fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
+ + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ጸርኁ ጻድቃን ወእግዚአብሔር ሰምዖሙ። ወእኲሎሙ ምዳቤሆመ አድኀኖሙ። ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ"። መዝ 33፥18-19 ወይም መዝ 99፥3። የሚነበበው ወንጌል ማቴ5፥1-14 ወይም ዮሐ 10፥1-7። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወቀተሉ ዕቤረ ወእጓለ ማውታ። ወቀተሉ ፈላሴ። ወይቤሉ ኢይሬኢ እግዚአብሔር"። መዝ 93፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ተሰ 2፥13-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 16፥22-28። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥23-35። ሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል፡ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን ለሐዋርያው ለቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ መታሰቢያው በዓሉ፣ ለቊስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ለጳውሎስ ለዕረፍት፣ ለከበረ ጳጳስ ለቅዱስ ኪራኮስ ከእናቱ ከቅድስት ሐና ጋራ በከሀዲው ንጉሥ በኤልያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአይድራዮስ፣ ከአዋርስ፣ ከሰማዕት አልድራክዎስና ከአድሮኖስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ፦ ቅዱሱ አባቱ እልፍዮስ ወይም ቀለዮጳ ይባላል፡፡ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በቅዱስ ወንጌል ላይ በአብዛኛው የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ እየተባለ ተጠርቷል፡፡ ማቴ 10፥3፣ ማር 3፦17፣ ሉቃ 6፥15፣ ሐዋ 1፥13፡፡ ❤ በሌላም በኩል ከታላቁ ያዕቆብ ከዘብድዮስ ልጅ ለመለየት ሲባል ታናሹ ያዕቆብ እየተባለ ተጠርቷል፡፡ ማር 5፥40፡፡ የእመቤታችን እኅት (ዘመድ) የቀለዮጳ ሚስት ማርያም ልጅ በመሆኑ "የጌታ ወንድም" ተብሏል፡፡ ማቴ 13፡55፣ ማር 6፡3፣ ገላ 1፡19፡፡ ሦስት ወንድሞች ያሉት ሲሆን እነርሱም ይሁዳ፣ ስምዖንና ዮሳ ናቸው፡፡ ❤ ሐዋርያው ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ብዙ ሀገራት ላይ ዞሮ ወንጌልን ካስተማረና ብዙዎችን ካጠመቀ በኋላ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም ገብቶ በምኩራባቸው አስተማረ፡፡ ክፉዎች አይሁድም "ደሙ በእኛ ላይ ይሁን" ብለው ከመካከላቸው አውጥተው ወስደው ለሮማው ንጉሥ ለቄሳር እንደራሴ ለሆነው ለንጉሥ ቀላውዴዎስ አቅርበውት "ይህ ሰው ስለ ቄሳር ሳይሆን ስለ ሌላ ንጉሥ ይሰብካል" ብለው ወነጀሉት፡፡ ንጉሡም ይህን ሲሰማ በድንጋይ ወግረው እንዲገድሉት አዘዘና ፈጥነው ወስደው ወግረው ገደሉት፡፡ ዕረፍቱ የካቲት 10 ነው፤ በዚህችም ቀን መታሰቢያው እንደሆነ የጥቅምት አምስት ስንክሳር ይናገራል። ከሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቱም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን። ❤ የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጳውሎስ፦ ይህም ቅዱስ ከእርሱ አስቀድሞ በቁስጥንጥንያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ለነበረው ለአባ እለእስክንድሮስ ደቀ መዝሙሩ ነው። አባ እለእስክንድሮስም በሞተ ጊዜ በርሱ ፈንታ ይህ አባት አባ ጳውሎስ ተሾመ። ❤ በጵጵስናውም ወንበር በተቀመጠ ጊዜ የአርዮስን ወገኖች ከቊስጥንጥንያ አገር ከአውራጃውም ሁሉ አውግዞ አሳደዳቸው። ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ከሞተ በኋላ ልጁ ሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ በቊስጥንጥንያ አገር ላይ ነገሠ ወንድሙ ቊንስጣም በሮሜ ሀገር ነገሠ። ይህ ቈስጠንጢኖስም አርዮስን ይወደዋል በረከሰች ሃይማኖቱም ያምናል ቅዱስ አባ ጳውሎስም አርዮሳውያንን አውግዞ እንዳሳደዳቸው ሰምቶ እጅግ አዘነ። ❤ አባ ጳውሎስንም "ከእንግዲህ የአርዮስን ወገኖች ተዋቸው አታውግዛቸው" አለው እርሱ ግን ንጉሡን አልሰማውም ስለዚህም አባ ጳውሎስን ከቊስጥንጥንያ አገር አሳደደው። ❤ እንዲህም ሆነ ከእርሱ አስቀድሞ ከእስክንድርያ ሀገር አባ አትናቴዎስን አሳድዶት ነበርና በሮሜ አገር በሊቀ ጳጳሳት በቅዱስ አባ ዮልዮስ ዘንድ ሁለቱም ተሰበሰቡ። እርሱም በመልካም አቀባበል በፍቅር ተቀበላቸው ወደ ንጉሡም ወደ ሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ እንዲህ ብሎ መልእክትን ጻፈላቸው "እነርሱ እውነተኞች የተማሩ አዋቂዎች ሃይማኖታቸውም የቀና ናቸው ልትቀበላቸው ልታከብራቸውም ይገባል"። ❤ ሊቃነ ጳጳሳቱም አባ ጳውሎስና አባ አትናቴዎስ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በደረሱ ጊዜ የመልእክቱን ደብዳቤ ሰጡት አነበባትም ከሮሜው ሊቀ ጳጳሳት ቃል የተነሳ ፈራ። ተቀብሎም በየቦታቸው በሹመታቸው ወንበር አኖራቸውና ጥቂት ቀኖች በእነርሱ ላይ ታገሰ። ❤ ከዚህም በኋላ ሁለተኛ አሳደዳቸው እነርሱም ወደ ሮሜ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ዮልዮስ ተመልሰው ንጉሡ በእነርሱ ላይ ያደረገውን ሁሉ ነገሩት ሊቀ ጳጳሳት ዮልዮስም ወደ ወንድሙ ወደ ንጉሥ ቊንስጣ ይዟቸው ገብቶ ወንድሙ ቈስጠንጢኖስ በእነርሱ ላይ ያደረገውን ነገረው። ይህም ንጉሥ ቊንስጣ ይቀበላቸው ዘነድ ወደ ወንድሙ መልእክትን ጻፈ እንዲህም ብሎ አዘዘው። "እሊህን አባቶች ካልተቀበልካቸው ከእንግዲህ በመካከላችን ፍቅር አንድነት አይሆንም ሊቀ ጳጳሳቱም እንዲሁ ሁለተኛ ደብዳቤ ጻፈ። ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም የወንድሙን የንጉሥ ቊንስጣንና የሊቀ ጳጳሳቱን መልእክት ተቀበሎ ወደ ሹመታቸው ወንበር መለሳቸው። ❤ ንጉሥ ቊንስጣም በአመጸኞች እጅ ከተገደለ በኋላ ያን ጊዜ ቈስጠንጢኖስ አባ ጳውሎስን ወደ አርማንያ አገር አጋዘውና በዚያ ጥቂት ቀን አሠረው። ከዚህም በኋላ ከአርዮስ ወገን አንዱን በእሥር ቤት በሥውር አባ ጳውሎስን ይገድለው ዘንድ አዘዘው አንዱ አርዮሳዊም በሌሊት ገብቶ አንቆ ገደለው መላ ዕድሜውም አርባ ዓመት ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጳውሎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የከበረ ጳጳስ ቅዱስ ካራኮስና እናት ቅድስት ሐና፦ እነዚህም ሰማዕታት ተበከሀዲው ንጉሥ በኤልያኖስ እጅ ተገደለ። ከሀዲው ንጉሥም ይህን ቅዱስ ወደ አደባባይ በአቀረበው ጊዜ "ሰዎች አማልክትን እንዳያመልኩ እየጻፈች የምትከለክል ይቺ እጅህ ትቆረጥ ዘንድ ይገባታል" አለው። ኪራኮስም "ልብ የሌለህ ውሻ መልካም አደረግህ" አለው። ❤ ኤልያኖስም ሰምቶ እርሳስ አፍልተው በአፉ ውስጥ እንዲያፈሱት ደግሞ በጋለ የብረት ዐልጋ ፍም በተጐዘጐዘበት ላይ እንዲአስተኙት ጨውም እንዲነሰንሱበት በመጐተትና በማገላበጥም ሆዱንና ጀርባውን በብረት በትሮች ዐጥንቶቹ እስቲሰበሩ እንዲደበድቡት አዘዘ። ቅዱስ ኪራኮስም ይህን ሁሉ ታግሦ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጸለየ "ያሮክስ ለያማውታ ያለክ አሲያር ለሜዶር ኤሎሄ ናውና ያዮል ያቤል ቊራም ቤተል አዶናይ ኤሎሄ ሙታ"። ❤ ከዚህም በኋላ ፈትተው በእሥር ቤት እንዲያኖሩት እናቱንም ሐናን እንዲአመጧት በጠጉርዋም ሰቅለው ሦስት ሰዓት ያህል ሥጋዋን እንዲሠነጣጥቋት በእሳትም እንዲአቃጥሏት አዘዘ በእሳት ውስጥም እየጸለየች ነፍሷን አሳለፈች። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ኪራኮስን አምጥተው እባቦችና እፍኝቶች ከአሉበት ታላቅ ጉድጓድ ውስጥ ይጨምሩት ዘንድ አዘዘ ሲጨምሩትም ምንም የጐዳው ነገር የለም። ከወታደሮችም አንዱ ስሙ አድሞን የሚባል የክርስቶስን ማዳን አይቶ አደነቀ። ክብር ይግባውና በጌታችንም አመነ ንጉሡንና ጣዖታቱንም ረገመ ያን ጊዜም ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ ንጉሥ ኤልያኖስ አዘዘ እርሱም የኪራኮስ "አምላክ ነፍሴን ተቀበላት" እያለ አንገቱን አስተካክሎ ለሰይፍ ሰጠ ምስክርነቱንም ፈጸመ። ❤ ቅዱስ ኪራኮስንም ከዘይት ጋር ዝፍት ከፈላበት ምጣድ ውስጥ እንዲጨምሩት ሁለተኛም ደረቱን በጦር እንዲወጉት አዘዘ። እንዲህም ምስክርነቱን በዕለተ ሰንበት ፈጸመ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለጳውሎስ በቊስጥንጥንያ ዘተጰጰሰ። መራዕየ ክርስቶስ ይርዐይ እምእለ የሀጕሉ ነፍሰ። አስተኀቂሮ በምድር አርዮሳዌ ንጉሡ። መንግሥተ ዘበሰማያት ከመ ውእቱ ኀሠሠ። በቤተ ሞቅሕ ሕኑቀ ፈለሰ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 5።

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ኮከብ፡ብሩህ ዘሰረቀ እምአቅሌስያ ቤተክርስቲያን ዘንሰምያ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ"። ትርጉም፦ አቅሌስያ ብለን ከምንጠራት ቤተክርስቲያን የወጣ ብሩህ ኮከብ በዕውነት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ ለኢትዮጵያና ለግብጽ ሰዎች አባት ሆናቸው፡፡ ከሊቁ ቅዱስ ያሬድ ድጓ ላይ። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

photo content

❤ እነዚህም ሦስቱ ቅዱሳን በአባታችን ላይ አድሮ ድንቅ ነገርን የሚሠራ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዋልድባው አቡነ ሳሙኤልም አባታችንን "አባት ሆይ በዚህች ቀን ድንቅ ሥራን አየን፣ አርአያህ የእግዚአብሔርን መልአክ አርአያ ይመስላል፣ ቅድስናህ ፍጹም ነው፣ የጸሎትህ ኃይል ሙታንን ያስነሣል፣ የተበሉ አንበሶችን ከአንበሶች ሆድ አወጣህ" አሏቸው፡፡ቅዱሳኑም ሥራቸውን እያደነቁ በልተው ጠጥተው ጠገቡ፡፡ በማግሥቱም አባታችን ቅዱሳኑን "በሰላም ሂዱ " ብለው መርቀው ሸኟቸውና የእግዚአብሔር ሥራ እያደነቁ ወደየበዓታቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡ ❤ በመጨረሻም ከዚህ ዓለም የሚለዩበት በቀረበ ጊዜ እንሆ የክበር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ ተገለጠላቸው። ስማቸውን ለሚጠራና መታሰቢያቸውን ለሚያደርግ እስከ ዐሥራ አምስት ትውልድ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ዐሥራ ሁለት አክሊል ሰጣቸው። ቅዱስ ሚካኤል ሦስት አክሊሎች፣ ቅዱስ ገብርኤል ሦስት አክሊሎች፣ ቅዱስ ሱራፊ ሦስት አክሊሎችና ቅዱስ ኪሩብ ሦስት አክሊሎችን አቀዳጇቸው። የዕድሜያቸውም ዘመናት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን መጋቢት5 በሰላም በፍቅር ዐረፉ። ጌታችንም ነፍሳቸውን ተቀቡሎ አቅፎም ሳማት በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ ምስጋና አሳረጋት። ከአባትችን ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ የመጋቢት5 ስንክሳርና ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን በመለከቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰዎች ኃጢአታቸው በፊታቸው የተገለጠ ሆነ፡፡ ሰው የገዛ ፊቱን በመሥታወት እንደሚያይ የኃጥአንም ሥራቸው በአባታችን ፊት እንዲሁ የተገለጠ ነውና፡፡ ❤ አባታችንም የኢትዮጵያን ሰዎች ኃጢአታቸውን በግልጽ በተመለከቱ ጊዜ ተወርውረው ወደ ባሕሩ በመግባት ተዘቅዝቀው መጸለይ ጀመሩ፡፡ "ከባሕር እንዳልወጣ፣ በእግሬም እንዳልቆም በሕያው ስምህ ምያለሁ" ብለው አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ቆዩ፡፡በ40ኛ ቀናቸው የታዘዘ መልአክ መጥቶ "ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ ብሎሃ" አላቸው፡፡ አባታችንም መልአኩን "መላ ኢትዮጵያን ካልማረ ከዚህ ባሕር አልወጣም" አሉት፡፡ መልአኩም ከእሳቸው ተለይቶ ከሄደ በኋላ አባታችን በዚያ ባሕር ውስጥ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖሩ፡፡ ❤ አባታችንም በባሕሩ ውስጥ ተዘቅዝቀው መቶ ዓመት ሲጸልዩ ከኖሩ በኋላ ደማቸው ፈሶ አለቀና ውኃው ደም መሰለ፡፡ ሥጋቸውም አልቆ አጥንቶቻው እንደበረዶ ሆኑ፡፡ ሰባት ሺህ እልፍ ሦስት መቶ የሚሆኑ አጋንንትም ከአራቱም አቅጣጫ እየመጡ ሰውነታቸውን በፍላፃዎቻቸው ይወጓቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ወደ አባታችን መጥቶ ከባሕሩ ዳር በመቆም "ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! መላ ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁና ተነሥ ከባሕሩ ውጣ" አላቸው፡፡ አባታችንም አጥንታቸው እንደመርፌ ቀዳዳ ተበሳስቶ ፈጽመው ደክመው ነበርና ጌታችን በክቡራን እጆቹ ሁለንተናቸውን ቢዳስሳቸው እንደቀድሞው ደህና ሆኑ፡፡ጌታችንም ከባረካቸው በኋላ ወደ ምድረ ከብድ እንዲሄዱ ነገራቸው፡፡ ❤ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምድረ ከብድ እንደደረሱ እንደ ዓምድ ተተክለው ሰባት ዓመት ቆመው ጸለዩ፡፡በዚህም ጊዜ ሰይጣን በቁራ ተመስሎ መጥቶ ሁለት ዐይኖቻቸውን አንቁሮ አጠፋቸው ነገር ግን አባታችን ጸሎታቸውን ሳያቋርጡ ሁለት ሳምንት በጸሎት ቆዩ፡፡ ከ2 ሳምንት በኋላ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው በዐይኖቻቸው ላይ እፍ ብለው ብርሃናቸውን ከመለሱላቸው በኋላ አባታችንን "ከሰማይ ፍጹም ኃይል ይሰጥሃልና ጠላቶችህን ትበቀል ዘንድ ወደ ዝቋላ ሂድ" ብለዋቸው ዐረጉ፡፡ ❤ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም እንደታዘዙት ወደ ዝቋላ እየሄዱ ሳለ በመንገድ ላይ ከዛፍ ሥር ያረፉ ሦስት ሽማግሌዎችን አገኙ፡፡ አባታችንም ባዩአቸው ጊዜ ለመሰወር ቢያስቡም ሽማግሌዎቹ ግን ይመጡ ዘንድ ጠሯቸውና "በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነናል ሦስታችንንም በጀርባህ አዝለህ አንድ አንድ ምዕራፍ ሸኘን" አሏቸው፡፡ አባታችንም ሽማግሌዎቹን በቀረቧቸው ሰዓት ሽበት የከበባቸው የደከሙ ሽማግሌዎች ሆነው አገኟቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን አንደኛውን ሽማግሌ አዝለው ከአንድ ምዕራፍ አደረሷቸው፡፡ ያም ሽማግሌ "ከዚህ አሳርፈኝ፣ አንተ ደክመሃል የማትበላ የማትጠጣ ነህና" አሏቸው፡፡አባታችንም "አባ የት ያውቁኛል?" አሏቸው፡፡ሽማግሌውም "አሁን ደግሞ ሄደህ ጓደኞቼን አምጣልኝ" አሏቸው፡፡ አባታችንም የቀሩት ሁለቱ ሽማግሌዎች ካሉበት ደርሰው ሁለቱንም በየተራ እያዘሉ የመጀመሪያውን ካደረሱበት ቦታ አደረሷቸው፡፡ከዚህም በኋላ እነዚያን ሽማግሌዎች "አባቶቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?" አሏቸው፡፡ ሦስቱም ሰዎች ተነሥተው ቆሙና ለአባታችን በአንድነት በሦስትነት ተገለጡላቸው፡፡ አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ሆኑ፡፡ ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም በመምሬ አድባር ሥር በአንድነት በሦስትነት እንደተገለጡለት ሁሉ አሁንም ለአባታችን ለገብረ መንፈስ ቅዱስ በአንድነት በሦስትነት ተገለጡላቸው፡፡ በጀርባቸውም አዘሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርንም ክብር ስላዩ አባታችን ፊታቸው እንደፀሐይ አበራ፡፡ ቅዱሳን መላእክት ወርደው እንደሻሽ ተነጥፈው ሲያመሰግኑ ሰማይና ምድር ተነዋውጠው ተራሮች ኮረብቶች ዓለቶች ተሰነጣጠቁ፡፡ በዚያችም ሰዓት ታላቅ ፍርሃት ሆነ፡፡ አባታችንም ዙሪያቸውን በከበባቸው በምሥጢራት ጎርፍ ተውጠው ተንቀጥቅጠው በግንባራቸው ወደቁና እንደ በድን ሆኑ፡፡በራእይ ውስጥም ሆነው እነዚያ ሽማግሌዎች አባታችንን እስከ ሰባተኛው ሰማይ እንዳደረሷቸው ተመለከቱ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደቀሰቀሳቸው አባታችንንም ቀሰቀሳቸውና "ወደ ዝቋላ ውረድ መቶ ዓመት ሙሉ አጥንትህን ሥጋህን እየነደፉ የተዋጉህን አጋንንት ታጠፋቸው ዘንድ፡፡ እነሆ እኔ እንደወሰድኩህ ባለማወቃቸው በትዕቢት ላይ ናቸውና "በባሕር ውስጥ አለ" ይሉሃል፡፡ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ይረዱሃል፤ መባርቅትም በፊት በኋላ ይከተሉሃል" አላቸው፡፡ ያንጊዜም አባታችን በመብረቅ ላይ ሆነው እነዚያ አጋንንት ወዳሉበት ወረዱ፡፡ አጋንንቱንም ደመናት ከበቡአቸው፣ መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው፣ በመብረቅ አጨዷቸው፤ አመድ ሆነው በነፋስ በተኗቸው፡፡ የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባ ሺህ እልፍ ከአንድ ሺህ ነበር፡፡ ሁሉም በአንድ ጊዜ አልቀዋልና ከእነርሱ ሸሽቶ ያመለጠም አልነበረም፡፡ ሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ወደ ሰማይ ዐረጉ፡፡ አባታችንም አንበሶችና ነብሮች፣ ድብና ዘንዶ ወዳሉበት ምድረ ከብድ ተመለሱ፡፡ ❤ አባታችንም ወደ ምድረ ከብድ ከተመለሱ በኋላ መንፈስ ቅዱስ የጠራቸው ሦስት ቅዱሳን ሁሉም በየአንበሶቻቸው ላይ ተቀምጠው ወደ ምድረ ከብድ መጡ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን የዋልድባው አቡነ ሳሙኤል፣ የአዘሎው አቡነ አንበስ እና ከላዕላይ ግብፅ ተነሥቶ የመጣው አቡነ ብንያም ናቸው፡፡ ነገር ግን አባታችን እነዚህን ቅዱሳን ስለተሰወሯቸው ቅዱሳኑ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በምህላ ሰነበቱ፡፡ የአባታችን የሚያስፈሩ አንበሶች ወጥተው የቅዱሳኑን አንበሶቻቸውን ገድለው ደማቸውን አፍስሰው ሥጋቸውን በሉ፡፡ ሦስቱም ቅዱሳን በዚህ ፈጽመው ደንግጠው ሳለ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ 60 ነብሮችንና 60 አንበሶችን አስከትለው ተገለጡላቸውና "ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ቅዱሳኑ አትፍሩ" አሏቸው፡፡ ቅዱሳኑም "አባታችን ሆይ! ጸሎትህ ቅድስት እንደሆነች ባወቅን ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንባረክ ዘንድ ወደ አንተ መጣን፡፡ ነገር ግን ባላገኘንህ ጊዜ እስከ ሰባት ቀን አለቀስን" አሏቸው፡፡ ዳግመኛም "የእርስዎም አንበሶች መጥተው አንበሶቻችንን በሉብን" አሏቸው፡፡ አባታችንም አንበሶቻውን "እስከ ዕለተ ሞቴ ድረስ በእግሬ ከረገጥኩት ምድር በቀር እግዚአብሔር ያላዘዛችሁን ለምን በላችሁ? አሁንም የበላችሁትን ትፉ" አሏቸው፡፡ እነዚያም አንበሶች አፋቸውን ከፈቱና የበሉትን የአንበሶቹን ሥጋቸውን አጥንታቸውን ከደም ጋር ተፉ፤ በሆዳቸውም የቀረ የለም፡፡ አባታችንም ወዲያው ወደ ምሥራቅ ዞረው እግዚአብሔር ካመሰገኑ በኋላ "አቤቱ አልዓዛርን ከሞት ያስነሣኸው አንተ ነህና አሁንም እነዚህን አናብስት ከሞት አስነሣቸው፤ ለባሮችህም የድካማቸውን ማረፊያ ይሆኑላቸው ዘንድ የሰጠሃቸውን አትከልክላቸው… " እያሉ ጸለዩ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ብለው ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ የአንበሶቹን ሥጋቸውን በመስቀል ምልክት ባርከ "በጌታዬ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ተነሡ"አሏቸው፡፡ አንበሶቹም እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነው ተነሡና እንደቀድሞው ሆኑ፡፡ ለአባታችንም እጅ ነሥተውና ሰግደው የእግሩን ትቢያ ላሱ፡፡ አባታችንም ወደ ጌቶቻቸው መለሳቸው፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ አባት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዝቋላ ተራራ በሐይቁ ውስጥ ለመቶ ዓመት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ምሕረት ለምነው ከእግዚአብሔር ዘንድ ቃል ኪዳን ለተቀበሉበት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ የዕለቱ እግ.ነግ ዜማ፦ "ጼና አልባሲሁ ለአባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከመ ጼና ስኂን አልባሲሁ ዘሜላት ዘወረደ ውስተ ገነት ከመ ይርአይ ሥነ ጽጌያት"። ትርጉም፦ የአባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የልብሱ መዓዛ እንደ ስኂን መዓዛ ነው፡፡ ልብሱ ነጭ የሐር ግምጃ ከገነት የወረደ የአበቦችን ውበት እንዲያይ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ። + + + ❤ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፦ ትውልድ አገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው፡፡አባታቸው ስም ቅዱስ ስምዖን እናታቸው ስም ቅድስት አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ወላጆቻቸው በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች፡፡ ❤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ እናታቸው ቅድስት አቅሌስያ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ "ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ ከፍ የሚል፣ ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ ንጽሕናው እንደ እንደ ነቢይ ኤልያስ፣ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ" አሏት። ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ። ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት"። እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡ ❤ ቅድስት አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ "የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን" አላት፡፡ ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ ዳግመኛም "ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን" አለ፡፡ ❤ ከ3 ዓመት በኋላም እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንዲህ ብሎ አዘዘው፡- "ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ተቀበል፣ ብዙ ገዳማውያን ወዳሉበት ገዳም ውሰድና ከበራቸው አስቀምጠው፣ አበ ምኔቱንም ዘመደ ብርሃንን ከበር አንሥተህ ካንተ ዘንድ አኑረው ስለ ልብሱ ስለ ምግቡ አታስብ ሕፃኑ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ነውና ምግቡም መንፈሳዊ ነው ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚወጣ ቃል ነው፣ ሰው በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ዕወቅ በለው" በማለት አዘዘው፡፡ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም እንደታዘዘው ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ወስዶ በክንፎቹ አቅፎ ስሞ እስከ ሰባቱ ሰማይ አውጥቶ በሥሉቅ ቅዱስ ፊት አቅርቦት አስባረከው፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩን "ወደ እናቴ ወደ ማርያም ውሰደውና ትባርከው" አለውና ወስዶት እመቤታችንም ባረከችው፡፡ ዳግመኛም ከአዳም ጀምሮ ኄሮድስ በግፍ እስካስፈጃቸው ሕፃናት ያሉት ሁሉም ቅዱሳን ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግልና መነኰሳት ሁሉም እንዲባርኩት አደረገው መልሶ ከእግዚአብሔር ፊት አቆመው፡፡ መድኅን ጌታም ሕፃን ገብረ መንፈስ ቅዱስን "በመንግሥቴ ከእኔ ጋር ትነግሣለህና ደስ ይበልህ፣ በርታ የሚደርስብህን ሁሉ ታገሥ ብዙ ነፍሳት በአንተ ምክንያት ይድናሉ፣ ሰላሜ ከአንተ ጋር ይሆናል" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ አባ ዘመደ ብርሃን ወዳለበት ገዳም አወረደውና ሕፃኑን ከበር ላይ አስቀምጦ እርሱ ወደ ውስጥ ገብቶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉን ነገረው፡፡ ❤ አባ ዘመደ ብርሃንም ሕፃኑን አስገብቶ በእንክብካቤ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ እያስተማረ አሳደገው፡፡ ሕፃኑም ትምህርቱን በጨረሰ ጊዜ ዲቁና ተቀብሎ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተመላ ሆነ፡፡ ፍጹም የእግዚአብሔር ጸጋ አድሮበታልና ሥራው ሁሉ በዕውቀት የተመላና የተቃና ሆነ፡፡ አባ ዘመድ ብርሃንም በሕፃኑ ላይ ያደረበትን ጸጋ እያየ እጅግ ደስ ይለው ስለነበር እንደ ቅዱስ እንጦንስ አስኬማን ሰጠው፡፡ ከዚህም በኋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅስናን ተቀበሉና በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡ ❤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዳግመኛ ተገልጦላቸው ወደ ሰማይ አሳረጋቸውና ከእግዚአብሔር ፊት አቆማቸው፡፡ ያን ጊዜም ጌታችን ክቡራን የሆኑ እጆቹን ዘርግቶ ከባረካቸው በኋላ "በጸሎትህ ከሲኦል የምታወጣቸው ብዙ ነፍሳት አሉ፤ ድውያንንም ትፈውሳለህ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ገብተህ ከአንበሶችና ከነብሮች ጋር ኑር" አላቸው ቁጥራቸውም ስልሳ ነብርና ስልሳ አንበሶች፡፡አባታችንም ጌታችንን "የሰጠኸኝ እነዚህ አንበሶችና ነብሮች ምን ይመገባሉ?" አሉት፡፡ ጌታችንም "የረገጥከውን መሬት ይልሳሉ በዚያም ይጠግባሉ፡፡ ወደ እኔም እስክትመጣ ድረስ ይኸው ምግብ ይሆናቸዋል" አላቸው፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ይህንን በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው፡፡ ጌታችንም መልአኩን ወደ ቀደመ ቦታቸው ይመልሳቸው ዘንድ አዘዘው፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከራሳቸው እስከ እግራቸው ድረስ ጠጉር በቀለላቸው፡፡ የጠጉራቸውም ርዝመቱ አንድ ክንድ ከስንዝር ነው፡፡ አባታችንም በታላቅ ተጋድሎ ሲኖሩ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨመረላቸው፡፡ከዕለታት በአንድ ቀን የፈወሳቸው ሕሙማን ብዛታቸው እልፍ ሆነ፡፡ የሀገሩ ሰዎችም ሥራቸውን ስላወቁባቸው አዘኑ፡፡ "ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንብኝ ተነሥቼ ሰው ወደማያውቀኝ አገር እሄዳለሁ" ብለው ተነሥተው ሄዱ፡፡ሕዝቡም አባታችን እንደተሰወሩ ባወቁ ጊዜ በሀዘን አለቀሱ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ጫካ ገብተው ብቻቸውን የበጋውን ሐሩር የክረምቱን ቁር ታግሰው ምንም ልብስ ሳይለብሱ ራቁታቸውን ሆነው በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ከጽኑው ተጋድሎአቸውና ከጫካው ቅዝቃዜ የተነሣ ሰውነታቸው አልቆ ከአጥንታቸው ጋር ተጣበቀ፡፡ ፍራፍሬም ሆነ ምንም ነገር አይመገቡም ውኃም ፈጽሞ አይጠጡም ነበር፡፡ አባታችን በምድረ በዳ እንደሰው ሳይሆን እንደመላእክት ኖሩ፡፡ ቅዱሳን መልእክትም ዘወትር ይጎበኟቸው ነበር፤ ስለምግባቸውም ሰማያዊ ኅብስት አምጥተው ይሰጧቸዋል ነገር ግን አባታችን ያንን ኅብስት አይመገቡትም ይልቁንም ጽዋውን ባሸቱት ጊዜ እንዲሁ ይጠግባሉ ይረካሉ፡፡ ❤ ዕድአቸው 300 ዓመት በሆነ ጊዜ ጌታችን "ወደ ኢትዮጵያ ሂድ በዚያም ከደይን የምታወጣቸው ነፍሳት አሉ" አላቸው፡፡ አባታችንም "አምላኬ ሆይ ወደዚያች አገር ማን ያደርሰኛል?" አሉት፡፡ እግዚአብሔርም "እኔ በሥልጣኔ አደርስሃለሁ" ካላቸው በኋላ ከእርሳቸው ተሰወረ፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ስድሳ አንበሶችና ስድሳ ነብሮች እየተከተሏቸው ወደ አገራችን ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚሁ ተከታዮቻቸው ጋር በነፋስ ሠረገላ ጭኖ ምድረ ከብድ አደረሳቸው፡፡ ዳግመኛም "ደብር ቅዱስ" ወደሚባለው ወደ ዝቋላ ወሰዳቸው፡፡ አባታችንም በውኃው ዳር ቆመው ምሥራቁን፣

ሼር ሼር ሼር ይደረግ! ታላቅ የንግሥ ጥሪና መንፈሳዊ ጉባኤ ለምእመናን በሙሉ! ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረውን የጻድቁ አባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከጥ
+1
ሼር ሼር ሼር ይደረግ! ታላቅ የንግሥ ጥሪና መንፈሳዊ ጉባኤ ለምእመናን በሙሉ! ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረውን የጻድቁ አባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከጥቅምት ፬-፭ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የትምህርተ ወንጌልና የዝማሬ መርሐ ግብር በታሪካዊው በሰዋስው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ ተዘጋጅቷል፡፡ በመሆኑም የበዓሉና የጉባኤው ተሳታፊ እንድትሆኑ በጻድቁ ስም ተጋብዛችኋል፡፡ አድራሻ፦ ኮልፌ 18 ልኳንዳ ፈጥኖ ደራሽ ካንፕ አጠገብ እንደ አማራጭ፦ ከመርካቶ 21 ቁጥር አውቶቡስን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ልኳንዳ ጋር መውረድ

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 10:17-25፡ "ወተመይጡ እልክቱ ፸" - "ሰብዓውም፡በደስታ፡ተመልሰው፦ጌታ፡ሆይ፥አጋንንት፡እንኳ፡በስምህ፡ተገዝተውልናል፡አሉት። እንዲህም፡አላቸው፡ሰይጣንን፡እንደ፡መብረቅ፡ከሰማይ፡ሲወድቅ፡አየሁ።እንሆ፥እባቡንና፡ጊንጡን፡ትረግጡ፡ዘንድ፥በጠላትም፡ኃይል፡ሁሉ፡ላይ፡ሥልጣን፡ሰጥቻችኋለሁ፥የሚጐዳችሁም፡ምንም፡የለም። ነገር፡ግን፥መናፍስት፡ስለ፡ተገዙላችሁ፡በዚህ፡ደስ፡አይበላችሁ፥ስማችሁ፡ግን፡በሰማያት፡ሰለ፡ተጻፈ፡ደስ፡ይበላችሁ። በዚያን፡ሰዓት፡ኢየሱስ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ሐሴት፡አደረገና፦የሰማይና፡የምድር፡ጌታ፡አባት፡ሆይ፥ይህን፡ከጥበበኛዎችና፡ከአስተዋዮች፡ሰውረህ፡ለሕፃናት፡ስለ፡ገለጥህላቸው፥አመሰግናለሁ፤አዎን፡አባት፡ ሆይ፥ፈቃድህ፡በፊትህ፡እንዲህ፡ሆኗልና። ሁሉ፡ከአባቴ፡ዘንድ፡ተሰጥቶኛል፥ወልድንም፡ማን፡እንደ፡ሆነ፡ከአብ፡በቀር፡የሚያውቅ፡የለም፥አብንም፡ማን፡እንደ፡ሆነ፡ከወልድ፡በቀር፡ወልድም፡ሊገልጥለት፡ከሚፈቅድ፡በቀር፡የሚያውቅ፡የለም፡አለ። ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡ዘወር፡ብሎ፡ለብቻቸው፦የምታዩትን፡የሚያዩ፡ዐይኖች፡ብፁዓን፡ናቸው። እላችኋለሁና፥እናንተ፡የምታዩትን፡ብዙዎች፡ነቢያትና፡ነገሥታት፡ሊያዩ፡ወደዱ፡አላዩምም፥የምትሰሙትንም፡ሊሰሙ፡ወደ፟ው፡አልሰሙም፡አለ። እንሆም፥አንድ፡ሕግ፡ዐዋቂ፡0ሊፈትነው፡ተነሥቶ፦መምህር፡ሆይ፥የዘለዓለምን፡ሕይወት፡እንድወርስ፡ምን፡ላድርግ?አለው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.76 KB

4/2/2015 ዓ.ም (፬/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር። ነገሥተ ምድር ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር። ወዘምሩ ለአምላክነ፡፡ መዝ. 67፥31 🕯 ትርጉም ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። የምድር ነገሥታት ለእግዚአብሔር ተቀኙ። ለጌታም ዘምሩ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በዕለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 13:47-53 "ካዕበ ትመስል መንግሥተ ሰማያት"- "ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤ በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፥ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት። በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኃጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል ኢየሱስም ይህን ሁሉ አስተዋላችሁን? አላቸው አዎን አሉት። እርሱም ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል አላቸው። ኢየሱስም እነዚህም ምሳሌዎች ከጨረሰ በኋላ ከዚያ ሄደ። ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.58 KB

4/2/2015 ዓ.ም (፬/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 እግዚኦ ስብሐተ ሐዲስ እሴብሐከ። ወበመዝሙር ዘ፲ቱ አውታሪሁ እዜምር ለከ። ዘይሁቦሙ ለነገሥት መድኃኒት። መዝ. 143፥9 🕯 ትርጉም አቤቱ ዐዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ። ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ። ለነገሥታት መድኀኒትን የሚሰጥ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ለሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በደማስቆ ላጠመቀው ሐዋርያ ቅዱስ ሐናንያ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለቅዱስ ሰርጊስ ባልንጀራ ለቅዱስ ባኮስ በከሀዲ ንጉሥ በአንጥያኮስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ የቅዱስ ባኮስ ሥጋ ወደ በዓታቸው ከወሰዱ ከቅዱሳን ወንድማማቾች ባሕታውያን ከባባና ከማማ ከመታሰቢያቸው፣ ከከበሩ ሮማውያን ጻድቃን ከጃንደረባው ዮሐንስና ገብረ ክርስቶስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ሐናንያ፦ ይህም ቅዱስ ቁጥሩ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ነው። በሐዋርያት እጅ ለደማስቆ አገር ኤጲስቆጶስነት ተሾመ እርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን በደማስቆ ጐዳና ተገልጦለት ለወንጌል ትምህርት በጠራው ጊዜ ሐዋርያ ጳውሎስን ያጠመቀው እርሱ ነው ። ❤ እርሱም አስቀድሞ ለግብሪል ወገኖች አስተማረ ብዙዎች በሽተኞችን አዳናቸው ብዙ ሰዎችንም ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መለሳቸው ። ❤ ከዚህም በኋላ ስሙ ሉቅያኖስ የሚባል መኰንን ያዘው በምድር ላይ ደሙ እንደውኃ እስከሚፈስ ድረስ ገረፈው ጐኖቹንም በብረት በትሮች ሠነጣጠቀ ደረቱንም በእሳት መብራቶች አቃጠለ ። ከዚህም በኋላ ከከተማ ውጭ አውጥተው በደንጊያ ይወግሩት ዘንድ አዘዘ በዚህም ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ሐናንያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የቅዱስ ሰርጊስ ባልንጀራ ቅዱስ ባኮስ፦ ይህም እንዲህ ነው እሊህን ቅዱሳን ከሀዲው ንጉሥ መክስምያኖስ በያዛቸው ጊዜ እነርሱ ወታደሮች ነበሩና ትጥቃቸውን ቆርጦ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ከዚህም በኋላ ወደ ሶርያ አገር ወደ ንጉሥ አንጥያኮስ ሰደዳቸው። እርሱም ቅዱስ ሰርጊስን አሠረው ቅዱስ ባኮስን ግን ሰቅለው እንዲደበድቡት በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠልጥለው ከኤፍራጥስ ወንዝ ከባሕር እንዲጥሉት አዘዘ ንጉሡም እንደ አዘዘ እንዲሁ አደረጉ። ❤ እግዚአብሔር ግን የቅዱስ ባኮስን ሥጋ ጠብቆ ወደ ወደብ አደረሰው በዚያ ወደብ አቅራቢያም በገድል ተጠምደው የሚኖሩ የአንደኛው ስሙ ማማ የሁለተኛው ባባ የሚባሉ ባሕታውያን አሉ። ለእሊህ ወንድሞችም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጠላቸውና ሒደው የቅዱስ ባኮስን ሥጋ ወደ በዓታቸው እንዲወስዱ አዘዛቸው። ❤ በዚያንም ጊዜ መልአክ እንዳዘዛቸው ሔዱ የቅዱስ ባኮስንም ሥጋ አገኙ በአጠገቡም አንድ ቀንና አንድ ሌሊት ሲጠብቁት የነበሩ አንበሳና ተኵላ አሉ እነርሱም ከሰው ሥጋና ከእንስሳ በቀር የማይመገቡ ሲሆኑ ግን ከልዑል አምላክ ዘንድ ስለታዘዙ ነው። እሊያ ቅዱሳንም የቅዱስ ባኮስን ሥጋ ወሰዱ በታላቅ ክብር እያመሰገኑ እስከ በዓታቸውም አድርሰው በዚያ ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ባኮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለሐናንያ ለጳውሎስ መጥምቁ። ወውስተ ኍልቈ አርዳእ ኊልቊ። እኩያን ዕደው እምአሚነ ክርስቶስ ዘርኅቁ። በበትረ ኀፂን ገበዋቲሁ ሠጠቁ። ወበውግረተ ዕብን ካዕበ ኵለንታሁ ደመቁ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እግዚኦ ስብሐተ ሐዲስ እሴብሐከ። ወበመዝሙር ዘዓሠርቱ አውታሪሁ እዜምር ለከ። ዘይሁቦሙ ለነገሥት መድኃኒተ"። መዝ 143፥9-10። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥47-53። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር። ነገሥተ ምድር ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር። ወዘምሩ ለአምላክነ"። መዝ67፥31-32። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥29-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥16-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 9፥10-20 የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1ዐ፥17-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቄርሎስ ወይም የቅዱስ ባስልዮስ ወይም የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱሳን ነገሥታት የአብርሀ አጽብሐና የአቡነ በርተሎሜዎስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw