cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ethiopian Embassy in Rome

Official channel for the Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, Rome, Italy. Website: https://rome.mfa.gov.et

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 492
مشترکین
+124 ساعت
+307 روز
+12330 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
ለዲያስፖራው የቢዝነስ ክህሎት ስለጠና እየተሰጠ ነው፣ ========================= (ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም): በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት በጣሊያን ሮምና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ በኤምባሲው አዳራሽ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ነው። በሮም የኢፌዲሪ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አቶ አሰፋ አብዩ የስልጠናው መርሀ ግብር መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ዳያስፖራው ከሚኖርበት አገር የሚያገኘውን ሀብት፣ ልምድ እና ዕውቀት ተጠቅሞ ተደራጅቶም ሆነ በግሉ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢንቨስትመንት የሰጠውን ዕድል ለመጠቀም የሚያስችለውን ግንዛቤ እና የስራ ክህሎት የሚያገኝበት እንደሚሆን ገልጸዋል። በስልጠናው ወቅት የጣሊያን ኢንተርፕርነር ደጋፊ የሆኑት ሚስተር ቪንቸንሳ የተገኙ ሲሆን የጣሊያን መንግስት ኢንተርፕሪነርን ለማበረታታት ስራ እየሰራ መሆኑንና በዘርፉ ለሚሰሩ የስልጠናና መሰል ድጋፎች እንደሚደረግ ገልፀዋል። በስልጠናው ላይ በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፍ ላይ እየሰሩ የሚገኙ ታዳሚዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ለስራ እድል ፈጠራ እና ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ ሊያደርጉ የሚችሉ ዲያስፖራዎችን ማፍራት የሚያስችልና ለሌሎች ተሞክሮ የሚወሰድበት እንደሚሆን ይጠበቃል።
نمایش همه...
👍 3
ለዲያስፖራው የቢዝነስ ክህሎት ስለጠና እየተሰጠ ነው። ========================= (ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም): በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት በጣሊያን በሮምና አካባቢው ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በኤምባሲው አዳራሽ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ  ነው። የስልጠናው መርሀ ግብርን በንግግር የከፈቱት በሮም የኢፌዲሪ  ኤምባሲ ምክትል የሚሲዮን መሪ አቶ አሰፋ አብዩ ዳያስፖራው  ከሚኖርበት አገር የሚያገኘውን ሀብት፣ ልምድ እና ዕውቀት ተጠቅሞ ተደራጅቶም ሆነ በግሉ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢንቨስትመንት የሰጠውን ዕድል ለመጠቀም የሚያስችለውን ግንዛቤ እና የስራ ክህሎት የሚያገኝበት እንደሚሆን ገልጸዋል። በስልጠናው ላይ በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፍ የተሰማሩ  ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ለስራ እድል ፈጠራ እና ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ ሊያደርጉ የሚችሉ ዳያስፖራዎችን ማፍራት የሚያስችልና ለሌሎችም ተሞክሮ የሚወሰድበት እንደሚሆን ይጠበቃል::
نمایش همه...
የሚኒስትሮች ምክር ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎች #PMOEthiopia
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከሳይፕረስ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ። ===================== (ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም): ተቀማጭነታቸው በሮም ሆኖ በሳይፕረስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በሳይፕረስ ከሳይፕረስ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሆኑት  H.E Amb. Andreas S. Kakouri ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁትዮሽና የባለብዙ ወገን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በኒኮሲያ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል። በወቅቱም ክብርት አምባሳደር ደሚቱ በሁለቱን አገራት የቢዝነስ ማህበረብ መካከል ያለውን ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ እና ውጤታማ ግንኙነትን አውስተው፣  ግንኙነቱን በሌሎችም ዘርፎችም የበለጠ ለማጠናከር  የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል። በውይይታቸም በኢንቨስትመንትና በንግድ መስኮች በትብብር ለመስራት በቀጣይ የኢትዮጵያ-ሳይፕረስ የቢዝነስ ፎረም በጋራ ለማዘጋጀት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
نمایش همه...
👍 9
ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ከሳይፕረስ ኩባንያዎች የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፣ ============================ (ሰኔ 11 ቀን 2016): ተቀማጭነታቸው በሮም ሆኖ በሳይፕረስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በሳይፕረስ እያደረጉ ባለው የስራ ጉብኝት በሀገሪቱ በፋርማሲዩቲካል እና ኮንስትራክሽን ሴከትር ከተሰማሩ የሳይፕረስ ኩባንያዎች ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በወቅቱም ሜዶኬሚ(MEDOCHEMIE) ከተሰኘ በፋርማሲቲዩካል ዘርፍ ከቸሰማራው ኩባንያ የስራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የካምፓኒው ምርቶች በሀገራችን ገበያ ለበርካታ የሚታወቁ መሆኑን ገልጸው፣ በሀገራችን ፋብሪካውን በመገንባት በማምረት ስራ ቢሳተፍ ሀገራችን ካላት የህዝብ ቁጥር፣ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሁም ዘርፉ በሀገራችን ከሰተጠው ትኩረት አኳያ ተጠቃሚ እንደሚሆን አስረድተዋል። በተጨማሪም IACOVOU GROUP ከተሰኘ እና ትላልቅ የኮንስትራክሽን ግንባታ ፕሮጅቶች ላይ ከተሰማራው ድርጅት ኃላፊ ጋር በነበራቸው ውይይት ሀገራችን ፈጣን የኢኮኖሚያዊ እድገት አንጻር በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያለውን እድገት በዝርዝር አስረድተዋል። ኩባንያው በሀገራችን እንዲሰማራም ጠይቀዋል። የኩንያዎቹ የስራ ኃላፊዎችም ሀገራችን በተለያዩ ዘርፎች ያላትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንደሚረዱ ገልጸው፣ የቅድመ ኢንቨስትምንተ ጉብኝት በማድረግ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚስችላቸውን ሂደት ለመጀመር ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።
نمایش همه...
👍 4😁 1
ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ 34ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች https://www.facebook.com/share/p/2VwDrDYXGps1uij7/?mibextid=oFDknk
نمایش همه...
👍 4👎 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቤሳ ከጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ፣ ======================== (ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም): በጣሊያን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሐምቢሳ ከጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ከሆኑት ሚስተር ማርኮ ሪካርዶ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የልማት ትብብርን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። በወቅቱም ክብርት አምባሳደር ደሚቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ የልማት ትብብር ከሀገራችን የትኩረት መስኮችን ያማከለና ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አያይዘውም በሀገራችን በኩል ከጣሊያን በትብብር ለማከናወን የታቀዱ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ስለመኖሩ በዝርዝር አብራርተዋል። ሚስተር ማርኮ ሪካርደ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ዘርፈ ብዚ ትብብር ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰዋል። በቀጣይም በተለያዩ ዘርፎች የተጀመሩ ትብብሮች አጠናክሮ ለማስቀጠልና እና አዳዲስ የትብብር መስኮችንም ለማስጀመር ተቋማቸው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
نمایش همه...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
ምክክር ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል- ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት የምክክር አስፈላጊነትን አስመልክቶ በይፋዊ የማሀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ነው። ''ጦርነትን ኖረንበታል። የተወሰኑ ችግሮቻችንን ፈትተንበታል። አብዮትን ደጋግመነዋል። የተወሰኑ ችግሮችን ፈትተንበታል። በሁለቱም ያልተፈቱትን ችግሮች ለመፍታት የቀረን መንገድ ምክክር ነው። ምክክርን ግን አልተጠቀምንበትም። ጦርነትና አብዮት የተሟላ መፍትሔ የማያመጡት አሸናፊ እና ተሸናፊ ስለሚያስከትሉ ነው። ቢዘገይም የተሸነፈው ለማሸነፍ ይታገላል። ያሸነፈውም ድሉን ለመጠበቅ ይዋጋል። ምክክር ግን ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል። ከተሸነፍንም ሁላችንም ለሀገራችን ብለን ነው የምንሸነፈው። ይሄ የምክክር ሂደት ሦስት ነገሮች ያስገኝልናል። 1. ሁሉንም ባይሆን እንኳን ዋና ዋና ችግሮችን ይፈታል 2. ከጦርነት ይልቅ ምክክር ባህል እንዲሆን ያደርጋል 3. በተቃራኒ ኃይሎች መካከል መቀራረብና መግባባት ይፈጥራል። ይሄንን መቀራረብ በመጠቀምም ወደፊት በጉዳዮች እየተነጋገርን ለመቀጠል ያስችለናል። በመሆኑም ይኽንን እድል ሳናበላሽ ወደ ተሟላ ድል እንድናሸጋግረው እጠይቃለሁ።''
نمایش همه...
👍 6👎 1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.