fa
Feedback
🅐🅑 🄳🄸🅂🄷

🅐🅑 🄳🄸🅂🄷

رفتن به کانال در Telegram
999
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-87 عوز
-2830 عوز
آرشیو پست ها
ዕገዳ ጥሰው ሲጠጡ የነበሩ ፖሊሶች ተያዙ❗️ በኬንያ አንድ ግዛት ውስጥ በርካታ ሰዎች በአልኮል መጠጥ ምክንያት ለሞት ከተዳረጉ በኋላ የተጣለውን ክልከላ ጥሰው ሲጠጡ የተገኙ የፖሊስ መኮንኖች በቁጥጥር
ዕገዳ ጥሰው ሲጠጡ የነበሩ ፖሊሶች ተያዙ❗️ በኬንያ አንድ ግዛት ውስጥ በርካታ ሰዎች በአልኮል መጠጥ ምክንያት ለሞት ከተዳረጉ በኋላ የተጣለውን ክልከላ ጥሰው ሲጠጡ የተገኙ የፖሊስ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በማዕከላዊዋ የኬንያ ግዛት ኪሪኒያጋ ውስጥ ኤታኖል ከተባለው ኬሚካል ጋር የተደባለቀ የአልኮል መጠጥ የጠጡ ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወት ከጠፋ በኋላ ነው በግዛቲቱ ያሉ መጠጥ ቤቶች እንዲዘጉ የተወሰነው። የግዛቲቲ አስተዳዳሪ አን ዋይጉሩ በርካታ ሰዎች በመጠጥ ምክንያት መሞታቸውን ተከትሎ ባለፈው ቅዳሜ ሁሉም የመጠጥ መሸጫ ቤቶች እንዲዘጉ ማዘዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። አስተዳዳሪዋ መጠጥ ቤቶች እንዲዘጉ የወሰኑት በመጠጥ ንግድ ላይ በተሰማሩት ድርጅቶች ላይ ምርመራ ለማድረግ እና ተገቢው ፈቃድ እንዳላቸው ለማጣራት መሆኑ ተገልጿል። የአስተዳዳሪዋን ትዕዛዝ እንዲያስፈጽሙ ከተሰማሩት የፖሊስ መኮንኖች መካከል አራቱ አንድ መጠጥ ቤት ውስጥ አልኮል ሲጠጡ ተይዘዋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ የተገደሉ ንፁሃን ዜጎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተነገረ‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ከጥር 20 እስከ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ድ
በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ የተገደሉ ንፁሃን ዜጎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተነገረ‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ከጥር 20 እስከ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች የተገደሉ ንፁሃን ቁጥር ከ45 በላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል። በአማራ ክልል (ኢሰመኮ) ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለባቸው ብርሃኑ ለአራዳ ኤፍ ኤም እንዳሉት፥ ግድያው በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ከተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ በኋላ የመንግስት ወታደሮች ቤት ለቤት በመግባት መፈጸማቸውን አረጋግጠናል ብለዋል። ህብረተሰቡ በፍራቻ ውስጥ በመሆኑ መረጃ ለማግኘት ቀላል አለመሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፥ ምርመራችንን አላጠናቀቅንም በመግለጫ ያወጣነው የመጀመሪያ ግኝታችንን በመሆኑ ምርመራው ቀጥሏልም ነው ያሉት። አራዳ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች በበኩላቸው ወጣቱን “ፋኖ ሰልጥነሃል፤ ዘመድህ ፋኖ ነው” በሚል ወከባ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል። ከጦርነቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስቱ ጥበቃ ሊያደርጉላቸው ይገባልም ብለዋል ነዋሪዎቹ።

ሰበር ዜና‼ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) 1 ታይገር የሚባለው ቡድን ባህርዳር ከተማ በሚገኙ የስርዓቱ የፀጥታ አካላት ላይ በደፈጣ ጥ*ቃ*ት መፈፀሙ ተገለፀ‼ አገዛዙ በትናትናው ዕለት በባህርዳር ከተማ የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ የግለሰቦችን ወርቅ መዝረፍ፣ ቴሌቪዥንና ዲሺ እያወረዱ መስበራቸውን ተከትሎ በከተማዋ በስውር የሚንቀሳቀሰው የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ታይገር 1የሚባለው ቡድን በደፈጣ በስርዓቱ የፀጥታ ኃይሎች ላይ  መብረቃዊ የኃይል እ*ር*ም*ጃ ማድረሳቸው  ተገልጿል። እስካሁን የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ብሬን ተኳሽ አባል የነበረው ኮንስታብል አማረ መ*ገ*ደ*ሉ ፋኖዎቹ ያረጋገጠ ሲሆን ሌሎች የፀጥታ አካላት ላይም መጠነኛ ጉ*ዳ*ት ደርሷል ብለዋል። ስለ ጉዳት መጠኑ ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን የምናጋራ ይሆናል።

ሰበር ዜና አገዛዙ በመሸንቲና ዙሪያዋ የሚገኙ ወጣቶችን እያፈሰ መሆኑ ተገለፀ።    ወራሪው ሰራዊት ከአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ጋር የጀመረው ጦርነት እየተወሳሰበበት መሆኑን ሲገነዘብ በበርካታ አካባቢዎች ንፁሐንን መረሸን ፣ በጅምላ ማሰርና ማሰቃየት የየእለት ተግባሩ ካደረገው ቆይቷል። ከሰሞኑ በመሸንቲ በተለይም ቆጥቆጥማ ተብሎ በሚጠራው አካበቢ የካቲት 5 እና 7 ተከታታይ ውጊያዎች መደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ፣ በዚህ አውደ ውጊያ ታላቅ ሽንፈት የገጠመው ይህ ስርዓት አሁን ላይ ንፁሐንን ቤት ለቤት እያፈነ እየሰወረ መሆኑ ታውቋል። ዛሬ በመሸንቲ በመሐል ገበያ ላይ ተኩስ በመክፈት በበርካታ ንፁሐን ላይ ጉዳት አድርሰዋል ወጣቶችንም አፍነው ወስደዋል ሲሉ የአይን እማኞች በስልክ መረጃውን አድርሰውናል።    የበቀል እርምጃ በሚመስል መልኩ የተፈፀመ ኢሰብአዊ የሆነ ተግባር ነው ያሉት መረጃ ሰጭው በጥቃቱ ምን ያህል ንፁሓን እንደተጎዱ መረጃዎችን እያጣራን ነው ሲሉ ገልፀዋል።

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
🥇3.87 GPA👏 አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ካስመረቃቸው ሴት ተማሪዎች መካከል ዶ/ር ረድኤት ጌቱ ከበደ በህክምና ዶክትሬት 3.87 GPA በማስመዝገብ ተሸላሚ ሆናለች። #AAU
+1
🥇3.87 GPA👏 አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ካስመረቃቸው ሴት ተማሪዎች መካከል ዶ/ር ረድኤት ጌቱ ከበደ በህክምና ዶክትሬት 3.87 GPA በማስመዝገብ ተሸላሚ ሆናለች። #AAU @tikvahethiopia

ሁለት መረጃዎች 1) በደጀን ወረዳ አባይ ሸለቆ እሰከ ምንጅ  ቀበሌ ድረስ ፋኖዎቻችን ከወራሪው የፋሽስት ብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ጋር እየተፋለሙ ይገኛል። የጠላት ኃይል በዚሁ አውደ ግንባር 2 ዙ23 ማሰለፉ ታውቋል። በተመሳሳይ በባሶሊበን ወረዳ በደን ግንባር እና በሉማሜ ዙሪያም ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ ይገኛል። ▪︎እነዚህን መረጃዎች የምናወጣው 1) የጠላት ኃይል ተጨማሪ ኃይል ማስገባት እንዳይችል እንዲገታ 2) ሌሎች በአካባቢያቸው ያለን የሳሳን የጠላት ኃይል እንደነገሩ እንዲያደርጉት ነው። 2) በባህር ዳር ከተማ ይህን 3 ቀናት የፍተሻ ስልጠና በወሰዱ የሚሊሽያዎችና ፖሊሶች የቤት ለቤት ፍተሻ እየተደረገ እንዳለ ለማወቅ ችለናል። እስከአሁንም ቀበሌ 14፣ 13፣ 16፣ 3 እና 8 ፍተሻ እንደተደረገና ህጋዊ መሳሪያ ሳይቀር እንደነጠቁ ለማወቅ ተችሏል። ▪︎አስገራሚው ነገር ደግሞ መረጃ ቴሌቪዥን ታያላችሁ እያሉ ቴሌቪዥን እስከመስበር ከመድረሳቸውም በኋላ በግለሰቦች ቤት ጌጣጌጥ፣ ብርና ላፕቶፐ እየዘረፉ እንዳለ ታውቋል። ŠBW

ቀን 05/06/2016 ዓ.ም በዓለም ከተማ ሕዝብ እየደረሰ ያለ የግፍ ጥግ !!! መርሐቤቴ ዓለም ከተማ ሕዝብ ላይ አሰቃቂ ወንጀልና በደል በመፈጸም የበቀል ዱላውን ማሳረፉን አጠናክሮ መቀጠሉን የከተማው ነዋሪ አቤቱታውን ለዓለም ሕዝብ ይወቅልን በማለት ድምጻቸውን አሳውቀዋል። አንድ ስማቸው እንድጠቀስ ያልፈለጉ ታላቅ አባት ፋኖ ሲያስተዳድር በነበረበት ወቅት ሁሉም በሰላም ገብቶ እየወጣ ስራውንም ባግባቡ እየሰራ ለ7 ወራት ያክል በሰላምና በደስታ መኖሩን ገልጸው አሁን ግን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ነን ብለው ሲገቡ የኢትዮጵያ ዳር ደንበር ጠባቂወች ናቸው ምንም አያደርጉንም ብለን ዝም ብለን በሰላም ተቀብለን ነበር። በሰላም በተቀመጥንበት ሁኔታ የፋኖን በትር መቋቋም ሲያቅተው የመሳሪያ አፈ ሙዙን ወደ ንጹሃን ሰወች በማዞር በጎዳና ላይ እየታፈሰ ከሚወሰደው ወጣት እና ህዝብ በተጨማሪ ቤት ለቤት በመዞር ልጆቻችንን እፍነው ከመውሰድም በላይ በፍተሻ ስም ኪሳችን በመግባት ብራችንን ፣ ሞባይላችንን፣ የልጆቻችንን የአንገት ሐብል እና ጌጣጌጥ ጭምር ፣ ላፕቶፖችንም ጭምር ፣ አዳድስ ልብስም  ጭምር  እየገፈፋ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ እህል ውስጥ ተተኳሽና መሳሪያ ቀብራችኋላ በማለት ጎተራችንን በመገልበጥ በዚህ ኑሮ ውድነት ያስቀመጥነውን እህል የትም ቦታ እየደፉብን ይገኛሉ። በቋንቋ እንኳን መግባባትና ማስረዳትም አልቻልንም በማለት እያለቀሱ ያስረዱ ሲሆን ሴት ልጆቻችንንም ሞራል በሚነካ ሁኔታ ይሰድቧቸዋል፣ እየጎተቱ ያንገላቷቸዋል ብለዋል። ከዚህም የተነሳ ብዙ የከተማችን ወጣቶች፣ ሽማግሌወች፣ ሙህራን ሁሉ በህልውና ዘመቻው ወቅት ፋኖ ሲሰለጥን የለበሱትን ልብስ፣ እንድሁም በእየ አመቱ የዐድዋ በዐል ሲከበር የሚኒሊክን ፎቶ ያለበት ቲሸርት በባህልና ቱሪዝም የወረዳው ጽፈት ቤት ስለሚታደል እርሱን አገኝንባችሁ በማለት እና ሌላም የሆነ ነገር ቤታችሁ ውስጥ አግኝተናል በማለት እያፈኑ እየወሰዱ ነው ብለዋል። የእርሳቸው ጓደኞች በሙሉ እንደተወሰዱ ገልጸው እኔም ተራየን በመጠባበቅ ላይ ነኝ ብለዋል። ሌላዋ እናት ደግሞ ጠላ በመሸጥ የምትተዳደር እናት እንደገለጹልን በሚደርሰው ወከባ ምንም ገበያ ባለመኖሩ ልጆቸን የማበላው አጥቸ ሊሞቱብኝ ነው ያሉ ሲሆን በሚደርሰው ወከባ በዝቅተኛ ኑሮ የምንኖር ሰወች ከባድ ችግር ውስጥ ነን ብለዋል። ይህ ዓለም ከተማ ላይ ካምፕ ውስጥ ተወሽቆ በመመሸግ ህዝቡና ወጣቱን በማፈን አረጋውያን አባቶች ሳይቀሩ በማፈን እና ቶርች በማድረግ ጥፍራቸውን በመንቀል ፣ በመደብደብ ፣በመግደል፣ በማሰቃየት እንድሁም ያገኘውን ሁሉ በመዝረፍ እና በማውደም ፣ ለፋኖ ስትረዱ ነበር ያላቸውን ባለሃብቶችን ንብረት በመዝረፍና እነርሱንም አፍኖ በመደብደብ ታይቶ የማይታወቅ ግፍ በመፈጸም ላይ ስለሆነ እባካችሁ ለመላው ዓለም ህዝብ አሳውቁልን በማለት የከተማው ህዝብ በምሬት አቤቱታውን አቅርቡልኝ ብሏል። ህዝብን በማሰቃየትና በመዝረፍ የሚገኝ ድል የለም። ድል ለዐማራ ህዝብ !!! መርሐቤቴ ዓለም ከተማ

#መረጃ ሸዋ ደራ! በዛሬው እለት የኦነግ ብልፅግና መከላለያ አራዊት በሸዋ ደራ ቱቲ ሰኞ ገበያ ውስጥ የነበሩ ንፁሀን አማራዎች ላይ በከባድ መሳሪያ የተኮሰ ሲሆን እስከአሁን በንፁሀን ላይ የደረሰው የሙትና ቁስለኛ ቁጥር በወል አልታወቀም:: ደም በደም ብቻ ይጠራል:: #ውጣና_ግጠም! 05/06/16 ዓ.ም @NISIREamhra

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ውጤት አልተገኘም " ደቡብ ወሎ ዞን ፣ ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ የተደረመሰባቸውን በርካታ ሰዎች ለማውጣት የሚደረገው ጥረት 4 ቀኑን
+1
" ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ውጤት አልተገኘም " ደቡብ ወሎ ዞን ፣ ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ የተደረመሰባቸውን በርካታ ሰዎች ለማውጣት የሚደረገው ጥረት 4 ቀኑን እንደያዘ ተነግሯል። የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የከበረ ማዕድን አውጪዎች ማኅበር በሰጡት ቃል  ፤ በቁጥር ከ8 እስከ 30 የሚገመቱትን ሰዎች ለማውጣት የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን ውጤት አልተገኘም። የወገል ጤና ከተማ አስተዳደር ፍለጋውን በማሽን ለማገዝ የአካባቢው መልከዓ ምድር ምቹ ባለመሆኑ ጥረቱን አዳጋች እንዳደረገው አሳስውቋል። በሕጋዊ መንገድ ተሰማርተው በማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ናዳ የተጫናቸው ከ4 ቀናት በፊት ነበር። ሌሎች የአካባቢው ወጣቶችም አብረው ሳይኖሩ እንዳልቀረ ተነግሯል። አሁን ወጣቶቹ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አልተቻለም። የወረዳው አስተዳዳር ባለፉት ቀናት ከ500 በላይ ሰዎች በነፍስ አድን ሥራው ላይ እገዛ ለማድረግ ወደ ሥፍራው ቢያቀኑም፣ ወደ ዋሻው ለማምራት የሚያስችለው መንገድ ጠባብ እና በአንድ ጊዜ ከ10 ሰዎች በላይ ማስገባት ባለመቻሉ ጥሩቱ አዝጋሚ ነው ሲል ገልጿል። ወርቅ ዋሻ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ፤ በናዳው ተይዘው ከሚገኙት 8ቱ የማኅበሩ አባላት ናቸው ያለ ሲሆን እስካሁን በተደረገው ጥረት 150 ሜትር ርዝማኔ ወዳለው ዋሻ ዘልቆ ለመግባት መቆፈር የተቻለው 33 ሜትር ገደማ ብቻ ነው። " የአካባቢው ሕዝብ ሌት ተቀን ርብርብ እያደረገ ነው " ያለው ማህበሩ በመንግሥት በኩል የተቀበሩትን ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅም ሆነ ከዋሻው ለማውጣት የተደረገ ድጋፍ የለም ብሏል። የወገል ጤና አስተዳደር ግን የከተማ እና የወረዳው አመራሮች በሥፍራው እንደሚገኙ አስታውቆ ፤ " በቂ ድጋፍ ማድረግ ያልተቻለው አማራጭ ስለሌለ ነው " ሲል ገልጿል። " ጥረቱን በማሽን ለማገዝ አልተቻለም፤ ማዕድን አውጪዎቹም ባህላዊ ማዕድን አምራች ተብለው የተሰማሩት ቦታው ከባህላዊ ቁፋሮ ውጪ የሚቻል ባለመሆኑ ነው። ቦታው ለእግር መንገድ እንኳን ምቹ አይደለም " ብሏል አስተዳደሩ። መረጃው የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው። @tikvahethiopia

#ሜክሲኮ ሄጀ ነበር!! ሕሩይ አምሓራ ነኝ። ታማኙ፣ ሀቀኛው፣ አይበገሬ  የሰብዐዊነት ታጋይና የግፉዐን ልሳን የሆነው ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱን የፋሽስቱ አገዛዝ አምሓራን ማሰቃያ  ካንፕ ወደሆነው ሜክሲኮ ማጎሪያ በጥበብ ወርጄ  አገኘሁት። ይህ ጀግና ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ፣ በማንነቱ ሀቀኛ ሰብዐዊ ጋዜጠኛነቱ ምክንያት ብቻ፣ አብዛኛው ጊዜውን በኦሮሙማ ኦነጋዊ ፋሽስት አገዛዝ ማሰቃያ ካንፖች አሳልፏል። የቀደመ የወያኔ ፀረ አምሓራ አፓርታይድ አገዛዝን በመቃዎሙ ምክንያት በግንቦት ሰባትነት ክስ ተመስርቶበት በወያኔ እና አሽከሩ ብዐዴን ብዙ ግፍና መከራ ደርሶበት ቢያልፍም  ሸብረክ አላለም። የዚህ ሰው የህይወት ልምድ ፣ ፅናትና  ሰብዐዊ ትግል ነው። እርሱ…የአባቶቹ ልጅ ባለ ማህተብ ጀግና ነው። ላመነበት መስመረኛነቱና ሀቅን ማጥበቁ  "ደረቅ" አስብሎታል። ነገር ግን፣ የዋህ፣ ሩህሩህ፣ በወገኖቹ የሚፈፀመው ግፍና መከራ በራሱ ህመም ሆኖ የሚያሰቃዬው ከራስ ወጥቶ አደር የሰብዐዊነት መናኒ ነው። ጋዜጠኛ እና የሰብዐዊ መብት ታጋዩ አባይ ዘውዱ። ለዚህ ምስክሩ የሚሆኑት የሰብዐዊነቱ ማሳያ ያልወለዳቸው አራት ወላጅ አልባ ልጆች ያሳድጋል። በወለጋ የዘር ፍጅት ሰለባ በሆኑት ወላጆቻቸው ምክንያት ጎዳና የወጡ አራት ህፃናትን ሰብዐውያንን በማስተባበርና ከሌለው ላይ አጉድሎ ላለፉት አራት አመታት ቤት አከራይቶ የሚያስተምራቸው ህፃናት አሉት። ይህ ልበ ቀና ጀግና አላገባም፣ አልወለደም። ከእስር እና ትግሉ የተረፉትን ሽርፍራፊ ሰዐታት ከሚያሳድጋቸው ወላጅ አልባ ህፃናት ጋር የሚያሳልፍ የአላማው ፃድቅ ሰው ነው። አባይ ዘውዱ በፋሽስታዊ አገዛዙ ተደጋጋሚ የአዲስ አበባ ማዕከላዊ የእስር ስቃይ በኋላ… አይበገሬነቱ አንዳች ከአላማው እንደማያፈገፍግ ቢያውቁ ጊዜ… ከሌሎች የአማራ ቁርጥ ቀን ልጆች ጋር ወደ አዋሽ የፋሽስቱ ኦነጋዊ አገዛዝ ኦሽዊትዝ ካምፕ ካጋዙት ሶስት ወራት በኋላ…ወደ ሜክሲኮ ማሰቃያ መመለሳቸውን ሰማን። እናም… በጥበብ ወደ ሜክሲኮ ወርደን አገኘነው። ሚክሲኮ ውስጥ ያለውን የተያዘ ሰው መከራ እና ኢሰብዐዊ ሁኔታ በሌላ ጊዜ የሚገለጥ ሆኖ አባይ ዘውዱን እንዳገኘሁት የተሰማውን እና የተሰማኝን ስሜት ላሳይ… የበር ላይ ከፍተኛ ፍተሻ አልፌ ወደ ውስጥ እንደገባሁ በመስታወት አይን ለአይን እየተያየን በስልክ ብቻ የምናወራበት መጠየቂያ መስኮት ላይ ደረስኩ። አባይ ተጠርቶ መጣ እና ፊት ለፊት በደስታ እና ሳግ በተቀላቀለበት ቁጭት ስሜት ተፋጠን የምልክት ሰላምታ እየተለዋወጥን በስልኩ ወሬ ጀመርን። ወዲያው የፌደራል ፖሊስ መጥቶ ከአባይ ጎን ቆሞ የምናወራውን መስማት ቀጠለ። በኔም በኩል ሴት ፖሊስ ከአጠገቤ ቆመች። ብዙ ሚስጥር ለመነጋገር እድሉ ባይኖረንም…  አንድ ጥያቄ ጠየኩት። "አሁን ያላችሁበትና አያያዝ ሁኔታ እንዴት ነው?" አልኩት። ወዲያው ፊቱ ቅጭም አለና… "በአፋር ምድር አዋሽ አርባ ያሳለፍነውን ጊዜ ይግለጠዋል፣ እዚህ ከመጣን በኋላ ግን፣ በቀን የውጭ ብርሃን የሚያሳዩን ለአንድ ሰዐት ብቻ ነው፣ በአንድ ጠባብ ፍፁም የማይመች ክላስ ውስጥ አምስት ሆነን ነው ያለነው፣ ከዚያ የመጣነው አስር ሆነን ነው። ከሁለት ከፍለው በ2 ጠባብ ክፍል አጉረውናል። ሁላችንም በማንነታችን አማራ የሆንን የኦነጋዊ ስርዐት ማንነት ተኮር ጥቃት ሰለባዎች ነን። በክፍላችን የተከበሩ ዮሃንስ ቧ ያለው እና ክርስቲያን ታደለ፣ የተከበሩ ዶ/ር ካሳ ዶ/ር ንጉሴና መሰል ጀገኖች አብረውን አሉ።  የሚፈፀምብንን እና ተፈፅሞብን ያለፈ ግፍ በቃላት ለመግለፅ ቢከብድም ፣ ከቤቱ እያወጡ ከሚረሽኑት የአማራ ወገኔ መከራ አንፃር፣ ይህ የእኛ ምንም ነው። በመራይ የተፈፀመውን ዘግናኝ የዘር ፍጅትና ጭፍጨፋ ሰማሁ፣ እጅጉን ቁጭትም ሀዘንም ተሰምቶኛል፣ ሀዘኔን ግለፅልኝ…" አለኝ እና ትንፋሹ ተቆራረጠብኝ፣ አይኑ ይበልጥ መቅላቱን በመስታውቱ አሻግሬ አስተዋልኩ። "አይዞህ ወንድሜ፣ ሊነጋ ሲል ይጨልማል፣ እናልፈዋለን" አልኩት። አይኔን እያዬ…የሚለውን ያጣ ሳይሆን፣ የተደራረበበት፣ ብዙ ሊለኝ፣ ብዙ ሊያወጋኝ ጊዜና ትዕግስት የፈተነው፣ ቁጭት ያበገነው ሰው በሚያስቆጭ ጉስቁል ፊቱ እያየኝ፣  እኔም እያየሁት ጥቂት ሰከንዶች በፀፅታ አለፉ… ድንገት ግን የተከበሩ ዮሃንስ  ቧ ያለው ከኋላው ሲመጡ አየሁና፣ "አባይ ጥራቸው" አልኩትና ስልኩን ለእርሳቸው ሰጠልኝ… አቶ ዮሃንስ ቧ ያለው ጋር ጥቂት አወራን፣ ሰውዬው የዋዛ አይደለም። ስጋውን ባጎሳቆሉት ልክ መንፈሱ ከብረት ጠንክሮ አገኘሁት። አማራ እጅጉን ተስፋ እንዳለው፣ ሲመቱት እንደ ሚስማር የሚጠነክር ለመሆኑ… ዶ/ር ካሳ እና አቶ ዮሃንስ ቧያለው ላይ ያየሁት በግርማ የተሞላ ደፋር ፈገግታ የተሞላበት ንግግር ምስክር ነው። በመጨረሻ አባይ ዘውዱን ለስንብት ጠርቼው በደማቅ ፈገግታው ሸኝቶኝ ወጥቻለሁ… የሰጡኝ አበርች ሞራል ገራሚ ነበር። እነርሱ በዚያ ሆነው፣ እኛ በውዲህ… በሚያበረታ ጥንኩር መንፈስ ሆነው በዚያ አሉ። የሜክሲኮ ማሰቃያ ካንፕን ለቅቄ ስወጣ…  የአባይ ዘውዱ የቁጭት ድምፅና ገፅ፣ የነ ዮኃንስ እና ዶ/ር ካሳ የተስፋ ባለ ግርማ አበርች ንግግርና ገፀ መልክ፣ አብሮኝ ወጥቷል። ይሄው… አሁንም አብሮኝ አለ። በርቱ፣ አምሓራ ያሸንፋል!!! ተብላችኋል። #ሕሩይ አምሓራ #ድል ለመላው አምሓራ ፋኖ!

በአቡነ ጴጥሮስ ላይ የተሰራው ግፍ አገር አለን ብለን ለምናስብ ሁሉ: አገር አልባነታችንን በግልፅ ያሳየ ነው:: አንድ ኢትዮጵያዊ ሰው : ያውም የብዙ ሚሊዎኖች አባት: ወደ ሃገርህ አትገባም ተብሎ ሲ
በአቡነ ጴጥሮስ ላይ የተሰራው ግፍ አገር አለን ብለን ለምናስብ ሁሉ: አገር አልባነታችንን በግልፅ ያሳየ ነው:: አንድ ኢትዮጵያዊ ሰው : ያውም የብዙ ሚሊዎኖች አባት: ወደ ሃገርህ አትገባም ተብሎ ሲከለከል መስማት ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ነው:: ማንም የሃገር ባለቤትነት ሰጪና ነሽ መሆን አይችልም:: አሁን የሰዎች ጭምብል ወልቆ እውነተኛ ማንነታቸው እየተገለጠ ነው::

አዛውንቱን የደበደበው ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ዋለ❗️ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ምዕራብ ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በስራ ላይ የነበረ ኮንስታብል ጋትኦች ፖል የተባለ የፖሊስ አባል አንድን ግለሰብ በመምታት በፈፀመው ድርጊት በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ይገኛል፡፡ የፖሊስ አባሉ በሰጠው ቃል በወቅቱ በአካባቢው ሲጓዝ  ግለሰቡ ምንም አይነት መነሻ ምክንያት ሳይኖራቸው  ማንነትን መሰረት ያደረገ ክብረ ነክ ስድብ ስለሰደቡት ስሜታዊ ሆኖ የወሰደው ያልተገባ እርምጃ  መሆኑን  ገልጿል፡፡ ፖሊስ ባሰባሰበው መረጃ በስፍራው የነበሩ ሌሎች ሰዎችም ኮንስታብል ጋትኦች  ድርጊቱን የፈፀመው የግለሰቡን ስድብ ተከትሎ እንደሆነ በማረጋገጥ ለፖሊስ ቃላቸውን መስጠታቸውን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን፤ ፖሊስነት ስሜታዊነትን በማስወገድ በትዕግስት እና በብስለት ሃላፊነትን መወጣት የሚጠይቅ ሙያ በመሆኑ  የፖሊስ አባሉ የወሰደው እርምጃ ተገቢነት እንደሌለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። በቀጣይ የፖሊስ አባሉ ላይ የሚኖረው የወንጀል ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ በተቋሙ የስነ-ምግባር መመሪያም አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል፡፡

አዛውንቱን የደበደበው ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ዋለ❗️ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ምዕራብ ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በስራ ላይ የነበረ ኮንስታብል ጋትኦች ፖል የተባለ የፖሊስ አባል አንድን ግለሰብ በመምታት በፈፀመው ድርጊት በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ይገኛል፡፡ የፖሊስ አባሉ በሰጠው ቃል በወቅቱ በአካባቢው ሲጓዝ  ግለሰቡ ምንም አይነት መነሻ ምክንያት ሳይኖራቸው  ማንነትን መሰረት ያደረገ ክብረ ነክ ስድብ ስለሰደቡት ስሜታዊ ሆኖ የወሰደው ያልተገባ እርምጃ  መሆኑን  ገልጿል፡፡ ፖሊስ ባሰባሰበው መረጃ በስፍራው የነበሩ ሌሎች ሰዎችም ኮንስታብል ጋትኦች  ድርጊቱን የፈፀመው የግለሰቡን ስድብ ተከትሎ እንደሆነ በማረጋገጥ ለፖሊስ ቃላቸውን መስጠታቸውን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን፤ ፖሊስነት ስሜታዊነትን በማስወገድ በትዕግስት እና በብስለት ሃላፊነትን መወጣት የሚጠይቅ ሙያ በመሆኑ  የፖሊስ አባሉ የወሰደው እርምጃ ተገቢነት እንደሌለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። በቀጣይ የፖሊስ አባሉ ላይ የሚኖረው የወንጀል ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ በተቋሙ የስነ-ምግባር መመሪያም አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል፡፡

ለገነነ መኩሪያ /ሊብሮ/ አበበ ማንደፍሮ ምርጥ ከሚባሉት ጓደኞቹ አንዱ ነው። መቼም ገኔ የትኛውንም መረጃ ሲሰጠን ዘና እንድንል ይፈልጋል። "የት እንደተዋወቅን ታውቃለህ?" ይላል። "ዛፍ ላይ!" አስ
ለገነነ መኩሪያ /ሊብሮ/ አበበ ማንደፍሮ ምርጥ ከሚባሉት ጓደኞቹ አንዱ ነው። መቼም ገኔ የትኛውንም መረጃ ሲሰጠን ዘና እንድንል ይፈልጋል። "የት እንደተዋወቅን ታውቃለህ?" ይላል። "ዛፍ ላይ!" አስቡት የእኔ የምትሉትን ጓደኛ ዛፍ ላይ ስታገኙት። መቼም 'እንዴት?' ማለታችሁ አይቀርም። እንዲህ ሲል ዘና ያደርጋችኋል "...ተማሪ እያለን ነው። ተደብቄ ሰው ጊቢ እገባለሁ። ዛፍ ላይ ወጥቼ ኮክ ስቀጥፍ የሚንኮሻኮሽ ድምጽ ሰማሁ። ዘበኛ የመጣ መስሎኝ ነበር። ሳይ ዘይቱን የሚቀጥፍ ሰው ነው። ሁለታችንም የያዝነውን ይዘን አብረን መሄድ ጀመርን። እኔ ኮክ እሱ ዘይቱን እየተሰጣጠን አብረን ተጓዝን። ሌላ ጊዜም መምጣት እንዳለብን ተነጋገርን። እስከዛሬም ይኸው አብረን ነን!" የሜታ ቢራ ተጫዋች እያለ ደግሞ በፍጻሜ ጨዋታ ለበረኛ አቀብላለሁ ብሎ ራሱ ላይ ጎል ማስገባቱን ፈገግ እያሰኘን ለተወዳጅ ሚዲያ ገልጾ ነበር። " በታሪክ ብቸኛው ሰው ነኝ... አሸናፊው ቡድን የተጋጣሚው ተጫዋች አግብቶለት ዋንጫ ሲበላ!" ይላል። ይሄኛውን ጎል ጨምሮ በዓመቱ ውስጥ አምስት ጊዜ ራሱ ላይ ማግባቱን በማስታወስ "ራሴ ላይ የማገባው የጎል ድርቅ ሲኖር ነው... እዚያ ማግባት ካልቻልክ እዚህ ታገባለህ" ይላል በቀልድ መልክ። ገነነ ተንቀሳቃሽ ቤተ- መፅሐፍ ነው። ሁለ ገብ አዋቂ። ወደ ስምንት የሚጠጉ መጽሐፍትም ሰጥቶናል። * ኢህአፓና ስፖርት 1፣2፣3 * ኢትዮጵያዊ ስልጣኔ * የእግር ኳስ ወጎች * የአሸናፊ ግርማ የህይወት ታሪክ * ፍትሐዊ የጠጅ ክፍፍል * መኩሪያ ይጠቀሱለታል። ገነነ መኩሪያ መጋቢት 5 ቀን 1957 ዓ/ም ነው ይርጋለም የተወለደው። ነፍስህ በሰላም ትረፍ፣ለቤተሰቦቹ፣ለወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ይስጣችሁ። 👆 (በውድነህ ክፍሌ)

ቀደም ሲል ቋንቋን በተመለከተ በፃፍኩት ፅሁፍ ላይ ማብራሪያ አግኝቻለሁ:: 12ኛ ክፍል ላይ አማርኛ ፈተና መሰጠት ከቆመ እንደቆየ ተረዳሁ:: አሁን ላይ አዲሱ ነገር ትምህርቱም እንደማይሰጥ መገለፁ ነው:: የትናንቱም የዛሬውም ወንጀል ነው:: ትምህርቱም ፈተናውም እስከ መጨረሻው መሰጠት ነበረበት:: በአውሮፖ ውስጥ ቋንቋና ሂሳብ ዋና የተማሪዎች መለያ መስፈርቶች ናቸው:: ሆላንድ ውስጥ ተማሪዎች እስከ 12ኛ ክፍል ደች ዋና ትምህርት ሆኖ ይሰጣል :: በእኛ ሃገር ይህ አለመደረጉ ትክክል አይደለም:: ምክንያቱም የስራ ቋንቋና ብሄራዊ መግባቢያ እስከሆነ ድረስ ትምህርቱም ፈተናውም መሰጠት አለበት:: አንድን ቋንቋ ለማሳደግ ነባሩን መግደል ወንጀል ነው::

የዚህን ሰነድ ትክክለኛነት የሚያረጋግጥልኝ ይኖራል? በውስጥ ፃፉልኝ:: እውነት ከሆነ ጣሊያን በየት ዞሮ መጣ የሚያስብል ነው:: በየት ሃገር ነው አንድ ሃገር የራሱን የስራ ቋንቋ ከትምህርትና ፈተና
የዚህን ሰነድ ትክክለኛነት የሚያረጋግጥልኝ ይኖራል? በውስጥ ፃፉልኝ:: እውነት ከሆነ ጣሊያን በየት ዞሮ መጣ የሚያስብል ነው:: በየት ሃገር ነው አንድ ሃገር የራሱን የስራ ቋንቋ ከትምህርትና ፈተና ውጭ አድርጎ የሌላ ሃገር ቋንቋ የሚያስፈትነው? የቱንም ያክል አማርኛን ቢጠሉ: በዚህ ደረጃ ይወርዳሉ ብየ አላስብም ነበር:: እውነትካልሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ:: ከእንግዲህ እንደ ሃገር የሚያግባባን ቋንቋም የለም:: ችግሩ ከላይ እስከታች እንግሊዝኛውንም በዳዴ ነው የሚያስኬዱት::

የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ! በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በደበሶ ከተማ የቃና ዘገሊላ በዓል እያከበሩ ባሉ ምዕመናን ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሰባት ሰዎች በላይ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ በር
+1
የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ! በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በደበሶ ከተማ የቃና ዘገሊላ በዓል እያከበሩ ባሉ ምዕመናን ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሰባት ሰዎች በላይ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ በርካታዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ይገኛሉ። ከሟቾቹ መካከል ህጻናትና የጸጥታ አካላት እንደሚገኙበት የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዘግቧል። አደጋውን ያደረሰው ከድሬደዋ መስመር እየመጣ ያለ ከባድ የጭነት ተሽከሪካሪ ሲሆን የቃና ዘገሊላ በዓልን ለማክበር ከጥምቀተ ባህር በመመለስ ላይ ባሉ ምእመናን ላይ በፍጥነት በማሽከርከር እንደሆነ ሀገረስብከቱ አሳውቋል።

ሰሞኑን በእንጅባራ ከተማ ጃዊ ላይ ረዘም ላለ ቀናት በጀግናው ሻለቃ ቻሌ መንግስቱ እና በአራዊቱ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት መካከል ጦርነት ሲካሄድ ሰንብቷል - እናም የጃዊ ፋኖ እጅግ አስደናቂ ጀብድ ሲፈጽም ሰንብቷል። ይህ በአዊ ዞን እየተንቀሳቀሰ ያለው የጃዊ ብርጌድ አራዊቱ ሰራዊት መተከል ዞን ካሉ ልዩ ኋይል ሚኒሻ እና እንዲሁም አንዳንድ የአመራር አሸርጋጆች በሌላ ስማቸው ራሳቸውን ማህበራዊ አንቂ ብለው ከሚጠሩ ሰዎች ጋር በጥምረት ውጊያ ቢከፈትበትም የጃዊ ብርጌድ ግን ጠላትን ከማጋደም ወደ ኋላ አላለም ። የአራዊቱ ሰራዊትን ሙትና ቁስለኛ ሲሆን እሬሳውንም እየለቀመ በጃዊ ስኳር ፋብሪካ ሲያጠራቅም እንደነበር የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። በዚህ አጋጣሚ በመተከል ዞን ውስጥ በተለይ ፓዊ እና ፓዊ ዙሪያ የማህበራዊ አንቂ ነን የምትሉ ሰዎች ብዙ መረጃዎች ውስጥ ለውስጥ እየደረሰን ስለሆነ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን በተጨማሪም ሲሉም ገልጸዋል ። በተጨማሪም እስከ ግልገል በለስ ድረስ ያለው ማህበረሰብ በአብዛኛው አማራ ስለሆነ ሲሆን ሲሆን ለእኛ ለጃዊ ብርጌድ ምቹ ሁኔታ መፍጠር አጋር እንድትሆኑ ካልሆነ ግን ከመንገዳችን ላይ እንቅፋት እንዳትሆኑብን እና ከአመራሩ ጋር ሁናችሁ የምትሰሩትን ፕሮፓጋንዳ እንድታቆሙ እናሳስባለን ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል!

አቶ ለግሰ ቱሉ፣ የአማራ ሕዝብን ወክለው ነው በብልፅግና የተሾሙት። ተፅፎ የሚሰጣቸውን የአማርኛ መግለጫ በቅጡ ማንበብ ዳገት የሚሆንባቸው። ምፀቱ አማርኛን መፃፍ እንኳ የማይችሉ የመንግስት የኮሚኒኬሽ
+2
አቶ ለግሰ ቱሉ፣ የአማራ ሕዝብን ወክለው ነው በብልፅግና የተሾሙት። ተፅፎ የሚሰጣቸውን የአማርኛ  መግለጫ በቅጡ ማንበብ ዳገት የሚሆንባቸው። ምፀቱ አማርኛን መፃፍ እንኳ የማይችሉ የመንግስት የኮሚኒኬሽን ምኒስትር መሆናቸው ነው። ቀድሞ በኢህዴን ውስጥ የትህነግ ምንጣፍ አንጣፊ ነበሩ መሆናቸውን አንዘነጋም።   ከዚህ ቀደም ብልፅግናን አውቀውም ይሁን ሳያውቁ “ብልግና” ብለው ነበር የገለፁት። ዛሬ ደግሞ ለክርስትና እምነት ተከታዮች እላለሁ ብሎ የክርስትያን ሲል በገፁ ላይ ፅፏል።   እንግዲህ ብልፅግና እንደዚህ ባሉ ምኒስትሮች መታጨቁ ነው የቁልቁለት ጉዞውን ያፋጠነለት።