጨጓራ ህመም መገለጫዎች ቢሆንም በተደጋጋሚ የሚከሰት ማስመለስ ግን ከጨጓራ ህመሙ ጋ ተያይዞ የሚከሰት የበሽታ መወሳሰብ/complication እንዳይሆን ማስተዋል ያስፈልጋል።     በጨጓራ ህመም መወሳሰብ ችግሮች መካከል አንዱ  Gastric outlet obstruction /GOO በመባል ይታወቃል  ያልታከመና ስር የሰደደ የጨጓራ ህመም Pylorus የሚባል የጨጓራ ክፍል ላይ በሚፈጠር ብግነት ምክንያት የሚከሰት የጨጓራ ክፍል መጥበብ ሲሆን በዚህ የተጠቁ ታማሚዎች የበሉት ነገር ሁሉ ተመልሶ ይመጣል ፣ ምንም ምግብ አይስማማቸውም በአጭር ጊዜ ብዙ  ክብደት ይቀንሳሉ - ይህ ችግር የሚታወቀው ከላይ በተጠቀሱት ምልክቶችና  ኢንዶስኮፒ በሚባል ምርመራ ሲሆን እናታችንም ይህንን እንዲያደርጉ እንመክራለን። - ኢንዶስኮፒ ማለት ጥቃቅን ካሜራዎችን በመጠቀም የውስጠኛውን የጨጓራ ክፍል የሚያሳይ መሳሪያ ነው። በአጠቃላይ የሚከተሉት   ምልክቶችን ያስተዋሉ የጨጓራ ታማሚዎች በ ኢንዶስኮፒ መታየት ያስፈልጋቸዋል - መክሳት/ብዙ ክብደት መቀነስ -   ደም የቀላቀለ  ትውከት - የማያቋርጥ ትውከት - የሰገራ መጥቆር  ምክንያቱ የማይታወቅ ደም ማነስ ካለ - ከ50 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች - በተደጋጋሚ ታክመው ያልተሻላቸው  ምርመራውን ቢያደርጉ ብዙ ይጠቀማሉ። # ስለዚህ የመጀመሪያው ጥያቄ መፍትሔ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ የጨጓራ ባክቴሪያ ምርሠራ ማድረግና ኢንዶስኮፒ መነሳት - ቀጣይ ህክምናዎቹ በ ምርመራዎቹ ውጤት የሚቀጥል ይሆናል።    በዚ አጋጣሚ በሌላ ጊዜ ስለጨጓራ ህመም በሰፊው እንደምንመለስ ለመግለፅ እንወዳለን ሰላም እንዴት ናችሁ አባቴ የደም ግፊት እንዳለበት ነበር የምናቀው አሁን ደሞ የደም ማነስ አለበት አሉን ? የደም ግፊቱ ጠፍቶ ነው? 💥 ጥያቄዎቻችሁ 💥 ጥያቄ 👉 አባቴ የደም ግፊት እንዳለበት ነበር የምናቀው አሁን ደሞ የደም ማነስ አለበት አሉን ? የደም ግፊቱ ጠፍቶ ነው? መልስ 👉 ውድ አባላችን ሁለቱ ነገሮች የተለያዩ የጤና ችግሮች ናቸው። አንድ ሰው ሁለቱንም በአንዴ ሊኖረው ይችላል! 👉 የደም ማነስ  🔥 ማለት በተለያየ ምክንያት  በሰውነታችን ውስጥ ያለው የቀይ የደም ህዋስ(red blood cell) መጠን ሲያንስ የሚፈጠር ችግር ነው። የሰውነታችን አካላት ስራቸውን በትክክል እንዲሰሩ oxygen በበቂ ሁኔታ ማግኘት ይኖርባቸዋል። ቀይ የደም ሴል ደሞ እክስጅንን በመሸከም ለተለያዩ አካሎቻችን የሚያደርስ የደም ህዋስ ነው። -  ደም የሚለው ስያሜ  በዋነኝነት 4 ገሮችን ይይዛል plasma , ቀይ የደምሴል  ነጭ የደም ሴል ፕሌትሌት - በመሆኑም የደም ማነስ የሚለው ቃል የቀይ ደም ህዋሳትን መቀነስ ለመግለፅ የሚያለግል ሲሆን የደም ማነስ የሚለው ቃል ያላግባብ ስያሜ /misnomer/ ሆና እናገኘዋለን ከዛ ይልቅ የቀይ የደም ህዋስ ማነስ ቢባል የችግሩ ገላጭ ይሆናል        💥የቀይ ደም ሴል ልኬት መጠን/Hematorcrit      _ለሴት ከ 36%      _ ለወንድ  ከ 41% በታች ከሆነ የደም ማነስ አለባቸው ይባላል። 👉 የደም ግፊት ግን 🔥 በልብ ምት ግዜ ሰውነታችችን ውስጥ ባለ ደም እና በልብ የመርጨት ጉልበት ምክንያት  የደም ባንቧዎች ላይ የሚፈጠር ጫና ነው። 👉ይህ ግፊት        ደም፣ የደም ቧንቧ እና ልብ እስካለ ድረስ የሚኖር ነገር ነው።(ቦይ ላይ የሚሄድ ውሀ ትቦው ላይ ይነስም ይብዛም ጫና ማሳደሩ እንደማይቀር ሁሉ የደም ግፊት ደም የደም ቧንቧና ልብ እስካሉ ድረስ ሁሉም ሰው ላይ  የሚኖር ነገር ነው) ⚠️  ነገር ግን ይህ የደም ግፊት በአማካይ ከ 120/80 mm Hg  በላይ ሲሆን የተለያዩ የሰውነት አካላት ላይ በሚያስከትለው ቅፅበታዊም ሆነ የረጅም ጊዜ  የጤና እክል ምክንያት የደም ግፊት በሽታ ይባላል። ስለዚህ የደም ግፊት የነበረበት ሰው የደም ማነስ( ቀይ የደም ሴል ማነስ)  አለበት ማለት..... ደም ግፊቱ ጠፍቷል የሚል ትርጉም የለውም ሁለቱም በጣም የተለያዩና የተራራቁ  በሽታዎች ናቸው። ስለ ጥያቄው እናመሰግናለን!! 🖍 ሀሳብ 🖍ጥያቄ 🖍አስታየት ካላችሁ ...በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ገፆች ላኩልን ይህ ኢትዮሜድስታር ነው!! የናንተ ገፅ! ኢትዮሜድስታር_የናንተ_ነው! 👉 ቤተሰባችንን ና ጓደኞቻችንን ወደዚ ገፅ በመጋበዝ የማህበረሰብ ጤና አጠባበቅ ሀላፊነታችንን እንወጣ! 👇👇👇👇👇👇👇👇 ቴሌግራም ቻናል https://t.me/ethiomedstar 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/+ifm_wiqB_6kzZTY0 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@michael.habtee?_t=8egaPijGUhJ&_r=1
نمایش همه...
ስለ ጨጓራህመምና ና ስለ ደም ግፊት የተነሱ ጥያቄዎች / questions on Gastritis and Hypertension /

👉 በዚህ ሳሞንት ኢትዮሜድስታር የናንተ የ ተከታታዎቹን ጥያቄዎች  መልስና ማብራሪያዎች በአጭሩ ይዞ ቀርቧል። - ስለ ጨጓራ ህመም - ስለ ደም ማነስና ስለ ደም ግፊት የተነሱ ጥያቄዎች  መልስና ማብራሪያ #የጨጓራ_ህመም #የደም_ግፊት #የደም_ማነስ #ጤናችን #ቀይ_የደም_ህዋስ #ማቅለሽለሽ #ማስመለስ #ጤና_ነክ #tena #health #gastritis #anemia #hypertension #Ethiopia

የጡንቻ መሸማቀቅ ➖〰️▪️🔸▪️〰️➖ የጡንቻ መሸማቀቅ በድንገት ሊከሰት የሚችል ነው። በብዛት እግር እና እጃችን ላይ ሚከሰት ሲሆን አልፎ አልፎም በሆዳችን አካባቢ ሊከሰት ይችላል። በርካታ ጊዜም ከእርግዝና፣ ከሰውነት ድርቀት እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ በሚያጋጥመን ጊዜ የህመም ስሜቱ በደቂቃዎች ውስጥ የሚለቅ ሲሆን ከሰዓታት በላይ እኛ ላይ ከቆየ ግን ችግሩ ከዛም በላይ ሊሆን ይችላል። ✅ የጡንቻ መሸማቀቅ እንዴት ይከሰታል? ➖〰️➖〰️➖〰️♾️➖〰️➖〰️➖〰️ ▪️በተመሳሳይ አቅጣጫ ለረጅም ሰዓት በመቀመጥ ለምሳሌ ለረጅም ሰዓት እግራችንን አጣምረን መቀመጥ። ▪️ከልክ ያለፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራት። ▪️በሰውነታችን ውስጥ ያለው የጨው እና የውሃ መጠን ማነስ። ▪️በተገቢው ሰውነታችንን ሳናሟሙቅ ስፖርት መስራት ይከሰታል። ✅ ለችግሩ ተጋላጭ እነማን ናቸው? ➖〰️➖〰️➖♾️➖〰️➖〰️➖ 🔸 በሞቃታማ አካባቢዎች የሚሰሩ የኮንስትራክሽንና የፋብሪካ ሠራተኞች 🔸 የደም ቧንቧዎች ላይ ችግር ካለ 🔸 በልብ ድካም፣ በደም ግፊት፣ በከፍተኛ ኮሌስትሮል እና በስኳር በሽታ ተጠቂ መሆን 🔸 ሥር የሰደደ የነርቭ ችግር ያለባቸው ታካሚዎች ለጡንቻ መኮማተር ተጋላጮች ናቸው፡፡ ✅ የጡንቻ መሸማቀቅ በሚያጋጥመን ጊዜ ምን ማድረግ አለብን? ➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️♾️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️ የጡንቻ መሸማቀቅ በሚያጋጥመን ጊዜ ሚፈጠርብንን ህመም ስሜት ለማስታገስ የተለያዩ ዘዴዎች እንዳሉ ይነገራሉ። ከእነዚህም ውስጥ:- 🔹 የተኮማተረውን ወይም የተሸማቀቀውን ጡንቻ እንዲወጠር በማድረግ ማፍታታት፣ እኩል የሆነ መሬት ላይ እግራችንን በማስቀመጥ እግራችንን መዘርጋት፣ ቀስ እያልን መራመድ። 🔹 ሆዳችን አካባቢ በተለይም ከወር አበባ ጋር ተያይዞ ለሚከሰት የጡንቻ መሸማቀቅ ደግሞ ለብ ያለ ውሃ በእቃ ውስጥ በማድረግ ሆዳችንን በስሱ ማሸት ይመከራል። 🔹 የተሸማቀቀዉን ወይም የተኮማተረውን ጡንቻ በስሱ ማሸት ወይም ማሳጅ ማድረግ። 🔹 በሐኪም ትእዛዝ የሚሰጡ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን መውሰድ። 🔹 ከዚህ አልፎ ግን በተደጋጋሚ የጡንቻ መሸማቀቅ የሚያጋጥመን ከሆነ፤ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የጤና ባለሙያ ማማከር ይኖርብናል። ✅ የጡንቻ መሸማቀቅ እንዳያጋጥመን ምን ማድረግ አለብን? ➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️♾️➖〰️➖〰️➖〰️➖ 🍑 የአካል ብቃት ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ከመስራታችን በፊት ሰውነታችንን በደንብ ማማሟቅ እና ሰርተን ስንጨርስም ሰውነታችንን ለማረጋጋት ወይም ለማቀዝቀዝ ሚረዱንን እንቅስቃሴዎች ማድረግ። 🍑 ውሃን በበቂ ሁኔታ መጠጣት በተለይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በምናደገርግበት ጊዜ ሁሌም ከመስራታችን በፊት እንዲሁም እየሰራን ደግሞ ቢቻል በ15 ደቂቃ ልዩነት ዉሃ መጠጣት አለብን። 🍑 በካልሽየም እና በፖታሲም የበለጸጉ ምግቦችን ማለትም እንደ ሙዝ እና ሌሎችም አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ማዘውተር ይመከራል። ©EthioTena #ኢትዮጤና ፌስቡክ ገፅ የተወሰደ ▪️➖➖➖➖➖➖➖〰️➖➖➖➖
نمایش همه...