cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ETH Coffee Network News

አስተማማኝ እና ጊዜውን የጠበቀ ትኩስ የቡና መረጃዎችን እዚህ ያገኛሉ። Join Group @EthCoffeeCommunity

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 422
مشترکین
-524 ساعت
+77 روز
+7830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
በቡና ልማትና ግብይት ላይ የሚሰሩ ተዋንያንን በማገናኘት የዘርፉን ችግሮች የመፍታት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ ቡና አምራች በሆኑ አራት ክልሎች የሚገኙ የቡና አምራች፣ አቅራቢ እና ላኪዎችን ያገናኘ የቡና አውደ ርዕይ በሀዋሳ ከተማ ሰኔ 22 እና 23 ተካሄዳ። በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ በቡና ንግድ ሂደት ውስጥ አምራች፣አቅራቢና ላኪ ብዙም አይተዋወቁም ነበር ያሉት። ዶክተር አዱኛ አውደ ርዕዩ እነዚህን አካላት በማገናኘት ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል። አውደ ርዕዩ የገበያ እድልን በማስፋት ምርትና ምርታማነት ላይ ለውጥ ለማምጣት እንደሚያግዝም ተናግረዋል። በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከ300 የሚበልጡ ቡና አብቃይ ከሆኑ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎች የተውጣጡ ቡና አምራች ማህበራት፣ አቅራቢዎችና ላኪዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል። ቡና አቅራቢና ላኪዎች ቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት የሚፈራረሙበት ሁኔታና ትስስር እንደሚፈጠርም ዶክተር አዱኛ አስታውቀዋል። ምንጭ፡ ኢዜአ @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
نمایش همه...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
መንግስት የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመከፈት የሚያስችል የአዋጪነት ጥናት መጀመሩ ተነገረ የፈደራሉ መንግስት በዓመት 2 ነጥብ 5 ሚሊያን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማምረት የሚስችል ፋብሪካ ለማቋቋም የአዋጭነት ጥናት እይሰራ ነው። የፕላን እና ልማት ሚኒስተር ያወጣው የ10 ወር ሪፖርት እንደሚያሳየው ዩሪያን ከሶማሌ ክልል በሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ በመታገዝ ለማምራት ስለ ተደረገ የስድስት ወር ጥናት ያመለክታል። ሪፖርቱ እንዳሚያሳያውም የቻይና እና ሆንግ ኮንግ ሁለት ድርጅቶች ጣምራ የሆነው ፖሊ ጂ ኤስ ኤል የተባለ ኩባንያ በክለሉ የተገኘውን 198 ቢሊያን ኪዩቢክ ሜትር ነዳጅ ለማውጣት የመጅምሪያ ዙር ስራ እያካሄድ ነው። አንድ አንድ ባለስልጣናት እንደሚሉት ይህ ዙር ሲጥናቀቅ 182 ሺ ሜትሪክ ቶን የተፈጥሮ ጋዝ በየቀኑ ማውጣት ይቻላል ተብሎም ይጠበቃል። ምንጭ፡ @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
نمایش همه...
የደን ልማትን ወደ ሃብት ሊቀይር የሚችል አዲስ ደንብ በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ጸደቀ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት የደን ልማት፣ ጥበቃ እና አጥቃቀም ደንብ ቁጥር 544/2016 ባወጣው አዲስ አዋጅ የደን አልሚዎች ካርበን ክሬዲትን በመሸጥ ሃብት ማግኘት እንዲችሉ ደንግጓል። አልሚዎቹን በሶስት የከፈለው ደንቡ ከ5 ሔክታር በታች መሬት ያላቸውን የግል አነስተና የደን አልሚዎች፣ ከ5 ሔክታር በላይ የመሬት ይዞታ የሚያለሙትን ሰፋፊ የግል ደን አልሚ እንዲሁም የማህበረሰብ ደን አልሚዎችን ደሞ በአሳታፊ የደን ልማት አስተዳደር ስር በማካተት ለይቷቸዋል። በዚህም የደን አልሚዎቹ የተለያዩ ጥቅሞችን እንደሚያገኙ አዋጁ ሲያትት ከዚህ ውስጥም ከሊዝ ነጸ የደን መሬት የማግኘት፣ የግብር እፎይታ፣ ያለሙትን ደን በመጠቀም ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት ብደር የማግኘት መብት እና የካርበን ክሬዲትን በመሸጥ ከሚያገኙት ገቢ ተጥቃሚ እንዲሆኑ ይደነግጋል። ይህ በእንዲ እንዳለም አዋጁ አልሚዎች ካርበን በመሸጥ ከሚያገኙት ገቢ 5 በመቶውን ለፌደራሉ መንግስት እንዲሁም 15 በመቶ ደሞ ለሚያለሙበት ክልል የመክፈል ግዴታ እንዳለባችውም አመላክቷል። ደን በማልማት ካርበን ክሬዲትን እንዴት መሸጥ ይቻላል የሚለውን ነገ ቅዳሜ 4 ሰዓት ላይ በቀጥታ ውይይታ ላይ የሚብራራ ይሆናል። ይህንን ሂደት የሚያካሂዱትን ተቋማት ሙሉ መረጃም በዚህ ግሩፕ ውስጥ በቅርቡ እናሳውቅዎታለን። @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
نمایش همه...
Forest_Dev't,_Protection_and_Utilization_Regulatio_240621_045632.pdf6.45 MB
1
NYCE Market Closing Date: 27/06/2024 Arabica = +2.65 US cents lb.                                             (+1.18%)               226.77 Closing @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ ነው ተባለ የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ ነው። በየአመቱም ወደ ቻይና የሚላከው ቡና መጠን በአማካኝ 27 በመቶ እያደገ እንደመጣ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ተናግረዋል። ከጥቂት አመታት በፊት ቻይና ከኢትዮጵያ የምትገዛው ቡና በአመት ከስምንት እስከ አስር ሺ ቶን የማይበልጥ እንደነበረ እና በዚህም ከኢትዮጵያ ቡና ገዢዎች 33 ደረጃ ይዛ የነበረች ሲሆም በቅርብ አመታት ግን ቻይና ከኢትዮጵያ የምታስገባውን ቡና ወደ 20 ሺ ቶን በማሳደግ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ቡና ገዢዎች መሃል ስምንተኛ ደረጃን እንድትይዝ አስችሏታል ሲሉ ዳይሬክተሩ ጥቅሰዋል። በተለይ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ አማራጭ የገበያ መዳረሻዎችን በምትፈልገበት ሰአት የቻይና የቡና ፍላጎት ማደገ ለኢትዮጵያ ቡና መልካም ነገር እንደሆነም ጠቅሰዋል። @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
نمایش همه...
👍 4
NYCE Market Closing Date: 26/06/2024 Arabica = -5.60 US cents lb.                                             (-2.44%)               224.12 Closing @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
نمایش همه...
ከቡና እና ሻይ የተገኘ ሳምንታዊ የሃገር ውስጥ ቡና ቀጥተኛ ግብይት የአነስተኛ እና ከፍተኛ ዋጋ ማንፃፀሪያ ከሰኔ 26/10/2016 እስከ ሰኔ 24/10/2016 (June 25 - July 1/2024)
نمایش همه...
JUNE_25_july_01_coffee_upper_and_lower_coffee_purchase_price.xlsx0.32 KB
JUNE 25-JULY 01 COFFEE MINIMUM PRICE DATA.xlsx0.30 KB
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከቅመማ ቅመም ወጪ ንግድ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተነገረ ባለፉት 11 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቅመማ ቅመም ምርት 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከ50 በላይ ቅመማቅመሞች እንደሚመረቱ ጠቁመው÷ ከእነዚህ ውስጥም 16ቱ ለዓለም ገበያ ይቀርባሉ ብለዋል፡፡ ለዚህም ኮረሪማ፣ ዕርድ፣ ጥምዝ፣ ቁንዶ በርበሬ እና በርበሬ ያሉ ቅመሞች ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ ምርቶችም ወደ 39 የተለያዩ ሀገራት እንደሚላኩ ነው ዋና ዳይሬክተሩ የጠቀሱት፡፡ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት 8 ሺህ 400 ቶን ቅመማቅመም ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት በመላክ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ተገልጿል፡፡ አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር በመጠን ሲነጻጸር ከ2 ሺህ ቶን በላይ ብልጫ ማሳየቱንም ተናግረዋል፡፡ ምንጭ፡ ኤፍ ቢ ሲ @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
نمایش همه...
👍 1 1
NYCE Market Closing Date: 25/06/2024 Arabica = -7.30 US cents lb.                                             (-3.08%)                229.72 Closing @EthCoffeeCommunity @EthCoffeeNetworkNews
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የቡና አቅራቢዎችንና ላኪዎችን የቀጥታ ትስስር ግብይት ለማጠናከር የሚያስችል የቡና አውደ ርዕይ ሊካሄድ መሆኑ ተነገረ ቡና ላኪዎችና አቅራቢዎችን የሚያገናኝ የቡና አውደ ርዕይ በሐዋሳና ጅማ ከተሞች ሊያካሂድ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) አውደ ርዕዩ፥ ሃገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይበልጥ ለማሳደግና የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ ታልሞ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በሃገሪቱ የሚመረቱ የቡና ዓይነቶችንና የጥራት ደረጃዎቻቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ፥ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራልም ነው ያሉት። አውደ ርዕዩ በሐዋሳ ከተማ ከሰኔ 21 እስከ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲሁም በጅማ ከተማ ከሰኔ 26 እስከ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል። ከአውደ ርዕዩ ጎን ለጎን በቡና ምርት፣ ጥራትና መሰል ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ መናገራቸው ተዘግቧል። @EthCoffeeCommunity @EthCoffeNetworkNews
نمایش همه...
👍 6👏 1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.