cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አይናፋሯ_ሊና

" #አይናፋሯ_ሊና አዲስ ምርጥ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ታሪክ #አይናፋሯ_ሊና ታሪኮችና ወጎች የቴሌግራም ቻናል የቀረበ ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመዶ #ሼር ያድርጉ። #ይቀላቀሉን👇 https://t.me/lovelife_channel

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
501
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓           ". #አይናፋሯ_ሊና ".#P18              ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ ┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛            ┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒ .  በ https://t.me/newlatif1227የቀረበ         . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ. ┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚ ┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯    #ክፍል_አስራ_ሰባት {⓱} ┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷ ወሬያቸውን ለመጀመር  ተዘጋጁ  ዝም ተባብለዋል ሊና እሱ ያወራ ዘንድ  በጉጉት እየጠበቀች ነው  እሱም ቆይ አታወራም እንዴ  እጃቸውን እንደተያያዙ ነው   አልተላቀቁም አሁንም ጥብቅ አርጎ ይዟታል  ግን አያወሩም የፍርሀት አለም   ኡመር ቤቱ ውስጥ ጋደም ብሏል ስራ አልገባም በቃ ራሱን እየወቀሰ ነው ኡመር እንዲህ አልነበርክም አላህ ይቀጣሀል አንድ ተራ ሴት ወደህ እንዲህ ትሆናለህ ሀ ማቆም አለብህ ከዚህ በኋላ ቆንጂየው ወጣቱ ጠንካራው ኡመር ይመለሳል አዎ እጆቹን አቆላለፋቸውና በሀሳብ ርቆ ሄደ  ረሚዝ ቆይ ኢብራ የት ሄዶ ነው ዛሬ እህ ላይብረሪ ገብቶ ይሁን ቢሆንስ ሳይነግረኝ ለማንኛውም እዚሁ ልጠብቀው ሰአቱ አለቀ ምሳ ሰአት ተደወለ ምንም ሳያወሩ እሱ እሷን ሲጠብቅ እሷም በተመሳሳይ እሱን ስትጠብቅ ሰአቱ ሄደ የደውል ጥሪው ሲያሰማቸው ተነሱ   አሁንም ዝም እንደተባባሉ ነው እጃቸውን አልተላቀቁም   የሆነ የሚያምር መድረክ ላይ  ቤተሰብ ተሰብስቦ ብዙ ሰው ኗራ ውዱ ባሏ ኢብሮ እጇን ይዟት የሙሽራ ቀሚሷን አርጋ  እያጨበጨቡላት  ስታልፍ ሊና ይሄን   እያሰበች ክፍል ደረሰች   እንደ አጋጣሚ ሆኖ  አስተማሪ ገብቷል ደሞ ፈተና ነው እየፈሩ ለመግባት ወሰኑ መያያዛቸውን ረስተውታል እንደተያያዙ ወደ ክፍል ዘለቁ .. . . ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ ╬╬═════════════╬╬     #ክፍል_አስራ_ስምንት {⓲}            .....ይቀጥላል...... ╬╬═════════════╬╬ ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤     https://t.me/newlatif1227የቀረበ ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
نمایش همه...
┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓           ". #አይናፋሯ_ሊና "👉#P17.              ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ ┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛            ┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒ .  በ https://t.me/newlatif1227የቀረበ .         . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ. ┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚ ┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯   #ክፍል_አስራ_ስድስት {⓰} ┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷ ...ማውራት አለብን 🧕ስለምን? ...ስለ እኛ. ስለ እኔና ስላንቺ ፈርታለች ልቧ እየመታ ነው ግን አብራው  መሆን ትፈልጋለች::  ግን ምናልባት እሱ አብረን መሆን አንችልም ሊለኝ ቢሆንስ አይ :አይ ሊሆን አይችልም ግን እኔን አቁመሺኝ የት ሄድሽ? ጥያቃው ከሀሳቧ አነቃትና እሺ አናውራ... ፈርታለች እሱም ቢሆን ማታ ሲለማመድ ነበር ምክኒያቱም እሱም ማውራት አይደፍርም በዚያ ላይ ሴት ይፈራል መቼ?? 🧕እኔንጃ መቼ ይሁን?? ጥያቄውን በጥያቄ መለሰች ከቻልሽ አሁን ምሳ ሰአት ስለሆነ እ እሺ ቁርጧን ማወቅ እንዳለባት ወስናለች በቃ እንሂድ ታች ብንወርድ ለማውራትም ጥሩ ይመቻል አይመስልሽም 🧕ልክ ነህ እንውረድ ፈርቷል ቆመ እጇን ሊይዛት አስቦ ነበር ግን ፈራ ኧረ ተው ከራሱ ጋር ለደቂቃዎች ታግሎ እጇን ያዛት ጥብቅ አርጎ ነው የያዛት  የሆነ የምትሄድበት ወይም ከሰማይ የሆነ መልዐክ ወርዶ የሚነጥቀው ነው የሚመስለው  በትምህርት ቤቱ ውስጥ ብዙ couple አሉ እጅ ለእጅ መያያዝ የሚካበድ አይደለም ሊና እጇን ከመያዙ በላይ ጥብቅ ማድረጉ ገርሟታል እሷም ያዘችው እንደተያያዙ ከክፍል ወጡ ከክፍላቸው ፊት ለፊት ያለውን ደረጃ መውረድ ሲጀምሩ  የክፍላቸው ተማሪ የሆኑት አብረሀምና ኢዘዲን ድምፃቸውን ከፍ አርገው መሳቅ ጀመሩሀ...ሀ...ሀሀ   አብረሀም አስከትሎ በስመአብ "ድስት ግጣሙን አያጣም " ይሉሀል ይሄ ነው ዋው ግን ይደነቃል  ኢዘዲን የአብረሀምን ንግግር ሳያስጨርስ ጣልቃ በመግባት ኧረ ያምራል ማዘር ትሙት ያሳካላችሁ ውለዱ ክበዱ አለ አብረሀም በእግሩ መንገድ ዘግቶባቸዋል  አስከትሎም አይ ኢዙ የምን መውለድ  "ምንም ቢዋደዱ ቢመስሉ ጨረቃ የተማሪ ፎንቃ መጨረሻው ጭቃ" ሲባል አልሰማህም ኢብሮ ተናደደ አሳልፈኝ ሰውዬ  ባላሳልፍህስ? አሳይሀለዋ ብሎ ሲጠጋው አሳለፈው እንደተያያዙ ወረዱ ሊናና ኢብሮ የሚሰማቸው ስሜት ተመሳሳይ ነው ፍርሀት ግን ደስ የሚል ነገር... ካሰቡት ቦታ ተቀመጡና ወሬያቸውን ለመጀመር ተዘጋጁ... . . . ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ ╬╬═════════════╬╬       #ክፍል_አስራ_ሰባት {⓱}            .....ይቀጥላል...... ╬╬═════════════╬╬ ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤        https://t.me/newlatif1227 ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
نمایش همه...
አይናፋሯ_ሊና

" #አይናፋሯ_ሊና አዲስ ምርጥ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ታሪክ #አይናፋሯ_ሊና ታሪኮችና ወጎች የቴሌግራም ቻናል የቀረበ ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመዶ #ሼር ያድርጉ። #ይቀላቀሉን👇

https://t.me/lovelife_channel

👍 5 3
┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓           ". #አይናፋሯ_ሊና "➔.#P16              ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ ┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛            ┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒ .  በ https://t.me/newlatif1227የቀረበ .         . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ. ┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚ ┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯   #ክፍል_አስራ_አምስት {⓯} ┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷ ...ስትታገለው ኢብሮ አየ ቆይ በፍቅረኛሞች መሀል መግባት የለብኝም  ብሎ አሰበ ግን እኮ እጇን እያሳመማት በቃ ሄጄ ሁኔታውን ላረጋግጥ ወደነሱ ቀረብ ብሎ ሊና ችግር አለ አላት  ኡመርም ኢብሮን ችላ ብሎ አውቃለሁ እየረበሽኩሽ ነው ግን በጣም ስለምወድሽ ነው ማለት እኔ መጀመሪያ ያፈቀርኩሽ ሴት ስለሆንሽ ነው ሊኑ ይቅርታ አዎ እሱን ፍቅረኛዬ ነው ብለሸኝ ነበር ግን ከኢብራሂም ልወስድሽ ነበር ያሰብኩት በቃ ደግሜ አልረብሻችሁም ወደ ኢብሮ ዞረና ኢብሮ የባለፈው ነገር ፀፅቶኛል ፍቅርን በሀይል ማግኘት እንደማይቻል ተረድቻለሁ እኔ መጥፎ ሰው አልነበርኩም ሊና የምታፈቅርህ አንተን ነው ፍቅረኛዬ ኢብሮ ነው ራቅ ከኛ ብላኝ ነበር እኔ ግን  ገልብጬ ነገርኩህ ኢብሮ በቃ ይቅርታ ሊና ደግሜ በህይወትሽ አልገባም ግን በጣም አፈቅርሻለሁ ወደ መኪናው ገባ እምባው መቷል ግን ይዞታል ልቡ ሲሰበር እየተሰማው ነው እንደምንም ብሎ ለመቆጣጠር እየሞከረ ነው ቀጥታ ወደ መስጂድ ነዳው ኢብራሂም የሰማው ነገር አስደንግጦታል ሊና በተለይ አፍራለች ሊና ብሎ ቀና ሲል እንደምታፈቅረው ስላወቀ የሆነ ነገር የሚላት መስሏት ቻው በቃ ብላው ሄደች ኢብሮ ፈገግ እያለ ወደ ቤቱ ሄደ  ገና ከመግባቱ ልብሱን ቀይሮ ሊወጣ ሲል ኢባ መክሰስ አትበላም አለች እናቱ አልበላም ማማ በቃኝ ምላሿን ሳይሰማ ወጣ ረሚዝ ጋር አንድ ሰፈር ናቸው  ደውሎለት ተገናኙ ከዛም ረሚዝ surprise ምን ተገኘ?? ሊና ታፈቅረኛለች  ልክ እኔ እንደማፈቅራት ረሚዝ ልክ እኔ እንደማፈቅራት ሲል ደነገጠ ኢባ ታፈቅራታለህ ከዛም  ደነገጠ ማ እኔ ኧረ በፍፁም ረሚዝም ድብቅ ነህ  ግን በጣም ኢባ ድብቅነት እኮ አይደለም በቃ እኔ እፈራለሁ ታውቅ የለ ረሚዝም ግን ኢብሮ ሊና ዝምተኛነትህን የምትወደው  ይመስልሀል    አዎ ይመስለኛል ብዙ ሴቶች የሚወዱት ዝምተኛነቴን  አይደል አው እሱማ ግን እኔ አትቀየመኝና ሁለታችሁም ዝምተኛ ስትሆኑ ልጃችሁ ዲዳ የሚሆን ነው የሚመስለኝ ሀሀሀሀሀ ተሳሳቁ ዛሬ ትምህርት ቤት ለመሄድ ኢብሮ ጓግቷል ሊና ግን ፈርታለች ግን ላትቀር ወስና ሄደች ተምረው ምሳ ሰአት እንደደረሰ ልትወጣ ስትል እጇን ያዛትና ማውራት አለብን አላት... . . ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ ╬╬═════════════╬╬     #ክፍል_አስራ_ስድስት {⓰}            .....ይቀጥላል...... ╬╬═════════════╬╬ ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤         https://t.me/newlatif1227 ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
نمایش همه...
አይናፋሯ_ሊና

" #አይናፋሯ_ሊና አዲስ ምርጥ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ታሪክ #አይናፋሯ_ሊና ታሪኮችና ወጎች የቴሌግራም ቻናል የቀረበ ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመዶ #ሼር ያድርጉ። #ይቀላቀሉን👇

https://t.me/lovelife_channel

👍 2 2
🛑#ሩሲያዊቷ_ሱመያ 👉#P9 🛑««ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ »» 🛑(ፅሁፍ✍፡ ፍሮምሲስ አወል) 🛑አቅራቢ😎፡ ማሜ 🛑#ክፍል_9 አሻግሬ የባለቤቴን ፊት አየሁኝ ፡፡ ወደግራና ቀኝ ትመለከታለች፡፡ ፊቷ ቀልቷል፣ ቆዳዋ በልዟል፡፡ልብሷ በደም ተጨማልቋል፡፡ በጣም ጎድተዋታል፡፡ሁኔታዋ አስደነገጠኝ፡፡አሳዘነችኝ ፡፡ ፈጠን ብዬ ወደ በሩ ቀረብኩኝ፡፡በቅርበት ሁኜ ለረጅም ጊዜ ተመለከትኳት፡፡ፊቷ ቆሳስሏል፡፡ከእጅና እግሯ ደም ይፈሳል፡፡ ልብሷም ተበጣጥሷል፣ እራፊ ጨርቅ ብቻ ነው የሚታይባት፡፡ እጅ ና እግሯ በሰንሰለት ታስሯል፡፡ሳያት አለቀስኩ ፡፡ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ድምፄን ከፍ አርጌ  ጠራዋት፡፡ ስጠራት ወደኔ ዞረች ስቃይዋን እየቻለች ኻሊድ ሆይ !!ስማኝ አለችኝ፡፡"ኻሊድ ስለኔ አታስብ ፡፡እኔ በቃሌ እንደፀናው ነኝ፡፡ከአላህ  በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን መሰክራለሁ ::አሁን እኔን የሚያገኘኝ ስቃይ  ነቢያችንን የአላህ መልዕክተኛ ፣ሰሀቦችን ፣ ታቢኢዮችን ካገኘው አንፃር ምንም ማለት አይደለም፡፡ ኻሊድ ሆይ! "ኻሊድ ሆይ በኔና በቤተሰቦቼ መሀል አትግባ፡፡አሁን ቶሎ ሂድ፡፡እዚያው ክፍልህ ጠብቀኝ ፡፡ኢንሻአላህ እመጣለሁ፡፡ነገር ግን በደንብ ዱአ አብዛ ፣ ሰላት ,የሌሊት ሰላት አብዛ አደራ" አለችኝ :: ውስጤ በቁጭት እየነደደ ወደ ክፍሌ ሄድኩኝ፡፡ቀኑን ሙሉ ጠበኩአት ፡፡መምጣቷን እየናፈኩ ቆየሁ ተጨማሪ ቀን አለፈ፡፡ ሶስተኛ ቀንም እንዲሁ አለፈ፡፡ መሸ፡፡በዚ ሁኔታ ላይ እያለሁ ድንገት የክፍሌ በር ተንኳኳ፡፡ደነገጥኩ፡፡ማን ይሆን?ያረፍኩበትን አውቀው ሊገሉኝ መተው ይሆን?በሰኮንዶች ቅፅበት ብዙ ነገር ውስጤ ተመላለሰ፡፡የሞት ፍርሀት ፈራሁ፡፡በመሀከላችን ያለው ርቀትም የጠበበ መሰለኝ፡፡ የሞት ሞቴን "ማነው?" አልኩኝ፡፡ "እኔ እገሌ ነኝ ክፈትልኝ"ረጋ ያለው የባለቤቴ ድምፅ ነው፡፡ክፍሌ ፣ ተስፋዬ በብርሃን ተሞላ፡፡ በሩን ከፈትኩላት፡፡ቆሳስላለች ፡፡ተጎሳቁላለች፡፡ ቁና ቁና እየተነፈሰች ወደ ውስጥ እንደገባች "በል ቶሎ እንሂድ እንውጣ!" አለችኝ፡፡በዚህ ሁኔታሽ ላይ ሆነሽ ወዴት አልኳት ፡፡ዝም አለችኝ... #ክፍል_10_ይቀጥላል.. SHARE👇👇👇SHARE https://www.facebook.com/profile.php?id=100064370604661
نمایش همه...
እውነታ

እውነታ, Addis Ababa, Ethiopia. 4,854 likes · 20,066 talking about this. 📗📙📕 (በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።) 👇 Telegram-

https://t.me/ewntamedia

🛑#ሩሲያዊቷ_ሱመያ 👉#P8 🛑ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ 🛑(ፅሁፍ✍፡ ፍሮምሲስ አወል) 🛑አቅራቢ😎 :ማሜ 🛑#ክፍል_8 ተነሳሁና የቻልኩትን ያህል ሰገድኩ፡፡ተመልሼ ተኛሁ፡፡እሷ ግን በሰላቷ ቀጠለች፡፡በነቃው ቁጥር ሩኩዕ ላይ፣ ሱጁድ ወርዳ ፣ቆማ ዱአ ስታረግ ፣ስታለቅስና ስትማፀን አያታለሁ፡፡ፈጅር እስኪወጣ እስኪወጣ ድረስ በዚሁ ሁኔታ ቆየች፡፡ ከዚያ ቀሰቀሰችኝ፡፡"በል ተነስ ሱብሒ ደርሷል፡፡አብረን እንስገድ ፡፡" አለችኝ፡፡ ሰገድን ጥቂት ተኛች፡፡ ፀሀይ ስትወጣ በል ወደ ፓስፓርት ጣቢያው እንሂድ ከ አለችኝ፡፡ "እንዴ ....ወዴት ?ምን ልናረግ?በምን መረጃ ..የታለ ፎቶው? አልኳት፡፡ "ሄደን እንሞክር" አለችኝ ።ከአላህ እዝነት ተስፋ ለምን እንቁረጥ አለችኝ፡፡ ሄድን፡፡ወላሂ ጣቢያው ግቢ እንደገባን በለበሰችው ኒቃብ እሷ መሆኗን እንዳዐ ወቁ አንደኛው ሰራተኛ "አንቺ እገሌ ነሽ አይደል? አላት፡፡"አዎን" አለችው፡፡ "በይ ፓስፖርትሽን ውሰጂ ተሰርቶልሻል አላት፡፡ ስታየው ከነ ሒጃቧ በሰጠችው ፎቶ ተሰርቶላታል፡፡ ደስ አላት፡፡"አላህን ለሚፈራ ሰው እሱ መውጫ ያበጅለታል፡፡ አላልኩህም ወይ !"አለችኝ፡፡ ለመውጣት ስንንደረደር አንደኛው ሰራተኛ "ወደ መጣችሁበት ሀገር ሄዳቹ ምህተም ማስመታት አለባቹ " በማለት አሳሰበን፡፡ ወደ ትውልድ ከተማዋ ተመለስን፡፡እኔም በውስጤ ቤተሰቧን ለመጠየቅ ይህ የመጨረሻ እድሏ ነው ፡፡አልኩኝ፡፡ከትንሿ ከተማ ደረስን፡፡ ማረፍያ ቤት ተከራይተን አረፍን፡፡ማህተም አስመታን ፡፡ ከዚያም ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ብለን ተንቀሳቀስን ፡፡ደርሰን በሩን አንኳኳን፡፡ቤታቸው ያረጀና እዚ ግባ የማይባል ነው፡፡ድህነት በአከባቢው ነዋሪዎች ላይ ይንፀባረቃል፡፡ታላቅ ወንድሟ በሩን ከፈተልን ፡፡ወጣትና ፈርጠም ያለ ጎረምሳ ነው፡፡ስታገኘው እጅግ ደስ አላት፡፡በፈገግታ ፊቷን ገልጣ መደሱ ሄደች፡፡ሰላምታ አቀረበችለት ፡፡እሱ ግን ገና እንዳያት ፊቱ ተቀያየረ... #ክፍል_9_ይቀጥላል... 👇👇𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚊𝚗𝚍 𝚜𝚑𝚊𝚛𝚎👇👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064370604661
نمایش همه...
እውነታ

እውነታ, Addis Ababa, Ethiopia. 4,854 likes · 20,066 talking about this. 📗📙📕 (በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።) 👇 Telegram-

https://t.me/ewntamedia

👇#ለጥንቃቄበደንብያንብቡት!!! Share,,,share ❌እውነተኛ ታሪክ🔞 አንዲት ሴት በጣም፡የምትወደው የቤት እንስሳ አድርጋ የምትከባከበው አንድ እባብ ነበራት። ርዝመቱ ወደ ሁለት ሜትር ከግማሽ ይሆናል ከተወስኑ ቀናቶች ጀምሮ ግን እባቡ ምግብ መመገብ ስላቆመ እንዲመገብ ብዙ ጥረት ብታደርግም ስላልተሳከላት ተጨንቃ ወደ እንስሳት ሀኪም ይዛው ትሄዳለች ከዛም የእንስሳቱ ሀኪሙ የተወሰኑ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመረ። ከቅርብ ጊዜ ወዲያ እባቡ እንዴት ነው የሚተኛው? ሴቲቱም መለስች። ከምኝታዬ ስነቃ አንድ ከጎኔ ሙሉ በሙሉ ተዘርግቶ ተኝቶ አገኘሁት። ሌላ ቀን ደግሞ ራሱን በግርጌዬ አድርጎ ዝርግትግት ብሎ ተኝቶ አገኘሁት ምኑም ስላልገባኝ ልረድው አልቻልኩም ትላላች ። ሀኪሙም በጣም ከተገርመ በኃላ እርስዋ አደጋ ላይ እንደሆነችና እባቡን ለእንስሳ ማርቢያ ጣብያ እንድትሰጠው መከራት። እባቡ መመገብ ያቆመው ሆዱን ባዶ ለማድረግ ሆዱ ውስጥ ስፊ ቦታ እንዲኖረው ለማድረግ ነው ። በተለያዩ እቅጣጫዎች ተኝቶ የምታገኝውም አንቺን እንዴት አድርጎ እንደሚውጥሽ ልክሽን እየለካ ነው።አላት ሁሉም ፍቅር ፍቅር አይደለም። ሁሉም ጓደኛ ጓደኛ አይደለም። ልዩነቱን እናስተውል። ጠላት ወዳጅ መስሎ ሊቀርብክ ይችላል።ትህትና ርህራኤ ሊያሳይክ ይችላል። ግን በጥንቃቄ እንመርምር ምክንያቱም ወዳጃችን መስሎ ደካማ ጎናችን እያጠና ወይም እንዴት አድርጎ ሊያጠፋን እንደሚችል በፍቅር ስም ጉድጓዳችንን እየማስልን ሊሆን ይችላልና የሚቀርባችሁን ሰው መርምሩ ከህይወት ትምህርት ውሰዱ። ሰው ሲጠላን ብቻ ሳይሆን ሲወደንም ለምን ብለን እንጠይቅ? ??? አስተማሪ ስለሆነ በየ ጉሩፑ ሼር ፔጁን ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ #ከደራሲያንአለምፔጅ✔
نمایش همه...
🛑#ሩሲያዊቷ_ሱመያ >>>#P7 🛑««ሙሉ በሙሉ እውነተኛ»» 🛑(ፅሁፍ✍፡ ፍሮምሲስ አወል 🛑አቅራቢ😎:ማሜ 🛑#ክፍል_7 በሰላም መመለሷ ያስደሰተው ቢመስልም ሙሉ አካሏን በሚሸፍነው ልብሷ ግን ሳይገረም አልቀረም፡፡በፈገግታ ተሞልታ ወንድሟን አቅፋ ወደ ቤቱ ዘለቀች፡፡ከኃላዋ ተከትዬ በመግባት ብቻዬን ሳሎን ውስጥ ተቀመጥኩኝ፡፡ እሷ ወደ ውስጥ ዘለቀች፡፡በሩሲያ ቋንቋ ታወራቸዋለች፡፡ሚያወሩትን ማወቅ አልቻልኩም፡፡በሂደት ግን ድምፃቸው ከፍ እያለ መጯጯህ ጀመሩ፡፡ሁሉም በዚህ እና በዚያ እየጮሁ ያዋክቧት ጀመር፡፡ሁኔታው አላማረኝም፡፡የሚሉትን በርግጠኝነት አላወኩም ምንም ማረግ አልቻልኩም ፡፡ በሂደት ድምፁ እኔ ወዳለሁበት ክፍልእየቀረበ መጣ፡፡አንድ ጎረምሳ ሰው ከፊት ሆኖ ሶስት ወጣቶች ወደኔ እየጦቀሙ መጡ፡፡ መጀመርያ አስቤ የነበረው ያቀረብኩትን የጋብቻ ጥያቄ ይቀበሉኛል ብዬ ነበር፡፡ሆኖም ግን ወድያው እንደ አውሬ ሰፈሩብኝ፡፡በቅፅበት ቡጢ ፣ ጥፊ ፣ እርግጫ ....አከታትለው አሳረፉብኝ፡፡ለመከላከል ሞከርኩኝ ፡፡ሰዎች እንዲደርሱም ጮውኩ ፡፡ማንም የደረሰልኝ አልነበረም፡፡ በመጨረሻም ደክሞኝ ወደኩኝ፡፡ይህ ቤት ለህይወት ዘመኔ የመጨረሻዬ ነው ብዬ አሰብኩ፡፡ዱላው በዛብኝ፡፡ ለመሸሽ አሰብኩና በአይና የገባሁበትን በር ማፈላለግ ጀመርኩ፡፡በሩን እንዳስተዋልኩ ወድያው ሩጨ ወጥቼ ማምለጥ ቻልኩ፡፡ተከትለው አሳደዱኝ፡፡በአከባቢው ብዙ ሰው ስለነበር በሰዎች መሀል ገብቼ ተሰወርኩባቸው፡፡ከዚያም ትንሽ አርፌ ወደነበርኩበት ማረፊያ ሄድኩኝ፡፡ከቤቱ ብዙ አይርቅም፡፡ክፍሌ ገብቼ የደረሰብኝን ማየት ጀመርኩ፡፡ጥርሴና ከንፈሬ ደምቷል፡፡ፊቴ በደም ተለውሷል፤ልብሴ ተበጣጥሷል፡፡ ታጠብኩኝ፡፡ከነዛ አውሬዎች ያስመለጠኝን ከላህ አመሰገንኩ ፡፡ ወድያው ደግም የባለቤቴ ጉዳይ በሀሳቤ መጣብኝ፡፡እንዴት አድርገዋት ይሆን ፊቷ ድቅን አለብኝ፡፡እኔን በደበደቡበት ሁኔታ ይደበድቧት ይሆን!እኔ መቋቋም ያልቻልኩትን ዱላ እሷ በሴት አቅሟ እንዴት ትችላለች፡፡ሚስኪን ባለቤቴ፡፡ በዱላ ብዛት እጅ እንዳትሰጥ እና አቋሟን እንዳትለውጥ ሰጋሁ፡፡ ከሷ ከተለየሁበት ጊዜ ጀምሮ ሸይጧን ስራውን መስራት ጀመረ፡.. #ክፍል_8_ይቀጥላል... SHARE👇👇👇SHAR https://www.facebook.com/profile.php?id=100064370604661
نمایش همه...
እውነታ

እውነታ, Addis Ababa, Ethiopia. 4,854 likes · 20,066 talking about this. 📗📙📕 (በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።) 👇 Telegram-

https://t.me/ewntamedia

🛑#ሩሲያዊቷ_ሱመያ 👉#P6 🛑ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ 🛑(ፅሁፍ✍፡ ፍሮምሲስ አወል) 🛑አቅራቢ😎 :ማሜ 🛑#ክፍል_6 ተነሳሁና የቻልኩትን ያህል ሰገድኩ፡፡ተመልሼ ተኛሁ፡፡እሷ ግን በሰላቷ ቀጠለች፡፡በነቃው ቁጥር ሩኩዕ ላይ፣ ሱጁድ ወርዳ ፣ቆማ ዱአ ስታረግ ፣ስታለቅስና ስትማፀን አያታለሁ፡፡ፈጅር እስኪወጣ እስኪወጣ ድረስ በዚሁ ሁኔታ ቆየች፡፡ ከዚያ ቀሰቀሰችኝ፡፡"በል ተነስ ሱብሒ ደርሷል፡፡አብረን እንስገድ ፡፡" አለችኝ፡፡ ሰገድን ጥቂት ተኛች፡፡ ፀሀይ ስትወጣ በል ወደ ፓስፓርት ጣቢያው እንሂድ ከ አለችኝ፡፡ "እንዴ ....ወዴት ?ምን ልናረግ?በምን መረጃ ..የታለ ፎቶው? አልኳት፡፡ "ሄደን እንሞክር" አለችኝ ።ከአላህ እዝነት ተስፋ ለምን እንቁረጥ አለችኝ፡፡ ሄድን፡፡ወላሂ ጣቢያው ግቢ እንደገባን በለበሰችው ኒቃብ እሷ መሆኗን እንዳዐ ወቁ አንደኛው ሰራተኛ "አንቺ እገሌ ነሽ አይደል? አላት፡፡"አዎን" አለችው፡፡ "በይ ፓስፖርትሽን ውሰጂ ተሰርቶልሻል አላት፡፡ ስታየው ከነ ሒጃቧ በሰጠችው ፎቶ ተሰርቶላታል፡፡ ደስ አላት፡፡"አላህን ለሚፈራ ሰው እሱ መውጫ ያበጅለታል፡፡ አላልኩህም ወይ !"አለችኝ፡፡ ለመውጣት ስንንደረደር አንደኛው ሰራተኛ "ወደ መጣችሁበት ሀገር ሄዳቹ ምህተም ማስመታት አለባቹ " በማለት አሳሰበን፡፡ ወደ ትውልድ ከተማዋ ተመለስን፡፡እኔም በውስጤ ቤተሰቧን ለመጠየቅ ይህ የመጨረሻ እድሏ ነው ፡፡አልኩኝ፡፡ከትንሿ ከተማ ደረስን፡፡ ማረፍያ ቤት ተከራይተን አረፍን፡፡ማህተም አስመታን ፡፡ ከዚያም ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ብለን ተንቀሳቀስን ፡፡ደርሰን በሩን አንኳኳን፡፡ቤታቸው ያረጀና እዚ ግባ የማይባል ነው፡፡ድህነት በአከባቢው ነዋሪዎች ላይ ይንፀባረቃል፡፡ታላቅ ወንድሟ በሩን ከፈተልን ፡፡ወጣትና ፈርጠም ያለ ጎረምሳ ነው፡፡ስታገኘው እጅግ ደስ አላት፡፡በፈገግታ ፊቷን ገልጣ መደሱ ሄደች፡፡ሰላምታ አቀረበችለት ፡፡እሱ ግን ገና እንዳያት ፊቱ ተቀያየረ... #ክፍል_7_ይቀጥላል... 👇👇𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚊𝚗𝚍 𝚜𝚑𝚊𝚛𝚎👇👇
نمایش همه...
🛑#ሩሲያዊቷ_ሱመያ👉 #p5 🛑««ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ ሳይቀነስ 🛑ሳይጨመር የሚቀርብ ታሪክ »» 🛑(ፅሁፍ✍፡ ፍሮምሲስ አወል) 🛑አቅራቢ😎:ማሜ 🛑#ክፍል_5 ከዚያም ወደ ባለቤቴ ቀና በማለት የዚህ ፓስፓርት ፎቶው የሷ መሆኑን በምን ላውቅ እችላለሁ? አለ ለማመሳከር ፈልጎ ፊቷን ገልጣ እንድታሳየው ያሰበ ይመሰላል፡፡"ላንተ ፊቴን አልገልጥም፡፡ሴት ሰራተኞቾ ካሉ ሊያዩኝ ይችላሉ፡፡ አለችው ባለቤቴ፡፡በዚህን ጊዜ ሰውዬው ክፍኛ ተቆጣ፡፡ የድሮውን ፓስፓርት ፣ፎቶዎቹንና ሌሎቹን ሰነዶች ጨምሮ ወደ ራሱ የማስቀመጫ ቦታ ወረወራቸው፡፡ ትክክለኛውን የፓስፓርት ፎቶ ይዘሽ ካልመጣሽ በስተቀር ከአሁን በኃላ የበፊቱንም ሆነ አዲስ ፓስፓርት አይኖርሽም፡፡ አላት፡፡ ባለቤቴ ከሱ ጋር በማውራት ልታሳምነው ጣረች ፡፡በሩሲያኛ ነበር የሚያወሩት ፡፡ባለቤቴ ተናዳለች፡፡ ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኛል፡፡ ሀላፊው ከያዘው አቋሙ የሚመለስ አይመስልም ፡፡  በፍፁም አይሆንም አለ ፡፡እሷም ተስፋ ሳትቆርጥ ተከራከረች፡፡ ጠብ ያለላት ነገር የለም፡፡ ለጥቂት ጊዜ ዝም ብላ ቆመች፡፡ ወደሷ ጠጋ አልኩኝ፡፡ አላህ ነፍስን ከምትችለው በላይ አያስገድዳትም ፤ችግር ላይ መሆናችንን ልብ በይ፡፡ በዚህ መልኩ የምንጉላላው እስከ መቼ ነው?  አልኳት፡፡ "አላህ እሱን ለሚፈራ ሰው መውጫ ያበጅለታል ፤ባላሰበውም በኩል ሲሳዮን ይለግሰዋል፡፡" አለች፡፡ እዚያው ሆነን ከኔ ጋር ብዙ ተከራከርን፡፡የጣቢያው ሀላፊ በሁኔታችን ተቆጣና እንድንወጣለት አስገደደን፡፡ወጣን፡፡ደክሞናል፡፡ በአንድ በኩል ስታሳዝነኝ በሌላ በኩል አናዳኛለች፡፡ተቀምጠን በሰፊው እንድናወራ በማሰብ ወደተከራየነው ክፍላችን አመራን፡፡እኔ ላሳምናት እጥራለሁ፡፡ እሷም ልታሳምነኝ ትሞክራለች፡፡ዕለቱ መሸ ፡፡ዒሻ ሰገድን ፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ በሀሳብ ተወጥሬያለሁ፡፡ርቦን ስለነበር ያገኘነውን በላን፡፡ለመተኛት ብዬ ራሴን ከትራስ ጋር አገናኘው፡፡ ለመተኛት ማሰቤን ስታይ ፊቷ ላይ ቁጣ አነበብኩኝ፡፡ወደኔ ዞረችና "ኻሊድ ትተኛለህ?የ አለችኝ፡፡"አዎን ደክሞኛል እኮ "አልኳት፡፡"ሑብሀን አላህ የምትገርም ነህ ፡፡በዚ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለን መተኛት ታስባለህ?በዚህ ሁኔታ ውስጥ እኮ መተኛት ሳይሆን ወደ አላህ (ሱ.ወ) መጠጋት፤ ወደሱ ፊታችንን ማዞር ነው  ያለብን፡፡በል ተነስና አላህን እንለምን እሱ ነው የሚሻለን፡፡"አለችኝ፡፡ #ክፍል_6_ይቀጥላል..... 👇SHARE👇👇👇SHARE👇
نمایش همه...
👍 1
#ሩሲያዊቷ_ሱመያ 👉#P4 ««ሙሉ በሙሉ እውነተኛ»»     (ፅሁፍ✍፡ ፍሮምሲስ አወል) #ክፍል_4 ብቻዋን መሄድም አልፈለገችም::የሩሲያ የአየር መንገድ አውሮፕላን የሆነውን ተሳፈሩ፡፡ከነ ኒቃቧ ነበር የተሳፈረችው፡፡ ከባሏ ጎን ኩራት እየተሰማት ተቀመጠች፡፡ ኻሊድ "በሂጃብሽ የተነሳ ችግር እንዳይገጥመን እፈራለሁ፡፡" አላት፡፡ እሷም "ሱብሀን አላህ! እነዚን ኢ-አማንያን እንድታዘዝና በአላህ እንድክድ ትፈልጋለህን? ወላሂ ፈፅሞ አይሆንም፡፡ አላደርገውም፡፡ ያሉትን ይበሉ፡፡" አለችው፡፡ ሰዎች በግርምት ወደሷ ይመለከታሉ ፡፡አስተናጋጆች ምግብ ማቅረብ ጀመሩ፡፡ ከምግቡ ጋር መጠጥ ይቀርብ ነበር፡፡ የጠጡት ሞቅ እያላቸው ሲሄድ መናገርና እሷን በነገር መውጋት ጀመሩ፡፡ ከዚህም ከዚያም ያሾፉባት ጀመር፡፡ አንዱ ይሳለቃል ፣ሌላው ይስቃል ፣ ሌላው ያላግጣል፡፡አጠገቧ ቆመው ስለሷ ያወራሉ ፣ያጣጥላሉ፡፡ ኻሊድ ይመለከታቸዋል፡፡ ሆኖም ግን በራሳቸው ቋንቋ ያወሩ ስለነበር የሚሉት አይገባውም ፡፡ እሷ ግን እየሰማች እና፡እየሳቀች የሚሉትን ትተረጉምለታለች፡፡ በዚህን ጊዜ ኻሊድ ተቆጣ፡፡ እሷ ግን እንዲረጋጋ መከረችው፡፡"አይዞህ አትዘን ፤ አትጨናነቅ፡፡ሶሐቦችን ካገኛቸው ችግር አንፃር ሲታይ ይሄ በጣም ቀላል ነገር ነው፡፡" አለችው፡፡ እሷም ባሏም ትዕግስትን መረጡ፡፡ በመጨረሻም የተሳፈሩበት አውሮፕላን አረፈ፡፡ ኻሊድ እንዲህ ይላል፡- ሩሲያ ስንደርስ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት በመሄድ እነርሱ ዘንድ ቀናትን ቆይተን ጉዳያችንን ጨርሰን የምንመለስ ነበር የመሰለኝ፡፡የሚስቴ ሀሳብ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነበር፡፡ እንዲህ አለችኝ፡- "ቤተሰቦቼ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ሀይማኖታቸውን በጣም ያጠብቃሉ ፡፡አሁን እነሱ ዘንድ መሄድ የለብንም፡፡ማረፊያ ቤት እንከራይ፡፡እዚያው ቆይተንም የፖስፖርቱን ጉዳይ እናስጨርስ፡፡ከጨረስን በኃላ ሄደን ቤተሰቦቼን እንገናኛለን፡፡" በሐሳቧ ተስማማሁ፡፡ማረፊያ ተከራየንና እዚያው ቆየን ፡፡በነጋታው ወደ ፓስፓርት ማደሻ ማዕከል ሄድን፡ወደ ቢሮው ዘለቅን፡፡ አስተናጋጃችን የቀድሞውን ፓስፓርትና ሌላ ፎቶ ጠየቀን፡፡ በጥቁርና ነጭ የተነሳችውን ፎቶ አቀበለችው፡፡ የፊቷ ቅርፅ ብቻ ነበር የሚታየው፡፡ አስተናጋጁ "ይህ ፎቶ ለፓስፓርት አይሆንም ፡፡ባለቀለም ፎቶ ነው የምንፈልገው ፡፡ፀጉርና ተከሻሽ መታየት አለበት፡፡" አላት፡፡ ከዚህ ፎቶ ውጭ ሌላ እንደማትሰጥ አስረግጣ ነገረችው... #ክፍል_5_ይቀጥላል... SHARE 👇👇👇 SHARE https://www.facebook.com/profile.php?id=100064370604661
نمایش همه...
እውነታ

እውነታ, Addis Ababa, Ethiopia. 4,854 likes · 20,066 talking about this. 📗📙📕 (በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።) 👇 Telegram-

https://t.me/ewntamedia

👍 3