fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
ባቂው ደጅ ደረሰ በግጠባቂውን "እስከ ነገ የምናድርበት ማደሪያ በአንተ ዘንድ እናገኛለን? ኪራዩንም እሰጥሃለሁ" አለው በግ አርቢውም "እንዳልክ ይሁንና እደር" አለው ባለጸጋውም በዚያ አደረ። ራት በሚቀርብም ጊዜ ሕፃኑን ባሕራን ብሎ ጠራው ባለጸጋውም ሰምቶ "ልጅህ ነውን?" ብሎ ጠየቀው በግ ጠባቂውም "አዎን ታናሽ ሕፃን ሆኖ ሳለ ከባሕር አግኝቼዋለሁና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጄ ነው" አለው ባለጸጋውም "በምን ዘመን አገኘኸው" አለው እርሱም "ከሃያ ዓመት በፊት" ብሎ መለሰለት። ያን ጊዜም እርሱ ወደ ባሕር የጣለው መሆኑን አውቆ አጅግ አዘነ። ❤ በማግሥቱም ጎዳናውን ሊጓዝ በተነሣ ጊዜ ሰይጣናዊ ምክንያት አመካኝቶ በግ ጠባቂውን እንዲህ አለው "ዕገሊት ወደምትባል አገር በቤቴ የረሳሁት ጉዳይ ስለ አለ እንድልከው ልጅህን ትሰጠኝ ዘንድ እሻለሁ እኔም የድካም ወጋውን ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሃለሁ" አለው። የብላቴናውም አባት ስለገንዘቡ ደስ ብሎት ልጁ ባሕራንን ሰጠው እንዲህም ብሎ አዘዘው "ልጄ ባሕራን ይህ የከበረ ሰው ስለ ጉዳዩ ወደ ቤቱ ይልክህ ዘንድ ና ወደ ቤትህም በሰላም ትመለሳለህ"። ባሕራንም "አባቴ ሆይ እሽ በጎ ያዘዝከኝ ሁሉ አደርጋለሁ" አለ። ❤ ያን ጊዜም ባለጸጋው ወደ መጋቢው እንዲህ ብሎ ደብዳቤ ጻፈ "ይችን ደብዳቤ በምታነባት ጊዜ ደብዳቤዋን ይዞ የመጣውን ገድለህ በጒድጓድ ውስጥ ጣለው ማንም አይወቅ" በመካከላቸውም የሚተዋወቁበትን ምልክት ጽፎ አሸጋት። ለባሕራንም ሰጠው ለመንገዱም የሚሆነውን ስንቅ ሰጠው ባሕራንም ተነሥቶ ጉዞውን ጀመረ ሲጓዝም ሰንብቶ የአንዲት ቀን ጉዞ ሲቀረው እንሆ የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ "አንተ ጐልማሳ የያዝኸው ምንድነው?" አለው "ወደ ዕገሌ አገር ወደ ቤቱ ለማድረስ ከአንድ ባለጸጋ የተጻፈች መልክት ናት" አለው "ያቺን ደብዳቤ አሳየኝ" አለው እርሱም ስለ ፈራ ሰጠው። ❤ በዚያን ጊዜም የከበረው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያቺን የሞት መልክት ደመሰሳት በእርሷ ፈንታም በንፍሐት ለውጦ እንዲህ ብሎ ጻፈ "ይቺን ደብዳቤ ይዞ ለመጣ ባሕራን ለሚባል ሰው ይቺ ደብዳቤ ደርሳ በምትነበብበት ጊዜ ልጄ ዕገሊትን አጋቡት በውስጥና በውጭ ያለ ንብረቴንና ጥሪቴን ወንዶችና ሴትች ባሮቼን ጠቅላላ ንብረቴንም አውርሼዋለሁና የፈለገውንም ሊያደርግ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና እኔን አትጠብቁኝ። እኔ ብዙ እዘገያለሁ የኔ ሹም ዕገሌ ሆይ በእኔና በአንተ መካከል ይቺ ምልክት እነኋት" ከዚህ በኋላ አሽጐ ለባሕራን ሰጠውና "ወደ ባለጸጋው ቤት ሒደህ ይቺን ደብዳቤ ለሹሙ ስጠው በጎዳናም እኔ እንደ ተገናኘሁህ አትንገረው እንዳይገድልህም ይህን የሞት ደብዳቤ ለውጨልሃለሁ" አለው። ባሕራንም እሺ ጌታዬ ያዘዜኸኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለ። ❤ ባሕራንም ወደ ባለጸጋው ቤት በደረሰ ጊዜ ያቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው በአነበባትም ጊዜ በመካከላቸው ያለውን ምልክት አገኘ አስተውሎም እርግጠኛ እንደሆነ አወቀ። ከዚህም በኋላ ለባሕራን ሠርግ አዘጋጅቶ እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተክሊል የባለጸጋውን ልጁ አጋቡት። አርባ ቀን ያህልም ደስታና ሐሴት እያደረጉ ኖሩ። ❤ ከዚህ በኋላ ባለጸጋው ከሔደበት መመለሻው ጊዜ ሁኖ በደስታ የሆነውን የመሰንቆና የእንዚራ ድምጽ ሰምቶ "ይህ የምሰማው ምንድነው?" ብሎ ጠየቀ እነርሱም "ስሙ ባሕራን ለተባለ የአንተን ደብዳቤ ላመጣ ጐልማሳ ሰው ልጅህ ዕገሊትን አጋቡት እንሆ ለአርባ ቀናት በሠርግ ላይ ነው። ገንዘብህንና ጥሪትህን ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ባሮችህን አንተ እንዳዘዝክ ሰጥተውታል" አሉት። ይህንንም በሰማ ጊዜ ደንግጦ ከፈረሱ ላይ ወድቆ በድንገትም ሞተ። ❤ ባሕራንም በጎ ሥራዎችን የሚሠራ ሆነ የተገለጸለትና ከመገደል ያዳነው የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊገድለው የሚሻውን የባለጸጋውን ጥሪቱን ሁሉ ያወረሰውም እርሱ እንደ ሆነ ተረዳ የዚህንም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ በየወሩ ያደርግ ጀመረ ቤተ ክርስቲያንም ሠራለት የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕሉን አሥሎ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ አደረገው ከእርሱም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ባሕራንም ቅስና ተሹሞ እስከ ዕለተ ሞቱ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ሁኖ ኖረ በዚህ በከበረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ከእናቱና ከአባቱ ከልጆቹም ጋራ የዘላለም ሕይወትን ወረሰ። + + + ❤ ቅዱስ አስተራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አፎምያ፦ ይህም ሰው በየወሩ ሦስት በዓላቶችን እያከበረ ኖረ እሊህም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በየወሩ በሃያ ዘጠኝ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል መታሰቢያ በየወሩ በሃያ አንድ የከበረ የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያም በየወሩ በዐሥራ ሁለት ናቸው። ❤ የሚሞትበትም ጊዜው ሲቀርብ እርሱ ሲሠራው የነበረውን ምጽዋት ይልቁንም እሊህን ሦስቱን በዓላት እንዳታስታጉል ሚስቱን ቅድስት አፎምያን አዘዛት። እርሷም የከበረ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባሏን ለመነችው እርሱም አሠርቶ ሰጣትና በቤቷ ውስጥ በክብር አኖረችው። ❤ ባሏም ከዐረፈ በኋላ ባሏ ያዘዛትን መሥራት ጀመረች ሰይጣንም ግን ቀናባት በመበለት ሴት መነኵሲት ተመስሎ ከእርሷ ጋራ ተነጋገረ እንዲህም አላት "እኔ አዝንልሻለሀለ እራራልሻለሁም ገንዘብሽ ሳያልቅ የልጅነትሽም ወራት ሳያልፍ አግብተሽ ልጅ ትወልጂ ዘንድ እመክርሻለሁ ባልሽም መንግሥተ ሰማያት ወርሷል ምጽዋትም አይሻም"። አፎምያም እንዲህ ብላ መለሰችለት "እኔ ከሌላ ሰው ጋራ ላልገኛኝ ለእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አድርጌያለሁ ርግቦችና መንጢጦች እንኳ ሌላ ባል አያውቁም በእግዚአብሔር አርያ ከተፈጠሩ ሰዎች ይህ ሊሆን እንዴት ይገባል"። ምክሩንም ባልሰማች ጊዜ አርያውን ለውጦ በላይዋ ጮኸባት እንዲህም አላት እኔ በሌላ ጊዜ እመጣለሁ" እርሷም የከበረ የመላኩ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ይዛ አሳደደችው። ❤ ከዚህም በኋላ ሰኔ ዐሥራ ሁለት የከበረ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል በዓል በሚከብርበት ዕለት እርሷም የበዓሉን ዝግጅት ስታዘጋጅ ሳለች ብርሃናዊ መልአክ መስሎ ሰይጣን መጣ "አፎምያ ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እኔ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነኝ ጌታ ወደ አንቺ ልኮኛልና እርሱም ይህን መመጽወትሽን ትተሽ ለአንድ ምዕመን ሚስት ትሆኚ ዘንድ ጌታ አዞሻል ባል የሌላት ሴት መልሕቅ የሌለውን መርከብ እንደምትመስል ዕወቂ እንደ አብርሃምና ያዕቆብ እንደ ዳዊትም እንደእነርሱ ያሉ ብዙ ሴቶችን እንዳገቡ እግዚአብሔርንም ደስ እንዳሰኙት" ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጥቅሶችን ያመጣላት ጀመረ። ❤ ቅድስት አፎምያም መልሳ "አንተ የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ የመስቀል ምልክት ከአንተ ጋራ ወዴት አለ የንጉሥ ጭፍራ የሆነ ሁሉ የንጉሡን ማሕተም ሳይዝ ወደ ሌላ ቦታ አይሔድምና" አለችው። ሰይጣንም ይህንን በሰማ ጊዜ መልኩ ተለውጠና አነቃት እርሷም ወደከበረው መልአክ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ጮኸች ወዲያውኑም ደርሶ አዳናት። ያንንም ሰይጣን ይዞ ይቀጣው ጀመረ ሰይጣኑም ጮኸ "ማረኝ ያለ ጊዜዬ አታጥፋኝ እግዚአብሔር እስከ ዓለም ፍጻሜ ታግሦናልና" እያለ ለመነው ከዚያም ተወውና አበረረው። የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልም እንዲህ አላት "ብፅዕት አፎምያ ሆይ ሒደሽ የቤትሽን ሥራ አዘጋጂ አንቺ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ትለዪአለሽና እነሆ እግዚአብሔርም ዐይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሰኔ ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ለሚበር ንሥረ አርያም ለሚባል ውዳሴው እንደ ማር ለጣፈጠ ንዑድ ክቡር ለሆነ ለከበረ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ለተሾመበት፣ የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ቀዶ እርሱን ለታላቅ ክብር ላበቃባት ቅድስት አፎምያን ለአዳነበት (ለረዳበት)፣ ቅዱስ እለእስክንድሮስ አንድን ቤተ ጣዖት አፍርሶ ከቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ቅዱስ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በደስታ በሐሴት ላከበሩበት ዕለት በዓል፣ ለቅዱስ አስተራኒቆስ ለሚስቱ ቅድስት አፎምያ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል፣ ለእስክንድርያ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ዮስጦስና ለስልሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ቄርሎስ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ፦ "አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ ፀሓይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኵሉ"። ትርጉም፦ ጌታችንን አይሁድ በሰቀሉት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ዝም አለ፤ ቅዱስ ገብርኤልም ተደነቀ፤ ፀሓይ ጨለመ ፤ ጨረቃም ደም ኾነ፤ ከመስቀሉ ወርዶ ለኹሉ አበራ። + + + ❤ "ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ"። ትርጉም፦ የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል። ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ በዚች ዕለት እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው። ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይግባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረቱም ሁሉ ይለምናል ይማልዳል። ❤ መድኃኒታችን በተነሣባትም ቀን ይህ ክብር መልአክ ሚካኤል ከውስጠኛው መጋረጃ ውስጥ ገብቶ በክብር ባለቤት ፊት እንዲህ እያለ ይለምናል "እውነት ስለሆነ ቃል ኪዳንህ በምድር መታሰቢያዬን የሚያደርገውን ትምርልኝ ዘንድ ፈጣሪዬ ሆይ እኔ አገልጋይህና መልአክተኛህ ከቸርነትህ እለምናለሁ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህና"። የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ ብሎ ይመልስለታል "የመንፈሳውያን ሰማያውያን መላእክት አለቃቸው ሚካኤል ሆይ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ መሸከም እንደሚችል ከሲዖል ሦስት ጊዜ በክንፈሸችህ ተሸክመህ እንድታወጣ እንሆ እኔ አዝዤሃለሁ"። ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት የበዓሉን መታሰቢያ ከሚያደርጉት በክንፎቹ ተሸክሞ የእሳትን ባሕር አሳልፋቸው እነርሱንም ከብቻው ጌታ በቀር የሚቆጥራቸው የለም። ❤ ስለዚህም የዚህን ታላቅ የከበረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ለማድረግ መታገል ይገባናል እርሱ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን ዘንድ በዘመናችን ሁሉም ይጠብቀን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይ ዘንድ መከራችንንም ያርቅ ዘንድ የምድራችንንም ፍሬ ይባክ ዘንድ ከእኛ ወገን የሞቱትን ዕረፍተ ነፍስ ይሰጥ ዘንድ ወደ መንገድ የሔዱ አባቶቻችንና ወንድሞቻችንን ወደ ቤቶቻቸው በሰላም በጤና ይመልሳቸው ዘንድ በመካከላችንም ፍቅር ያደርግልን ዘንድ እስከ መጨረሻዪቱም ሕቅታ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ ይለምናልና። ❤ የክርስቶስ ወገኖች የሆኑ መኳንንቶቻችንንም ጠብቆ በወንበሮቻቸው ላይ ያጸናቸው ዘንድ የሳቱትንም ወደ ቀናች ሃይማኖቱ ይመልሳቸው ዘንድ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላችነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ12 ስንክሳር። + + + ❤ ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን እንደረዳው፦ እግዚአብሔር የሚፈራ አንድ ሰው ነበር እርሱም የከበረ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ይልቁንም በሰኔና በኅዳር ወር አብልጦ ያከብር ነበር። በጐረቤቱም ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጠጋ ሰው ነበረ። ይህም እግዚአብሔርን የሚፈራውን ሰው የከበረ መልአክ የቅዱስ የሚካኤልን በዓል በሚያደርግበት ጊዜ ይጠላውና ያቃልለው ነበር ለድኆች ስለ መራራቱም ይዘባበትበት ነበር። የሕይወቱ ዘመንም ተፈጽሞ የሚሞትበትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ድካምም የሚያርፍበት ጊዜ ሲቀርብ የክብር መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ታደርግ ዘንድ ምጽዋት ሰጭም ትሆን ዘንድ ሚስቱን አዘዛተሰ። ❤ ከዚህም በኋላ ዐረፈና ገንዘው ቀበሩት ሚስቱም ፀንሳ ነበረች የመውለጃዋ ጊዜም ደርሶ ምጥ ያዛት በታላቅ ጭንቀት ውስጥ ሳለችም እንዲህ ብላ ጸለየች "የእግዚአብሔር መልአኩ ሆይ ራራልኝ በእርሱ ዘንድ ባለሟልነት አለህና በእግዚአብሔር ዘንድ ስለ እኔ ለምንልኝ"። ይንንም በአለች ጊዜ በቤቷ ውስጥ ብርሃን በራ ከችግርም ዳነች መልኩ ውብ የሆነ ወንድ ልጅንም ወለደች የእግዚአብሔርም መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን እንዲህ ብሎ ባረከው "ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት ጥሪቱንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዝዟል" ባለጸጋውም በቤቱ በዐልጋው ላይ ሳለ ጌታ ጆሮውን ከፍቶለት ይህን ነገር ከመልአኩ ሰማ። ይህንንም በሰማ ጊዜ ታላቅ ኀዘን ደረሰበት ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር ነገር ግን ክብር ይግባውና ጌታ ይጠብቀው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ምክንያት አዘጋጅቶ "የሚያገለግለኝ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ ልጅሽን ስጪኝ እኔም እየመገብኩና እያለበስኩ አሳድገዋለሁ ለአንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለሁ" አላት። ይህንንም ነገር ከበለጸጋው በሰማች ጊዜ ስለችግራ እጅግ ደስ አላት ልጅዋንም ሰጠችው እርሱም ሃያውን ወቄት ወርቅ ሰጣት ልጅዋንም ወሰደው የምሻው ተፈጸመልኝ ብሎ ደስ አለው። ❤ ከዚህም በኋላ በልጁ ቁመት ልክ ሣጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ አስገብቶ ዘጋበት እስከ ባሕርም ተሸክመው ወስደው በባሕር ጣሉት ክብር ይግባውና በጌታችን ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሠጥም ከዚያች አገር የሃያ ቀን መንገድ ያህል ርቃ ወደምትገኝ ወደ አንዲት አገር ወደብ እስከ ሚደርስ ባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ። በባሕሩም አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ሣጥኑን በውኃ ላይ ተንሳፎ አየው እርሱም ከባሕሩ አውጥቶ ወደ ቤቱ ወሰደው ይህንም ሣጥን እንዴት እንደሚከፍተው ያስብ ጀመረ ይህንም ሲያስብ ወደ ባሕሩ ይሔድ ዘንድ ጌታችን በልቡናው ኃሳብ አሳደረበት ወዲያውኑም ተነሥቶ ወደ ባሕሩ ሔደና አንድ ዓሣ የሚያጠምድ ሰው አገኘ። ዓሣ አጥማጁንም "መረብህን በኔ ስም ጣል ለሚያዘውም ዓሣ ዋጋውን እሰጥሃለሁ" አለው። አጥማጁም እንዳለው አደረገ ያን ጊዜም ታላቅ ዓሣ ተያዘ ዋጋውንም ሰጥቶ ዓሣውን ተቀበለ ዓሣውንም ይዞ ወደቤቱ ሔደ ለራትም ይጠብሰው ዘንድ አረደው በሆዱም ውስጥ መክፈቻ አገኘ። በልቡም ይህ መክፈቻ ይህን ሣጥን ይከፍተው ይሆን" አለ በሣጥኑ ቀዳዳም በአስገባው ጊዜ ፈጥኖ ተከፈተ በውስጡም ይህን ታናሽ ብላቴና አገኘ። ልጅ የለውም ነበርና ታላቅ ደስታም ደስ አለው ጌታችንንም አመሰገነው። ሕፃኑንም በመልካም አስተዳደግ አሳደገው ሕፃኑንም አድጎ ጐልማሳ ሆነ። ❤ ከብዙ ዘመናትም በኋላ ያ ባለ ጸጋ ተነሥቶ ወደ ዚያ አገር ሔደ በመሸም ጊዜ ወደ በግ ጠ

photo content

photo content

ት ዘንድ ንጉሡ እንደ አዘዘ በአወቀ ጊዜ የእኅቱ ባል የሆነ ሲድራማኮስን ጠርቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን በማመን እንዲጸና ወገኖቹንም እንዲያጸናቸው አደራ አለውና በሰላምታ ተሰናበተው። ❤ ወደ እንዴናው ገዥ ወደ አርያኖስም በደረሰ ጊዜ አርያኖስ አይቶ ደነገጠ ተነሥቶም እጁን ሳመው እንዲህም ብሎ ለመነው "ጌታዬ ገላውዴዎስ ሆይ ይህን ሥራ አትሥራ የንጉሥንም ትዕዛዝ አትተላለፍ። ቅዱስ ገላውዴዎስም እንዲህ ሲል መለሰለት "ንጉሥ ያዘዘህን ልትፈጽም እንጂ በነገርህ ልታስተኝ አልተላክሁም" አለው። መኰንኑም እስከሚቆጣ ድረስ እንዲህ እርስበርሳቸው ይነጋገሩ ነበር በመኰንኑም እጅ ጦር ነበር ቅዱስ ገላውዴዎስ ወጋው ነፍሱንም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ሰኔ 11 ቀን ሰጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። ምዕመናንም መጥተው የቅዱስ ገላውዴዎስን ሥጋ ወሰዱ በመልካም አገናነዝም ገነዙት ከቅዱስ ፊቅጦር ሥጋ ጋርም በሣጥን ውስጥ አኖሩት። የስደቱም ዘመን እስኪሚፈጸም ጠበቁት። ❤ ከዚህም በኋላም የቅዱስ ፊቅጦር እናት ቅድስት ሶፍያ ወደ እንዴናው አገር መጣች የቅዱሳን ገላውዴዎስንና የፊቅጦርን ሥጋቸውንም ወስዳ ወደ አንጾኪያ አደረሰች። የቅዱስ ገላውዴዎስ ሥጋ አስዩጥ በሚባል አገር ይኖራል የሚልም አለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ መስተጋድል በቅዱስ ገላውዴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላሀሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ12 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለገላውዴዎስ ሃይማኖተ ክርስቶስ ተአረዞ። አልባሰ መንግሥት ኢሐወዞ። ለመኰንን ዐላዊ እንዘ ይትገዐዞ። እምይስማዕ ቃሎ ወእምይሰጠው ትዕዛዞ። በኲናተ እዱ አብደረ ተረግዞ"። ትርጉም፦ የክርስቶስ ሃይማኖትን ተጐናጽፎ (በተጐናጸፈ ጊዜ) የመንግሥት ልብሶች ደስ ያላሰኘው ለኾነ ለገላውዴዎስ ሰላምታ ይገባል፤ ከሐዲው መኰንን ሲከራከረው ቃሉን ከሚሰማና ትዕዛዙን ከሚቀበል ይልቅ በእጁ ጦር መወጋትን ወደደ። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወኢትፈርህ እምግርማ ሌሊት። እምሐፅ ዘይሠርር በመዓልት። እምግብር ዘየሐውር በጽልመት"። መዝ90፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ማቴ10፥16-32። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም አቡነ ገብረ ኢየሱስ፣ አቡነ መዝሙረ ድንግልና የቅዱስ ገላውዴዎስ የዕረፍት በዓል። በሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሰኔ ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያኑ ቅዱሳን በግብጽ ቤተ ክርስቲያ ጨምር ቅድስና ለተሰጣቸው ለአብረ ገብረ ኢየሱስ፣ ነገረ ማርያምን ወደ ግእዝ ቋንቋና አራቱ ወንጌልን ወደ ተለያየ ቋንቋ ለተረጎሙት ለአቡነ መዝሙረ ድንግል ለዕረፍታቸው በዓልና በጦርነት ድል አድራጊው ከቤተ መንግሥት ወገን ለሆነ በንጽህናው የመላእክት አርያ ላለው ለከበረ ሰማዕት ለቅዱስ ገላውዴዎስ ለተጋድሎው ፍጻሜ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእስክንድርያ ከተማ ከተሠራች ከአርባ ሰማዕታት ከቅዳሴ ቤተ ክርስቲያንና ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከቅዱስ ክርዳኑ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ አቡነ ገብረ ኢየሱስ፦ የተባሉት ኢትዮጵያዊ ጻድቅ በአገራችን ብዙ ተአምራትን በማድረግ ወንጌል ሲሰብኩ ከኖሩ በኋላ የግብጽ ገዳማትን ለመሳለም ወደ ግብጽ ወርደው አባ መቃርስ ገዳም ገቡ። ከዚያም ወጥተው በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ገብተው በዚያ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ። አቡነ ገብረ ኢየሱስ ታላቅ የሆነ ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባት ስለሆኑ በዚህም ግብጻውያን ይቀኑባቸው ነበር። ❤ ስልሳ ስድስተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ገብረ ክርስቶስ ባረፉ ጊዜ ኤጲስቆጶሳቱ ተሰብስበው ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወደ አስቄጥስ መጥተው ለከበረች ሹመት የሚገባውን እየመረመሩ ሁለት ወር ተቀመጡ። በዚህም ጊዜ በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ለሚኖሩት ለጻድቁ አቡነ ገብረ ኢየሱስ የታዘዘ መልአክ ተገልጦላቸው "ለኤጲስ ቆጶሳቱ ለዚህች ለከበረች ሹመት የሚገባው ስሙ ገአርጊ የሚባል በመካከላችሁ አለና እርሱን ሹሙት አትዘኑ" በላቸው ብሎ ነገራቸው። አቡነ ገብረ ኢየሱስም "በመካከላችሁ ስሙ ስልሳ ሰባተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾመዋቸዋል። ❤ አባ ገአርጊም ስማቸው አባ ቄርሎስ ተብሎ ከተሾሙ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ አገልግለዋል። በወቅቱ የነበረው የግብጻውያኑ ንጉሥ በጣም ብዙ ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም አቡነ ገብረ ኢየሱስ ሄደው በድፍረት አስተምረውትና ገሥጸውት በአንድ ሚስት ብቻ እንዲጸና አድርገውታል። የጻድቁ አባታችን ገዳላቸው በጣና ይገኛል። ሰኔ11 ቀን ዐርፈው የተቀበሩት ግን በዛው በግብጽ በቊስቋም ገዳም ነው። ግብጻውያን የቅድስና ማዕረግ ሰጥተዋቸው ታቦት ቀርጸውላቸው በዓላቸውን በሚገባ ያከብሩላቸዋል። ከአቡነ ገብረ ኢየሱስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። + + + ❤ አቡነ መዝሙረ ድንግል፦ የተባሉት ጻድቅ አገራቸው ጎጃም ነው፤ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ባለ ውለታ ናቸው። ጻድቁ በአምስት ሊቃውንት እየተመሩ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራቱን ወንጌላት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም በግእዝ፣ በአረማይክ፣ በዕብራይስጥና በዐረብኛ ጽፈው በአራት ዓምት ያዘጋጁ ታላቅ አባት ናቸው። ዛሬም በሞጊና ገዳም ይገኛል። ❤ ከዚህም ሌላ ነገረ ማርያምንም በግእዝና በዕብራይስጥ አዘጋጅተው ጽፈውታል። ሌሎችንም በርካታ መጻሕፍት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች እየተረጎሙ ጽፈው ያስቀመጡ ነበር። በጣም ጸሎተኛ፣ ደራሲ፣ ባሕታዊ፣ ጻድቅና መናኝ የሆኑት አቡነ መዝሙረ ድንግል ዐርፈው የተቀበሩት ጣና ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነው። ከአቡነ መዝሙረ ድንግል ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን። + + + ❤ "ሰላም ለገላውዴዎስ ድንግል ወንጹሕ ወመስተዐግሥ"። ትርጉም፦ ድንግል፣ ንጹሕና ታጋሽም ለኾነ ለገላውዴዎስ ሰላምታ ይገባል። + + + ❤ ሰማዕቱ ቅዱስ ገላውዴዎስ፦ ይህ ቅዱስ ምድራዊ መንግሥትንና የዚህን ዓለም ክብር የናቀ ነበረ መልካም ገድልንም ተጋደለ። የማይጠፋ ሰማያዊ መንግሥትንና የማያልቅ ክብርንም ወረሰ። ❤ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብጥልዎስ ነው እርሱም ለሮሜ ንጉሥ ለኑማርያኖስ ወንድሙ ነው መልኩም እንደ እስራኤል ያዕቆብ ልጅ እንደ ዮሴፍ ውብ ነበር። እርሱም በጦርነት ላይ የበረታ ነበር። የአንጾኪያ ተወላጆችም ይመኩበት ነበር። ስለ ደም ግባቱና ጽናቱ በሁሉ ዘንድ የተወደደ ነበር። እርሱንም ከመውደዳቸው ብዛት የተነሣ ጠላቶችን ድል እንዳረጋቸው እነርሱም ድል ሁነው በውርደት በብዙ ድንጋጤ ከፊቱ እንደሸሹ አድርገው ሥዕሉን ሥለው በከተማው መግብያ በር ላይ ያኖሩት ነበር። ❤ ቅዱስ ገላውዴዎስ የቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር ያነብ ነበር። የሮሜ ንጉሥም ዜናውን ሰምቶ ሊያየው ወደደ ልጁ ገላውዴዎስንም ይልክለት ዘንድ ወደ አባቱ ላከ እርሱም ላከለት። በደረሰም ጊዜ በደስታ ሊቀበለው ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋራ ወጣ በአየውም ጊዜ ደስ ተሰኘበት የሮሜ ከተማ ሰዎች ሁሉም ደስ አላቸው። ከእነዚያ ወራቶችም በኋላ ከቊዝ አገር ሰዎችና ከአርማንያ ታላቅ ጸብ ተነሣ ይህም ቅዱስ ገላውዴዎስ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ታምኖ ወደ እነርሱ ወጣ ድልም አደረጋቸው ንጉሣቸውንም ያዘው ጣዖታቶቻቸውንም ሰበራቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ተመለሰ ዲዮስቆሮስም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክዶ አምልኮ ጣዖትን በአጸና ጊዜ እጅግ አዘነ ፊቅጦር የሚባል የኅርማኖስ ልጅ ወዳጅ ነበረው ሁልጊዜም የመጻሕፍትን ቃል ይሰሙ ነበር ስለ ነፍሳቸውም ድኅነት ያነቡ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ያፈሱ ዘንድ ተስማሙ። በዚያ ጊዜም ሰይጣን በሽማግሌ አምሳል ታያቸው ያዘነላቸውም መስሎ እንዲህ አላቸው "ልጆቼ ሆይ መልካምች ጐልማሶች ናችሁ የነገሥታት ልጆችም ናችሁ። ስለ እናንተ እፈራለሁ አዝንላችኋለሁም እኔም ከንጉሡ ጋር ትስማሙ ዘንድ ለአማልክትም ታጥኑ ዘንድ እመክራችኋለሁ ሲአዝዛችሁም ትእዛዙን አትተላለፉ እናንተም ክርስቶስን በቤታችሁ አምልኩት ይህ ንጉሥ ኃይለኛ ርኅራኄም የሌለው ጫካኝ ነውና" አላቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር የሚነጋገራቸው ሰይጣን እንደሆነ አስገነዘባቸው "ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሐሰት አባት ሆይ ከእኛ ራቅ አንተ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ሕግ ትቃረናለህና" አሉት። ያን ጊዜም መልኩን ለውጦ እንደ ጥቁር ባሪያ ሆነ እንዲህም አላቸው "እነሆ ከንጉሥ አጣልቼ ደማችሁን እንዲአፈስስ አደርገዋለሁ" ሰይጣኑም ይህንን ብሎ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ሔዶ "ፊቅጦርና ገላውዴዎስን ካልገደልካቸው በአንተ ላይ ይነሣሉ አንተንም ገድለው መንግሥትህን ይወስዳሉ እነርሱም የመንግሥት ልጆች ናቸውና" አለው። ❤ ስለዚህም ንጉሡ ወደ ቅዱስ ገላውዴዎስ ልኮ ወደርሱ አስመጣው ለጣዖታቱም እንዲሠዋ ለመነው የአባቱንም ሹመት ይሾመው ዘንድ ቃል ገባለት ሰምቶም አልታዘዘለትም። ንጉሡም ክፉ ቃልን ሊናገረው አልደፈረም ቅዱስ ገላውዴዎስ ግን በድፍረት ይናገረው ነበር ያለ መፍራትም ንጉሡንና የረከሱ አማልክቶቹን ሰደበ። ኅርማኖስም ቅዱስ ገላውዴዎስን ወደ ግብጽ እንዲልከውና በዚያ እንዲገድሉት ንጉሡን መከረው እርሱ እንደ ልጄ እንደ ፊቅጦር ዐመፀኛ ነውና። ❤ ንጉሡም ወደ እንዴናው ገዥ እንዲህ ብሎ ጻፈ "ገላውዴዎስ ትእዛዛችንን አልተቀበለም ቃላችንንም አልሰማም አንተም ወደ ትዕዛዛችን ይመለስ እንደሆነ በብዙ ድካም ሸንግለው ይህ ካልሆነ ራሱን በሰይፍ ቁረጥ"። ቅዱስ ገላውዴዎስ ወደ እስክንድርያ ይወስዱ

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሰኔ ፲ 10 ❤ እንኳን ለክርስቲያን ወገኖች በዓለሙ ሁሉ ታላቅ ደስታ ለሆነበት መላእክትም በሰማያት ደስ ለተሰኙባት ቀን በዓል (በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ የጣዖት ቤቶች እንዲዘጉ አብያ ክርስቲያናትም እንዲከፈቱ ትዕዛዝ ወጥቷልና)፣ ለቅዱሳን ደናግል ደባሞንና ብስጣሞን ለእናታቸው ለቅድስት ሶፍያ ሰማዕታት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከእነ ቅድስት ሶፍያ ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበሉ ከቅድስት ዮና ከቅዱሳን ዋርስኖፋና አውሎጊስ ከመታሰቢያቸው፣ ከሰማዕት ከቅዱስ አቅሊሞስ፣ ከአባ ነአንና ከይስካ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚች ዕለት ለክርስቲያን ወገኖች በዓለሙ ሁሉ ታላቅ ደስታ ሆነ መላእክትም በሰማያት ደስ ተሰኙባት። በዚች ቀን እውነተኛ ምዕመን ከሆነ ከንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ የጣዖት ቤቶች እንዲዘጉ አብያተ ክርስቲያናትም እንዲከፈቱ ትዕዛዝ ወጥቷልና። ❤ ደስታን የተመላች ያች መልእክት ወደ እስክንድርያ ከተማ እንደ ዛሬዋ ቀን በደረሰች ጊዜ ፈጽሞ ደስ ተሰኙ ወደ ግብጽ አውራጃዎችም ሁሉ ላኳት ምዕመናን ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን ክብር ከፍ ከፍ ማለት ደስ አላቸው የጣዖታት ቤቶችንም ዘጓቸው አብያተ ክርስቲያናትንም ከፈቱአቸው እንደ ዛሬም በዚች ዕለት ሰኔ 10 ቀን በዓል አደረጉ ይኸውም ቈስጠንጢኖስ በነገሠ በዐሥራ አንድ ዓመቱ ነበር እለእስክድሮስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመባት በመጀመሪያ ዓመት ነበር። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በእኛ ላይም ይቅርታውና ቸርነቱ ይደረግልን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱሳን ደናግል ደባሞንና ብስጣሞን እናታቸው ቅድስት ሶፍያ፦ እንዲህም ሆነ ስሙ ዋርስኖፍ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ኤጲስቆጶስነት ሊሾሙት በወደዱ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ናባ አውራጃ እሊህ ደናግል ወዳሉበት ወደ ግሕሙን ደርሶ በዚያ አደረ። በዚያቺም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት "ከዚህ ለምን ትተኛለህ ተነሥተህ ተጋደል ለአንተና ሰማዕት መሆን ለሚሹ ሁሉ አክሊል ተዘጋጅተቀልና አሁንም ተነሥተህ ወደ መኰንኑ ሒድ በፊቱም ቁመህ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመን" አለው። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ራእይን እንዳየ ለቅዱሳን ደናግል ነገራቸው። ❤ ሲነጋም ተነሥተው ከእርሱ ጋራ ወደ መኰንኑ ሔዱ በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ታመኑ። መኰንኑም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸውና ወደ ወህኒ ቤት ጨመራቸው ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ከዚያ አውጥቶ ከቅዱስ ዋርስኖፍ ጋራ ወደ ስንሑር ላካቸው እናታቸውም ትከተላቸው ነበር። መኰንኑም "ለአማልክት ዕጣን ዕጠኑ" አላቸው ባልታዘዙለትም ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ አጸናቸው ቊስላቸውንም ፈወሰ። ❤ ከዚህም በኋላ መኰኑኑ ከእርሱ ጋራ ወደ አገረ ፃ ይዞአቸው ሔደ። የጣዖታቱ ካህናትም ጣዖታቱን እንደምትረግም ስለ ቅድስት ደባሞን ነገሩት እንዲሁም ባልጀራዋ ዮና የምትባል ሴት እንዳለች ነገሩት እርሱም ኅብራቸው በየራሱ የሆኑ መልካም ልብሶችን እየሠሩ ለምግባቸው ይሸጡ ነበር የተረፋቸውንም ይመጸውቱ ነበር። መኰንኑም የዮናን ዜና ሰምቶ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጥ ባለሰይፉን ላከው የሰያፊውም ስም አውሎጊስ ነው። ወደርሷም በቀረበ ጊዜ ፊትዋ እንደ መላእክት ፊት ብርሃንን ተመልቶ አየና ፈራ እርሷንም ወደ መኰንኑ እንዲወስዳት እንጂ እንዳይገድላት የእግዚአብሔር ጸጋ አስገነዘበችው ቤተ ሰቦቿም ተሰናባብተዋት ጸንፋ ከሚባል አገር ወጣች ወደ አገረ ፃ ደርሳም መኰንኑን ተገናኘችው ከቅዱስ ወስኖፍና ከባልንጀሮቹ ጋራ እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ። ሰያፊው አውሎጊስም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነና ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ እንዲሁም እሊያን ቅዱሳት ደናግልንም ራሳቸውን ቈረጧቸው ገድላቸውንም ፈጽመው የድል አክሊልን ተቀበሉ። ❤ ቅድስት ደባሞንን ግን ጽኑዕ ሥቃይ ያሠቃዩአት ዘንድ በመንኰራኵር ላይ ሰቀሉአት። በዚህ ሥቃይም ውስጥ ለብዙ ቀኖች ኖረች የእግዚአብሔር መልአክም ያጸናት ያስችላትና ቊስሎቿን ይፈውሳት ነበር መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገባት በዚያም ጥቂት ቀን ኖረች ወደ ፍርድ ሸንጎም አስቀርቦ "ለአማልክት ሠዊ"" አላት ባልሰማችውም ጊዜ ራሷን እንዲቆርጡ አዘዘ። ራስዋንም ሊቆርጡ ከከተማ ወደ ውጭ በአወጧት ጊዜ ሴቶች ሁሉ እያለቀሱ ከብበዋት ነበር ራስዋንም በሰይፍ ቆረጥዋት እንዲሁም እናቷንና እኅቷን በሰይፍ ቆረጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የድል አክሊል ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳት ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይድረስን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ10 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለሶፍያ ወለአዋልዲሃ ዲባሞን ወብስጣሞን ዘሳተፋ። ይሰነዓዋ ለስምዕ ምስለ ዋርስኖፋ። እማ ወዮና ዘሀገረ ጸንፋ። እምነ ወዲቅ ኪያየ ይሐቅፋ። ከመ ዕጐሊሃ ተሐቅፍ ዶርሆ በክንፋ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ(አርኬ) የሰኔ 10። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ተፈሣሕነ ወተሐሰይነ በኲሉ መዋዕሊነ። ወተፈሣሕነ ህየንተ መዋዕል ዘአሕመምከነ። ወህየንተ ዓመተ አንተ ርኢናሃ ለእኪት"። መዝ 89፥14-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ11፥20-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ የዲዮስቆሮስ ወይም የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሰኔ ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ሳሙኤል ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለቅዱስ ሉክያኖስ ከሌሎች አራት ሰማዕታት ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከቅዱሳን ከዮሐንስና ከጳጳስ አርልክሳ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል፦ የዚህ ቅዱስ አባቱ ሕልቃና ይባላል የእናቱም ስሟ ሐና ነው እርሱም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ወገን ናቸው ሐናም መካን ነበረች ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር እያለቀሰች አዘውትራ ስለ ማለች ይህን የተባረከ ልጅ ሰጣት በቤቷም ሦስት ዓመት አሳደገችው። ❤ ከዚህም በኋላ ገና ስትፀንሰው እንደተሳለች ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አቀረበችው ካህኑ ኤሊንም በመላላክ የሚያገለግለው ሆነ። የካህኑ ልጆች ግን ክፉዎች ነበሩ እግዚአብሔርንም አይፈሩም ነበር በቅዱስ መሥዋዕቱም ላይ በደሉ። ይህ ሕፃን ሳሙኤል ግን በኤሊ ፊት ለእግዚአብሔር ሲያገለግል ኖረ በነዚያ ወራቶችም ቃለ እግዚአብሔር ውድ ነበር የሚታይ ራእይም አልነበረም። ❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ሌሊት እንዲህ ሆነ ኤሊ በመኝታው ተኝቶ ሳለ ዐይኖቹንም መፍዘዝ ጀምረው ነበር ማየትም አይችልም ነበር። የእግዚአብሔርንም መብራት አብርቶ ለማሳደር ገና አላዘጋጁም ነበር ሳሙኤል ግን በቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ማደሪያ ታቦት አጠገብ ተኝቶ ነበር። እግዚአብሔርም "ሳሙኤል ሳሙኤል ሳሙኤል" ብሎ ጠራው እነሆ እኔ አለሁ አለ። ወደ ኤሊም ፈጥኖ ሔደ "ስለጠራኸኝ እነሆ እኔ መጣሁ" አለው። ኤሊም "አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ" አለው ሒዶም ተኛ። እግዚአብሔርም ዳግመኛ "ሳሙኤል ሳሙኤል ሳሙኤል" ብሎ ጠራው ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ኤሊ ሔደ ስለ ጠራኸኝ እነሆ መጣሁ" አለው ኤሊም "አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ" አለው። ❤ ሳሙኤልም ከዚህ አስቀድሞ እግዚአብሔርን በራእይ ገና አላወቀውም ነበር ቃለ እግዚአብሔርም አልተገለጠለትም ነበር። ዳግመኛም እግዚአብሔር ሳሙኤልን ሦስት ጊዜ ጠራው ተነሥቶም ወደ ኤሊ ሔደ "ስለጠራኸኝ እነሆ መጣሁ" አለው ኤሊም ያንን ልጅ እግዚአብሔር እንደጠራው አሰበ። "ልጄ ተመልሰህ ተኛ የሚጠራህ ካለ እኔ ባሪያህ እሰማለሁና ጌታዬ ተናገር በለው" አለው ሳሙኤልም ሒዶ በመኝታው ተኛ። እግዚአብሔር መጥቶ እንደ መጀመሪያው በፊቱ ቁሞ ጠራው። ሳሙኤልም "እኔ ባሪያህ እሰማለሁና ጌታዬ በል ተናገር" አለው እግዚአብሔርም ሳሙኤል "የሰማው ሁሉ ሁለቱን ጆሮዎቹን ይይዝ ዘንድ እንሆ እኔ በእስራኤል ላይ የተናገርሁት ቃሌን አደርጋለሁ። በዚያችም ቀን በኤሊና በወገኑ ላይ የተናገርኹትን ሁሉ አጸናለሁ እጀምራለሁ እፈጽማለሁም። ልጆቹ እግዚአብሔርን ቃል አቃልለዋልና እርሱም አልገሠጻቸውምና በልጆቹ ኃጢአት እኔ ወገኑን በዘላለም እንደ ምበቀለው ነገርሁት። ስለዚህ ነገር በዕጣንም ቢሆን በመሥዋዕትም በመሆን የኤሊ የወገኑ ኃጢአት እስከ ዘላለሙ ድረስ እንዳይሠረይ ራሴ እንዲህ ብሎ ማልሁ"። በኤሊ ወገኖችና ልጆች ላይ እግዚአብሔር የተናገረው ሁሉ ተፈጸመ። ❤ ከዚህም በኋላ የቂስ ልጅ ሳኦልን ቀብቶ ለእስራኤል ልጆች ያነግሠው ዘንድ እግዚአብሔር ሳሙኤልን አዘዘው እንዲአነግሥላቸው ለምነዋልና። ሳኦልም የልዑል ትዕዛዝ በተላለፈ ጊዜ ዳግመኛ ለእስራኤል ንጉሥ ሊሆን የዕሴይ ልጅ ቅዱስ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ ይህን ነቢይ ሳሙኤልን ዳግመኛ አዘዘው። ❤ ይህም ነቢይ ሳሙኤል በሕይወት በኖረበት ዘመን ሁሉ እስራኤልን አስተዳደራቸው። ከዚህም በኋላ ሰኔ 9 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱስ ሉክያኖስና አራቱ ሰማዕታት፦ ይህም ቅዱስ አስቀድሞ የጣዖት ካህን ነበር የሰማዕታትንም መከራቸውን በእሳት ሲአቃጥሏቸውና ሕዋሳታቸውን ሲቆራርጧቸው ሲሰቅሏቸው ከእሳት ምድጃ ውስጥም ሲጥሏቸው ምንም ምን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው በአየ ጊዜ ከዚህ ሥራ የተነሣ አደነቀ ክብር ይግባውና በጌታችን አመነ ያገለግላቸው የነበሩ ጣዖታት ከእሳት ቢጥሏቸው ፈጥነው ይቃጠላሉ እንጂ ይህን ሥራ ሊሠሩ እንደማይችሉ ተረድቷልና። ዳግመኛም እንዲህ አለ "ይህን ድንቅ ሥራ የሚሠራ አምላክስ በእውነት እርሱ አምላክ ነው"። ❤ ከዚህ በኋላም በንጉሥ ፊት "እኔ ክርስቲያን ነኝ ክብር ይግባውና በክርስቶስ አምናለሁ" ብሎ በግልጥ ጮኾ ተናገረ። ንጉሡም ወደርሱ አቅርቦ ጣዖት ማምለክን እንዳይተው መከረው ወደ አምልኮ ጣዖት ይመለስ እንደሆነ ብሎ ብዙ ቃል ኪዳኖችን ገባለት። እርሱም ግን አልሰማውም ሥቃዩንም አልፈራም ከዚህም በኋላ ንጉሡ ጽኑዕ ሥቃይን ሊአሠቃየው ጀመረ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት መንጋጋውንም በደንጊያ አሰንዲሰብሩት ታላቅ ግርፋትንም እንዲገርፉት አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላም አራት ክርስቲያን እሥረኞች ቀረቡና ከእርሱ ጋራ አቆሟቸው ንጉሡም "ለአማልክት ዕጣን ዕጠኑ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሥቃይን አሠቃያችኋለሁ" አላቸው። እነርሱም ለስሕተቱ አልታዘዙለትም በላያቸውም ተቆጥቶ በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመራቸው ያንጊዜ ዝናብ ዘነበ እሳቱንም አጠፋው። ❤ ቅዱስ ሉክዮስን ግን "እንደ አምላክህ እሰቅልሃለሁ" ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ እንዲሰቅሉት አዘዘ በረጃጅም ችንካሮችም ሥጋውን ሁሉ ቸነከሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። እንዚያን አራቱን ሰዎችም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሉክያኖስና በከበሩ አራት ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ቴድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ9 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለሉክያኖስ ዘአድምዐ ተወድሶ። ምስለ ፬ቱ ዕደው ሥቃያተ ስምዕ በተዓግሦ። ሶበ ለአማልክት ኢሦዐ መሥዋዕተ ልዑል አስተኀይሶ። እለ ቀነውዎ እስከ ይመጡ ነፍሶ። እስመ በአዕባን ቀጥቀጡ መንከሶ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 9። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወሳሙኤልኒ ምስለ እለ ይጼውዑ ስሙ። ይጼውዕዎ ለእግዚአብሔር ውእቱኒ ይሰጠዎሙ። ወይትናገሮሙ በዐምደ ደመና"። መዝ 98፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥32-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcww

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሰኔ ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን አምላክን ለወለደች በሁለት ወገን ድንግል ለሆነች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ላለች ለቤተ ክርስቲያንዋ ለቅዳሴ ቤት ከእመቤታችን ከሠላሳ ሦስቱ በዓል አንዱ ለሆነ በዓል (እርሱም ጌታችን ከእርሷ ጋር ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ ሲመለስ ያፈለቀው የተባረከ መታጠቢያ ውሃ (ጠበል) ነው፣ ለርማኖስ እናት ለቅድስት ትምዳ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከአንድ ሽህ ሁለት ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ ከቅዱሳን ከአትካሮንና ከአውሎጊስ ከበዓላቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ ክርስቲያንዋ ለቅዳሴ ነው። እርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ጋር ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ ሲመለስ ያፈለቀው የተባረከ መታጠቢያ ነው። ❤ ይህም እንዲህ ነው ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት "ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ" አለው። ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ። ❤ ኄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት "ወደ እስራኤል አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ" አዘዘው። በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት እርሷም እስከ ዛሬ አለች ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ በዛሬዪቱ ሰኔ 8 ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ። ❤ እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 8 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ዕብል ለቅዳሴ ቤትኪ ሕንፅት። ኀበ አንቅዐ ወሌድኪ ማየ በረከት። ማርያም ድንግል በስምከመ በቊዔት። እስመ ይትወሀብ ለዘጸለየ በኵሉ ዕለት። ሠናይ ሀብት ወፍጹም ፍት"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 8። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እፎ እስፋሕ ለከ ሥጋየ። በምድረ በድው ኀበ አልቦ ዕፅ ወማይ። ከመዝ በመቅደስከ አስተርአይኩከ"። መዝ62፥1-2"። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ4፥14-17። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወአስተዮሙ ከመ ዘእምቀላይ ብዙኅ። ወአውኃዘ ማየ ከመ ዘእምአፍላግ። ወአውጽአ ማየ እምዕብን"። መዝ 77፥15-16። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 2፥13-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥10-13 እና የሐዋ ሥራ 7፥44-51። የሚነበበው ወንጌልን ዮሐ 4፥1-15። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለያዕቆብ ኤጲስ ቆጶስ ዘሀገረ ሥሩግ ወምህሮሙ ሕግ"። ትርጉም፦ ትምህርቱ ሕግና የሥሩግ ሀገር ኤጲስ ቆጶስ ለኾነ ለያዕቆብ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/Eotcw

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሰኔ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለተከፈተበትና ለከበረችበት፣ ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለአባታችን ለአቡነ ማቴዎስ ዘእንደርታ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓላቸውና ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም ለሆነ ለአባ አበስኪሮን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን በስክሳሩ ከሚታሰቡ፦ መኰንን አርማንዮስ ካሠቃያቸው ከአስራ ስድስት ሺህ ሰማዕታት ከዕረፍታቸው መታሰቢያና ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበትና የከበረችበት ነው። እርሷም ዌላ በሚባል አደባባይ ያለች ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ተዘግታ የኖረች ነበረች። ይኸውም በአንድ ሽህ ሃያ ዓመተ ሰማዕታት ነው። ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ሰው ለሆነ ሕይወትና መድኃኒት አድርጎ እርሷን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አቡነ ማቴዎስ፦ እኚህ ጻድቅ ትውልድ አገራቸው እንደርታ ሲሆን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሾሟቸውና በሀገራችን ለስብከተ ወንጌል ካሰማሯቸው ከ 47ቱ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው። ጻድቁ መላ ሰውነታቸው እንደ እሳት ያቃጥል ነበር። ወንጌልን በመስበክና በተአምራታቸው ድውያንን እየፈወሱ ብዙ ያገለገሉ ታላቅ አባት ናቸው። መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት ላይ። + + + ❤ አባ አበስኪሮስ፦ ይህም ቅዱስ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራ ውስጥ ነበር የከሀዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ስለ አምልኮ ጣዖት የሆነች ትእዛዝ በደረሰችው ጊዜ። ወዲያውኑ ይህ በሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ ወታደር ስለ ሆነም ያሠቃየው ዘንድ ማንም አልደፈረም ነገር ግን በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ አሠሩት። ❤ መኰነንኑም ወደ አገረ አስዩጥ በሔደ ጊዜ ወደ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋራ ሌሎች ወልደፍዮስ፣ አርማንዮስ፣ አርኪያስ፣ ጴጥሮስና ቀራንዮስ የተባሉ ነበሩ እሊህም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ሊአፈሱ ከአባ አበስኪሮስ ጋር ተስማሙ። በንጉሡም ፊት በቆሙ ጊዜ በጌታችን ታመኑ ንጉሡም ትጥቃቸውን ይቆርጡ ዘንድ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘም አደረጉባቸው። ከእኒህ ከአምስቱ ግን ራሶቻቸውን የቆረጡአቸው አሉ የሰቀሉአቸውም አሉ እንዲህም ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ። ❤ የከበረ አበስኪሮስን ግን ታላቅ ግርፋትን እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ ከራሱ እስከ አንገቱ ቆዳውን እንዲገፉ በፈረስ ጅራትም አሥረው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ። ይህንም ሁሉ አደረጉበት። ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ አድርገው በላዩ አፉን ዘግተው ተሸክመው ወስደው በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በሥቃዩም ውስጥ ሁሉ የእግዚአብሔር መልአክ ወደርሱ ይመጣና ያጽናናው ነበር ያስታግሠውም ነበር ያለ ምንም ጉዳት አድኖ በደኅና ያስነሣው ነበር። ❤ ከማሠቃየቱም በደከመ ጊዜ ከሥራየኞች ሁሉ የሚበልጥ በሥራዩም ወደ አየር ወጥቶ ከአጋንንት ጋራ የሚነጋገር ሥራየኛ አመጣለት። እርሱም የውሽባ ቤቱን ዘግተው ሽንት እንዲረጩበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። እባብንም ይዞ በላዩ አሾከሾከና ለሁለት ክፍልም ሁኖ ተሠነጠቀ መርዙንና ሆድ ዕቃውን ወስዶ በብረት ወጭት አድርጎ አበሰላቸው በውሽባ ቤቱ ውስጥ ወደ አባ አበስኪሮን አቅርቦ ያንን መርዝ ይበላ ዘንድ ሰጠው ቅዱሱም በላ ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። ያም መሠርይ "የመኳንንተ ጽልመት አለቃቸው ሆይ በዚህ ክርስቲያናዊ ላይ ኃይልህን አድርግ" ብሎ ጮኸ ምንም ምን ጥፋት ባልደረሰበት ጊዜ መሠርዩ አደነቀ። ቅዱስ አበስኪሮንም መሠርዩን "የሚራዳህ ሰይጣንህስ በክብር ባለበት በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አንተን ይቀጣሃል" አለው። ወዲያውኑ ጥሎ የሚያንከባልለው ክፉ ሰይጣን ተጫነበት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ታመነ ድረስ አሠቃየው። መኰንኑም የመሠርዩን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና በሰማዕትነት ሞተ። በቅዱስ አበስኪሮን ላይ ግን ቁጣና ብስጭትን በመጨመር ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው አባለ ዘሩንም እንዲቆርጡ አዘዘ እርሱ ግን በመከራው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ሰኔ 7 ቀን ቆረጡት የድል አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ❤ ከቅዱስ አበስኪሮን ተአምራትም አንዱን እንነግራችኋለን በግብጽ ደቡብ በስሙ የታነፀች ቤተ ክርስቲያን ነበረች ካህናቷም ክፉ ሥራ የሚሠሩ ክፉዎች ነበሩ ቅዱስ አበስኪሮንም ከክፋታቸው ተመልሰው ንስሓ ቢገቡ ብሎ ጠበቃቸው። ባልተመለሱ ጊዜ ግን የንዳድ በሽታ አምጥቶ ሁሉም በአንዲት ጊዜ ሞተ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አበስኪሮን በፈረስ ተቀምጦ የላዕላይ ግብጽ የሆነች ብያሁ ወደምትባል አገር ደረሰ የአገር ሰዎችም በደጃቸው ተቀምጠው ሳይተኙ በጨረቃ ብርሃን እርስ በርሳቸው ያወሩ ነበር። የከበረ አበስኪሮንም ከፊታቸው ደርሶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው በአዩትም ጊዜ የሰላምታውን አጸፋ እየመለሱ ተነሥተው ተቀበሉት ሁለተኛም "ያቺን የሚሻትን ምድር እያመለከታቸው ከምድራችሁ ጥቂት እንድትሰጡኝ እሻለሁ" አላቸው። እነርሱም "ጌታችን እንደወደድክ ይሁንልህ" አሉት መቶ የወርቅ ዲናርም ሰጥቷቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ከዚህ ራእይ የተነሣ አደነቁ። ❤ ከተኙ በኋላም ቤተ ክርስቲያኒቱን አፍልሶ ከግብጽ ደቡብ ወደ ላይ ግብጽ ብያሁ ወደምትባል አገር በመቶ የወርቅ ዲናር ወደ ገዛት ምድር ከንዋየ ቅዱሳቷ ሁሉና ከዐፀዷ ጋር አምጥቶ በዚያ አቆማት። የአገር ሰዎችም በጥዋት ነቅተው ወደ ውጭ በወጡ ጊዜ ቤተ ክርስቲያቱን በደጃቸው አገኙዋት እጅግ ፈጽሞም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ድንቅ ተአምር የሚደረግባት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በአባ በአበስኪሮን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 7 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ዕብል ለርኅወተ ቤትኪ ዮም። ከመ ኤልያስ አርኀወ ኆኅተ ዝናም። በስሱ አውራኅ ወበሠላስ ዓም። ማርያም ሥመሪ አርኅዎቶ ለሕሊናየ ሕቱም። ከመ ላዕሌሁ ይትከዐው ምስለ ጽድቅ ሰላም"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 7። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኵሉ ተዓይኒሁ ለያዕቆብ። ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር"። መዝ 86፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 6፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥6-10 እና የሐዋ ሥራ 12፥10-21። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 17፥14-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን ማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም በዓል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓልና የበዓሉ ዕርገቱ ሰሞን። ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሰኔ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ አባት ለጻድቁ ለሐዋርያም ለደራሲም ለተከራካሪ መምህርም ለያዕቆብ ዘሥሩግ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ያዕቆብ ዘሥሩግ፦ አገሩ ሶርያ ሲሆን አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። በኤጲስ ቆጶስነት የተሾመባት አገር በጤግሮስና በኤፍራጥስ መካከል በምትገኝ ሥሩግ በምትባል አገር ስለሆነ ያዕቆብ ዘሥሩግ ተባለ። በ 3 ዓመቱ እናቱ ቤተ መቅደስ ስትወስደው መልአክ እጁን ይዞ በሊቀ ጳጳሱ እጅ እንዲቆርብ አድርጎታል። በዚህም ጊዜ ምሥጢራት ሁሉ ተገልጠውለታል። ገና በ 7 ዓመቱ ስለ ሦስት ነገሮች በእጅጉ ያለቅስ ነበር። "ነፍሴ ከሥጋዬ ተለይታ ስትወጣ ከጌታችን ጋር ስትገናኝና መጨረሻውን ፍርድ ስሰማ እነዚህን ሦስት ነገሮች በእጅጉ እፈራለሁ" እያለ ያለቅስ ነበር። ❤ በ 12 ዓመቱ ብሉይንና ሐዲስን አጠናቆ ተመምሮ ጨርሷል። ጸጋውን ዐውቀው 5 ቱ ታዋቂ ሊቃነ ጳጳሳት መጥተው እጅ ነስተውት አዲስ ድርሰት ድረስልን ቢሉት እርሱም በፍጹም ትሕትና "በእናንተ ፊት እንኳን አዲስ ድርሰት ልደርስ ቀርቶ የተደረሰውንም መናገር አልችልም"። አላቸው። እርሱ በነበረበት ዘመን በሮማው መናፍቅ ልዮን አማካኝነት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመርያ ጊዜ ለሁለት የተከፈለችበት ጊዜ ነበርና እነ ዲዮስቆሮስ "የውሾች ጉባኤ" ከተባለው ከኬልቄዶን ጉባኤ ተለይተው ሃይማኖትን ሲያጸኑ ልዮንንም ማውገዛቸውን ያዕቆብ ሲሰማ በዲዮስቆሮስ ጽናት በእጅጉ ተደስቶ ደብዳቤ ጽፎ አመስግኖታል። እነ ልዮንን ግን አውግዞ እረግሟቸዋል። ልዮንም ተከታይ ባገኘ ብሎ "እኔን ምሰል" በማለት ለያዕቆብ ደብዳቤ ጻፈለት። ያዕቆብም "ሳጥናኤል ከመላእክት ጋር ምን አንድ አደረገው? አንተ ርኩስ ነህ፤ የዲዮስቆሮስን ጥርስ አስወልቀህ፣ ጢሞን አስነጭተህ፣ ሃይማኖትህን የቀየርህ ከሁለት ዓለም ስደተኛ ጋር አልተባበርም፣ ይልቅስ ንስሓ ግባ፣ ንስሓ ባትገባ ግን አንተ ዲያብሎስ ነህ ተከታዮችህም አጋንንት ናቸው። በማለት መልሱን ጽፎለታል። እምቢ ብሎ በክህደቱ ቢጸናበትም አውግዞ እረግሞ ንጽሕናውን ቅድስናው እንደ መላእክት ነው የተባለለት ያዕቆብ ዘሥሩግ ጻድቅም ሐዋርያም ደራሲም ተከራካሪ መምህርም ነው። ሦስት ድርሰቶች ያሉት ሲሆን በስሙ የተጠራው ቅዳሴም አለው። ዕረፍቱ ሰኔ 7 ቀን ነው። ከአባታችን ከአቡነ ያዕቆብ ዘሥሩግ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቱም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን። https://t.me/Eotcw

+ + + ❤ የዕለቱ ዓራራይ ዜማ፦ "ዐቢየ ተስፋ ዘአስፈዎሙ ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እስእሎ ለአቡየ ይፈኑ ለክሙ መንፈሰ ጽድቅ ጰራቅሊጦስ"። ትርጉም፡- ታላቅ ተስፋ ያደረገላቸው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን አባቴን እለምነዋለሁ እውነት መንፈስን ይልክላችኋል። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ"። መዝ 77፥65-66። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 28፥1-ፍ.ም፣ ማር16፥1-ፍ.ም፣ ሉቃ 24፥1-13። + + + ❤ የዕለቱ ቅዳሴ ምስባክ፦ "ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር። ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ። ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።" መዝ117፥24-25 ። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥20-41፣ 1ጴጥ 1፥1-13 እና የሐዋ ሥራ 2፥22-37። የሚነበው ወንጌል ዮሐ 20፥1-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጰራቅሊጦስ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

photo content
+1