cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ethiopian Coffee and Tea Authority

Ethiopian Coffee and Tea Authority

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
3 365
مشترکین
+924 ساعت
+617 روز
+21130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ኢትዮጵያ በሻይ ቅጠል ምርት ባለኃብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ትሻለች (አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር) የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ባለኃብቶች በሻይ ቅጠል ምርት በስፋት እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ። ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት ወደ ሥራ የተገባው የሻይ ቅጠል ምርትን የማስፋት ሥራ ጥሩ ጅማሮ ማሳየቱ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የዛሬ ሦስት ዓመት በሻይ ቅጠል ምርት ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነችውን ኬንያን ከጎበኙ በኃላ ተሞክሮውን ለማስፋት በስፋት እየተሰራ መሆኑም ተጠቅሷል። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ምርቱን ለማስፋት 460 ሚሊየን ችግኝ አባዝቶ በተያዘው በጀት ዓመት 30 ሺህ ሄክታር የሚሸፍን የሻይ ቅጠል ምርት መተከሉን ለኢዜአ ገልፀዋል። በሀገራችን በቀዳሚነት ተጠቃሽ የሆነው የውሽውሽና ጉመሮ ምርት በ5 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ብቻ ያረፈ እንደነበረም ነው የተገለፀው። በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት 950 ቶን በአግባቡ የተዘጋጀ የሻይ ቅጠል ምርት ለውጭ ገበያ በመላክ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ብቻ ተገኝቷል። ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ50 ሺህ ቶን ብልጫ ቢኖረውም አገሪቱ ካላት አቅም አንጻር ብዙ መሥራት እንደሚጠይቅ ገልፀዋል። ባለኃብቶች በዘርፉ በስፋት ባለመሳተፋቸው ኢትዮጵያ ካላት እምቅ ኃብት አንጻር ማግኘት ያለባትን የውጭ ምንዛሬ እንዳታገኝ እንቅፋት ሆኖባታል ተብሏል። እስካሁን ከሻይ ቅጠል የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ በዓመት ከ3 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር አለመብለጡንም ነው ዳይሬክተሩ ያብራሩት። ኢትዮጵያ ለሻይ ምርት ምቹ የሆነ የአየር ጸባይና የአፈር ሁኔታ ያላት አገር መሆኗን ጠቁመው፤ የሻይ ቅጠል ምርት አሲዳማና ተዳፋት በሆኑ መሬቶች ላይ ጭምር መብቀል የሚችል በመሆኑ ምርቱን ለማስፋት አርሶ አደሩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል። የሻይ ምርት በአርሶ አደሩ ብቻ የሚሰፋ ባለመሆኑ ባለኃብቶች ዘርፉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል። መንግስትም በዘርፉ ለሚሳተፉ ባለሃብቶች የተለያያ ማበረታቻዎች እያደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል። የሻይ ቅጠል ምርት አንድ ጊዜ ከተተከለ ለ30 እና 40 ዓመታት ምርቱ የሚቆይና በየ15 ቀኑ ምርቱን በመቅጠፍ ገቢ ማግኘት የሚያስችል ነው። ዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ ሌሎች ክልሎችም የሻይ ምርትን ለማስፋት በትኩረት እንዲሰሩ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ 99 በመቶ የሚሆነውን የሻይ ምርት ወደ እንግሊዝ ትልካለች።
نمایش همه...
በተዘጋጀ የሻይ ልማት ስትራቴጂ እና ፓኬጅ ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል!! ሰኔ 24/2016 ኢ/ቡ/ሻ/ባለስልጣን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ያዘጋጀው እና የፌዴራል፣ ክልል፣ የምርምር ተቋማት እና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የሻይ ልማት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ባለሙያዎችን ያሳተፈ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ውይይቱ በዋነኝነት ያተኮረው በተዘጋጀው ረቂቅ የሻይ ልማት ስትራቴጂ እና ፓኬጅ ላይ በዘርፉ ላይ በተሰማሩ ባለሙያዎች እና ክልሎች ለሰነዱ መዳበር አስፈላጊውን ግብአት እንዲያቀርቡ ለማስቻል ነው፡፡ ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት አገራችን ከቡና በተጨማሪ በሻይ እና ቅ/ቅመም እምቅ ሀብት እንዳላት እና አግሮ ኢኮሎጂውም ከሚታሰበው በላይ ምቹ በመሆኑ የውጭ ምንዛሬ ገቢያችንን የማሳደግ እና አማራጭ እድሎችንም የመጠቀም ስትራቴጂ መከተል የግድ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ በዚህ በኩል ሻይ ልማት ሰፊ ምርት የሚሰጥ ከመሆኑም ሌላ እጅግ በርካታ የስራ እድሎችን በመፍጠር ረገድ ያለው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከውጭ የሚገባውን ምርት በመተካት እና እንደቡናው ሁሉ ተወዳጅ እና ተመራች ምርት ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ለመሸጥ የሚያስችል አቅም እንዳለ ነው የገለጹት፡፡ ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ቀደም ሲል በአገር አቀፍ ደረጃ የነበረው ምርት ከ5ሺህ ሄክታር እንደማይበልጥ ተናግረው በተለይም በኦሮሚያ ክልል ከባለፈው አመት ጀምሮ በተሰራ ስራ ሰፊ የሻይ ልማት እየተካሄደ መሆኑን አውስተው በሌሎችም ክልሎች ለማስፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ይህ የተዘጋጀ ረቂቅ ስትራቴጂም ዕውቀቱ እና ልምዱ ባላቸው ባለሙያዎች ዳብሮ እና ግብኣቶች ተካተውበት መላ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለውይይት እንደሚቀርብ አስታውቀዋል፡፡ ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ የባለስልጣን መ/ቤቱ የልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው መንግስት ለሻይ ልማቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥቶት በመስራት ላይ እንደሚገኝ እና እጅግ በርካታ መሬትም በዚሁ ሰብል እየተሸፈነ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ ረቂቅ ስትራቴጂው የተዘጋጀው አቅሙ እና ልምዱ ባላቸው ባለሙያዎች መሆኑን እና ዛሬም ለረቂቅ ሰነዱ ግብኣት እንዲቀርቡ የተጋበዙት ባለሙያዎች ረጅም ጊዜ በምርምር ላይ የቆዩ እና ለስትራቴጂ ሰነዱ መዳበር ጉልህ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክቱ የታመነባቸው እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም ይህ ቁልፍ ሰነድ ምን መምሰል ኖርበታል፣ ምን ምን ጉዳዮችን ሊያካትት ይገባል፣ ተግባሪዎችስ እነማን መሆን አለባቸው፣ ተሳትፏቸውስ በምን መልኩ ነው ወዘተ. የሚለውን በጥንቃቄ በማካተት የበኩላቸውን አሻራ እንዲያሳርፉና በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ባለሙያዎቹም ረቂቅ ስትራቴጂው እና ፓኬጁ ከቀረበ በኋላ በስፋት በመወያየት ላይ ይገኛሉ፡፡
نمایش همه...
نمایش همه...
በቡና ልማትና ግብይት ላይ የሚሰሩ ተዋንያንን በማገናኘት የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት  እየተሰራ ነው

ሀዋሳ፤ ሰኔ 21/2016 (ኢዜአ) -በቡና ልማትና ግብይት ላይ የሚሰሩ ተዋንያንን በማገናኘት የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ...

የአቅራቢ ላኪዎች ኤግዚቢሽን ማጠቃለያ እና ለዘርፉ ወሳኝ ውይይት ተካሄደ!! ሰኔ 24/2016 ሀዋሳ በቡና ግብይት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀዋሳ ከተማ የተካሄደው አቅራቢ እና ላኪዎችን በአንድ መድረክ ያገናኘው በአይነቱ ልዩ የሆነ ኤግዚቢሽን ማጠቃለያ የሆነ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ከ400 በላይ በቡናው ዘርፍ የተሰማሩ አ/አደሮች፣ አቅራቢዎች፣ አልሚዎች፣ ላኪዎች፤ የፌዴራል፣ የክልል እና ዞን የስራ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ይህ መድረክ ሲዘጋጅ የቡና ቤተሰብ የሆኑትን እና ወሳኝ ድርሻ ያላቸውን አካላት በማቀራረብ የበለጠ ትስስር እና መተማመንን እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው ብለዋል ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የውይይት መድረኩን በይፋ ሲከፍቱ፡፡ በጋራ ሆኖ ከተሰራ አስደናቂ ለውጥ ማምጣት ይቻላልም ነው ጨምረው ያሉት፡፡ ቡና የአገሪቱን 35-40 በመቶ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንደሚሸፍን እና ከአጠቃላይ ህዝብ ብዛት 25 በመቶ የሚሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ኑሮውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተሸከመ ዘርፍ በመሆኑም በጥንቃቄ እና ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተመራ የሚገኝ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ በተለይም ደግሞ በግብይቱ በኩል የተከማቹበት እጅግ በርካታ ውስብስብ ተግዳሮቶች የነበሩበት ሲሆን ተገቢው ጥናት እየተደረገ በየጊዜው ችግሮቹ እየተለዩ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እየተቀመጡ በመሄዳቸው በየደረጃው የሚገኘው ተዋናይ ተጠቃሚነቱ እየጨመረ፣ አገሪቱ የምታገኝም የውጭ ምንዛሬ እያደገ መሄዱን የተናገሩት ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ ሪፎርሙ ከተካሄደበት ሶስት አመታት ወዲህ የአገሪቱንም ሆነ የዜጋውን መጻዒ ዕድል ብሩህ ሊያደርጉ የሚያስችሉ አጓጊ ተስፋዎች እየመጡ መሆናቸውን፣ አርሶ አደሩን በቀጥታ ወደ አለም ገበያ ምርቱን እንዲያርብ መደረጉን፣ አቅራቢዎችንም ወደ ላኪነት የማሸጋገር ስራ ስኬታማ መሆኑን አሁንም በስፋት እየተሄደበት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትንም ለመቅረፍ ብዙ ርቀት የተሄደበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አቅራቢ እና ላኪዎችን በማቀራረብ እና ያሉ ዕድሎችን በማስፋት ተጠቃሚ ለማድረግ የተካሄደው ኤግዚቢሽንም በስኬት መጠናቀቁን እና በቅርቡም በጅማ ከተማ ተመሳሳይ መድረክ መዘጋጀቱንም ነው የጠቆሙት፡፡ ይህ ዝግጅት እውን እንዲሆን ቀን ከሌት ለደከሙ የባለስልጣን መ/ቤቱ አመራር እና ሰራተኞች፣ ለሲዳማ ክልል፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እንዲሁም ኦሮሚያ ክልሎችም ከልብ አመስግነዋል፡፡ ከእነሱ በተጨማሪ የቡና ማህበራትም ላበረከቱት አስተዋጽዖ የላቀ ምስጋና ቸረዋቸዋል፡፡ ክቡር አቶ መምሩ ሞኬ የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው ለዝግጅቱ መድመቅ የላቀ አስተዋጽዖ ለነበራቸው አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ለላቀ ተግባር የበለጠ መነሳሳት እና ወደ ሌሎች ቡና አምራች ክልሎችም መሰል መድረኮች መዘጋጀት እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል፡፡ ተፈጥሮ የቸረችንን ልዩ እና ተዝቆ የማያልቅ ቡና ሀብት በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ሀላፊው ለጥራት ልዩ ትኩረት መስጠት እና በመጠንም ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ለአለም ገበያ ማቅረብ ይገባልም ሲሉ ነው የተደመጡት፡፡ በዚህ በኩል ደግሞ ችግሩ በአንድ አካል ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የቡናና ሻይ መዋቅሮች እንዲሁም ከአርሶ አደሩ ጀምሮ የሚገን ባለድርሻ እጅ ለእጅ ተያይዞ ወደ ፊት መገስገስ ይገባዋል ብለው ተናግረዋል፡፡ ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል የተከናወኑ ተግባራት በተለይም ከሪፎርሙ ጋር በተያያዘ የነበሩ ስኬቶች እና አልፎ አልፎ የታዩ ችግሮች እንደሁም የተፈቱበትን መንገድ አስመልክቶ እንደመነሻ የሚሆን መወያያ ሰነድ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ሰነዱ ከቀረበ በኋላም መላው የቡና ቤተሰብ በስፋት ሲወያይበት እና ሀሳቦችን ሲሰነዝር የዋለ ሲሆን ክቡር ዶ/ር አዱኛ፣ ክቡር አቶ ሻፊ እና ክቡር አቶ መምሩ ከመድረክ ማብራሪያዎችን እና ቀጣይ የታሰቡ ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡
نمایش همه...
# World of Coffee in Copenhagen! 🌍☕️
نمایش همه...
آرشیو پست ها
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.