cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services

በዚህ ገፅ ስለ ገቢና ወጪ ንግድ አሰራር ፣ሰነዶች አይነትና አዘገጃጀት ፣ስለ ጉሙሩክ፣ አዳዲስ መረጃዎች፣ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች አለመአቀፋዊ እና አገራዊ መረጃዎች በፍጥነት እንዲደረሰው፣ ጠቃሚ ትምህርቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ እናደርጋለን፡፡ አላማችን የገቢ እና የወጪ ንግድ አሰራረውን ማገዝ ነው፡፡ www.sebeztraining.com

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 370
مشترکین
-124 ساعت
+37 روز
-2030 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ከወጪ ንግድ ከ2.5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ መግኘቱ ተገለፀ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር እንደገለፀዉ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ ከ 2.5 ቢሊየን በላይ የአሜሪከን ዶላር ገቢ መገኘት ችሏል ብሏል። ሚንስትሩ እንደገለፀዉ በዘጠኝ ወሩ 3.56 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ  2.511 ቢሊዮን ዶላር ወይም 70.49 በመቶ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ ከተገኘው ገቢ የግብርና ምርቶች 73.6%፣ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 51.54%፣ ማዕድን ዘርፍ 66.53% እዲሁም  ኤሌክትሪክና ሌሎች ምርቶች 71.25% ዕቅድ አፈፃፀም ማሳየት ችለዋል በማለት በሪፖርቱ ገልጿል ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ክትትል የሚደረግባቸው የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ምርቶች፣ የብርዕና አገዳ ሰብሎች፣ የጫት ምርት፣ የቁም እንስሳት እና የደንና ደን ውጤቶች እንዲሁም የቁም እንሰሳት መኖ  699.11 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘት ችሏል ማለቱን ከተቋሙ ለካፒታል የደረሰዉ መረጃ ያመለክታል ። ምንጭ፦ ካፒታል ጋዜጣ @sebeztraining
نمایش همه...
👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአጭር ጊዜ ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ስልጠና በኦንላይን ማታ ከ1፡00 በአካል እሁድ እና ቅዳሜ ስፔሻል ክላስ በልዩ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ 30% ቅናሽ • Documentation • Payment System • Import Procedure • Export Procedure • Government Regulations • Customs Procedure • Logistics and Transportation • Ethiopian Single Window System • FOREX Source and Usage • Networking Opportunity • And Many more ስልጠናው በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው እና በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ስልጠናዎችን በወሰዱ ባለሙያዎች የሚሰጥ ነው፡፡
نمایش همه...
👍 13
የፕላስቲክ አምራቾች የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶችን በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ! 👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛👛 አካባቢን ሊበክሉ የሚችሉ ስስ ፕላስቲኮችን የሚያመርቱ ድርጅቶች የአካባቢ ብክለትን የሚቀንሱ የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶች በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡ ፕላስቲክ በማምረት የተሰማሩ ድርጅቶችና ባለቤቶች ከተፈቀደላቸው 0.03 ማይክሮ ሜትር በታች ሲያመርቱ ከተገኙ፣ ከመዝጋታቸው ባሻገር፣ ከሦስት ዓመት እስከ አሥር ዓመት የእስር ቅጣት እንደሚያስከትልባቸው ተገልጿል፡፡ አካባቢን የሚበክሉ የፕላስቲክ ምርቶች ውፍረታቸው ከ0.03 ማይክሮ ሜትር በታች ሆነው እንዳይመረቱና አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ፣ በፕላስቲክ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ታክስ መጣል፣ እንዲሁም በካይ ይክፈል የሚለውን ተግባራዊ ማድረግ  የሚሉትና ሌሎች ምርቶቹን ለመቀነስ የሚወሰዱ ዕርምጃዎችን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡  ምንጭ:-ሪፓርተር       ✍    Sebez Training and Consultancy ✍
نمایش همه...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበዝ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት Sebez Training and Consultancy services የአጭር ጊዜ ስልጠና ምዝገባ ጀምሯል
نمایش همه...
3👏 3
نمایش همه...
TikTok · ገቢና ወጪ ንግድ መረጃ Imp Exp info

Check out ገቢና ወጪ ንግድ መረጃ Imp Exp info’s video.

2
የጉሙሩክ ኮሚሽን በቀን መጋቢት 9 2016 በቁጥር 4.0/1260/16 ለአዲስ አበባ ኤርፖረት ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት፣ ለአዲስ አበባ ቃልቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት እና ለሞጆ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በፃፋው ደብዳቤ ክልከላ ተደርጎባቸው በጉሙሩክ ኮሚሽን መጋዘን ባሉ ተሽከርካሪዎች ላይ ውሳኔ እንደተሰጠ አሳውቋል፡፡ በዚህም መሰረት 1.  ኮሚሽኑ ቀደሞ ማለትም የካቲት 14 ቀን 2016 በቁጥር 6/0686/16 በፃፈው ደብዳቤ መሰረት ከመጋቢት 22/2015 በፊት በህጋዊ መንገድ የባንክ ፍቃድ አግኝተው አገር ውስጥ ለገቡ ተሸከርካሪዎች 2.  በመመሪያ ቁጥር 66/2004 አንቀፅ 8/3 መሰረት በፍራንኮ ቫሎታ የራሳቸውን የውጭ ምንዛሪ ተጠቅመው በተመለሻ ኢትዮጵያውያን ስም የገቡ ተሸከርካሪች በአስር ቀናት ውስጥ ተገቢውን ቀረጥ እና ታክስ ከፍለው የጉሙሩክ ስነ-ስርዓት ፈፅመው እንዲሰተናገዱ ውሳኔ ተላልፎላቸዋል፡፡ ተሸከርካሪው በተመላሽ ኢትዮጵያውን ስም የገባ ከሆነ  አስመጪዎቹ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ከተመለሱበት አገር የኢትዮጵያ ኢምባሲ ወይም ቆንሰላ የተሰጠ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ደብዳቤ እና ሌሎች ህጋዊ ሰነዶች እንድታቀርቡ ተበላችኋል፡፡
نمایش همه...
👍 4 1