cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

መርጌታ ሠናይ የባህል መዳህናኒት ህክምና🌴🌿🌿🌿🌿🌴

የባህል መዳህኒትና ሰው ሰራሽ ችግሮች መፍትሄ አለን

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
4 756
مشترکین
-1324 ساعت
-687 روز
-25830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ይህ በሚጠጣ ነገር ወደ ሆዱ የገባው መተት ሰውዬው ሳያውቀው ከቆየ፣ሥጋዊ በሽታም ከመሰለው በጊዜ ሂደት ሆዱ ውስጥ የገባው መተት እራሱን በመቀየር #እንደ_እባብ #እንደ_እንቁራሪት #እንደ_አይጥ ሆኖ ውስጡ ተቀምጦ ሥጋውን በመብላት ደሙን በመጠጣት ለከፍተኛ ጤና መታወክና ጉዳት ይዳርገዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ሊገድለውም ይችላል፡፡ 👉 ዛሬ ሆዳችንን እያመመን፣የሆድ ህመማችን ትልቅ ጭንቀት ፈጥሮብን በየ ሆስፒታሉ ሄደን መፍትሔ የምናጣው መተት ቢሆንስ? ምክንያቱም በመተት ወደ ሆድ ገብቶ ደዌና አውሬ ሆኖ የተቀመጠው ነገር በሕክምና ምርመራና መሣሪያዎች አይታይም ይሠወራቸዋል፡፡ 👉ስለዚህ የመተት አጋንንት ውስጣችን ከገባ እራሱን እየቀያየረ የተለያየ በሽታ ይሆናል፡፡ በሚበላና በሚጠጣ ወደ ሆዳችን የገባው፣በቁሳቁስ ወደ እኛ የሰረጸው መተት #ሆዳችንን ሊያሳምመን #ለአእምሮ ሕመም/እብደት/ ሊዳርገን #እጅ እግራችንን ሽባ ሊያደርገን #ለወገብ ለልብ ሕመም #ለጨጓራ ሕመም #ለደም ግፊት ለስኳር ሕመም #ለአስም ሊዳርገን ይችላል፡፡ መተትን አደገኛ የሚያደርገው ይህ ነው፡፡ ⏩#ዓይነ ጥላ ሕይወታችንን የማጎሳቆል ሥራ የሚሠራው በስውር ነው፡፡ መተት ግን በግልጥ ነው፡፡ ⏩#ዓይነ ጥላ በውስጣችን አሸምቆ ተደብቆ ከእኛው ጠባይ ጋር ተስማምቶ አድብቶ ነው የሚኖረው፡፡ መተት ግን ጥቃቱ የሚታይና ግልጥ ነው፡፡ ⏩#የዓይነ ጥላ አጋንንት የሚጎዳን በጊዜ ሂደት ነው፡፡ መተት ግን በድንገት ነው፡፡ ⏩#መፍትሔ 🔷#የአበዘንጣ ሥርና ቅጠል 🔶#የግራዋ ሥርና ቅጠል 🔶#የአንቧጮ ሥርና ቅጠል 🔶#የሀረግ እሬሳ(እጸ ሳቤቅ) ሥርና ቅጠል 🔶#የልምጭ ሥርና ቅጠል 🔶#ሰባት የሎሚ ፍሬ 🔶#የነጭ ሽንኩርት ፍሬ 🔷#የፌጦ ፍሬ 👉 አዘገጃጀት ሁሉንም እፅዋቶች በንፅህና በሥራ ቀን ከቻሉ በእለተ ሥሉስ ሥሮችን ነቅሎ ቅጠሎችን ቆርጦ ቀጥቅጦ አንድነት አቀላቅሎ ሽንኩርቱን ጭቅጭቆች ፌጦውን ወቅጦ ሎሚውን ከትፎ ሁሉንም በአንድ እቃ አቀላቅሎ በእለት ውሀ ዘፍዝፎ ጥዋት ጥዋት ከ፯-፲፬ (7-14) ቀን መታጠብ በንፅህና ። ⏩#የመተትና የዓይነ ጥላ ችግርን ፈፅሞ ያጠፋዋል ፍቱን መፍትሔ ነው ። ⏩#የሚከለክሉ ነገሮች #አልኮል #ተልባ ⏩የአባቶቻችን የእጸዋት ጥበብ ፣ ዓይነ ጥላን ፣ ገርጋሪ መናፍስትን እንዴት ማራቅና ማስወገድ እንዳለብን ፣ ስለ ጠልሰም ፣ ስለብራና መጽሐፍት ጥቅማቸው ይተነተናል። ⏩ ለበለጠ መረጃ ☎ 09 10 55 96 00 ይደውሉ ☎️ 09 10 55 96 00 ⏯በዚህ መልዕክት ያስቀምጡልኝ
نمایش همه...
⏩#የመተትና #የዓይነ ጥላ ልዩነትና አንድነታቸው ላካፍላችሁ ⏩#ለማንበብ_አንሰልች ችግሩ ካለብን ልንፈወስበት ከለለብን ወደፊት ልንጠነቀቅበት ስለምንችል ሸር ያድርጉልን 💚#መተት ከዓይነ ጥላ አጋንንት ጋር አንድ የሚያደርገው ሁለቱም የሰውን ልጅ ሕይወት ማበላሸት፣ ውጥኑን፣ እቅዱን ማኮላሸት ላይ ስለሚያተኩሩ ነው፡፡ ሁለቱም አለን፣እጄ ገባ፣እርግጠኛ ነኝ በምንላቸው ነገሮቻችን ላይ የሚያደርሱብን ስውር ጥቃት አንድ ነው፡፡ 💚#መተት እና ዓይነ ጥላ በዕድላችን፣ በእውቀታችን ፣በትምህርታችን፣በእጮኛችን እና በትዳር ሕይወታችን እንዳንጠቀም ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ ድግሱ ድረስ የመደንቀር፣የማበላሸት ሥራን ይሠራሉ፡፡ 👉 ሁለቱም አሉኝ በምንላቸው ነገሮች እንዳንጠቀም የመጠርቀም ሥራን ይሠራሉ፡፡ 👉ሁለቱም ተስፋ በጣልንባቸው ከመቶ ፐርሰንት በላይ እርግጠኛ በሆንባቸው ነገሮቻችን ላይ ፣አጋንንታዊ የበላይ በመሆን በግልጽና በስውር፣ የማይታይ ምስማር በመሆን ጠስቀው ይይዙብናል፡፡ ⏩መተትና ዓይነ ጥላ ሲላቸው በራሳቸው ሲላቸው በሰው እያደሩ፣የእኛን ነገር ገና ከጅምሩ እየገረገሩ ያበላሹብናል፡፡ 💚#ዓይነ ጥላና መተት የሰው ልጅ ዳግም የማያገኝውን፣ ተመልሶ የማይኖረውን ውድ ሕይወቱን በማባከን ፣የያዘውን በማስጣል ብሎም በመንጠቅ አንድ ናቸው፡፡ 💛#መተት እና የዓይነ ጥላ አጋንንት የሚለያቸው ወይም አንድ የማያደርጋቸው እንይ ▶#መተት በደጋሚዎች ወይም በጠንቋዮች በመጎተት ሰውን የሚቆራኝ አጋንንት ነው፡፡ ▶#መተት በሰው እድል የሚቀና፣በሰው መልካም ሕይወት በብግነት የሚኖር ሰው በሚበላ በሚጠጣ፣በቁስ ወዘተ በማስደገም የሚያቆራኘው አጋንንት ነው፡፡ ⏩#ዓይነ ጥላ በደጋሚዎች የሚጎተት አጋንንት አይደለም፡፡ እራሱን ችሎ፣ክፋቱን ተንኮሉን ጠቅልሎ ወደ ሰው ሕይወት የሚገባ አጋንንት ነው እንጂ በደጋሚዎች የሚቆራኝ አይደለም፡፡ ⏩ዓይነ ጥላ የሰውን ልጅ ከማኅፀን ጀምሮ በጽንስ ጊዜ በመቆራኘት አብሮ የሚያድግ ፣ የሰውን ሕይወት የሚያጠወልግ አጋንንት ነው፡፡ ▶#መተት ግን ድንገት ወደ እኛ ሕይወት በሰው ክፋት የሚመጣ አጋንንት ነው፡፡ ⏩#ዓይነ ጥላ የማንም አጋንንታዊ ድግምት የማያዘው በራሱ የክፋት መንገድ የሚራመድ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ 👉በእርግጥ መተት ገና በማኅፀን ባለ ጽንስ ላይ ቢደገምም መተትን ወደ ሰው ሕይወት ለማስገባት ገፊ አካላት ያስፈልጋል ፡፡ 👉ዓይነ ጥላ ግን ዕድላችን ላይ በመቅናት ሰተት ብሎ የሚገባ ነው፡፡ ልብ ይበሉ‼ ✅#መተት በሰው ቅናት የሚገባ አጋንንት ሲሆን ✅#ዓይነ ጥላ እራሱ መንፈሱ በእኛ በመቅናት የሚገባ ነው፡፡ ✅#ዓይነ ጥላ በውስጣችን ከገባ በኃላ እራሱን እየቀያየረ በሕመም እየተመሰለ ይቀመጣል፡፡ ✅#መተትም ውስጣችን ከገባ ደዌ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ 👉#ልዩነታቸው ☑ዓይነ ጥላ አንዴ ውስጣችን ከገባ እንደ ግል ይዞታው ተደላድሎ ይቀመጣል፡፡ ☑#መተት ግን ውስጣችን ከገባ በኃላ እድሳት የሚባል አጋንንታዊ ሥርዓት አለው፡፡ እድሳት ማለት አንድ ሰው ላይ በመልካም ነገሩ መተት ሲመተትበት፣የሚያስመትተው ሰው በደጋሚው ወይም በመታቹ በኩል ለአጋንንቱ ግብር ያቀርብለታል፡፡ ለምሳሌ ገንዘብ፣በግ፣ደም ወዘተ ያቀርባል፡፡ ይህንን ያስደገመ ቀን ያቀረበውን ግብር በየ ዓመቱ ሲያቀርብ አጋንንታዊ ውል ይገባል፡፡ ይህንን የሚያደርገው የሰውን እድል ስለወሰደ በዛም ስለሚጠቀምበት ከሰው የወሰደው ዕድል፣ እውቀት፣ የትዳር፣የሥራ እድል ወዘተ በአጋንንት ተጠብቆ እንዲቆይለት እንዲጠቀምበት የሚያደርገው ነው፡፡ ⏩ብዙ ጊዜ መተት የተመተተባቸው ሰዎች ከአጋንንቱ በቀላሉ መላቀቅ የሚያቅታቸው በአጋንንቱና በሚደገምበት ሰው መሃል ያለው አስደጋሚው ሰው በየዓመቱ ወይም በየወራቶቹ በተደገመበት ሰው ስም ለአጋንንቱ ስለሚገበር የተመተተበት ሰው ሲታደስበት አጋንንቱ እንደ አዲስ ወደ ውስጡ ይገባል፣ ጤና ያጣል፣ የጀመራቸው ነገሮች በአስገራሚና ለማመን በማያስችል ሁኔታ ይበላሻል፡፡ 👉 አንድ ሰው በተለይ መተት የተመተተበት ሰው መተቱ ሲታደስበት የሚያሳየው ጠባይ አለ፡፡ #በድንገት ጭው የሚል ስሜት መሰማት #ያለ ምክንያት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባት #መረበሽ #መጨናነቅ #ፍርሃት መሰማት #የሆነ የማናውቀው ነገር ውስጣችን ሲገባ መሰማት #እራስን ስቶ መውደቅ/ይህ መንፈሱ ውስጣችን ሲገባ ነው/ #በጠራራ ፀሐይ ብርድ ብርድ ማለት #ውልብ ብሎ ሰውነታችንን የሚከብድ ስሜት መሰማት #በድንገት የልብ ምት መጨመርና ዝብርቅረቅ የሚል ስሜት መሰማት #ከፍተኛ ድንገተኛ የሰውነት ድካምና የመክበድ ስሜት መሰማት #ሰላም ማጣት #ድንገተኛ የባሕርይ ለውጥ ማሳየት #ያለ ምክንያት ብስጭት ብስጭት ማለት #ማዞር መቅለሽለሽ፣ጭንቅላት #ልብ ላይ ጭንቅ የሚል ስሜት መሰማት #ጩኽ ጩኽ የሚል ስሜት ከውስጥ መግፋት #እጮኛሞች እና ባለ ትዳሮች ከሆኑ ድንገት የማስጠላት እና የመጥላት ስሜት ውስጥ መግባት #መሳደብ #ከፍቅር አጋር ጋር እንለያይ ማለት #የትዳር አጋርንና ልጆችን መጥላት #ያለ ጥፋት መምታት ወዘተ ሊከሰቱብን ይችላል፡፡ ስለዚህ የተመተተበት ሰው መተቱ ሲታደስበት እንኳን ለሰው ለራሱም የማያውቃቸው የሚይጨበጡ የባሕርይ ለውጦችን ያሳያል፡፡ ለምሳሌ ፦ 👉 በመጠጥ የተመተተበት ሰው በስንት ጸሎት እና ጸበል መጠጡን ከተወ የታደሰበት ቀን ንጉልያው እስኪዞር ድረስ ጠጥቶ ይሰክራል፡፡ 👉 በእጮኛውና በትዳሩ ላይ በመቅናት የተመተተበት ሰው ከሆነ የታደሰበት ቀን ከእጮኛውና ከትዳር አጋሩ እና ከልጆቹ ጋር ያለ ምክንያት ከፍተኛ ጠብ ውስጥ ይገባል፡፡ 👉 በእውቀቱ የተመተተበት ሰው ከሆነ የታደሰበት ቀን በዛን ሰሞን ደንዝዞ ፈዞ ይከርማል፡፡ 👉 በገንዘቡ የተመተተበት ሰው ገንዘቡ ከኪሱ ለመውጣት የሚያጨበጭቡ ይመስል ያለ ምክንያት ይወጣል፡፡ ግን በምን እንዳወጣው ፣ገንዘቡን የት እንዳደረሰው፣ምን ቁም ነገር ላይ እንዳዋለው አይውቅም፡፡ ሌላም ሌላ …. በአጠቃላይ እድሳት ማለት ከአጋንንቱ ጋር በሰው ሕይወት እና እድል ላይ ውል ማራዘም ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በሰው ሕይወት ላይ በአጋንንት ስውር ምስጢር መቆመር ማለት ነው፡፡ ✅#መተት ከዓይነ ጥላ አንዱ የሚለይበት፦ #መተት በምንበላው ምግብ፣ በምንጠጣው መጠጥ፣በምንለብሰው የውስጥ እና ውጭ ልብስ/በላብ በወዝ/ በምንይዘው ቁስ ወዘተ ስለሚደገም በቀላሉ ሕይወታችን ሊያመሰቃቅል ፣ጤናችን ሊቃወስ ይችላል፡፡ ✅#መተት ከዓይነ ጥላ የሚለይበት ምክንያት፦ #መተት አደገኛና ገዳይ መሆኑ ነው፡፡ ምንክያቱም መተት በመርዝ መልክ ሊሠራ ስለሚችል የተመተተበትን ምግብ የበላ ወይም መጠጥ የጠጣ ሰው በድንገት ሊሞት ይችላል፡፡ #በተለይ ወደ ሆድ በሚገቡ ነገሮች አጋንንቱ በሰውነታችን ሕዋሶች በመሰራጨት፣ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስብን ይችላል፡፡ ⏩#መተት እና የዓይነ ጥላ መንፈስ በልዩነታቸው መተት የሚከብድበት አንዱ መተት አጋንንት እራሱን መቀየር መቻሉ ነው፡፡ መተት በሆድ ውስጥ አውሬ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ #ለምሳሌ አንድ ሰው በሻይ፣በጠላ፣በሚሪንዳ መተት ተመትቶ ቢሰጠው ያንንም ቢጠጣ ወደ ሆዱ ከገባበት ቀን ጀምሮ ጤና ማጣት፣ ህመም መሰማት ይጀምረዋል፡፡
نمایش همه...
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
የሴት ልጅ አይነጥላ ምንድነው ??? 👉 🔷ሴት_ልጅ_በባሏ ፣በፍቅረኛዋ (በወንዶች) እንዴት ትጠላለች? 👉 🔷እንዴትስ ወንዶች ቀርበው ይርቋታል ? 👉 🔷እንዴት ወደው በአጭር ጊዜ ይርቋታል (ይጠሏታል)? 👉🔷 ለምንስ ወንዶችን በፍቅር ቀርባ ትርቃቸውአለች ? 👉 🔷ለምንስ ወንዶች ያስጠሏታል? 🔶ዓይነጥላ ገርጋሪ ወይም ዛር ውላጅ የሚባለው መንፈስ ብዙውን ጊዜ ከሴቶች ግንባር ላይ ተቀምጦ ባሏ የፍቅር ጓደኛዋ በጥቅሉ ሁሉም ወንድ እንዲጠላትና በወንዶች ዘንድ የማትረባ ከንቱ ሰው መስላ እንድትታይ ያደርጋል። 🔶የመልክ የፀባይ የሴትነት የእውቀት ችግር ሳይኖርባት 🌱ወይም ጎደሎ ሳይኖራት የገርጋሪ መንፈሱ በእሷላይ ሁኖ 🌱ወንዶች ቀርበው ፍቅርን ሲጀምሩ መንፈሱ ከፍተኛ ቅናት 🌱ያድርበትና በወንዱች ላይ ይዛወርና 🔶ተዋት ተዋት አትረባህም አትመጥንህም አትጠቅምህም ክፉ ናት አታምርም እያለ በአይምሮው እያሾከሾከ እንዲተዋት ያደርገዋል ከተለያት በኋላ ደግሞ ሳትበድለኝ ክፉ ሳትናገረኝ ለምነው የተውኳት ምንስ ጎደላት እያለ ይፀፅተዋል 🌿🌿🌿 🔶ሴቷም ወንዶችን ወዳቸው ቀርባ መቀራረብ ከጀመረች በኋላ መጥፎ ነገር ሳታይባቸው ፈፅሞ ይህወንድ አይሆንሽ አያስፈልግሽም አይመጥንሽም በማለት ስልኳን አጥፍታ እንድትርቃቸው እንድትሰወራቸው ያደርጋትና። ከተለያዩ ከተረሳሱ በኃላ ምንአድርጎሽ ነው የተውሽው እያለ እንዲፀፅታት ያደርጋታል ። 🌿 🌿🌿 🔶ብዙዎችን ደግሞ የሚጠቅማቸውን የሚሆናቸውን ሰው አስትቶ ከማይጠቅማቸው ከሱሰኛው ከአጫሹ ከጠጩ አላማ ከሌለው ወስዶ ያላትማቸዋል እያጓተተ ከንቱ አድርጎ ያስቀራቸዋል። 👉 #በጣም የሚገርመው ደግሞ በውጫዊ ፍቅር 7 -15 አመት ያቆያቸውና ወደ ትዳር ሊገቡ ሲሉ ብትንትን ያደርጋቸዋል 👉የሴት ልጅ የአይነጥላ ወይም ወንድ ዛር ሴቷ ብታገባ እንኳን ከባሏጋር ሰላም ማሳጣት ማነጫነጭ ማጋጨት ኩርፍተኛ ማድረግ በረከት ማሳጣት እንዳይግባቡ ማድረግ ሲለያዩ መነፋፈቅ ሊረገዝ ሲል ፅንሱ እንዳይረጋ እየበጠበጠ በወር አበባ መልክ ማስወገድ 🌱⏭ከማህፀን ውጭ ማርገዝ የማህፀን ቱቦ መዝጋት 🌱⏭በኪንታሮት 🌱⏭በማህፀን ካንሰር 🌱⏭በማህፀን እጢ በመንደፍ ህይወታቸውን ጉስቁልቁል ማድረግ ስኳር ጨጓራ ኩላሊት ግፊት ሳይነስ የክፉው የሴት ልጅ አይነጥላ ወይም ወንድ ዛር ስራው፦ ✅ወንድ ማስጠላት ✅ከቤት አለማስወጣት ✅ወንድ መፍራት ማድረግ ✅ከፍተኛ ላብ የጠረን መቀየር ✅የወር አበባ ማዛባት ✅በህልም ግንኙነት ማድረግ ✅ወገብ ሕመም ✅የማህፀን ፈሳሽ ሽታመቀየር ✅በሰው ዘንድ ማስጠላት ✅ግንኙነት መጠላት ✅ማስወረድ (አቦርሽን) ✅የመጣ ትዳር መመለስ ✅ማስጨነቅ ድብርት ቅዥት ✅እንቅልፍ ማጣት (መብዛት ) ✅የውጭ ፕሮሰስ ማበላሸት ✅ገንዘብ አባካኝ ማድረግ ✅ቤት አለመውጣት ✅ቤት ዘግቶ ማልቀስ ✅ስራ ማስጠላት ስራ ጀምሮ ማቋረጥ ✅እራስሽን አጥፊ አጥፊ ማለት ✅ከፍተኛ ማይግሬን (ራስምታት) ✅መሐን ማድረግ ✅ከሆድላይ ሁኖ መገላበጥ ✅ሆድ መንፋት ሆድ መጮህ ✅ጸሎት ማስጠላት ማዛጋት ✅ፀባይ መቀያየር መነጫነጭ ✅የስሜት ጫፍ ላይ አለመድረስ ✅በግንኙነት ጊዜ ስሜት አለመኖር ወዘተ ✅የመሳሰሉት የሴት ልጅ አይነጥላ ምልክቶችናቸው። 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ✅ለዚህ ዓይነ ጥላ መፍትሔ 🌱💠#እፀ ሳቤቅ ስር 🌱💠#ጊዜዋ ስር 🌱💠#የቀጠጥና ስር 🌱💠#ከርቤእጣን 🌱💠#የታሪገማ ስር 🌱💠#የአጋም ስር 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ቀጥቅጦ አቀላቅሎ ማታ ማታ እየታጠኑ መተኛት ከ 7-14 - 21 ቀን ማታማታ መታጠን የሚከለክሉ ነገሮች ተልባ አልኮልና ፆታዊ ግንኙነት በተጨማሪ #ለኪታሮት #ለጭርት ለበለጠመረጃ፦09 10 55 96 00
نمایش همه...
❤️❤️❤️ሰላም❤️❤️❤️ ❤️❤️❤️ጤና❤️❤️❤️ ❤️❤️❤️ፍቅር❤️❤️❤️ የምመኝላችሁ ውድ የዚህ ገፅ ተከታታዩቼ እንደምን ሰነበታችሁ ??? ዛሬ ደግሞ እስኪ ስለ መተት እናውራ መተት ምንድን ነው ? መተት በተለያየ ቦታ የተለያየ ስያሜና አጠራር ሲኖረው #ድግምት #ውለሽ #የሰው እጅ #ደንቀራ #ስልበት በመባል ይታወቃል 👉 መተት ፈሪሐ እግዚአብሔር በሌላቸው ክፉ ሰሪዎችና አሰሪዎች የሚከናወን የክፋት  (የመናፍስት) ስራ ነው ። ብዙውን ጊዜ ጥቁር አስማት የሚባሉት #መቅትል #መስተሐምም #መስተአብድ #መስተባርር #ህልመ ደብድብ #መድፍነ ፀር #ማዕፀወ ምስያጥ (የገብያ መዝጊያ) #ሀብተ ገልብጥ በመባል ይታወቃል እንዳለመታደል ሁኖ አንዳንድ ሰዎች  ሰርተው ከማደግና ይልቅ ከፈጣሪ ሕግ በመውጣት በሰው ሀብት፣ ንብረት እድልና ግንባር በመቅናት የተለያየ መተት ተጠቅመው የሰውን ልጅ ህይወት ሲያመሰቃቅሉ ይኖራሉ። #መተት በዋነኛነት በ3 ይከፈላል ፩. በስም በማስደገምና በማስመተት ፪. በሚበላ በሚጠጣ በማቅመስ ፫. በመርጨት (ደንቀራ በመጣል)          #የመተት ተፅኖውና ክፋቱ ✅ሀገር አስለቅቆ መስደድ ✅ማሳበድ ፣ዘዋሪና ከርታታ ማድረግ ✅እራስን አጥፋ አጥፋ ማለት ✅ሽባ ማድረግ ✅እስርስር አድርጎ ቤት ማዋል ✅የአልጋ ቁራኛ ማድረግ ✅ሌሊት እየመጣ በህልም ማሰቃየት ✅መንፈሱ በህልመ ሌሊት ተመስሎ በመንደፍ ማርከስ ✅ጥቁር ሰው ፣በሬ ፣ውሻ ፣እባብ እየመሰለ ሌሊት ማሰቃየት ✅ሆድን ቀትቶ መንፋት ✅ከሆድ ላይ መገለባበጥ (መጮህ) ✅ሰውነትን መቆርጠም (መሰቅሰቅ) ✅ማፍዘዝ ማደንገዝ ማንቀጥቀጥ ✅ጭንቅላትን (እወቀትን)ባዶ ማድረግ ✅ንቃተ ህሊናን እስከ እድል መስለብ ✅ንቡዘ ልብ ማድረግ (ማስረሳት) ✅ፍርሃት ጭንቀት ድብርት ብስጭት ✅ስንፈተ ወሲብ ማምጣት ✅ሰውነትን መሸምቀቅ ✅እራብ እራብ ማለት ✅እህል መከልከል ✅ከመጠን ያለፈ ውፍረት ✅በጣም መክሳት ✅እንቅልፍ መከልከል ✅እንቅፍ እንቅልፍ ማለት ✅ሱሰኛ መሆን የጫት የመጠጥ የሽሻ ✅ገንዘብ መበተን ✅ስራ ጀምሮ አለመሳካት ✅የውጭ እድል መዘጋጋት ✅እንከን ሳይኖረን ከፍቅርኛ ጋር መለያየት ✅ባልና ሚስት ማለያዩት ✅መካንነት ✅አግኝቶ ማጣት ✅የገብያ መዘጋጋት. 👉 ታዲያ ይህ ችግር  በሀገራችን ብሎም በአለማች የስንቱን ህይወት እንዳበላሸውና የስንቱን ቤት እንደፈታው ስንቶቻችን ነው የምናውቀው ? ይህ ችግር በቤታችን ካለና ከተከሰተ መፍትሔውን በመጠቀም ችግሩን ማስወገድ  አለበለዚያ ግን የችግሩ ሰለባ ሁነን እንቀራለን እንደየ እምነታችን በርትተን መፀለይ ንስሐ መግባት በፆም በፀሎት በስግደት ክፉ የመናፍስት መተትንና ማስወገድ የተለያዩ መአቅቦችን መያዝና ፀልየን መውጣት ወሳኝነው። ችግሩ በዚህ የማይፈታ ከሆነ ደግሞ የቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባቶችን ጥበብ ተጠቅመን ችግሩን ማስወገድ ግድ ይለናል ፀሎቱን እንሆ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሱ ፩ አምላክ አሜን በእንተ መፍትሔ ሥራይ በስመ እግዚአብሔር መሐሪ ወመስተዓግሥ ለዓለም በአዶናይ በስተናዊ ንጉስ ዘይነብር መልዕልተ ሠረገላ ኪሩቤል ዘይዴዓን አፍራሰ ሕይወት አምሐልኩክሙ ወአውነዝክሙ በማኅተመ ዕሌኒ ንግስት ወበጊዮርጊስ ሰማዕት መስተጋድል ወበዮሐንስ መጥምቅ ወበማሪያም ወላዲተ አምላክ አምሐልኩክሙ ወአወገዝኩክሙ ከመ ኢትግብሩ ሥራየ በላዕሌየ ወኢታምጽኡ ደዌ ወሕማም ውስተ ቤትየ ወኅበ ሰብእየ ወእንስሳየ አምሐሌኩክሙ ወአወገዝኩክሙ በድማኤል ኅቡ ስሙ ለእግዚአብሔር ወበቃሉ ቅዱስ ወበቅቅያኖስ ወበሐኬ በዝንቱ አስማተ ተሰደዱ ኩልክሙ መናፍስት ርኩሳን ወአጋንንት ፀዋጋን ኢትቅረቡ ኀበ ነፍስየ ወሥጋየ ለገብርከ (ለአመትከ) እገሌ ወተወካፌ ዝንቱ ጸሎት አወግዘክሙ በምናቴር ወበ ፀባዖት ወበሥሉስ ቅዱስ አምሐልኩክሙ ወአወገዝኩክሙ ይብሐም አፉክሙ ወይትዓሥር ልሳንክሙ ወይትዓፀው ጉርዔክሙ ወይድክም ኀይልክሙ ከመ ኢትቅረቡ ኀበ ነፍስየ ወሥጋየ ሊተ ለገብርከ (ለአመትከ) እገሌ .. አማሐልልኩክሙ በሚካኤል ወገብርኤል በሱራፌል ወኪሩቤል በ፳ወ፬ ካህናት ሰማይ ወበ፬ቱ እንስሳ ከመ ኢትቅረቡ ኀበ ነፍስየ ወሥጋየ ወኀበ ቤትየ ወኀበ ስብእየ ወእንስሳየ አወገዝኩክሙ ከመ ትርኃቁ እምዛቲ ትውልድ እስከ ለዓለም ዓለም አማሐልኩክሙ በ፳በ፬ ካህናት ሰማይ እለ የዓጥኑ መንበሮ ወይቀውሙ ቅድሜሁ ለአብ ወዝውእቱ አስማቲሆሙ ክቡር አክያል ቅርትያል ፉኑኤል ግራኤል አፍዳኤል ጥታኤል ሂልታኤሌ ዳክኤል ቀለምታኤል ምርታኤል ናርታኤል ከሠታኤል አፓኤል ጰጣኤል ርታኤል ሰላታኤል ጣውርሮኤል አኑኤል ጥስልድኤል ጥላልኤል ከልድኤል ኤልትኤል ይእዜኒ አውርድ መንፈስከ ቅዱስ ውስተ ዝንቱ ቅብዕ ምላዕ ዓዲ ሀበኒ ሞገሰ ወብርሃነ አዕይንትየ ወሕሊናየ ወአብጽሐኒ ለገቢረ ፈቃድከ በዘይሰደዱ አጋንንት ወመናፍስተ ርኩሳን ወኩሉ ኅሡም ዘሀሎ በቤትየ ኀበ ነፍስየ ወሥጋየ አርኅቆሙ ወስድዶሙ እሰግድ ለከ አብ አኀዜ ኩሉ ዓለም ወቦ እለ ይፀውሩ ማኅበረከ ወ፬ እንስሳ ወኩሎሙ ምሉዓነ አዕይንት ወመፍቅደ አዕይንቲሆሙ ለለ፩__ ወ፬ ወለካልዑሂ ፳ወ፩ ወለሣልሱሂ ፵ ወለራብዑሂ ፵ወ፬ ወኢይትናጸሩ በገጾሙ በአዕይንቲሆሙ ለይከሥቱ አፉሆሙ ኅቡረ ወይብሉ አግዮስ፫ በዝንቱ ስምከ ተማኅፀንኩ ሐራይሮኅ ድልያፎን ያጥፍዕክሙ ወይድፍንክሙ ወይብትክ ኀይለ መሥገርትክሙ ወይቀጥቅጥ እገሪክሙ ወያድክም ኃይልክሙ ወይርአድ ኃይለ አባልክሙ  በሐመ ይኩን ልሳንክሙ ወአዕዛኒጸክሙ ወይትዓሠር አፈክሙ አምሐልኩክሙ ወአውገዝኩክሙ ዓሠርኩክሙ ወለጎምኩክሙ በኃይለ ዝንቱ አስማተ ቅንዋት ሳዶር አላዶር ዳናት አዴራ ሮዳስ ውጉዛነ ኩኑ በቤቃ በቃብዕ በአኮስባኤል ርእስ መሐላ ለዓለም ዓለም አኃትም ወአድህነኒ እምስራይ ወአልጉም እምጠምዛዥ ወእም ቆልዛዥ ወአልጉም አድኅነኒ ሊተ ለገብርከ እገሌ ... በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ዘይወፅእ እምአፉሁ ሰይፈ እሳት ዘይባልሕ እምሰይፍ ወይበርቅ እመብረቅ ዘይዘርዎሙ ለመናፍስት እርኩሳን ወያጠፍኦሙ ከመ ጢስ ከማሁ ዝርዎሙ ለፀርየ ወለጸላዕትየ እለመከሩ ዕኩየ በላዕሌየ ለገብርከ (ለአመትከ) እገሌ ለዓለም ዓለም አሜን         #ገቢር #የአንባጮ ስሩን ቅጠሉን (ተቀፅላውን ) #የሎሚ ተቀፅላ #የአርግፍጋፎ ስሩን ቅጠሉን #የልምጭ ስሩን ቅጠሉን (ተቀፅላ) #የግራዋ  ቅጠል (ተቀፅላ) #የአቱች ስሩን ቅጠሉን #የፈላፁት ስሩን ቅጠሉን #፯ የሎሚ ፍሬ #የታሪገም ስሩን ቅጠሉን #የምድር እንቧይ ስሩን ቅጠሉን        #አዘገጃጀት የተዘረዘሩትን እፅዋቶች በንፅህና አዘጋጅቶ በእለት ውሀ ዘፍዝፎ ጥዋት ጥዋት መፍትሔ ሥራዩን ፯ ፯ ጊዜ እየጸለዩ መጠመቅና ቤትን መርጨት የተዘጋ ገብያን መርጨት ነው።ስልክ        0910559600        0910559600
نمایش همه...
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች ❖ሰላም ❖ጤና ❖እድገት ❖ብልፅግና  በያላችሁበት ተመኘው      ❤በቅንነት ሸር እናድርግ 👉 ዛሬ ስለ #ግርማሞገስ እና #መፍትሔ ሀብት እናያለን #ግርማሞገስ ምንድነው  ? 👉 ግርማሞገስ ማለት አንድ ሰው በሰው ዘንድ (በማሕበረሰቡ) 🍀እንዲከበር  🍀እንዲፈራ 🍀ሲያዩት እንዲያስደነግጥ 🍀ተቀባይነት እንዲኖረው 🍀ተሰሚነት እንዲኖረው 🍀ተወዳጅነት እንዲኖረው 🍀ስኬት እንዲኖረው 🍀ሰው እንዳይደፍረው ወዘተ የመሳሰሉት ፀጋዎች እንዲኖሩት የሚያደርግ ጥበብ ነው። #ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች መልክ ቁመና  ፀባይ ሥራ ገንዘብ ደግነት ሳያንሳቸው በሰው ዘንድ ከበሬታ ሲያጡና ሲናቁ ሰው ዝቅአድርጎ ሲያያቸው ፍቅር ሲነፍጋቸው ይስተዋላል ። ታዲያ ይህችግር አንዳንዴ በተፈጥሮ የፀጋ እግዚአብሔር መራቅይሆናል በሌላበኩ ደግሞ የክፉ መናፍስት የዓይነ ጥላ፣ የገርግር፣ የዛር ፣የመተት፣ የሰው እጅና የስልበት ችግር ይህን ያስከትላል ታዲያ ለዚህ ችግር መፍትሔ ቀደምት  ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባቶቻችን የተለያዩ ጥበቦች ተጠበው አልፈውበታል ለምሳሌ ፦ #ለዚሁ የሚሆን ህቡዕ ስም በመፀለይ #ህቡዕ ስሞችን ፅፎ ከትቦ በመያዝ #በብርቀለበት #በብር መስቀል #በተለያየ ጠልሰም ፀልዮ በመያዝ #የተለያዩ እፅዋቶችን ቀምሞ በመነቀስ #የእፅዋት ቅመሞችን በማር በመቅመስ #የእፅዋት ቅመሞችን በሜሮን በቅባቅዱስ ፀልዮና አንግሦ በመቀባት የተወሰደብንን ፀጋ እግዚአብሔር መመለስና #ግርማሞገስ ፣ግርማ መደንግፅ፣ ግርማ መሐባ  ፣ተፈሪነት ፣ተወዳጅነትና ተከባሪነት እንዲኖረን በማድረግ ተፅኖ ፈጣሪ መሆን እንችላለን ። ሸር ሸር ያድርጉ ጥበብን እንፈልጋት እናክራት ጥበብ ታላቋን ታከብራለች የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት 📞09 10 55 96 00
نمایش همه...
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable