cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

በብእሲ

እንኳን ወደ በብእሲ የቴሌግራም ቻናል መጣችሁ። በቻናላችን ግጥም 📕አዳዲስ መፅሀፍት 🤗የታዋቂ ሰዎች ታሪክ 😌 ስዕሎች 📖አጫጭር ወጎች 🤗ጭውውት ና ትረካዎች ወደናንተ ይደርሳሉ። አብራችሁን ለመስራት እንዲሁም ማስታወቂያ እንድንሰራላችሁ የምትፈልጉ በራችን ክፍት ነው። 👇 @BebesiEthiopia

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
258
مشترکین
-124 ساعت
-27 روز
-430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

እንኳን አደረሳችሁ! #በብእሲ @fikermahi
نمایش همه...
ፈጣሪ ያጎደለብኝ ምን አለ? ሰፈራችንን የሚጠብቁ አንድ ሰውዬ አሉ፣ አንድ እይታ ይበቃል እሳቸውን ለማስተዋል ብዙም ያልተቸገረ የሚመስለው ፈገግታቸው ከሩቅ ይጣራል፣ ሁሌም እናቴ ስላሉበት ሁኔታ ስጠይቃቸው ፈጣሪ ያጎደለብኝ ምን አለ ሲሉ ነው የምሰማቸው፣ እግር ጣለኝና ትናንት በወሬያቸው መሀል ገባሁ፡ በምን እንደተነሳ ባላውቀውም፡ የሶስት ልጆች አባት እንደሆኑ እናም ብዙ ብዙ ውስጠ ሚስጥራቸውን ለእናቴ አጫወቷት፣ በንግግራቸው መሀል መሀል ላይ ጣል የሚያደርጓት ፈገግታቸው ግን ሀሴት ይሰጣል፣ በመኖር ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ልጆቼን እና ባለቤቴን ብቻ ነው፡ ቀሪ ሀብት ንብረት የለኝም ለመኖር ስል ማብቂያ የሌለው ገንዘብ ሳባርር፣ በህይወት ላይ ማቆሚያ የሌለው ሰልፍ ስጠብቅ ማብቂያው ምን እንደሆነ ሳላውቅም ስሮጥ ኖሪያለሁ፣ ብቻ ሳላውቀው እየሮጥኩኝ የሆነ ነገር ብቻ ለመያዝ እያሳደድኩ እንዳልሞት እፈራለሁ፣ ለዚ ነው ፈጣሪ ያጎደለብኝ አንዳች ነገር እንደሌለ እያወራሁ በፈገግታ እና በምስጋና ህይወቴን ምገፋው አሏት፥ የህይወት ትግል የማያልቅ እና ማብቂያ የሌለው ነው…ያለትርጉም ያለፋይዳ ማብቂያ የሌለው ሩጫ...ድንገት ተራ ሲደርስ ደግሞ ባኖደውም ማረፍ…አለቀ!! ግን ደግሞ በዚህ ስክንሳር በሞላበት አለም ላይ ፈገግታ ካለን ጠላት አይኖረንም፡ ፈገግታ የሀሴት መርጫ ሲሪንጅ ነው፡ ዛሬን በሀዘን አትግደሉ አለም ላይ የሌለን ነገር ሁሉ ቢደመር እና ቀመር ቢሰራ ያለንን ግማሽ አያክልምና!! @fikermahi
نمایش همه...
እርግጡን ልንገርሽ "አፈቅርሻለሁኝ" ❤️ ህልሜን እንዳዋይሽ ህልምሽን ንገሪኝ ህልም እንደ ፈቺው ነው እባክሽ አትፍሪኝ ብዬ ባልኩሽ ጊዜ ህልምሽን ብትነግሪኝ እንደዚህ ፈታሁት እ'ህ" ብለሽ ስሚኝ ። ፡ ህልምሽን ስፈታው ትርጉሙ ይኸው ነው መጣላት ለሚለው በፍቅር መውደቅ ነው ዕንባ ማለት ደግሞ ደስታና ፌሽታ ነው ፈልገሽ ማጣትሽ እኔን ማግኘትሽ ነው ። ፡ ህልምሽን ነግረሽኝ እኔም ፈታሁልሽ ህልሜን ደግሞ ስሚኝ እታለም ልንገርሽ ?! ፡ በነጭ ፈረስ ላይ አንቺ ተቀምጠሽ እኔ ስከተልሽ እርቀሽኝ ሳለሽ ብጣራ አትሰሚኝ ሰግረሽ ትሄጃለሽ ምንድነው ትርጉሙ ንገሪኝ አስልተሽ ። ፡ እሷ.. ህልምህን ስፈታው እንዲህ ነው የሆነው ካንተ እቅፍ ውጪ ሌላው ወዳቂ ነው በፈረስ መስገሩም እድሜና ጽድቅ ነው እውነቱን ልንገርህ ሁሉም የፍቅር ነው ። ፡ እኔ... ህልምሽን ነገርሽኝ ህልሜንም ነገርኩሽ ህልም እንደ ፈቺው ነው እውን ይሁን አልኩሽ ግን ....... ግን ግን - እታለሜ .....? ህልም ተተርጉሞ ህይወት እንዲዘራ ነይና ልቀፍሽ አዝመራው ይዘራ እሸት ሳለሽ ልብላሽ እሸት ሳለው ብይኝ እርግጡን ልንገርሽ - አፈቅርሻለሁኝ ። ©noahbookdelivery @fikermahi
نمایش همه...
1
#5ቱን_አስመሳይ_ሰዎች_ተጠንቀቃቸው! #አንድ አስመሳይ ሰዎችን ከሕይወቴ ቆርጬ ማስወጣቴ ክፉ ስለሆንኩ አይደለም፤ ራሴን ስለማከብር እንጅ! #ሁለት አስመሳይ ሰዎች ጥላህን ይመስላሉ። ጥላህ ለአንተ እጅግ ቅርብ ቢሆንም በሕይወትህ የምትፈልገውን ከለላ ግን አይሰጥህም። #ሶስት አስመሳይ ጓደኞች አሪፍ ነህ ብለው ሲያስቡ ብቻ ከጎንህ ይገኛሉ። እውነተኛ ጓደኞች ግን ሞኝ በሆንክ ጊዜ እንኳ አይርቁህም። #አራት እጅግ አሳዛኙ ቀን ጓደኞቼ ብለህ ያሰብካቸው፣ ጓደኞችህ አለመሆናቸውን ያወቅክበት ቀን ነው! #አምስት ምርጥ ጓደኛዬ የምትለው ሰው፣ አስመሳይ ሲሆንና ከጀርባህ ሲወጋህ ከሚሰማህ የሕመም ስሜት በላይ የሚያሳምም ምንም ነገር የለም። ©Ethiopian_Psychology @fikermahi
نمایش همه...
"ንጹህ ምንጭ"የብራና አውደርዕይ ነገ ይጠናቀቃል በሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ስራ ድርጅት የተዘጋጀው "ንፁሕ ምንጭ ኢትዮጵያ" የተሰኘ ታሪካዊ አውደርዕይ ከሚያዝያ 4 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። ዛሬ እና ነገ የመጨረሻ ቀናት ናቸው። "ንጹህ ምንጭ ኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውና የጥንታዊ የብራና ዝግጅትና ጽሑፍ በአካል የሚያዩበት፤ ጥንታውያን ሥዕላት ከእነ አሳሳላቸው የሚመለከቱበት፤ እንዲሁም በጥበባተ እድ ሥራዎች ጎብኚዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያን ንጹህ ምንጭነት በትክክል የሚመለከቱበት አውደርዕይ ነው ተብሏል። በዚህ ዝግጅት ላይ ዛሬ ሚያዚያ 12 እና ነገ ሚያዝያ 13 ከምሽት 11:00  ጀምሮ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የኪነጥበብ ምሽት ከዐውደ ርዕዩ ጋር በጥምረት ይቀርባል። በዕለቱ የሚገኙ የክብር እንግዶች ዲስኩር ግጥምና የተለያዩ ኪናዊ ሥራዎች ለማቅረብ መጋቤሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ፣መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ፣ዲያቆን ዶክተር ቴዎድሮስ በለጠ፣ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ፣ሠርጸ ፍሬስብሐት፣አርቲስት አለማየሁ ታደሰ ፣አርቲስት ይገረም ደጀኔ ፣አርቲስት ንብረት ገላው፣አርቲስት ናርዶስ አዳነ ፣ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፣ገጣሚ አስታውሰኸኝ ረጋሳ ፣ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን … በሥፍራው ይገኛሉ ተብሏል። ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1 @fikermahi
نمایش همه...
እኛ እራሳችንን እና ሌሎች እኛን ምን ያህል ያውቁናል? አንዳንድ ግዜ ሰዎች እኔ እራሴን በደንብ አውቀዋለሁ ወይም እከሌን በደንብ አውቀዋለሁ ሲሉ ይደመጣል ነገር ግን የስነ-ባህሪ አጥኚዎች ሰው ራሱንም እንዲሁም ሌሎችን ሙሉ በሙሉ እንደማያውቅ እንደሚከተለው ያስረዱናል። 4ቱ ማንነቶቻችን፦ 1. Open- ግልፅ ሆኖ የሚታየው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን እና ሌሎች እኛን የሚያውቁት ግልፅ የሆነው ማንነት ክፍል ነው። 2. Hidden- ድብቅ የሆነው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን የምናውቅው ሌሎች ግን ስለእኛ የማያውቁት ክፍል ነው። 3. Blind- ሰዎች ስለኛ የሚያውቁት እኛ ግን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል ነው። 4. Unknown- ሌሎች ሰዎችም ሆኑ እኛ ራሳችን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል ነው። ስለዚህ ከሰዎች ጋር መልካም እና ሚዛናዊ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን ከላይ የተዘረዘሩትን የማንነት ክፍሎች ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው። ካልሆነ ግን እከሌን አውቀዋለሁ ብለው ሲያስቡ አንድ ቀን ድብቁ/ የማያውቁት ማንነት ሲገለጥ ሊጎዱ ይችላሉ። እንዲሁም ራስዎትን ራሴን በደንብ አውቀዋለሁ በማለት ሌሎች ከሚሰጥዎት ምክር ባለመማር ራስዎትን ከማሳደግ እና ከማሻሻል እንዳይገደቡ ጥንንቃቄ ያድርጉ። በ መአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት) @fikermahi
نمایش همه...
👍 1
🐶 ቅብጥብጡ ውሻ 🐶የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡ 🐶በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡ የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡ 🐶የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡ 🐶ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡ ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . . 🐶ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡ ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!                          ✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ   @fikermahi    
نمایش همه...
👍 2
እንኳን ለኢድ ዓል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! @fikermahi
نمایش همه...
#ብስለት_ላይ_መሆንህን_የሚናገሩ_ባህሪዎች 1- አብዝተህ ይቅር ትላለህ 2- አዳዲስ ሐሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ ነህ 3- ልዩነቶችን ታከብራለህ 4- በቀላሉ አትፈርድም 5- የልብ ጉዳቶችን ትቀበላለህ 6- ከማይረባ ጭቅጭቅ ይልቅ ዝምታን ታስቀድማለህ 7- ሰዎች እንዲወዱህ አታስገድድም 8- በተራ ወሬ ጊዜህን አታባክንም #ስሜትን_በብልኃት_መምራት መጽሐፍ @fikermahi
نمایش همه...
ዛሬ በሳዑዲ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ እንደሚከበር ተገለጸ፡፡
نمایش همه...