cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኢስላማዊ|| Profile pic||

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
648
مشترکین
-124 ساعت
-17 روز
+6030 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ዘመቻ–በድር በወፍ በረር ቅኝት [ ክፍል 2 ] ▇ የአቡ ሱፍያን ቅፍለት ፦    ለታላቁ የበድር ዘመቻ መከሰት ዋነኛ ምክንያት የሆነችው ከሻም ተነስታ ወደ መካ ታቀና የነበረችና በአቡ ሱፍያን ብን ሀርብ ትመራ የነበረች የጣኦታዊያኑ የንግድ ቅፍለት ናት ። ቅፍለቷ በ 1,000 ግመል የተጫነ ሀብትን ሸክፋ ነበር ። ነብዩ ﷺ ስለ ቅፍለቷ መረጃ ደረሳቸው ። ይህችን የንግድ ቅፍለት አጥቅቶ የያዘችውን ሀብት መማረክ ከተቻለ መካዊያኑን ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊ ኪሳራ ላይ መጣል የሚቻል ይሆናል ።   ነብዩም ﷺ ቅፍለቷን ለማጥቃት ጥሪ አቀረቡ ፣ ጥሪው በግዴታ መልክ የቀረበ ስላልነበር በዘመቻው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ 317 አማኞች ተዘጋጁ ። አላማቸው የነበረው ከ 50 ባነሱ ሰዎች የሚመራውን የአቡ ሱፍያን ቅፍለት በድንገት ከበው በማጥቃት የያዘውን ንብረት ለመማረክ ነበር ፤ በዚህም ምክንያት ለታላቅ የግምባር ለግምባር ጦርነት በቂ ዝግጅት አላደረጉም ። **   አቡ ሱፍያን ብን ሀርብ አል– መኽዙሚይ ስል አዕምሮን የተቸረ ብልህና ጠንቃቃ ሰው ነበር ። የመዲና ጦር ሊያጠቃው እንደሚችል ስለገመተ ቅፍለቱን በከፍተኛ ጥንቃቄ’ና ንቃት ይመራው ነበር ፣ ከቅፍለቱ ወደ ፊት ገስግሶ ባደረገው ፍተሻ የነብዩ ﷺ ጦር ሊያጠቃው መሆኑን ደረሰበት ። አቡ ሱፍያን ወዲያው ሁለት እርምጃዎችን ወሰደ ። ወደ መካዊያኑ "ንብረታችሁን አድኑ" የሚል መልዕክት ሰደደ ፣ የንግድ ቅፍለቱን አቅጣጫ ቀይሮ ፊቱን ወደ ቀይ ባህር በማዞር ብዙም ያልተለመደን መንገድ ይዞ ጉዞውን ቀጠለ ።     የአቡ ሱፍያን መልዕክተኛ መካ ደርሶ ዜናውን እንዳሰማ ጣኦታዊያኑ በንዴት ጦዙ !  " ... እንዴት ሙሐመድ ይህን ያህል ይዳፈረናል ? " አሉ ! በአቡ ጀህል መሪነት  በፈረሰኛ ፣ በብረት ለበስ’ና በእግረኛ የተዋቀረ 1000 ጦር ይዘው ወደ ሙስሊሞች ገሰገሱ ። ኋላ ላይ አቡ ሱፍያን የንግድ ቅፍለቱን ማስመለጡን በማብሰር ጦሩ እንዲመለስ የሚጠይቅ  ደብዳቤ ቢልክም በእብሪት የተወጠረው የመካ ጦር ግን የኢስላምን ብርሀን እስከመጨረሻው ሳያዳፍን በስተፊት ላለመመለስ ተማምሎ ጉዞውን ቀጠለ ። *    ነብዩ ﷺ የንግድ ቅፍለቱ ማምለጡና የመካ ጣኦታዊያን ጦር ወደ እነሱ አቅጣጫ እየገሰገሱ የመሆኑ መረጃ ደረሳቸው ። በጥቂት የሰው ሀይል የሚመራን የንግድ ቅፍለት ለማጥቃት በሚል ያለ በቂ ዝግጅት የወጣው የነብዩ ﷺ ጦር ፤  በሚገባ ከታጠቀው’ና በሶስት እጥፍ ከሚበልጠው ሰራዊት ጋር ከመፋለም ከባድ ፈተና ጋር ተፋጠጠ ።  **** ነብዩ ﷺ ባልደረቦቻቸውን ሰብስበው ለ "ሹራ" ምክክር ተቀመጡ ። ከነብዩ ﷺ ለተነሳው  ሀሳብ የመካ ሙሀጂሮችን በመወከል በቅድሚያ አቡበከር እና ዑመር ገምቢ አስተያየት ሰጡ ፣ ሚቅዳድ ቢን ዐምር ተከተሉ ፣ አንሷሮችን በመወከልም ታላቁ ሶሀባ ሰዐድ ቢን ሙዐዝ እጅግ አነቃቂ ንግግር አደረጉ ። ነብዩ ﷺ እጅግ ተደሰቱ ፣ በዚህ መልኩ ያለ ምንም የጦርነት ዝግጅት የወጣው የነብዩ ﷺ ጦር ምንም እንኳ ሸሽቶ ወደ መዲና የመግባት እድል የነበረው ቢሆንም ከአሏህ ውጭ ያለን ማንኛውም ምድራዊ ሀይል እንዳይፈራ ሆኖ ታንጿልና በሽሽት የሙሽሪኮችን ጦር ስነ–ልቦና ከፍ ከማድረግና የሙስሊሞችን አንገት ከማስደፋት ይልቅ በቁጥርም ሆነ በመሳሪያ ሀይል በ 3 እጥፍ ከሚበልጠው ሀይል ጋር ለመተናነቅ ወሰነ ። *    ምሽቱን ነብዩ ﷺ ዱዐ ሲያደርጉ’ና ወደ አሏህ ሲዋደቁ አደሩ ፣ ሁለቱ ጦሮች እንደተያዩም መልዕክተኛው ﷺ ቀጣዩን ዱዐ አደረጉ ፦ " አሏህ ሆይ ! እነሆ ቁረይሾች ከነ ትዕቢት’ና ኩራታቸው አንተን ለመቀናቀን’ና መልዕክተኛህን ለማስተባበል ታድመዋል አሏህ ሆይ ቃል የገባህልኝን ድል ስጠኝ! " ____   በቀደምት አረቦች የጦርነት ባህል መሰረት ከሁለቱም ወገን የተውጣጡ ፈቃደኛ ተፋላሚዎች ጦርነቱን ይባርኩት ዘንድ ለብቻ ብቻ ፍልሚያ ወደ ፊት ወጡ ። ቁረይሾችን በመወከል ዑትባ ቢን ረቢዐ ፣ ሸይባ ቢን ረቢዐ’ና ወሊድ ቢን ዑትባ ወጡ ። ከሙስሊሞች ወገንም ሐምዛ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ ፣ ዐሊይ ቢን አቢ ጣሊብ’ና  አቡ ዑበይዳህ ቢን ሐሪስ ወደ ፊት ወጡ ። ሐምዛና ዐሊ ተፋላሚዎቻቸውን ወዲያው አሰናበቱ አቡ ዑበይዳና ወሊድ እርስበርስ ተጎዳድተው ወደቁ ሐምዛና ዐሊ በፍጥነት ደርሰው የአቡ ዑበይዳን ተፋላሚ ካስወገዱ በኋላ ወንድማቸውን ደግፈው ወደ ጦር ሰልፉ ተመለሱ ።    ጅማሮው ያላማረላቸው ቁረይሾች አጠቃላይ ጥቃት ከፈቱ ፣ እናም ከዛሬ 14 ክ/ዘመን በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት በኩፍር’ና በኢማን ሀይል መሀከል የሚደረገው የመሳሪያ ትንቀንቅ ተጀመረ ። አሸዋው ቦነነ ፣ ሰይፎች ተፋጩ ፣ የሲቃ ድምጾች ከዚም ከዚያም አስተጋቡ ። ሙስሊሞች ከመስዋዕትነት ድልድይ በኋላ የምትገኘውን ጀነት አሻግረው እየተመለከቱ’ና "አሏሁ አክበር" የምትል የእምነት ወኔ ማቀጣጠያ ቃል እያስተጋቡ  ስለ እምነት’ና ነፃነታቸው ሲሉ በ3 እጥፍ ከሚበልጣቸው ጦር ጋር በሰይፍና ጦር ተሞሸላለቁ ።      የጦርነቱ ጫና በአርማ ተሸካሚዎቹ በኩል በረታ ፣ በውጫዊ ሀይሉ ተታሎ በትዕቢተ’ና እብሪት እየተነዳ የመጣው የኩፍር ሀይል አንድ በአንድ አባላቶቹን ያጣ ጀመር ፣ የጣኦታዊያኑ ጦር ያለውን ሀይል ሁሉ ተጠቅሞ ለማጥቃት ቢሞክርም የኢማንን ጋሻ አልፎ ባለቤቶቹን ማንበርከክ ተሳነው ፣ አርማቸውን መጣል የጀመሩት ሙሽሪኮች በቀላሉ የሰይፍ ራት መሆን ጀመሩ ፣ በነብዩ ﷺ አንደበት "የዚህች ኡማ ፈርኦን" ተብሎ የተሰየመው የጦሩ መሪ አቡ ጃህል በሁለት የመዲና ወጣቶች ሰይፍ የምሱን አጊኝቶ ቁልቁል ከመሬት ሲጋደም ደሞ የቁረይሾች ጦር ከመሸሽ ውጪ ያለን አማራጭ ያጣ መሰለ ፣ እናም በመጨረሻ በማን አለብኝነት ኩራት ተወጥሮ የመጣው የሙሽሪኮች ጦር መራራ የሽንፈት ፅዋን ተጎንጭቶ ተፈታ ፣ 70 አባላቶቹን ለሰይፍ ገብሮና ሌሎች 70 አባላቶቹን በምርኮኝነት ጥሎ የኋሊት ፈረጠጠ።    በድር በመዲና እና መካ መሀከል የሚገኝ’ና የውሀ ጉድጓዶችን የያዘ አከባቢ ነው ፤ ዘመቻው በድር የሚል መጠርያውን ያገኘውም ከዛ በመነሳት ነው ። አሏህ ሱብሀነሁ ወተዐላ የዘመቻውን ዝርዝር ሂደት የሚዳስስ የቁርአን ምዕራፍ አወረደ ፣ ከዘመቻው የምንቀስመውን ትምህርት ዘረዘረ ፣  የበድር ዘማቾችን ደረጃ አላቀ፡፡ ** የነብዩ ﷺ ባልደረባዎች ለልጆቻቸው ቁርአንን በሚያስተምሩት ልክ ስለ ነብዩ የዘመቻ ውሎዎች ያስተምሯቸው እንደነበር ተዘግቧል ። የነብዩ ﷺ የትግል ሜዳ ውሎዎች ታሪክን ከማወቅ በዘለለ አያሌ ፋኢዳዎችን ይዘዋል ፣ ክስተቶቹ ልብን በኢማን ይሞላሉ ፣ የራስን ጉድለት መመልከት የሚያስችል የንፅፅር መስታወትን ይፈጥራሉ ፣ ለተሻለ ስራ ያነሳሳሉ ፣ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ ስብዕናዎችንም ያቀርባሉ ። እናም የነብዩን ﷺ ሲራ በማጥናት ላይ ያለንን ፍላጎት ማጎልበት እንዳለብን አደራ እያልን ዝግጅታችንን እናጠቃልላለን https://t.me/islamic_quate https://t.me/islamic_quate https://t.me/islamic_quate
نمایش همه...
👍
👎
😍
🥰
👍
👎
😍
🥰
💚      አላህ እኮ ሲወደን  ሰው አደለም የሚሰጠን ገንዘብም አደለም ዱንያንም አደለም የሚሰጠን  አላህ  በጣም ከወደደን  እሱን የምናስታወስበትንና  የሚያረጋጋን ኢማን ነው የሚሰጠን  💚💕 አላህ በጣም የሚወዳቸው ሰዎች ያርገን  💛💛💛 መልካም እሁድ
نمایش همه...
👍 6
😘
🥰
👍
👎
😍
🥰
ሲትር ታዉቃላችሁ ? ሸፈና ማለት ነዉ። የገመና መሸፈን። አዎ😊 በድብቅ ከምንሰራቸዉ ወንጀሎች አንፃር የአላህ ሲትር ባይኖርልን ኖሮ ሁላችንም እርቃናችንን በቀረን ነበር። ስንቶቻችን በተዋረድን!😔😔 ቀላል ፀጋ እንዳይመስላችሁ !😊 የ አላህ ሲትር ከላያችን ቢገፈፍ ስንት  ፀጋዎቻችን በረገፉ ነበር ። በሰዉ ዘንድ ያለን ክብር ፣መወደሱም፣ መደነቁም በአንድ ጊዜ እርግፍ ይል ነበር።😔😔 ሲትሮቻችን ሚሸፈንበት ወንጀሎቻችን ሚማረበት ሀጃዎቻችን ሚፈቱበት ዱአዎቻችን ተቀባይነት ሚያገኝበት ዉብ ጁመአ ይሁንልን ኢላሂ ጌትዬ አሁንም ወደፊትም ሰትረን ድብቅ ወንጀል እንጂ ድብቅ መልካም ስራ የሌለን ሚስኪን ሰዎች ነንና ከድብቁም ከግልፁም አዉቀንም ሳናዉቅም ባመፅነዉ ነገር ምህረትን ለግሰን💚💚 በሰለዋትና በሱረቱል ከህፍ የደመቀ ዉብ ጁመአ ይሁንልን 💚💚💚                                                                  Juma💚💚                                  Sumeya😊😊
نمایش همه...
እኛ በዚህች ዓለም ላይ እስካለን ድረስ በፈተና ክፍል ዉስጥ ፈተናዉን በመስራት ላይ እንገኛለን ።በየትኛውም ሰዓት ላይ አላህ ለኛ የመደበዉ ሰአት ይጠናቀቅና በድንገት የፈተናው ወረቀት ተስቦ ሊወስድብን ይችላል 😔😔 ስለዚህ የሌላን ሰዉ የፈተና ወረቀት ትተን በራሳችን የፈተና ወረቀት ላይ እናተኩር "" ፈተናዉን በአግባቡ ሰርተዉ ሽልማታቸዉ ጀነት ከሚሆኑ ሰዎች አላህ ያድረርገን ከእለታት በአንዱ ቀን እፈተናለዉ ብለን አስበን እንደማናውቅ ሁሉ በእለታት በአንዱ ቀን ደሞ ልንደሰት እንችላለን ብቻ በ አላህ ላይ የማያልቅ ተስፍ ይኑረን😊😊😊 💚💚ኢላሂ ያረብ.... ልባችንን ሚያሰጨንቁንን ጉዳዮቻችንን ወደ አንተ አስጠግተናል ስለምላሽህ ጥርጥር የለንም 😊😊😊😊 ሀጃዎቻችን ሚፈቱበት ዱአችን ተቀባይነት ሚያገኝበት ዉብ ጁመአ ይሁንልን 😊😊                                          መልካም ጁመአ💚💚                              Sumeya
نمایش همه...
4
👍
👎
😍
🥰