cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

መንፈሳዊ ግጥም BY ESUBALEW___MESESRET

እግዘብሔርን አመስግኑ ቸር ነዉና ምህረቱ ለዘላለም ናትና መዝሙር 118፣1

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
212
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ተውት አትምከሩኝ ከወርቅ የነጠረ በእሳት ተፈትኖ ልቤን የነሳ ድል እራሱን የሰጠኝ አንድም ሳያጎድል በብልጭልጭ ነገር ነፍሴን ሳደልላት ንፁህ ፍቅሩን ብቻ ሳይሰስት ያደላት ራሱን አዋርዶ ዘንግቶት ዙፋኑን እኔን አስቀድሞ እሱ ረስቶ ክብሩን ልጁ ለኔ ደስታ በጦር የተወጋ እሱ ለኔ ሀጥያት የከፈለው ዋጋ የወደደኝ ያፈቀረኝ በደሙ አጥቦ ያከበረኝ ከመቅበዝበዝ ያሳረፈኝ ነፃነቴን ያወጀልኝ መፅናናትን የላከልኝ በምድረ በዳ ላይ በዚያ በቃጠሎ የሆነልኝ ጥላ ያኔ ተሸክሞኝ ሆኖልኝ ከለላ ጊዜና ሁኔታ የማይለዋውጠው ዛሬም እየሱስ ከእኔ ጋራ ነው ያኔ... ያኔ...... ስፈራ ስጨነቅ ቀንበር ተጭኖብኝ እንዲያው ስቅበዘበዝ እንዲያው ስንከራተት በድቅድቅ ጨለማው ማንም በሌለበት ከጠላት መንጋጋ መውጫ መንገድ ጠፍቶኝ ነገር ጨላልሞብኝ የሞት ፍርሃት ተጭኖብኝ ጨለማው በርትቶ ማይነጋ ሲመስል ማዕበሉም በርትቶ አላቋርጥም ሲል አለውልህ አለኝ የሚያስጨንቅህን በእኔ ላይ ጣል አለኝ ታድያ ይሄ አባት ምንም ሳትሰራ ነፍሴን የወደዳት የቀደሰኝ ያፀደቀኝ ከአባቱም ጋር ያስታረቀኝ ሰላሜ ነው ለአዕምሮዬ መሸሸጊያ መመኪያዬ የማይሰለች እረኛዬ የማይደክም ጠባቂዬ የነፍሴ መድኃኒት የህይወቴ ጌታ የታደገኝ ከመከራ እርሱ ብቻ እየሰራ ወዳጄ ነው አለኝታዬ የቅርብ አፅናኝ መካሪዬ መሰላል ነው ለእኔነቴ መድረሻዬ ወደ አባቴ ደም ግባቴ መዓዛዬ አለቴ ነው መሠረቴ የዘላለም ሽልማቴ በመሆንህ አንተ የእኔ ሰላም አለኝ በዘመኔ ፍፁም ምሉዕ ሆነህልኝ እኔ ያልኩትን ጥያለሁኝ አዲስ ፍጥረት ሆኛለውኝ እፎይ ብያለሁኝ ባንተ ተረጋጋሁ ሰላሜን አገኘሁ ከጣሪያዬ በታች በጓዳዬ ገብተህ ስራዬን ሰራኸው ጎዶሎዬን ሞልተህ ሸክሜን አራግፈህ ለአንድ ለተናቀ ሰላምን ሰጠኸው ክብርን አጎናፅፈህ እንደ ሰው አይደለም ወድቄ አልተወኝም ፊቱን አዙሮብኝ እኔን አልካደኝም አይጥልም አይረሳም ሰው ማድረግ ይችላል ከአመድ ላይ ያነሳል ታድያ ለዚ ጌታ ምስጋናን እንጂ ክህደት አልከፍለውም ተወው አትበሉኝ መቼም አልተወውም እንደ እየሱስ ፍቅር ዳግም ላታፈራ ላትሸለም ምድር ተውት አትምከሩኝ ተወው ብሎ ምክር። ✍Abaki @MenfesawiGixm @MenfesawiGixm 👆👆👆👆👆👆👆👆👆       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺            Join us          🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲  ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
نمایش همه...
2👍 1
✍✍ቀድሞ በሞተልኝ ጨለማዬ በርቶልኝ-ሞቴ ተገፍፎልኝ በግርግሩ ዓለም-ሠላም ያየሁኝ የድምጼ ቅላጼ-ያማረ የሆነው የአረማመዴ ኮቴ-በእውነት የተዋበው የተዛባ ሕይወቴ-መስመር የያዘው የሞት ወጥመድ-ከመንገዴ የተወገደው የዘላለም ሕይወት-ተካፋይ የሆንኩኝ ከተዎርዋሪ ጦር-በክንዱ የተከለልኩኝ የተማሰው ጉድጓድ-ተደፍኖ የተሻገርኩኝ በብጥብጡ ዓለም-እርጋታን ያገኘሁኝ የኃጢአት ኪስ-ለዘላለም የተሰረየልኝ የሕይወት መታወቂያዬ-በፍጹም የታደሰልኝ ሕይወትን በደስታ-በእጄ የጨበጥኩኝ ቀድሞ በሞተልኝ ነው-ዛሬን ያየሁኝ። ቀድሞ በሞተልኝ (ቁጥር 2*)      ተጻፈ በshallom(soለn) Date:15/4/14 e.c @MenfesawiGixm @MenfesawiGixm 👆👆👆👆👆👆👆👆👆       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺            Join us          🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲  ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
نمایش همه...
1
አለ..! ለደግነቱ ለመልካምነቱ ደግነቱ እግዚአብሔር አለ ከማግኘት ከማጣቴ ያልዋለ ደክሜ ዝዬበት ከሱነቱ የማያወጣ ትየዉ እስቲ ያለኔ የማይል ትቀጣ በአባይ ሚዛን መች ሊመዝን እግዜሩ እንደሆነ አለ አወይ ፍንክች እንዳላለ   አለ.......! ያው በክረምቱ በማያበቃው ምህረቱ የመጣው ሲያፈገፍግ ግዚያቱ ሲኖጉድ እንዳልሄደ ሲመልሰው የሰውኛው መንገድ ደግነቱ እግዚአብሔር አለ ከማግኘት ከማጣቴ ያልዋለ ወዳጅ ባይ ውስጡ ሸንጋይ ፍቅሩ በራድ ቢያከትም ቢኖግድ ሰው ነኝ እና ቢያይል ፈተናው እኔ ግን እንዲህ... ነዉ የምለው ደግነቱ እግዚአብሔር አለ!! 🙇 👉  Siyana  😊 @MenfesawiGixm @MenfesawiGixm 👆👆👆👆👆👆👆👆👆       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺            Join us          🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲  ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
نمایش همه...
👏 1
ራሴን ላጠፋ ነው ህይወት እጅግ መራኝ መኖር አስጠልቶኝ ይህ ዓለም ብቀፈኝ ደስታዬን ብነፍገኝ። መገላገል ስሻ የዝን ዓለም መርሻ ሞት ሆኖ ምርጫዬ የጭንቅ ማምለጫዬ አይደልም ምክንያቴ ራሴን የማጥፋቴ። ግን በተቃራንው የህይወት ጣፍጦት ነው የመኖር ጉጉት ነው ራስን የሚያስጠፋው። ያለም ማብረቅረቋ ለአይን ማስጎምጀቷ ይህ ነው የሚገድለኝ መሞቻም የሆነኝ ከራሴ ሚያሸሸኝ እንዳልኖር ሚያግደኝ። ስለዚህ ሞታለው መኖር አቆማለው። ይልቅ ለሁላቹም መኖር አይበቃቹም? መሞት አያምራቹም? እኔ በበኩሌ ኑሩ አልላቹም የኔን ምክር ሰምታቹ ሙቱ እባካቹ። ታድያ ስትሞቱ ምክሬን ከቶ አትርሱ መብራት አትጨብጡ መርዝም እንዳትጠጡ ደም ስር አትቁረጡ ውሃ ውስጥም አትግቡ፣ እንዳትታነቁ አንዳቸውም ብሆኑ አይገሉም እውቁ። ራስን ለማጥፈት የኔን ምክር ስሙ እኔነት ገድላቹ በእየሱስ ለምልሙ። መኖር አቁማቹ የሱሴን አኑሩ መኖር አጓጉቷቹ ያለሱ እንዳትቀሩ ጊዜው ከማብቃቱ ራሳቹን አጥፉ ጳውሎስን መስላችሁ በመሞት እረፉ ሀናን መስላችሁ በጸሎት አትርፉ በእግ/ር ክብር እንዴ ኤልያስ ተንሳፈፉ የዓለም መብረቅረቅ ግዝያዊ ነውና መኖርን አቁሙ ራሳቹን አጥፉና።    ✍️T.L @MenfesawiGixm @MenfesawiGixm 👆👆👆👆👆👆👆👆👆       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺            Join us          🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲  ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
نمایش همه...
👍 2 1😱 1
✍✍የጊዜው አሜንታ ሲሰጥ ትምህርት፣ በቆንጆ ስብከት፣ እውነቱን ለማስተጋባት፣ በሰኞ በሰንበት፣ በበጋ በክረምት፣ በድካም በብርታት፣ ሰባኪው የላኪውን፣ ስናገር እውነቱን፣ ሲያስተጋባ መልዕክቱን፣ ሳያስቀር ሀቁን፣ አሜን ስሉ ምዕመኑ፣ ስደረግላቸው ላመኑ፣ ሳይፈጠር ጫጫታ፣ እንደጊዜው አሜንታ፣ ምዕመኑ በደሰታ ፣ ተቀብለው ሳያመነታ፣ በአባቶች ዘመን ያኔ ድሮ፣ እግ/ርም ያደርግ ነበረ ተናግሮ። የጊዜው አሜንታ፣ ሲፈጥር ጫጫታ፣ ምዕመኑ ሳይቀበል፣ ትምህርቱን በትክክል፣ ወንበር ሲሰበር፣ ስፈጠር ክርክር፣ የምመስል አምልኮን፣ የሳተ ተልዕኮን፣ እውነት የሌለበት፣ ተስፋ ያልተገኘበት፣ ጌታን የማያስከብር፣ የማይሆን ለስሙ ክብር፣ ወደ ማደሪያው የማይገባ፣ ምዕመኑን በደስታ የማያግባባ፣ እየፈጠረ ጫጫታ፣ ሆኗል የጊዜው አሜንታ። ድሮ ዘመን፣ ስሉ አሜን፣ ሳይሰበር ወንበር፣ ሳይፈጠር ግርግር፣ ሁሉም በደስታ፣ ተቀብለው በእርጋታ፣ ልባቸው ሳያመነታ፣ ስሉ ኢየሱስ ጌታ፣ ስሰራ ያመኑት፣ ሲሆን ተስፋ ያደረጉት፣ ጌታን አክብረው፣ አልፈዋሉ ለጌታ ተሰውተው። አያርገው የዛረውን፣ አይበለውና የአሁኑን፣ የአሁኑ አሜንታ፣ ሲፈጥር ጫጫታ፣ ሶፍት ስወረውር፣ ሰው ስንፈራፈር፣ ማስተዋል ስከፋ፣ ዕውቀት ስጠፋ፣ ከደም ከስጋ፣ አሜን ሲል ሳይረጋጋ፣ የጊዜው አሜንታ፣ ተበላሽቷል በመሆኑ ጫጫታ። በShallom (ሶሌን) Date:5/8/13 e.c @MenfesawiGixm 👆👆👆👆👆👆👆👆👆       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺            Join us          🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲  ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
نمایش همه...
👏 2 1
............እኔም አልክደውም አለም ሳይፈጠር ሳይመጣ ሰማይ በላይ የነበርከው ከአብ አንድ ላይ አባቶች ያወሩት የነቢያት ትንቢት እውነት ብርሃን መንገድና ህይወት ከመጣህማ ቤቴ ሆነህ ስጋ ለባሽ ለተገፋው አጋዥ ለተራበ ደራሽ ገብተህ ከጓዳዬ ስትሆን ከኔ ጋራ ፍቅር ያዛት ነብሴን በሰራውኸው ስራ አምላክነት ስትችል ሆነህ ሀጥያተኛ ለነብሴ መድህን ሆነህ ፈራጅ ዳኛ ካለሁበት አዘቅት ከድቅድቅ ጨለማ ከሀጥያት ባህር ውስጥ ከሙታን ከተማ ባለዕዳ ሳለሁ በደም የሚከፈል ቀንበሬም ከባድ ነው ይዞኝ ሚከት ገደል ሰው ሚፀየፈኝ የሆንኩ መፃተኛ ህመም የከበደኝ ሳለሁ በደለኛ የበግና ዋኖሱ የእርግብ የኮርማው ሊከፍለው አልቻለም ብዙ ነው እዳው ሮጬ እንዳልሸሽ ሩሩሩቅ ነው ከተማዋ ይዘው ይንዳይገድሉኝ የመማፀኛዋ ..........አንተ ግን.....አንተ... አንተማ የዘላም እረፍት የህይወት ዉሃ ነህ ለተጠማ አየሄኝ ከሰማይ የቀንበሬን ክብደት መዳን እንደማልችል እንዲኖረኝ ህይወት መጣህልኛ ወደ እኔ ከከበረው ቦታ ዕዳዬን ከፍለከው ዋልክልኝ ዉለታ ሊገድሉኝ ባሉት ፊት ፍርዴን አቀናህና በሰላም ሂድ አልከኝ አባ የኔ ጀግና .......ታዲያ.....ታዲያ ቆይ እንዴት? ምንሰጠህ ምትሉኝ ጌታ ጌታ ነው ስል ማን ነበር ሚያድነኝ ሞቶልኝ በመስቀል ደግሞም አላፈሩም የእምነት አባቶቼ እኔም አላፍርበት ግርማውን አይቼ ጴጥሮስ ችኩል ሳለ በስተመጨረሻ ለሞት አልሰሰተም አውቋልና መዳረሻ እንደውም ሲሰቅሉት በእንጨት ጠፍረው ዘቅዝቀው ሲሰቅሉት በሚስማር ቸንክረው ካልካደ ያ ከሀዲ ፈሪ የነበረው እኔም አልክደውም ኢየሱስ ጌታ ነው ዉሃ በሌለበት ኖኅ መርከብ ከሰራ በእምነት ካገባ ፍጥረትን በተራ ሰማይ ሲነደል አለት ተሰንጥቆ በእምነት ታዘዘ ሊያደርግ ያለውን አውቆ እኔም አምነዋለው አትነዝንዘኝ ጠላቴ ሸለቆ ዉሃ ሞልቶት ያውቀዋል አባቴ በእዕድሜ መጨረሻ አብርሃም ከወለደ ሳራም ከሳቀች ይሰሀቅ ከተወለደ ታዲያ ምን አሰጋኝ ለምን ብዬ ልካድ በባህሩ ላይ ተራምዶ ካበጀልኝ መንገድ ክፋት በተሞላ በሰዶም ከተማ በእሳት ሲጠፉ ሀጥያን በጨለማ ከኖረ ፃዲቅ ሎጥ ነብሱን አስጨንቆ ካመለጠ በእምነት እግዚአብሔርን አውቆ እኔም እኖራለሁ በዚህ ክፉ አለም ፊትለፊት እስካየው የሰላሙን አለም አምነዋለሁ ጌታን ኤልሻዳይ ነውና ያለ የነበረ የሚኖር ነውና ✍✍✍ተፃፈ በጌታሁን አናሞ 22/12/2015✍✍✍ @MenfesawiGixm 👆👆👆👆👆👆👆👆👆       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺            Join us          🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲  ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳe
نمایش همه...
👍 5 2
ለሠርጉ ማለዳ ለሠርጉ ማለዳ ለሙሽራዉ መምጣት  ዝግጅቱ ጦፎ በዝቶ ሽር ጉድ ማለት ሁሉም ስሯሯጥ በየፍናዉ አዉቆ የስራ ድርሻዉን ሁኔታዉም ይናገራል ግዜዉም ሰዓቱን፡፡ መመረጣቸዉን ያወቁ ደግሞም መጠራታቸዉን ንጉሱን ለመቀበል እንዳለባቸዉ መዘጋጀት ስተጉ ነበር እነዚያ አስርቱ ቆነጃጅት መብራታቸዉን ይዘዉ ዘይታቸዉን ሞለተዉ በመቅረዝ በብርቱ መጠባበቅ በፅናት በመቆም ወደ ተዘጋጀላቸዉ መዕድ በደስታ ለመግባት ተዉበዉ ሲጠባበቁ ሊያዩ የናፈቁትን፡፡ ነገር ግን በዘገየ ግዜ ሙሽራዉ ሁሉም ስላቸዉ እንቅልፍ እንቅልፍ ተኝተዉ ሳሉ ሲሆን እኩል ሌሊት ድንገት ያልታሰብ ነገር ሆነና በማታ ሙሽራዉ እየመጣ ነዉ ተዘጋጁ የሚል ሁካታ፡፡ እንግዲህ አምስቱ ቆነጃጅት ተነሱና ለዝግጅት አልተቸገሩም ለመቀበል ሙሽራዉን ከደጅ ሞልተዉት ነበርና ዘይታቸዉን በመቅረዝ እንዳይጠፋባቸዉ መብራታቸዉ ለማቀጣጠል፡፡ ምንም ዝለት ድካም ብበረታባቸዉም አቅም ከድቷተዉ ቢያይልባቸዉ መከራም ዉጣ ዉረዱ የሚያስቆም ቢመስልም ከትጋት የሚጠብቁት ሙሽራ እንደምመጣ ስለሆኑ እርግጠኛ ተቋቁመዉታል ችግሩን የዚህን ዓለም ፈተና መብራታቸዉ በርቶ ስለነበረ ሞልቶ ዘይት በመቅረዛቸዉ ጊዜዉን አልተዘናጉትምና መምጫ የገታቸዉን በደስታ ተቀበሉት ሊያርፉ ከመከራቸ፡፡ ደግሞም ነበሩ በመካከላቸዉ አምስቱ ሰነፎች መብራታቸዉን ይዘዉ ነገርግን የለለዉን ዘይት ቀኒቱንና ሰዓቲቱን ያላዉቁት ዝንጉወች ዘይቱም አለቀና ከመቅረዛቸዉ ጠፋ ብርሃናቸዉ ቀድሞ አይተዉ ስጎድል ባለመዘጋጀታቸዉ ገና ለመግዛት ሲሄዱ ስንደፋደፉ ስሯሯጡ ለካስ ዘግይተዋሉና ተዘግቶባቸዉ በሩ ከቶ አላወኩአችሁም ተብለዉ ጎደሉ ከመንግስቱ፡፡ እኛ ግን እንደ እንግዳ እንደሚሄድ ሌላ ሀገር እንደሚናፍቀዉ ቤቱን ቶሎ ለመድረስ እንደማያጓጓዉ ሁሉ የዚያ ቦታ ኑሮ ከቶ እንደማይቆይ ተረጋግቶ ረግቶ ልቡም እንዳለ በዚያ መዝገቡ ባለበት ሳይዘን ስበቱ የምድር የዚህ ዓለም ራሳችንን እናዘጋጅ ሲመጣ እንዳንቸገር ለመሄድ:: ሙሽረዉ መምጣቱ አይቀርም የየዘገየ ብመስለም የተዘጋጁትን ለመዉሰድ ልብሳቸዉን አጥበዉ በበጉ ደም ከቶ ወደማይኖርባት ለቅሶና ሀዘን 2* በጉ እራሱ ብርሃኗ ወደሆነባት ሀገር አመረተች አሰፋ 18/12/15 ሀዋሳ @menfesawiGixm 👆👆👆👆👆👆👆👆👆       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺            Join us          🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲  ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
نمایش همه...
3👍 2
( ርዕስ );- ታድያ ለምን ገና ዓለም ስትፈጠር ሰውም ሲበጅ ከምድር አፈር መንፈስ በእርሱ ከነበረ ታድያ ለምን ሰው ከሰረ በገነት ውስጥ ሲመላለስ ሲነጋገር እርስ በእርስ ከሸፈነው የአንተ ፀጋ ታድያ ለምን ተዘናጋ ሞትን ሞቶ ገነት ቀረ በእግዜር ቁጣ ተባረረ ምድርም መጣ በቅጣቱ የከበረው አይ ሰው ከንቱ ፍቃደኛ ሆነው ያለ አንዳች ክፍተት መስዋዕት ከሰዉ ለውዴ በማለት ታናሽ ልቡን ከከፈተ ታላቁ ግን ከሸፈተ ታዲያ ለምን አቤል ሞተ ሁሌ መልካም በህይወቱ ክፋት ማያውቅ ማንነቱ ባለጠጋ በምድ ላይ እያንዳንዱን እኩል የሚያይ ቅን በመሆን የተለየ ኢዮብ ታማኝ ከነበረ ታድያ ለምን ተሰቃየ ምድር መቶ ልክ እንደሰው አፈር ስጋን የለበሰው ፍጹምፃድቅ ከነበረ ታዲያ ለምን አምላክ ሞተ ለምን ማለት ምን ይበጃል እርሱ ሁሉን ያዘጋጃል ባለ ብዙ አዋቂ ነው በስራውም ትክክል ነው የማይባል ከቶ ለምን ደግሞም ያያል እያንዳንዱን ሁሌ ታማኝ ደግ እረኛ ለመንጋው ሲል የማይተኛ ቢደገፉት አስተማማኝ ቢታመኑት የማይከዳ መድኅኒት ነውለተጎዳ ስለዚህ.... ስለሰጠን እናመስግን ቢነሳንም እናከብረው ሁሉም ያልፋል ለጊዜው ነው !!        ✍Selemon @menfesawigixm @menfesawigixm 👆👆👆👆👆👆👆👆👆       🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺            Join us          🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲  ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
نمایش همه...
👍 4 2
እውነትን መኖር      ለእውነት ቃል-ተሰውተው     አምላካቸውን-አስቀድመው እውነትን ኖሩ -ተሰጡ ለፈቃዱ በቅድስና ተጓዙ -በፍቅሩ በመንገዱ የአለምን ክብር -ሁሉን ትተው የክብር ጌታን -በልብ አንግሰው የልቡን ፈቃድ-የመውደዱን ሚስጥር የጎለጎታው-የመስቀል ፍቅር የተገለጠው -የሰማይ እውነት በእርሱ በማመን-በሚገኝ ድነት የሰው ልጅ አምኖ -እንዲፀድቅ ክርስቶስ በህይወቱ-እንዲደምቅ መጠራቱ ገብቶት-በዋጋ መገዛቱ ፍሬ እንዲያፈራ-እንዲበዛ በመክሊቱ ክብር ነው-የመኖር  ፀጋ ለናፈቀ ፊቱ-ለተጠጋ የበራ  በፍቅር -ያስመለጠ በወንጌሉ ገድል-የተገለጠ Join @menfesawiGixm
نمایش همه...
👍 4
ይበቃል ቅጣትህ ከሀጥያት ራቁ ባዕድ አታምኩ ቤታችሁ ይቀደስ በስጋ አትመኩ አምላካችሁ እኔ ነኝ አልፋና ኦሜጋ ነብሱን ያተርፋታል ወደኔ ሚጠጋ ብለህ የነገርከውን ኪዳንህን አፍርሰን በልብ ጓዳችን ላይ አለምን አንግሰን ለስጋችን ምኞት ሄደን ስንዳራ ሴት ከሴት ተጋብቶ ወንድም ከወንድ ጋራ የፍትወት ቃጠሎ ከመቅደስህ ገብቶ ክብርህ ብርቅ ሆነብን መንፈስህ ተለይቶ መሰዊያ ቀለለ በዘልማድ አምልኮ ሰላምና እረፍት ታጣ ሰይጣን ገባ ሾልኮ ሰሜን ምስራቅ ምዕራብ የደቡብ አበባ በቃኤል ሰይፍ ተቀልቶ በአቤል ደም ተቀባ የአንድ እናት ልጆች፣ ወንድም እና እህቶች የአምላክ ምሳሌ የምድር በረከቶች ምነካቸው ዛሬ ሲጋደሙ ስርቻ የከበረውን ጌታ ሊያረጉ መዘበቻ ኧረ ጌታ ኢየሱስ ዝምታህን ፈራን እንደ ሰዶም ገሞራ እሳት እንዳይበላን አውቃለሁ ታያለህ የሰማይ ጌታችን በእንባ እንመለስ ከስህተት ጎዳናችን አንተም ዝም አትበለን ተመልከት ወደኛ ይበቃል ቅጣትህ ፣ይቅር በለን ዳግመኛ እንመለሳለን አቤቱ መልሰን ከሰላሚቷ ሀገር በሰላም አድርሰን @menfesawiGixm
نمایش همه...
👍 4