fa
Feedback
ASTU General

ASTU General

رفتن به کانال در Telegram

We are dedicated to truth information! For Advertisement and information contact us on : @suraf_ell @maykberahi Lost and Found Materials Post here: https://t.me/astugeneral_lost_found

نمایش بیشتر
9 364
مشترکین
+924 ساعت
+177 روز
+41430 روز
آرشیو پست ها
#ማስታወቂያ‼️ በ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል ባለፈው በተለቀቀው ፎርም የተመዘገባችሁ እና ዛሬ ከኮኦርዲኔተሮች ስልክ የተደወለላችሁ ተማሪዎች፣ ነገ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ ኦዳ ናቤ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን።

For some department the internship results have been posted. Please check your results
For some department the internship results have been posted. Please check your results

photo content

Repost from N/a
🚨🔥 STOP OVERPAYING FOR PREMIUM TOOLS! 🔥🚨 🌟 WELCOME TO JAH SHOP 🌟 🇪🇹 Ethiopia’s Digital Store for Premium Subscription
🚨🔥 STOP OVERPAYING FOR PREMIUM TOOLS! 🔥🚨 🌟 WELCOME TO JAH SHOP 🌟 🇪🇹 Ethiopia’s Digital Store for Premium Subscriptions, AI Tools & Digital Products 💥🔥 HOT DEALS! 🔥💥 💎 Gemini Pro — 250 ETB 🎨 Canva Pro — 250 ETB 🤖 ChatGPT Plus — 350 ETB ✂️ CapCut Pro — From 250 ETB ⭐ Telegram Premium — From 1,000 ETB 🌟 Telegram Stars — From 5 ETB 🎓 Coursera — 1,000 ETB ⚡ Supabase Pro — 7,990 ETB 💻 Replit Core — 4,999 ETB 🎬 Netflix — 650 ETB 🎮 EA FC 26 PC — 599 ETB 🎮 GTA 5 RP — 2,390 ETB 🛡️ NordVPN — 700 ETB 📝 Notion Business — 499 ETB ✨ Gamma Pro • 🤖 QuillBot 💼 LinkedIn Business & Career ➕ AND MANY MORE! 💎 Gemini Pro for ONLY 200 ETB! 🎯 Students • Creators • Developers • Professionals 💎 WHY JAH SHOP? ⚡ Fast Delivery • 💰 Affordable Prices 🤖 Easy Ordering • 🔄 Quick Activation 🛒 Everything in One Place 🚀 DON’T MISS OUT! Your favorite premium tools are ONE CLICK AWAY! 👇 🛍️ ORDER NOW: @Jah_Shop_bot 🔥 JAH SHOP 💻 Premium Tools • Better Prices • Smarter Choices 🌐 YOUR DIGITAL FUTURE STARTS HERE!

Repost from Duma Store
✨🎓 HP ELITEBOOK 840 G6 💻✨ 🔥 The Ultimate Student Beast! 🚀📚 ​🎒 Super Slim & Light — Perfect for your backpack & campus l
+3
✨🎓 HP ELITEBOOK 840 G6 💻✨ 🔥 The Ultimate Student Beast! 🚀📚 ​🎒 Super Slim & Light — Perfect for your backpack & campus life! 🚶‍♂️⚡ 🚀 Zero Lag Multitasking — 16GB RAM for dozens of tabs & assignments! 📑💫 💾 Huge 512GB SSD — Store all your notes, projects & movies! 🎬📁 💎 Premium Metal Finish — Sleek, modern & super durable! 🌟🛡️ 🎧 Zoom & Study Ready — Crisp display & rich, clear audio! 🎥🔊 ​⚙️ QUICK SPECS: 🔹 CPU: Intel Core i5 / Core i7 (8th Gen) ⚡ 🔹 RAM: 16GB 🔥 🔹 Storage: 512GB SSD 💨 🔹 Condition: Super Clean & Like New ✨ ​💵 Price: dm 📍 Location: [Megenagna, Meseret Defar Mall Ground] 📌 📲 Telegram / Call: [@duma_store/ @0925143732] 💬📞 ​🛒 Limited Stock Available! Grab Yours Today! 🏃‍♂️💨✨

ስፖርት ⛹🏼‍♂️🤾‍♀️⚽️ ስፖርት እንደልብ መስራት ትችላላችሁ። አብዛኛውን ጊዜ ተማሪዎች ገንዘብ አዋጥተው ኳስ ይገዙ እና በቡድን በቡድን ሆነው በሳምንቱ መጨረሻ ይጋጠማሉ። እና በጣም ነው ደስ ሚለው። በተለይ ቅዳሴ ቅዳሜ ጠዋት ሁሌ ኳስ ጨዋታ አለ። ☑️ ስፖርት ስለሆነ ለጤንነትም ጥሩ ነው ☑️ ወዳጅነትን ማጠናከሪያ ይሆናል ☑️ ደስ የሚል የግቢ ላይፍ ማሳለፍያም ነው ☑️ እጅግ መሳጭ ሙድ አለው #ይመቻችሁ 🤗 መብራት 🔌💡 መብራት ምንም አይጠፋም ማለት ይቻላል። ቢጠፋም ወዲያውኑ ነው ሚመጣው። ስለዚህ አያሳስባችሁ። ውሃው 💦 ውሃው ሁሉ የሚሞቅ ነው። የሚጠጣ ውሃ የምትቀዱት በሃይላንድ ወይም በኮዳ ከካፌ ወይም ንፁህ ውሃ ከሚመጣበት ቧንቧ ሲሆን እንዲቀዘቅዝላችሁ ሎከራችሁ ውስጥ ማስቀመጥ ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ። ኤሌክትሪክ ማይጠቀም ፍሪጅ በሉት😁። የሻወሩ ጉዳይ ደሞ የውሃውን ሙቀት ለመልመድ ጊዜ ሊወስድባችሁ ይችላል። እናም መጀመሪያ ላይ እየተቃጠላችሁ ልትታጠቡ ትችላላችሁ 🥵😁። በኋላ ላይ ግን normal ይሆናል። Adapt እስከምታደርጉ መቸገራችሁ አይቀርም። በሳምንት ሶስት ወይ አራት ጊዜ ውሃ ይመጣል። ጠዋት ጠዋት ነው ሚመጣው። ስለዚህ ሻወር ከፈለጋችሁ በጠዋት ተነስታችሁ መሆን አለበት። ሃይላንዶች ያስፈልጓችኋል። ለምሳሌ ዛሬ ውሃ ቢኖር እና ነገ ባይኖር ዛሬ ውሃ ትቀዱና ለነገ ለመታጠብያ ታዘጋጃላችሁ ማለት ነው። ልብስ ለማጠብ ደሞ የማጠብያ ቦታዎች አሉ ስለዚህ እዛ ማጠብ ትችላላችሁ። ከፈለጋችሁ ደግሞ ውሃ ሲመጣ (በተለይ ቅዳሜ) ሻወር ያለበት የመታጠብያ ክፍል ውስጥ በማጠብያ ማጠብ ትችላላችሁ። ይሄ ለወንዶች ነው። በእርግጥ የሴቶች ዶርም ብዙውን ጊዜ ውሃ አይጠፋም ... 😒😁 ወደ ቤት መሄድ /ከግቢ መውጣት በፈለጋችሁት ሰዓት መሄድ ትችላላችሁ። ከምሽቱ 3 ሰዓት በኋላ ግን አይቻልም። አንዳንድ ተማሪዎች special case ሲኖርባቸው በትምህርት ቀናትም አስፈቅደው ይሄዳሉ። በተለይ የአዲስአበባ ልጆች ከተማው በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ አብዛኞቹ weekend ላይ ወደቤት ይሄዳሉ። ዋናው ነገር ክላስ አለመቅጣት እንጂ መውጣት መግባቱ መብታችሁ ነው። ስትወጡ ግን ፕሮክተር ጋር ሄዳችሁ መውጫ ማስፃፍ ይኖርባችኋል። አለበለዚያ ከግቢ እቃ ይዛችሁ መውጣት አይቻልም። ማታ ማታ እስከፈለጋችሁበት ሰዓት ድረስ ላይብረሪ መቆየት ትችላላችሁ። በእርግጥ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ይዘጋል እናም ጠዋት 2 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ማታ ላይ አንብባችሁ ስትመለሱ like 6 ፣ 7 ወይ 8 ሰዓት ላይ ብቻችሁን ባትሆኑ ይመረጣል። ሌባ አግኝቷችሁ ልትዘረፉ ትችላላችሁ (ይሄ ብዙም risk የለውም)። ምናልባት ጅቦቹ በብዛት አሉ በዛ ሰዓት። አይነኳችሁም። ግን ብቻችሁን ከሆናችሁ መፍራታችሁ እና መሸበራችሁ ስለማይቀር ከጓደኞቻችሁ ጋር ሆናችሁ አምሹ እንጂ ብቻችሁን አትሁኑ። ግቢው ውስጥ ጃርት 🦔 አለ። በተለይ ማታ ላይ ተጠንቀቁ። አምሽታችሁ ስትመጡ ጃርት ልታገኛችሁ ትችላለች። የዶርም ብሎክ ድረስ ይገባሉ። 😁 @ASTU_General

ፀጉር 🙄 በእርግጥ ይከለከላል ማለት አይቻልም። ግን ባለፈው አመት ህዝቤ ሁሉ ሹሩባ የሚያሰራ ፀጉር ተሸክሞ ባለበት በድንገት ያልተጠበቀ አንድ ማስታወቂያ ወጣ ... የቀን ገደብ አስቀምጦ በዚህ ጊዜ ውስጥ እንድትስተካከሉ የሚል ነበር። እና ሁሉም ኖርማል በሚባል መልኩ ነበር የተስተካከሉት 💇💇‍♂️። አንዳንዴ በተለይ ማታ ላይ ፀጉር ያሳደገ ሰው ግቢ ሲገባ ይይዛሉ። ደሞ ፌዴራል ፖሊስ ናቸው ... ስለዚህ ከስጋት ነፃ ለመሆን መጠነኛ/መካከለኛ ፀጉር ቢሆን ይመረጣል። አይ እንደምንም manage አደርገዋለሁ የምትሉ ከሆነ ደግሞ ራስታ 🧔🏻‍♀️ ሆናችሁም መምጣት ትችላላችሁ 😅

ፀጉር 🙄 በእርግጥ ይከለከላል ማለት አይቻልም። ግን ባለፈው አመት ህዝቤ ሁሉ ሹሩባ የሚያሰራ ፀጉር ተሸክሞ ባለበት በድንገት ያልተጠበቀ አንድ ማስታወቂያ ወጣ ... የቀን ገደብ አስቀምጦ በዚህ ጊዜ ውስጥ እንድትስተካከሉ የሚል ነበር። እና ሁሉም ኖርማል በሚባል መልኩ ነበር የተስተካከሉት 💇💇‍♂️። አንዳንዴ በተለይ ማታ ላይ ፀጉር ያሳደገ ሰው ግቢ ሲገባ ይይዛሉ። ደሞ ፌዴራል ፖሊስ ናቸው ... ስለዚህ ከስጋት ነፃ ለመሆን መጠነኛ/መካከለኛ ፀጉር ቢሆን ይመረጣል። አይ እንደምንም manage አደርገዋለሁ የምትሉ ከሆነ ደግሞ ራስታ 🧔🏻‍♀️ ሆናችሁም መምጣት ትችላላችሁ 😅

WiFi 🛜 ግቢው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች WiFi አለ። በየ ላይብረሪዎችም ይገኛል። ግቢው ውስጥ ያሉ ዋይፋይዎች የሚሰሩት በ IP address ነው እንጂ እንደማንኛውም በፓስወርድ አይደለም። ውጤታችሁን እና ሌሎች መረጃዎችን ምትከታተሉበት ፖርታል intranet ሲሆን የሚሰራውም በግቢው ዋይፋይ ብቻ ነው። አንዳንዴ በ special case ለተወሰነ ጊዜ በ data እንዲሰራ ይደረጋል። አሁን ግን ለረዥም ጊዜ በ mobile data እንዲሰራ ተርጓል ፤ አሁንም እየሰራ ነው።

ጂም 🏋🏻‍♂️ 👉 ግቢው ውስጥ ሁለት ያለ ሲሆን የሚገኘውም ስታዲየም ጋር ነው። አንደኛው የቀን እና የወር ክፍያ አለው በቀን =30ብር በወር =600ብር ነበር።ሁለተኛው ከላይ attach ያረኩት ግን የወር ክፍያ ብቻ ነው ያለው እሱም 2000ብር ነው :ሴቶችም ይሰራሉ 🫢🤭

DStv 📺 ግቢው ውስጥ ተማሪ ሚሰበሰብበት amphi ሚባል ቦታ አለ። እዛ ቦታ አንድ ግዙፍ screen አለ። የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ተማሪዎች በሚገባ ይከታተላሉ። ግቢው በኳስ አፍቃሪ የተሞላ ነው። አንዳንዴ እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ላይ ጨዋታውን ይከታተላሉ። ጎል ሲገባ ይጮኻሉ 😂። እዛው አከባቢ TV ምትመስልም screen አለች። አንዳንዴ ትልቁ ማይሰራ ከሆነ በዛም ይመለከታሉ።

እስከ ስንት ሰዓት ግቢ ውስጥ መንቀሳቀስ እንችላለን ❓ 👉 24Hrs ይቻላል። ሁሉም አንባቢ ነው ... Imagine አንተ ምሽት ስምንት ወይ ዘጠኝ ሰዓት ከላይብረሪ ስትመለስ የሆነ ሰው ለማንበብ እየሄደ ስታይ ..😁 .. ብቻ በፈለጋቹት ሰዓት መንቀሳቀስ ትችላላችሁ። ነገርግን አንዳንድ ቦታዎች ላይ አይፈቀድም። በተለይ ማታ ማታ ፌዴራል ፖሊሶች ናቸው ሚዞሩት እና ጠንቀቅ ማለት ግድ ነው። ውጪ እስከ ስንት ሰዓት መቆየት ይቻላል ❓ 👉 በሩ የሚዘጋው ከምሽቱ 3:00 ላይ ነው። ከዚህ በኋላ መግባትም መውጣትም አይቻልም። ክላስ መቅጣት 🥶 👉 በእርግጥ አንዳንድ አስተማሪዎች ምንም አይሉም። አንዳንዶቹ ደግሞ NG የሚሰጡ እና ተማሪውን ጠምደው እስከመጨረሻው ድረስ የማይፋቱ አሉ። ስለዚህ ክላስ መቅጣት አደገኛ ነገር ነው። መጀመሪያ ሲሆን ደግሞ የአስተማሪውን ፀባይ ስለማታውቁ ትቸገራላችሁ። Attendance 👇 👉 ግቢው በአቴንዳንስ ጉዳይ ቀልድ አያቅም። አቴንዳንሳችሁ የግቢው ፖርታል ላይ ሁሉ ይሞላል። እናንተ ወረቀት ላይ ትሞላላችሁ ፣ አስተማሪዎቹ ወደ ፖርታል ያስገቡታል። ስለዚህ በአቴንዳንስ አትቀልዱ። It's ASTU, not your high school 🫡

#Tigray ከትግራይ ክልል በ transfer ASTU የተመደባችሁ ተማሪዎች ግቢው እናንተን በተመለከተ እስካሁን ያወጣው ማስታወቂያ የለም። ምናልባት ከሌሎች ሲኒየሮች ጋር ትገቡ ይሆናል። ወይም ደግሞ ከምዝገባው ጥቂት ቀናት በኋላ ሊሆንም ይችላል። ግቢው አዲስ ነገር ካለ እናሳውቃለን። @ASTU_General

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል። በዚህ
+3
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል። በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር ተወስኗል። በተጨማሪም፦ 👉 የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 500 ብር የምዝገባና 3,000 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር። 👉 የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ፦ ለኢትዮጵያውያን 950 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር። 👉 የሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 1,000 ብር የምዝገባና 2,500 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 150 ዶላር። 👉 የትምህርት ማስረጃ ምትክ ሰርተፊኬት ፦ ለኢትዮጵያውያን 600 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 115 ዶላር። 👉 ምትክ ሰርተፊኬትና ማረጋገጫ ፦ ለኢትዮጵያውያን 900 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 170 ዶላር። 👉 የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ/ማጣራት ፦ ለኢትዮጵያውያን 400 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 75 ዶላር። 👉 በስም ላይ የፊደል ግድፈት ለማስተካከል ፦ ለኢትዮጵያውያን 700 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 130 ዶላር። 👉 ኦፊሴላዊ ትራንስክሪፕት መላክ ፦ ለኢትዮጵያውያን 750 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 50 ዶላር። የፈተና ውጤት መረጃን ለምርምር ለሚጠይቁ ተቋማት በአንድ ጥናት 10,000 ብር፣ ለውጭ ተቋማት 1,875 ዶላር ክፍያ ተወስኗል። ለግለሰቦች ደግሞ ለኢትዮጵያውያን 1,000 ብር፣ ለውጭ ዜጎች 190 ዶላር እንደሚከፈል ተገልጿል። በተጨማሪም ያገለገሉ የምዘና መሳሪያዎችን ለመጠቀም ከጠቅላላ ወጪው 5 በመቶ፣ አዲስ የምዘና መሳሪያ ለማዘጋጀት ደግሞ 10 በመቶ ክፍያ እንደሚፈጸም ደንቡ ያስቀምጣል። ደንቡ ለሌሎች የምዘናና የማረጋገጫ አገልግሎቶችም አዳዲስ የክፍያ ተመኖችን አካቷል። የተሻሻለው ደንብ ቁጥር 593/2018 ሙሉ ይዘት ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ይገኛል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

#PC 💻 ከቻላችሁ PC ይዛችሁ ብትመጡ ጥሩ ነው። Python Course ያለ PC አስቸጋሪ ነው። በተጨማሪም ደግሞ አብዛኞቹን አሳይመንቶች በኮምፒውተር ጽፋችሁ ፕሪንት አድርጋችሁ አስጠርዛችሁ ስለሆነ የምትሰጡት PC ከሌለ ይከብዳል። ይዘረፋል ይባላል ፤ ዋናው የናንተ ጥንቃቄ ነው። ካፌ ስትሄዱ ፣ ክላስ ስትገቡ እናም ሌላም ጊዜ ይዛችሁ መዞር ግድ ነው። ግዴታ ግን አይደለም! Library ያሉትን desktop መጠቀም ትቸላላችሁ! @ASTU_General

#SoEEC 📚 School of Electrical Engineering and Computing (#SoEEC) #Departments                            #Years 1. Computer Science                      5      and Engineering 2. Electronics and                           5     communication     engineering 3. Software Engineering                5 4. Electrical power and control engineering                       5 @ASTU_General

#SoMCME 📚 School of Mechanical, Chemical and Material Engineering (#SoMCME) #Departments                      #Years 1. Chemical Engineering          5 2. Material Science and            5     engineering 3. Mechanical Engineering      5 @ASTU_General

#SoCEA 📚 School of Civil Engineering and Architecture (#SoCEA) #Departments                      #Years    1. Architecture                           5 2. Civil Engineering                   5 3. Water Resource                     5      Engineering @ASTU_General

#SoASN 📚 School of Applied Natural Science (#SoASN) #Departments #Years 1. Applied Biology 4 2. Applied Chemistry 4 3. Applied Geology 4 4. Applied Mathematics 4 5. Applied Physics 4 6. Industrial Chemistry 4 7. Pharmacy 5 @ASTU_General

vየመጀመሪያ ሴሚስቴር ኮርሶች 1. Applied Mathematics I 2. General Physics 3. General Chemistry 4. Logic and Critical Thinking 5. Civics and Ethics 6. Communicative English I 7. Introduction to programming - Python 8. Physical Fitness and Conditioning I Logic and Critical Thinking እና Civics and Ethics ኮርሶች ተማሪዎች የሚበዙ ከሆነ በተራበተራ ይሰጣሉ። የመጀመሪያ ሴሚስቴር ላይ logic የተማረ ሁለተኛው ላይ Civics ይማራል። በመጀመሪያው Civics ከሆነ ደሞ በሁለተኛው logic... ይ ቀ ጥ ላ ል . . . @ASTU_General